Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo Media

Description
እሔ የቴሌግራም መንፈሳዊ ቻናላችን ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ምንማማርበት መንፈሳዊ መድረክ ነው። ለሌሎች ያጋሩ፣ አዳዲሶችም ተቀላቀሉ(join) አድርጉ።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 week, 6 days ago

ኢት 251 ሚድያ በጣም ነው የምና መሰግነው።

1 week, 6 days ago

በትንሣኤ እና በጠቅላላው በሐምሳው ቀናት ክርስቲያናዊ ሰላምታችን በረዥሙ እንዲሁም በአጭሩ (ሐሳብ መስጠት ይቻላል!!!)
+++
Orthodox Greetings at Easter & the 50 days:
++++
ሀ/ በረዥሙ

ካህን: ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
Priest:- Christ is risen from the dead

ሕዝብ፦ በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
People:- With great strength and authority

ካህን: ዓሠሮ ለሰይጣን
Priest:- He chained Satan

ሕዝብ፦ አግዓዞ ለአዳም
People:- He freed Adam

ካህን:- ሰላም
Priest:- Peace

ሕዝብ፦ እምይእዜሰ
People:- Henceforth

ካህን:- ኮነ
Priest:- Became …

ሕዝብ፦ ፍሥሐ ወሰላም
People:- Joy and peace

++++++
ለ/ በአጭሩ፤
+ Short greeting form (as in the Other Orthodox Churches) in our day to day encounters could be:-

ሰላምታ አቅራቢ:- "ክርስቶስ ተንሥአ [እሙታን]" = (ክርስቶስ ተነሥቷል)
++ Greeter:- Christ is risen [from the dead.]
ሰላምታ ተቀባይ:- "በአማን ተንሥአ እሙታን!!" = (በእውነት ተነሥቷል)
++ Person receiving the greeting:- "Truly He is risen [from the dead.]"

  • በሌሎች ክርስቲያኖች ዘንድ ያለው ሰላምታ!!!!

“Christ is Risen!”,
“Truly, He is Risen”.
(This is used in almost all Christian nations, each translating it to its own language.)

A/ Greek:
“Χριστός ἀνέστη! Ἀληθῶς ανέστη!
(Khristós Anésti! Alithós Anésti!)”,

B/ Latin:
** “Christus resurrexit! Resurrexit vere!”,

C/ Aramaic Syriac: “ܡܫܝܚܐ ܩܡ! ܫܪܝܪܐܝܬ ܩܡ!‎ (Mshiḥa qām! sharīrāīth qām! ; Mshiḥo Qom! Shariroith Qom!)”,

D/ Hebrew: “המשיח קם! באמת קם!‎ (Hameshiach qam! Be’emet qam!)”,

E/ Arabic: “المسيح قام! حقا قام!‎ (al-Masīḥ qām! Ḥaqqan qām!); المسيح قام! بالحقيقة قام!‎ (al-Masīḥ qām! Belḥāqiqāti qām!)”.

F/ Coptic, the Paschal greeting is:
** Neo-Bohairic as “Pikhristos Aftonf! Khen oumethmi aftonf!” and in Old Bohairic as “pikhristos afdonf! khen oumetmei afdonf!”.

++++
Note:-
** Comments are welcome.

1 week, 6 days ago

👉ለዓለም  ሕዝብ  የሚተርፍ ጸጋ እያለን ለራሳችን እንኳ መሆን የተሳነን ለምንድር ነው????
==========‼️=========
1) የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና የሚመጥን አገልጋይና ተገልጋይ ሆነን ባለመገኘታችን!

2) ሃይማኖታችን እንከን የሌለባት ንጽሂት ብትሆንም እንኳ ከግራኝ አሕመድ ወራራ በኋላ ያለው ትዉልድ ሃይማኖቱን ከልጅ ወደ ልጅ የሚያሸጋግረው በበሳል አእምሮና በኦርቶዶክሳዊ ማያነት ሳይሆን በልምድ ብቻ መሆኑ!

3) ዘመኑን በዋጁና ክርስቶሳዊ ልብ ባላቸው አገልጋዮች የሚመራ ቤተ ክህነት ስለሌለን! ምናልባት ጥቂት አገልጋዮች ካልሆኑ በስተቀር እንደ ተቋም ግን  አለ ብሎ ለማውራት ይከብዳል።

4) ቅዱስ ፣ሃይማኖተኛ፣ሃገር ወዳድ ፣ባለራዕይ ትዉልድ የሚፈራበት ታላቁ ተቋም ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻችን እየተዳከመ በመምጣቱ!

5)  ሃገር የመምራት ጥበብን(ፖለቲካን) እንደ ኃጢአት ቆጥረን  ለጸረ ኦርቶዶክሳዊያንና ለጸረ ኢትዮጵያዊያን ኃይሎች ወንበር መልቀቃችን!  ሊቃዉንቱ፣ ካህናትና መምህራን በደጀ ሰላሙ መርመስመስ ።ወጣቱ ጠቅሎ  ሰንበት ትምህርት ቤት ገባ  ከዚህ የተረፉት ደግሞ ሺሻ ቤት፣ጫት ቤት፣በዳንኪራ ቤት ቀሩ። ጎልማሶች ሰንበቴ ቤት ገቡ ሌላው አይመለከተንም አሉ።የቀበሌ ታጠቂ ሁኑ ሲባሉ  እንኳ ፈቃደኞች አይደሉም።

6) በኢኮኖሚ መበልጸግን እንደ ኃጢአት ቆጥረነው  ለሥራ ያለን ተነሳሽነት የወረደ በመሆኑ! በዚህ ምክንያት ድህነት በትከሻችን ላይ ወደቧን ሠራች !

6) ክርስቶስ በሰጠን ኦርቶዶክሳዊ  አንድነታችን ጸንተን ከመኖር ይልቅ   ለከፋፋይ "የጎሳ ፌዴራሊዝም/Ethnic Federalism/"የልቡና በራችንን ከፍተን በመቀበላችን ና በእርሱ በመመራታችን!

7)  ታሪካችንን አዉቀን እኛም ታሪክ ሠሪዎች እንዳን ሆን የትናንቱን ታሪክ የሚያጠልሽ ህገመንግሥት ስለተጻፈብን!

8)  ቤተ ክርስቲያኒቱ ሃገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ መዋቅር ዘርግታ ትኩረት ሰጥታት ባለ መሥራቷ! ሰንበት ትምህርት ቤት አቋቁማ ኮርስ ማስተማሯና መዝሙር ማስጠናቷ እንደ ተጠበቀ ሆኖ!

9)ተማርኩ፣ሠለጠንኩ የሚለው የዘመኑ ትዉልድ(እኔንም ጨምሮ) ያለፈውን ትዉልድ ከመዉቀስ በዘለለ  ሃገርንና ቤተ ክርስቲያኒቱን ማሻገር የሚችል   አዲስ አስተሳሰብ ይዞ ባለመገኘቱ! ምዕራባዊያን ጽፈው ከሰጡት ዉጭ በራሱ አእምሮ መጠቀም የማይችል የCopy Paste Generation ነው!

10)  የልዕልና አስተሳሰብ ምንጭ የሆኑ ኦርቶዶክሳዊና ኢትዮጵያዊ ባሕሎቻችንን አሽቀንጥረን ጥለን ማንነታችንን ለሚያጠፉ ለመጤና ለባዕድ ባሕሎች በመገዛታችን!

============///========

© ኢዮሳፍጥ ጌታቸው

ሚያዝያ 29/2015 ዓ.ም

2 weeks, 6 days ago

👉 ይሁዳ ሲለይ ይሁዳነት እንጂ ሐዋርያዊነት አልተለየንም

👉 ንስጥሮስ ሲወገዝ ንስጥሮሳዊነት እንጂ ጵጵስና አልተወገዘም

👉 ሉተር ሉተርነቱ ሲገለጥ ሉተራዊነት እንጂ ምንኩስና ክብሩ አልቀነሰም

👉 ካህን ሊወገዝ፣ ሊለይ፣ ሊነቀፍ፣ ሊክድ፣ ሊዋሽ፣ ሊያመነዝር፣ ሊሰርቅ ይችላል። ይህ
ሁሉ ግን ካህኑን እንጂ ክህነቱን አያስነቅፍም።

ገብረአብ ሀጎስ

2 weeks, 6 days ago

ጾም በሕማማት

የሕማማት ጾም ከሌላው ጊዜ ጠንከር ይላል። መጾም የሚቻለው ሰው ቢኖር ሁለት ቀን ይታገስ፡ ባይችል ግን በየ አንዲቱ ቀን ይጹም። በሕማማት ሳምንት በጨው ከተሰራ ቂጣና ውሃ በቀር ምንም አትጠብሉ አትጠጡ፡ ሥጋ ከመብላት ጠጅ ከመጠጣት ተጠበቁ፤ የልቅሶ የኅዘን ቀኖች ናቸውና። ጾሙ እስከ ምሽት ፩ ሰዓት ድረስ ተወስኗል። እንደ አቅም መኖር መፈጸም ነው (ዲዲስቅልያ አንቀጽ.30:10-12) 

ስግደቱ ሁሉ የአምልኮ ስግደት ይሰገዳል። ኪሪዬ ኤሌይሶን (በተለምዶ ኪሪያላይሶን) በማለት ይኽውም አቤቱ ይቅር በለን ማለት ነው።

+ማማተብና ሰላምታ መለዋወጥ

ይህ ጥያቄ ሁሌም የተለያየ አተያይ ይኖረዋል ባይ ነኝ። ይህንን በተመለከት  ግብረ ሕማሙም ምንም የሚጠቁመው ነገር የለም። በተለይ በገዳም ተወስነው ፤ ሱባኤ የያዙ ይኽንን ለመተግበር ቀላል ይሆናል፣ ይበልጥ ሕማማትን ያስታውሳል። የተወሰነ ስፍራ ስንሆን በማጎንበስ ብቻ ሰላምታ እንለዋወጣለን። ሰላምታ ክልክልክ አይደለም። ስመ እግዚአብሔር የሚጠራበት ነው። 

ነገር ግን በከተማ እየኖሩ፣ በሥራ ቦታ ላይ እያሉ ሰው ሰላም ሊለን ሲመጣ እንዳትጠጋኝ  አይነት ስሜት በሌላውን በራሳችንንም የሚፈጥረው ስሜት ከማስተማሩ ይልቅ ማሰናከሉ ይበልጣል። ሕማማት ስቃዩን ማሰቢያ እንጅ ሰላምታ መከልከያ አይደለም። ምክንያቱም ሰላም የሚለን ሁሉ ክርስቲያን ላይሆን ይችላል። ይህንን በየራሳችን ገጠመኝ የምናየው ስለሆነ የሚያከራክር አይሆንም። ትልቁ መከልከለ ያለበት የይሁዳ አይነት ሰላምታ ነው። አንደምን አደርክም ማለት ሰላምታ ስለሆነ ይኽንን መከልከል አይቻልም። እርሱ ሰላማችን ነው።

ማማተብ በሥርዓት መጽሐፍት የተከለከለ አይደለም። ነገር ግን በልምድ የሚባል ነው። በቤተ ክርስቲያን መጽሐፍት የተጻፈው መስቀል ማሳለም አንደማይገባ ብቻ ነው። ድኅነት ያልሆነበትን ጨለማውን ዘመን ስለምናስብ ነው። ለምሳሌ ሕማማት ነው ብለን “መስቀል” የሚል ቃል አልጠቀምም አንልም። መስቀልን ከአንገታችን አናወልቅም። ሰለሆነም ማማተብ የተከለከለበት ሥርዓት አላነበብኩም አልተማርኩም። 

ሌላው ማስረጃ ስናማትብ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ብለን ነው። ይኽ ደግሞ በሕማማት በየምንባቡና ጸሎቱ መጀመርያ የታዘዘ ነው። ስለሆነም በጣት ማማተብን የሚከለክል ማስረጃም ሆነ ትምህርት አላገኘሁም። የአንዳንድ አባቶች (ካህናትና መምህራን) ትምህርት ግን ጥቅል የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተደርጎ መወሰድ የለበትም። (ይህም የክርክራችን ማእከል መሆን የለበትም)። ትልቁ ክልክል መሆን ያለበት ግብረ ይሁዳነት ነው።

+የሕማማት ጸሎት

በሕማማት የሚጸለየው በአብዛኛው ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት፤ የነቢያት ጸሎት ሲሆን የጌታን መከራ መስቀል የሚያነሱ መጻሕፍት ይጸለያሉ፡ ሕማማተ መስቀል፤ ድርሳነ ማሕየዊ የመሳሰሉ። መልክአ መልኮች፤ ድርሳናትና ገድላት የማይጸለዩት ዋናውን ጸሎት በጌታ ሕማማና መከራ መስቀል ለመስጠት ስለሆነ ነው። በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያን የሚነበበው ንባብ (ግብረ ሕማም) ዋናው የጸሎት ክፍል በመሆኑ ያንንም መሳተፍ ትልቁ ጸሎት ነው።

+ጥብጠባ፡-

በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ  ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ  ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ  ምሳሌ ነው፡፡

ይኽ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ሥርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡  ይህም የጌታን ግርፋት ያሳያል።፡ህዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኃላ ሰርኆተ ሕዝብ ይሆናል። አርብ ከ 11 ሰአት በኋላ ስግደት እንደሌለ ግብረ ሕማሙ "አልቦ ስግደት "ይላል።

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

2 weeks, 6 days ago

ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15
------------------------------------------
ቁጥር 578፡ በሊህ በስድስቱ ቀኖች ከቂጣ ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፡፡ በሊህ ቀኖች ከወይን ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች
ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም፡፡ ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፡፡ የሚችል እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ
ምንም ምን አይቅመስባቸው ሰውየውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም፡፡
ቁጥር 588፡ አንድ ሰው በባሕር ቢኖር ሰሙነ ሕማማትን ባያውቅ ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ይጹም፡፡ ይኸውም ሰሙነ ሕማማትን የሚጠብቅ
አይደለም፡፡ ምሳሌውን ብቻ ነው እንጅ ስለእርሱ መጾም ይገባዋል፡፡
ቁጥር 590፡ ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፡፡ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ ስዑር
በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር፡፡
ቁጥር 596፡ ክብርት በምትሆን በአርባ ጾም በመጀመሪያው ሱባዔ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ይጹሙ፡፡ የመጀመሪያው ሱባዔ ካለፈ በኋላ እስከ
11 ሰዓት ድረስ ይጹሙ፡፡ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ድረስ ይጹሙ፡፡ በእነዚህም ወራቶች አያጊጡ፡፡
ቁጥር 597፡ ሴቶችም ጌጣቸውን ይተዉ፡፡ ሁሉም ለእያንዳንዱ በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና የኃጢአታችን
ሥርየት በእነርሱ ነውና፡፡ ይኸውም ሥራ አንዱስ እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ ሕግ የወጣ ነው፡፡ ክብርት
በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፡፡ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን
ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ?
ቁጥር 600፡ በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም፡፡ በእነዚህም ቀኖች በቤተ ክርስቲያን
ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፡፡ በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት
በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጅ፡፡
ቁጥር 601፡ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)፡፡ ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል
ፍትሐት ይፈታል፡፡ ከመሳለም በቀር ጸሎተ ዕጣንም ይጸለያል፡፡ በዕለተ እሑድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም፡፡ ዳግመኛም
በውስጧ በአርባ ጾም ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ መጋባት ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን
ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል፡፡

3 weeks, 6 days ago
እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo …
3 weeks, 6 days ago
እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo …
3 weeks, 6 days ago
ደሞዝህ ነው ተቀበል።

ደሞዝህ ነው ተቀበል።

"…አባ ገዳይ ጎበና ሆላ ልጁን ፎሌ ጎበናን የኦነግ ሸኔ አባልና ወታደራዊ አመራር አድርጎ፣ በኦሮሚያ ክልልም አዝምቶ፣ ዐማራንና ኦርቶዶክሳውያን እያዘረፈ፣ እያስገደለ፣ እያሳገተ፣ እሱ ግን እንደ ሃይማኖት አባት ባላየ፣ ባልሰማ አባ ገዳ ሆኖ በጨዋ ደንብ ስለሰላም እያወራ ሲቦተልክ የሚውል ሰው ነበርእሱ ግን በልጁ በኩል የሰው ነፍስ እያስቀጠፈ ለደጋ አጋዘን፣ ለደብረዘይት አህዮች የኦሮሞን "ውኃ ሲጠየቅ እርጎ ነው የሚሰጠው" ተረት እየተረተ የርህራሄ የሚያሳያቸው አባገዳይ ነበር። ውሎ አድሮ ቆይቶ የንጹሐን ደም ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ደረሰ። ከሥላሴም መንበር ዘንድ ደርሶ ጮኸ። እግዚአብሔርም ፈረደ።

• መሸ፣ ነጋ፣ እቡይ አህመድ በነገሠ፣ የአባገዳይ ጎበና ልጅ ዐማራን ማገት፣ መግደል እና ደም ማፍሰስ በጀመረም በ6ተኛው ዓመት በራሱ በኦሮሙማው ኃይል ፀረ ዐማራው፣ ፀረ ኦርቶዶክሱ የአባ ገዳይ ጎበና ልጅ በዚያው በኦሮሚያ ተገደለ። አባገዳይ ጎበናም አለቀሰ። አነባም። ሌሎች ቤት የገባው ኀዘን መከራም በአባገዳዩ በቤቱ ገባ። ይሄንንም ቢቢሲ የተሰኘው መከራ ጠማቂ ድርጅት ዘገበው።

"…የሌሎቹም ይቀጥላል። ደም ያፈሰሱት፣ የዘረፉት በሙሉ የኀዘን ድንኳንም በሁላቸውም ቤት ሰተት ብሎ ይገባል። አሁንም ገብቷል። እየገባም ነው። በኢትዮጵያም በኦሮሚያም ንፁሐን ብቻ እንዳለቀሱ አይቀሩም። ንጹሐን ያዩት ጭንቀት መከራም በሁሉም ጓዳ ይገባል። እንቅልፍም ታጣላችሁ። ትዋረዳላችሁም። ትራባላችሁ፣ ዘራችሁም እህል ይለምናል። ለምኖም ያጣል። በፈሰሰው የንጹሐን ደም የበቀለውን እህል የበላ ሁሉ በነቀርሳ ህመም ይሰቃያል። መንምኖ፣ ማቅቆም ይሞታል።

"…ቆይቼ እመለሳለሁ።

1 month ago

ጥሩ መረጃ ነው ሰው ያስገደልኩበት ነው እሄ ገንዘብ እያለ ነው

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago