Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

Description
ኦርቶዶክሳዊ ጽሑፎች ይቀርቡበታል !
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 неделя, 3 дня назад

"ማንን ላግባ?" የሚለው የሥልጠና መጽሐፍ በውስጡ ምን ምን አካቷል?

መጽሐፉ በዋናነት ስድስት ክፍለ ጊዜዎችን የሚሸፍን ሲኾን፡-

#አንድ፡- በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መዳን ጉዞ ነው - እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚደረግ ጉዞ! ይህን ጉዞ ለመጓዝም እግዚአብሔር ለሰው እንደ ዓቅሙ የሚሰጠው የጉዞ መስመር (ጥሪ) አለው:: ለአንዳንዱ የድንግልናን ጸጋ ሲሰጠው ለሌላው የጋብቻን ጸጋ ይሰጠዋል፡፡ የኹለቱም ዓላማቸው መንግሥተ እግዚአብሔርን መውረስ - መዳን እንደ መኾኑ፥ ወጣቶች ጥሪያቸው የትኛው የጉዞ መስመር እንደ ኾነና ይህን እንዴት መለየት እንደሚችሉ በመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ይዳስሳል፡፡

#ኹለት፦ ትዳር በሃይማኖትም በማኅበረሰብም ዘንድ ቅቡል ስለ ኾነ፡ ሌሎች ሰዎች ሲያገቡ እነርሱ ካላገቡ የዕድለቢስነት ስሜት የሚፈጥርባቸው ሰዎች ቍጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ክርስቲያኖች ማግባት ያለባቸው ግን ጋብቻ አንዱ የድኅነት መንገድ ስለ ኾነ ነው፡፡ በመኾኑም ወጣቶች ጥሪያቸው ማግባት ከኾነ ስለ ጋብቻ ምንነትና ዓላማ ሊኖሯቸው ስለሚገቡ መሠረታዊ ነጥቦችን በኹለተኛው ክፍለ ጊዜ ያስመለክታል፡፡

#ሦስት፦ ወጣቶች አሁን ስለ ትዳር ያላቸው ግንዛቤ በዋነኝነት የተማሩት ከወላጆቻቸው/ ከአሳዳጊዎቻቸው/ ከትምህርት ቤት/ ካነበቡት/ ከሰሙት ነው፡፡ ስለዚህም “የትዳር አጋር ይኾነኛል/ ትኾነኛለች" ብለው ለመምረጥ ከመነሣታቸው በፊት ራሳቸውን እንዲመለከቱ/ እንዲያውቁ፣ መለወጥ ያለባቸውን እንዲለውጡና ኦርቶዶክሳዊ የትዳር ጉዞን ለመጀመር በምን ረገድ መዘጋጀት እንዳለባቸው በሦስተኛው ክፍለ ጊዜ ይቃኛል፡፡

#አራት፦ ከውሳኔዎች ኹሉ እጅግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ውሳኔ ከሚያሻቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው የትዳር አጋርን በመምረጥ ረገድ የሚደረግ ውሳኔ ነው:: መዳረሻቸውን መንግሥተ ሰማያት ወይም እሳተ ገሃነም የማድረግ ዓቅም ያለው ነውና። በመኾኑም ወጣቶች እንደሚገባ ራሳቸውን ከለወጡና እንደ ዓቅማቸው ብቁ አድርገው ካዘጋጁ በኋላ የወደፊት የትዳር አጋራቸውን እንዴት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚመርጡ፣ በተለይም እንደ ተባለው መዳረሻቸውን የሚወስነው ኋኝነታቸውን (their Compatibilities) እንዴት አድርገው ማየት እንዳለባቸው በአራተኛው ክፍለ ጊዜ ይዳስሳል፡፡

#አምስተኛ፡- ወጣቶች ውሳኔያቸው ትክክል ይኹን አይኹን ማወቅ የሚችሉበት ምትሐታዊ ቀመር የለም፡፡ ስለዚህም ከመወሰናቸው በፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው በአምስተኛው ክፍለ ጊዜ ያስቃኛል፡፡

#ስድስተኛው፡- በትዳር አጋር ምርጫ ብቻ ሳይኾን በኹሉም የሕይወት ዘርፍ እርግጠኛ እየኾንን እንወስናለን ማለት አስቸጋሪ ነው:: የሚቻለውን ያህል እግዚአብሔር በሰጠን አእምሮ ከእኛ የሚጠበቀውን ማድረግ ነው:: ከዚህ ውጪ ያለው እምነት ነው፡፡ በመኾኑም በስድስተኛው ክፍለ ጊዜ የወሰኑት ውሳኔ ትክክል መኾኑን እንዴት እንደሚያውቁና ወደ ቀጣዩ ደረጃ - ወደ ዕጮኝነት - እንዴት እንደሚያሳድጉት፣ ምናልባት ግንኙነታቸው ጤናማ ካልኾነ ደግሞ ሲያቋርጡት በምን ረገድ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስዳስሶ ሥልጠናውን ያሳርጋል።

1 неделя, 3 дня назад
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
1 месяц назад

ጥንዶች አንዳቸው ለሌላኛቸው የሚያደርሱት ጸሎት

በቅዱሱ ሐዋርያህ [በተወዳጅ] ጳውሎስ በኩል አንዳችን የሌላኛችንን ሸክም እንሸከም ዘንድ ያስተማርከን እግዚእነ ወአምላክነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ቅዱስ የኾነውን ትእዛዝህን እፈጽም ዘንድ፥ እንደ ምሕረትህ የሚስቴን ሸክም በ[መንፈሳዊት] ፍቅር መሸከም ይቻለኝ ዘንድ ጸጋህን አትንሳኝ፤ ትሰጠኝ ዘንድ እማልድሃለሁ! ፍጹምና ሰላምን የሚያጎናጽፍ ፍቅርህን ወደ እኛ በመላክም፣ በአንድ ልብ በአንድ አሳብ በመጠበቅም፣ በአሚን እንድንጸና በማድረግም ትዳራችንን ባርክልን። አንተ በምትሰጠው ደስታ ደስ እንድትሰኝና በነገሮች ኹሉ አንተን ደስ ማሰኘት ይቻላት ዘንድ በሚስቴ (የክርስትና ስሟ ጥቀስ) ላይ ፍቅርህን አሳድርባት። ለዘለዓለም ቅዱስ የኾነውንና አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተሰኘ [የሦስትነት] ስምህን በአንድነት ማክበር ማግነን ይቻለን ዘንድም ከጸብ ከክርክር ከፈተናም [ኹሉ] ጠብቀን፤ በሰላምና በአንድነት አጽናን፤ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ፥ አሜን!

© Orthodox Faith

2 месяца, 1 неделя назад
[#የዕለቱ\_ስፔሻል](?q=%23%E1%8B%A8%E1%8B%95%E1%88%88%E1%89%B1_%E1%88%B5%E1%8D%94%E1%88%BB%E1%88%8D)

#የዕለቱ_ስፔሻል
📚 የመጽሐፉ ርእስ፦ "ማንን ላግባ?"
📚 አዘጋጅ፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
📚 ይዘት፦ ትምህርተ ኖሎት (ማሠልጠኛ ማኗል)
📚 የገጽ ብዛት፦ 123
📚 የሽፋን ዋጋ፦ 200 ብር
📚 ለዕለቱ የተተመነለት ዋጋ፦ 150 ብር
-------------------
📍 ይህ መጽሐፍ፥ ወጣቶች እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙበት መንገድ ጋብቻ ከኾነ ለዚህ ጉዞ እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው የሚያሠለጥን ነው። ማንን ላግባ ቢልም ቅሉ ዕጮኛ ያላቸውም ያገቡትም ቢኾኑ ቢያነቡት በብዙ መንገድ ይጠቅማቸዋል።
-----------------
ይጎብኙን - ለዐቢይ ፆም ሙሉ በምናወጣቸው የየዕለቱ ቅናሾች ተጠቃሚ ይኹኑ!
-------------
አድራሻችን፦ አምስት ኪሎ፥ አሐዱ ባንክ ፊት ለፊት
ስ.ቁ. 0920888887
-----------------
https://t.me/Bakosbookstore

2 месяца, 2 недели назад

ስንናደድ ለምን እንጮሃለን ?

አንድ ብልህ አረጋዊ አባት በገዳም የሚኖሩ ደቀ መዛሙርትን ሰብስበው እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው :-

" ስንናደድ ለምን እንጮሃለን ? ሰዎች ሲበሳጩ ስለምን እርስ በእርሳቸው ይጯጯሀሉ ?"

ደቀ መዛሙርቱ ለጥቂት ደቂቃ ዝም ብለው ካሰቡ በኋላ ከመካከላቸው አንዱ ተነስቶ እንዲህ ሲል መለሰ :-

" ስንናደድ መረጋጋት ስለሚያቅተን እንጮሀለን "

አረጋዊው አባትም ቀጠል አድርገው '' አብሮህ ያለው ሰው ከአጠገብህ ሆኖ ሳለ ታዲያ ስለምን ትጮህበታለህ ? በለሰለሰ ድምፅ መነጋገር የማይቻል ነገር ነውን ? ስትበሳጭ ስለምን ሌላኛው ሰው ላይ ትጮሀለህ ? "

ደቀ መዛሙርቱ በየተራ እየተነሱ የመሰላቸው ኹሉ መለሱ ። ነገር ግን አንዱም የደቀ መዛሙርቱ ምላሽ እኚህን ብልህ አረጋዊ አባት ስላላረካቸው የራሳቸውን ጥያቄ እንዲህ ሲሉ መለሱ:-

" ሁለት ሰዎች በሚበሳጬበት ሰዓት ልባቸው እጅግ ይራራቃል ይህን ርቀት ለመቀነስ እና ለመደማመጥ ደግሞ የግድ መጮህ አለባቸው ! አምርረው በተቆጡ መጠን በመካከላቸው ሰፊ መራራቅ ስለሚፈጠር ለመደማመጥ ይበልጡን መጮህ ግድ ይላቸዋል ።

አረጋዊው አባት ሌላ ጥያቄም አስከተሉ :-

"ሁለት ሰዎች ሲዋደዱስ ምን ይፈጠራል ? ይልቅ በለሰለሰ ድምፅ ያነጋገራሉ፡፡ ' ለምን ካላችሁኝ ምክንያቱ ልባቸው በጣም ስለሚቀራረብ ነው ! በመካከላቸው ያለው ርቀት ጥቂት ስለሚሆን እጅጉን እየተዋደዱ በመጡ ቁጥር ቃል ማውጣቱንም ትተው በሹክሹክታ ያወራሉ ። በመጨረሻም መንሾካሾክም ሳያስፈልጋቸው ዓይን ለዓይን በመተያየት ብቻ ይግባባሉ። እንዲህ ነው ሁለት የሚዋደዱ ሰዎች የሚቀራረቡት ።"

" በምትከራከሩ ጊዜ ልባችሁ እንዲራራቅ አትፍቀዱለት ፣ ይበልጥ የሚያራርቃችሁንም ቃላት አትጠቀሙ !ምክንያቱም አንድ ቀን በመካከላችሁ ያለው ርቀት እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ዞሮ መመለሻው መንገድ ይጠፋባችኋል ! "

" ፍቅር ልብን የተረጋጋ እና ሕይወትን የሚሰጥ ሲያደርገው በአንጻሩ ጥላቻ ደግሞ የተረበሸ ያደርገዋል በዚህም ሌላውን የሚጠሉ ራሳቸውን ያሰቃያሉ ! ከፍቅር በላይ ምን ጣፋጭ ነገር አለ ? "
"ለእኛ ያለህ የማይቋረጥ ፍቅርህ ከአባትም፣ ከእናትም ፣ ከሚስት እና ከባልም የሚበልጥ አቤቱ ፍቅር የሌለን ባሪያዎችህን ማረን አሜን !!! "

ምንጭ :- አባ ዮሐንስ ክሮንስታት የተባሉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባት እንደጻፉት

ትርጉም ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ

Telegram

Book club

በዚህ ቻናል ላይ ቆየት ያሉ አዳዲስ በገበያ ላይ የሌሉ መጽሐፍት በ pdf የሚለቀቅ ይሆናል

ስንናደድ ለምን እንጮሃለን ?
2 месяца, 3 недели назад
[#ማንን\_ላግባ](?q=%23%E1%88%9B%E1%8A%95%E1%8A%95_%E1%88%8B%E1%8C%8D%E1%89%A3) በሚል የተዘጋጀው የማሠልጠኛ ማኗል መጽሐፍ …

#ማንን_ላግባ በሚል የተዘጋጀው የማሠልጠኛ ማኗል መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል።

4 месяца, 1 неделя назад
"ማንን ላግባ?" ለሚሉ

"ማንን ላግባ?" ለሚሉ

በቅርቡ

4 месяца, 2 недели назад
[#የበዓል\_ስጦታ](?q=%23%E1%8B%A8%E1%89%A0%E1%8B%93%E1%88%8D_%E1%88%B5%E1%8C%A6%E1%89%B3)!

#የበዓል_ስጦታ!

በቅርቡ ለንባብ የበቃውና የሚነበብ ሳይኾን ዕጮኛሞች እንዲያወሩበት የሚፈለገው መጽሐፍ፥ መግዛት ለማይችሉ 10 ሰዎች ለበዓል መውሰድ ይችላሉ።

መስፈርቱ፦

፩. መግዛት የማይችሉ
፪. ተማሪዎች - በተለይም የመጨረሻ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች። ወይም ደግሞ የጉባኤ ቤት ተማሪዎች።

#ለቡ፥ መጽሐፉን ከባኮስ መጻሕፍት መደብር መውሰድ ይችላሉ።

4 месяца, 2 недели назад

ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ወደ ጋብቻ ከመግባታቸው በፊት እንዲሠለጥኑ የሚመከርበት ምክንያት ጋብቻ ዓላማው ጽድቅ ስለ ኾነ ነው። ግቡ ራስንም ሌላውንም ማዳን ስለ ኾነ ነው።

ይህን እንዴት መከወን እንደሚቻል ቀድሞ መማር ደግሞ ከውድቀት ይጠብቃል። ቢወድቁ እንኳን ለይቅርታ ብሎም ለንስሓ ቅርብ ያደርጋል። ከገቡ በኋላ ለማወቅ መሞከር በጣም ብዙ ዋጋ ያስከፍላልና። በነፍስ በሥጋ ይጎዳልና።

አሁን ያለው ባሕል በየጊዜው ተቀያያሪና ከክርስቲያናዊ አስተምህሮ እጅጉን እየራቀ ያለ ነው። ሲቀያየር ደግሞ ልዩ ልዩ ፈተናዎችን ይዞ ነው። ስለዚህም በዚህ ወጀብ መካከል እንዴት ቀዝፎ መዋኘት እንደሚቻል ማወቅ ያለብን ቀድመን እንጂ ትን ሲለንና በሞት አፋፍ ላይ ኾነን አይደለም።

ሥልጠናው እንዲኾን የሚመከረው የሰርግ ቀን ከመቆረጡ በፊት ነው - በትንሹ ከ6 ወር በፊት! ለምን ከተባለም ውሳኔያቸውን እንደ ገና ሊያዩ ወይም አንዳንድ መስተካከል ያለባቸው ነገሮችን ለማስተካከል ጊዜ ሊፈልጉ ይችላሉ።

ሥልጠናውን እንደ ቀላል ማየትም አያስፈልግም። በጣም ትንሿ ነገር እግዚአብሔር ወደሚጠላው ወደ ፍቺ ልታደርስ ትችላለችና።

5 месяцев назад

የጋብቻ ትምህርትን አስቸጋሪ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ፥ ጥንዶች እገዛ ፈልገው የሚመጡት ጉዳያቸው ሥር ከሰደደና እነርሱም ብዙ ከተቋሰሉ በኋላ ነው። ማከምና ቀድሞ መከላከል ግን እኩል ጉልበት ገንዘብ ጊዜ አይፈጁም። ስለዚህም ለጠቅላላ ዕውቀት ይህን ማወቁ መልካም ነው፦

1⃣ የቅድመ ጋብቻ ትምህርት ለዕጮኛሞች መሰጠት ያለበት የሰርግ ቀናቸውን ከመወሰናቸው በፊትና ከመጋባታቸው ከ6 ወር በፊት ነው።

2⃣ የድኅረ ጋብቻ ትምህርት ደግሞ ጥንዶች ከተጋቡ ከ6 ወራት በኋላ መውሰድ አለባቸው።

እነዚህ ጊዜያት የተመረጡበት የራቸው ምክንያት አላቸው።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago