The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months ago
ፍቅረኛ አሎት?😍🤷♂
#ቆንጆ **ነኝ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ስላንቺ ቁንጅና
ስላንቺ ቁመና
ከንፈር እና ዳሌ
ጥርስና ተረከዝ ፣ ፀጉር ገለመሌ
ለጡት ለወገብሽ ፣ ለፀባይሽ ጭምር
በግጥም በዝርው ፣ ባድናቆት ስዘምር
እስከዛሬ ድረስ...
ውበትሽን አግንኜ ፣ ሰርክ መለፈፌ
እኔ ስለራሴ ...
አንዳች ቀን እንኳን ፣ ግጥም አለመፃፌ
ሲትጠዪኝ ቆጨኝ
ቢሆንም ቆንጆ ነኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እርግጥ ነው ብዙዎች...
ስለኔ ሳወራ ፣ ድንገት ያኮርፉኛል
ያንተን ሌሎች ያውሩ ፣ ብለው ይነግሩኛል
እኔን ከኔ በላይ...
እርግጠኛ ሆኖ ፣ ሌላ እንዴት ያውቀኛል?!
።።።።፣፣
እናም እኔ ማለት...
ቁመቴ ከአክሱም ፣ በእጥፍ ይረዝማል
ጣፋጭ አንደበቴ...
መስማት ለተሳነው ፣ ለስልሶ ይሰማል
ውብ አረማመዴ...
እንኳን መንገደኛን ፣ መንገድን ያቆማል፡፡
፡፡፡፡፡፡
የከንፈሬ ወዙ ፣ ጥፍጥናው አያልቅም
ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው!
ሺ ሟች ላለማየት ፣ ኗሪ ፊት አልስቅም፡፡
ከአይኔ ብሌን ውስጥ ፣ ብርሐን ይፈልቃል
አይኔን ያየ ሁሉ
ልቡን አሳውሮ ፣ በፍቅር ይወድቃል፡፡
፡፡፡፡፡
የገላዬ ጠረን ፣ ከሽቱ እጥፍ ነው
መልካም ጠረን ሁሉ...
አለ ባሉት ስፍራ ፣ እኔ አለሁ ማለት ነው፡፡
ፀባየ ትሁት ነኝ ፣ ምጡቅ ነው እውቀቴ
ግርማ ሞገሳም ነው ፣ ተክለ ሰውነቴ
ያየኝ ይወደኛል
የወደየኝ ሁሉ ፣ መቼም አይጠላኝም
ከዚ በላይ እንኳን...
ብዙም ስለራሴ ፣ የማውቀው የለኝም፡፡
እንደውም እንደውም...
አልጎርርም እንጂ ፣
ያፈር ሰውነቴን ፣ በቁንጅና አብየው
ቆንጆ ማየት ሲያምረኝ ፣ራሴን ነው ማየው፡፡
ብቻ ግን ቆንጆ ነኝ!!!😜😂*📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱*
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
የሆነ ቀን አሞኝ አልጋ ላይ ብዙ ጌዜ ከረምኩ ምኔም እምድን አይመስልም ነበር እሚያስቡልኝ አምላክ ሞቴን ቢያፋጥንልኝ ጥሩ እንደሆነ በልባቸው የተመኙልኝ ይመስለኛል ...
እኔ ግን ዳንኩ
የሆነ ግዜ ሱስ ጀመርኩ ጫት ሲጋራ መጠጥ ፊቴን እስኪቀይረው ተከተብኩ አዬ መና ቀረ ተባልኩ
እኔ ግን ሱስ አቆምኩኝ ።
የሆነ ቀን ጓደኞቼ ሁሉ አልፈው እኔ አስረኛ ክፍል ወደኩ ሁሉም በጋራ አዘኑልኝ ብለን ነበረ አሉኝ ሰፈር ቀረ አሉኝ እኔ ግን ተመልሼ private ተፈትኜ አልፌ እስከሁለተኛ ድግሪ ድረስ ተማርኩ
የሆነ ግዜ እናቴ ለቆሶ ልቴድ ፈልጋ ነጠላ ስትበደር አይቻት እኔ ሳድግ አምስት ቅያሪ ነጠላ እገዛልሻለሁ አልኩኝ የሰሙ ሰዎች ሳቁብኝ ለምን እንደሳቁ አላቅም እኔ ግን ስራ ስይዝ አረ አምስት ነጠላ ምን ይሰራል እያሉኝ ጥለቱን እየቀያየርኩ ገዛው ....
ትላንት ብዙ አይሆንምን አልፌያለሁ ። ብዙ አበቃለትን ተሻግርያለሁ ፣ ነገ የተሻለ እንደሚሆን ትላንት ምስክሬ ነው ።
መሞከር ፣መማር፣ ለመሻሻል መጣር ፣መታገስ አናቆምም ሁሉም ይስተካከላል ❤
©Adhanom Mitiku
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ከልጅነቱ ጀምሮ እናቱን አያውቃትም። አባቱ ነው እንደ እናትም እንደ አባትም ሆኖ ያሳደገው። ስለ እናቱ አባቱን ደጋግሞ ሲጠይቀው "ግዜ መልስ ይሰጥሀል" ከማለት ውጭ ምንም ብሎት አያውቅም። ሰው ነው እና እድሜው ለፍቅር ሲደርስ ከአንድ መልከ መልካም ኮረዳ ጋር ተዋወቀ። ከልቡ አፈቀራት እርሷም ከልቧ እንደምታፈቅረው ነገረችው አመናትም። ከአንድ አመት የፍቅር ግዜያት በኋላ ያች ውብ እንስት እንቆቅልሽ በሚመስል መልኩ ከፊቱ ተሰወረች። ችግር ገጥሟት ነው ብሎ አሰበ በጣም ጨነቀው። የዛን ግዜ የጭንቅ አማላጇ ማሪያም ትዝ አለችው እና ወደ ቤቷ አመራ። በዱርየ ልቡ እንዲህ ሲል ፀለየ " ማሪያም ሆይ የእውነት ከጭንቅ የምታማልጅ ከሆነ በዚች ሰባት ቀን ውስጥ ከልቧ የምትወደኝን,ዘወትር ስለ እኔ የምትጨነቀዋን ሴት ከችግር ፈትተሽ ወደ እኔ አምጭልኝ " ። ከፀሎቱ ማግስት ልጄ በራብ እና በውሀ ጥም ከሚሰቃይ ብላ ስደትን የመረጠች እናቱ, በባዕድ ሀገር ላይ በወንበዴዎች ተይዛ የስቃይን ገፈት እየቀመሰች ግን ስቃይን ቸላ ብላ ስለ ልጇ ስትጨነቅ የኖረች እናቱ ከእስራቷ ነፃ ወጥታ በድንገት ከተፍ አለች። ልጁ አልመሰለውም። ስንት አመት ሙሉ ትታኝ የኖረች ሴት ካደግሁ በኋላ ለምን መጣች ብሎ ተናደደ። እነሆ ከፀለየ ሰባት ቀን ሆነው። ፍቅረኛው ግን የውሀ ሽታ ሆነች።
ዛሬም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደ እና
በቁጣ ቃል "እነሆ ከነገርሁሽ ሰባት ቀን ሆነኝ የፀሎቴ መልስ የት አለ?" ሲል አምባረቀ። የሚፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገውን እንደሰጠችው አላወቀም። ፀሎቱን ሰምታ ዘወትር ስለ እርሱ የምትጨነቀዋን ሴት እንደሰጠችው አላወቀም። የተሳሳተ ፀሎቱን አስተካክላ እንደሰማችው አላወቀም። የዱርየ ፀሎቱን ስለሰማችው (ባለሀብት አግብታ ወደ ሌላ ሀገር ኮብልላ ከእነመፈጠሩም የረሳችውን ፍቅረኛውን ትታ ሁለት አስርት አመታት ሙሉ በስቃይ እረመጥ እየተቃጠለች ስለእርሱ ታስብ እና ትጨነቅ የነበረች እናቱን) እንደሰጠችው አላወቀም😭😭
✍ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ተቁነጥንጣ ቀረበችኝ
ተቻኮለች እንዳፈቅራት ፣
ተጨነቀች ወዲያው ደሞ
ተቻኩየ ስላቀፍኳት ፣
ትፈጥናለች ለማግኜት
ልቤን አርጋው የቀበሌ ፣
ታምር አርጋ ቆጠረችው
በእሷ ፍቅር መቸኮሌ ፣
መቸኮልን አስለምዳኝ
ተጣድፎ ዝግታየን
አቻኩላ አገባችኝ
እይ ስትል እድሜየን ፣
ተቻኩላ አስለምዳኝ
ረጋ ያለ አረማመድ ፣
ተቻኩየ ጥያት ሄድኩኝ
ቀድማ ከእኔ እንዳትራመድ ፣
'
ግዕዝ ሙላት
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
*የተደበቀ ንስሀ
"""""""""""""""""
አስመሳይ ነኝ ወረተኛ
ታውቀኛለህ የኔ ጌታ፣
እየጠራሁ ለማመስገን
አንደበቴም አይፈታ፣
እልልታዬ ጊዜያዊ ነው
ማወደሴ ማሞገሴ፣
በቃልህ ጠግቤ ባድርም
ሽንገላ ነው ጠዋት ቁርሴ፣
አትማርም! ሀጢያት ተንኮል
ማታለል ነው ግብሯ ነብሴ፣
ክብር አድርገህ ያለበስከኝ
ተቀዳዷል ፀጋህ ልብሴ፣
ጎደሎ እምነት የበዛውን
ጾም ጸሎቴን አርገህ መባ፣
ለይስሙላ ደጆህ ስቆም
ብትፈቅድልኝ እንድገባ፣
ምህረትህ አረስርሳኝ
በንስሀ ብታጠብም፣
ዛሬም ልቤ ክፉን ብቻ
በጎን ነገር አያስብም።
ታውቀዋለህ ክንብንቤን
ገመናዬን ሁሉ ገልጠህ፣
ግን አኖርከኝ በም'ረትህ
ከበደሌ እኔን መርጠህ፣
ተዘርግተዋል እጆችህ
ሊቀበሉኝ በይቅርታ፣
ስሼሽ አይተህ አተዎኝም
አንተን መቅረብ ሳመነታ፣
በሀጢያቴ ስቅበዘበዝ
በስህተቴ ስደናቀፍ፣
አትሰለችም በምህረት
በቃሽ ብለህ እኔን ማቀፍ፣
ይቅር ባይ ነህ አትለወጥ
ለዘላለም በጎ መልካም፣
በቤትህ መመላለሴን
ቆጥረህልኝ እንደ ድካም፣
የሚያድነኝ አጣሁ ብልም
ብታነቅም በሾህ መሀል፣
ትርጉም የለሽ ልመናዬ
ጭንቅ ሀዘኔ ተሰምቶሀል።
ትሰማለህ ሹክሹክታዬን
ትረዳለህ የኔን ስሜት፣
አቻየን ካገኘሁ ቤትህ
ይቀናዋል ላኣፌ ሀሜት።
በከበረው አፀድ ቅጥር
ያንደበቷ ቃል የማይጥም
ብኩን ልጁን የሚያስገባት፣
የት ይገኛል ከአንተ በቀር
የሰማይስ የምድር አባት?#ኤዶምገነት_ፃፈችው@Edom_Ge📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱*
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ለባለ ጠመኔው
የትውልድ አሻራ የሀገር መሠረት
ዘመን አሻጋሪ የህመም መድሀኒት
የነገ አለኝታ የመበልፀግ ሀውልት
እውቀትን ደራቢ የመኖር ትሩፋት
የስራውን እሩብ ላልተነገረለት
ለሀገር መስራቹ አንዴ ልቀኝለት
"ባለመኖር ኖሮ መኖርን የሰጠ
ሀገር ለማስከበር ክብሩን የረገጠ
እውቀትን ሊገዛ ጉልበቱን የሸጠ"
"በረሀ ላይ ወርዶ
በውሀ ጥም ሲቀጣ
ከሰው በተለየ
ነጭ ላብ ለጠጣ"
"የሚበላ ጠፍቶ ራብ ሲደቁሰው
የጠመኔ ብናኝ ባፉ ለጎረሰው
ሌላው ነገር ቢቀር
እስኪ አንዴ እናስታውሰው"
"ብዙ ኪሎ ሜትር
በጭኝጫ ላይ ሄዶ
በበረሃው ነዳድ
በረሀ ላይ ነዶ
በውርጭ በውንሽፍር
ፊቱ ተጨማዶ
ሀገርን ሲያነሳ
ከሰው ክብር ወርዶ
ገና በልጅነት
ከፊቱ ሲጠፋ የልጅነት ወዙ
ቁራሽ እንጀራ እና
ስቃይ መከራ ነው የዚ ሰው ደሞዙ
ለዚህ ብርቱ ጀግና የሀገር ባላደራ
ታሪክን አስታውሶ ታሪክን ለሰራ
ሀገር ለገነባ ትውልድን ላኮራ
ሌላው ነገር ቢቀር
like እንለግሰው እንስጠው አሻራ
✍ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ያምላክ ጥላ ወዴት አለ
እባክህን ፀሀይ በዛ
በወዝ እንኳ ስናማኻኝ
ዕንባችን በአይን ወዛ
እባክሽን እመቤቴ
ክንድሽ እሳት በታቀፈው
ይቺን ሀገር ውሰጂልን
እቅፍሽን እንቀፈው
geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months ago