Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

Description
🌹የተለያዩ ታሪካችን ያገኛሉ 🌹


➴ ለአስተያየት➴ @Rominya_1

Since 2011 E.C.
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month, 2 weeks ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month ago

5 days, 23 hours ago

‍ ​​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹

በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ በ ፍቅር ታሪክ የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

ክፍል 1⃣2⃣

ጥያቄው ምን ብዬ ነው እቺን እብድ መቅዲን ከእንቅልፏ ተነሺ የምላት? ከእንቅልፏ ተነስታ ቤቱን ቅውጥ ከማድረጓ በፊት አንድ መፍትሔ መፈለግ አለብኝ🤔😛
ቆይ ክፍሉ የኔ አይደል?
እኮ እሷ አይደለች በእኔ ክፍል ውስጥ ያለችው? ታድያ ለምን ክፍሉን እኔ ቅውጥ አላደርገውም😃😆😛ብዬ እናቷ እና አባቷ እንዳይሰሙ ድምፅዠፄኝ ቀንሼ አንቺ መቅዲ ተኒሽ ተኒሽ ብዬ ከእንቅልፏ ደንግጣ ስትነሳ አንቺ በሰው ክፍል ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ? ብለሽ ብለሽ በማታ የሰው ክፍል ዙው ብለሽ ገብተሽ መተኛት ጀመረሽ?
ቆይ እነ እማማ አሁን እዚህ ክፍል ውስጥ ቢያገኙሽስ በቃ አሁን ቶሎ ብለሽ ወደ ራስሽ ክፍል ሂጅ አልኳት😛😆😃

አቦ ባክህ ምን ትቀበጥራለህ ከእኔ ጋር አንድ ክፍል መተኛት በራሱ ክብር መሆኑን አታውቅም የኔ ሽታ ራሱ ለህመምህ መድኃኒት እኮ ነው፣ በቃ ይወጣልካላ ምን ታካብዳለህ ብላ ቂጧን ዘጭ ዘጭ እያደረገች ስትወጣ የኔም ልብ ከትልቁ ቂጧ ጋር አብሮ ወጣ😛😆😅
እኛ ወንዶች በየትኛውም አጋጣሚ ያቺን ነገር ካየን እኮ አእምሮአችን ትክክል አይሰራም አይደል😛
በነገራችን ላይ ትላንት መቅዲ ስለ ሽቶ ስታወራ ልቤ ጥርጣሬ ውስጥ ገብቷል የትላንቱ የደስታ ሁኔታ ብዙም ደስ አላለኝም፣
ቆይ ለምን ለመቅዲ ሽንት ቤት ነኝ ብሎ ዋሻት? ከየት ነው የመጣው?
ሽንት ቤት ማንም ሰው አልነበረም አይደል? ለምን ከሽንት ቤት ነው የመጣውት ብሎ ይዋሻል?
ብቻ ሁሉም ነገር ደስ አላለኝም፤
ይኼን ነገር ለማጣራት ለደስታ በድጋሚ ናይት ክለብ እንሂድ የሚል ሃሳብ መስጠት አለብኝ፣
ለደስታ ስልክ ደውዬ አንተ ደስታ ቆይ ግን ሞኝ ነህ ሊባል? አንድ ቀን ብቻ መዝናኛ ቦታ ወስደህ ዝም ትላለህ? ሴቶች ምንያህል መዝናናት እንደሚወዱ ታውቃለህ አይደል የዚያን ቀን ናይት ክለብ ይዘሃት ስለሄድክ መቅዲ በጣም ደስ ብሏታል ለምን በድጋሚ ይዘሃት አትሄድም አልኩኝ
አንተ በጣም ምርጥ ሃሳብ ነው ለምን እንደውም በፍጥነት አንሄድም ሲለኝ እኮ ነገ ማታ ሄደን እንቀውጥ አልኩት ምርጥ ሃሳብ ነው አንተ ብቻ መቅዲን አሳምናት አለኝ ለመቅዲ ችግር የለም እሱን በእኔ ላይ ጣለው ብዬ ስልኩን ዘጋውትና መቅዲ ክፍል ሄጄ ሰርፕራይዝ አልኳት
ምንድነው? ዛሬ ምን አዲስ ነገር አለ ስትለኝ ነገ በድጋሚ መዝናኛ ቦታ እንሄዳለን አልኳት
ዋውውው ደስ ይላል ግን የት ብላ ጠየቀችኝ የባለፈው ቤት ነዋ አልኳት ባክህ እኔ እዛ ቤት መሄድ አልፈልግም እንደ ባለፈው ልትሆኑ ነው አይደል አልፈልግም ስትለኝ
መቅዲ አንቺ ደግሞ ቂም መያዝ ስትወጅ በቃ ይቅርታ አልኩሽ አይደል ብዬ ተቆጥጬ ልሄድ ስል አንተ ደግሞ በትንሽ በትልቁ ቁጣ ታበዛለህ በቃ እንሄዳለን አለችኝ
ዬስ ዬስ ብዬ ወደ ራሴ ክፍል ሄድኩኝ፣ በሁለተኛው ቀን እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ናይት ክለብ ሄደን... ገና ቤት እንደገባን መቅዲ እና ደስታ መቀወጥ ጀመሩ፣
እኔ ግን የመጣውት ለመዝናናት ሳይሆን ለምርመራ ስለሆነ አንድ ጥግ ላይ ቁጭ ብዬ አንድ መጠጥ ይዤ የትላንቷን ልጅ በአይኔ መጠበቅ ቀጠልኩኝ፣
በድንገት ከየት እንደሆነ ዱቅ አለች
ዋውውው እንዴት አባቷ ታምራለች!
አይደለም በልቶ በለመደ ሰው ይቅርና እኔ ላይ ራሱ እንትን ሳይሆንብኝ አይቀርም😆😅😃😛
ብቻ ትላንት እንደዚህ ደስ በሚል ድምፅ እየቀባጠራች የነበረችዋ ልጅ እሷ ናት እንዳትሉኝ😅😛😛
ደስታ ልጅቷ ቤት ከገባች በኋላ ዳንሱ ሁሉ ጠፍቶበታል ቆይ ቆይ ምስጢር ሳይኖር አይቀርም
.
እኔም አይኔን ከልጅቷ አንስቼ የደስታን ሁኔታ በጥብቅ መከታታል ቀጠልኩኝ፣ ደስታ ከኪሱ ስልክ አውጥቶ ምን እንደሆነ አላውቅም ብቻ የሆነ ነገር አንብቦ ነው መሰለኝ ለመቅዲ ፍገግታ ሰጥቶ እኔ ጋር መጣና አንተ በቃ ሁሌም እዚህ ቁጭ ለማለት ነው የምትመጣው ማለት ነው? ተነስ ዘና በል እንጂ ምንድነው እንደዚህ ቁጭ ብሎ ሰውን ማየት ይልና እጄን ይዞ አስነሳኝ፣
በአንተ ቤት ለኔ አዝነህ ሞታሃል አልኩና እኔም እሺ ብዬ ተነስቼ ከመቅዲ ጋር መደነስ ጀመርኩኝ፣
መቅዲ እኔ ስመጣ ይበልጥ በደስታ መቀወጥ ጀመረች የኔ የዋሀ እሷ እኮ እንደ ሰው ተንኮል ምናምን አታውቅም አይደለም እንደ'ኔ እና ደስታ የቅርብ ሰው ይቅርና የሩቅ ሰውንም ቢሆን ጥርጣሬ የሚባል ነገር አታውቅም፤በልቤ ቆይ ግን ደስታ ይቺን ልጅ ካየ ብቻ ነው እንዴ ሽንት የሚመጣበት?
የሆነ ሽንታም ነገር ዛሬ እስኪ ጉዱ ይወጣል ብዬ ለመቅዲ አሁኑኑ መጣሁኝ ቁጭ ብለሽ እረፍት አድርጊ ብዬ ከቤት ወጥቼ ሽንት ቤት ሄድኩኝ፣ እንደ ባለፈው ሁሉ ሁሉንም የወንዶች ሽንት ቤት ዞር ዞር ስል ሰው የለም፣
እሺ አሁን የት ሄደ ይባላል? ይመስለኛል ደስታ ጉደኛ ሰው ሳይሆን አይቀርም ብዬ ወደ ባለፈው የሴቶች ሽንት ቤት ሄድኩኝ🤔🤔🤔🤔
ዛሬ በአንዴ አልሰጥም ብላ ነው መሰለኝ የኔ ንግስት እኔ'ኮ ካንቺ ሌላ ሰው አላውቅም እባክሽ ሞትኩኝ ምናምን ይለታል😆😅
እሷም ዛሬ ሽንት ቤቱ ፖሊስ ጣቢያ መስሏት ነው መሰለኝ ጥያቄ አብዝታለች እሺ አብረህ እየደነሰች የነበረችሁ ልጅስ ማናት ብላ ትጠይቃለች እሱም እህቴ ናት እኮ ይለታል፣ እህትህ ከሆነች ታድያ እኔ ያንተ ፍቅረኛ እንደሆንኩ ለምን ትደብቃለህ ትላለች እሱን ነግሬሽ የለ ቤተሰቦቼ በዚህ ሰአት ይኼን ነገር አይፈልጉም እሷ አየች ማለት ደግሞ በቃ ቤተሰቦቼ ሰሙ ማለት ነው አላት፣ አንተ ግን እህትህ በጣም ወረኛ ናት ስትል
በጣም እንጂ በቃ አሁን ስጪኝ ይላታል፣
ሰጠችው መሰለኝ ቤቱ ለጥቂት ደቂቃ ዝም ዝም አለ😃😆😅😛😛በዝምታ ብዙም አልቆየም የተለመደው ጩኸት ተጀመረ...
እናንተ ጉደኞች ብዬ ልጁ ማን እንደሆነ የግድ ማወቅ ስላለብኝ ጆሮዬን ይዤ ዝም አልኩኝ😃
ጆሮ ለምን ትይዛለህ የሚል ግፍኛ ሰውም እኮ ይኖራል😆😅😛
ታዲያ ልሙት  እንዴ😛😛
እዛው ክፍል ወደ 40 ደቂቃ ያህል ደቂቃ ቆዩ፣ በልቤ እዚህ ክፍል ውስጥ ያለው ዓሳማ ነው ወይስ ሰው ነው ሰው ከሆነ ለምን አይወጣም እያልኩ  ቀበቶውን ጠበቅ ጠበቅ እያደረገ የኔው ደስታ ከክፍሉ ወጣ😢😢😢😢
🗡🔪🗡🔪በዚህ ነበረ ማለት

አንተ እዚህ ክፍል ምን ታደርጋለህ አልኩት ሽንት ቤት መሆኑን እያወክ ምን ታደርጋለህ ትላለህ አለኝ በእኔ ላይ እየሳቀ እኮ የሴቶች ሽንት ቤት አልኩት በስህተት ገብቼ ነዋ ብሎ ከአፉ አውጥቶ ሰይጨርስ ልጅቷ ተከትላ ወጣችና ምንድነው ምንድነው አለች ቲሺሺሺ አንቺ ደግሞ ምን አይነት ባለጌ ነሽ? ትንሽ ሼም የለሽም? ቢያንስ ክላስ እንያዝ አይባልም ደሞኮ እሱ ወንድ ነው ስለ ህይወትሽ ምንም አይጨንቅሽም? አንቺ ግን ሴት ነሽ ችግሩ ያንቺ ነው አልኳት
አንተ እንደዚህ አትበል ፍቅረኛዬ እኮ ነው አለችኝ ኧረ ወደዛ ሂጅ በመጀመርያ ደረጃ ለክብርሽ የሚጨነቅ ከልቡ የሚወድሽ ፍቅረኛ እዚህ ሽንት ቤት አምጥቶ ክብርሽን በአደባባይ አይገፈውም እሺ ሴቶች ግን ጅል ናችሁ ሲባል ሌላው ቢቀር ይቺን ብቻ ማስተዋል እንዴት ያቅታችዋል ብዬ ተናድጄ ሁለቱንም ጥዬ ሄድኩኝ።

ክፍል አስራ ሶስት ሐሙስ ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።

‌‌‌‌‌‌‌     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄
♥️ የክብር እስፖንሰር ♥️
      ‌   https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
••●◉Join us share

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@yefkrtarik @yefkrtarik

Telegram

ሳሎዳ ትሬዲንግ ️

***📣*** ለቤቶ ቢሉ ለመስርያ ቤቶ የሚሆኑ ህይወቶን ቀለል የሚያደርጉ ቁልፎች | እጀታዎች | ማጣበቂያዎች | ኤምዲኤፎች እኛ ጋር ያገኛሉ ይጎብኙን ***🌐*** :: ስልክ +251914855557

‍ ​​​***💟******🌹***ሚስጥራዊ ሚስት***💟******🌹***
1 week, 1 day ago

‍ ​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹

በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

ክፍል ❶❶

እብዶች ብቻ በሞሉበት ጭስ እና አረቄ ተደምሮ እኔንም ሞቅ ሞቅ ማድረግ ጀምሯል😃😆😛
መቅዲ ጆን ተነስ እንደንስ ብላ እጄን ይዛ አንስታ መደነስ ጀመረን
ግን እኔ ምንም አልችልም ለሷ ደስታ ብዬ ነው እንጂ ይመስለኛል ሁሉም ሰው በእኔ እየሳቀ ነው😃😆😛
ደስታ ለጥቂት ደቂቃዎች ቁጭ ብሎ ከተመለከተ በኋላ ብድግ ብሎ ተነስቶ መጣና የመቅዲን እጅ ይዞ ሁለቱም ዳንስ ጀመሩ....
ተመስገን ጨንቆኝ ነበረ እስኪ የእናንተን ደግሞ ልመልከት ብዬ ቁጭ ብዬ መጠጣት ቀጠልኩኝ፣
ኧረ ደስታ አልተቻለም ቀልድ አይደለም የእውነቴን ነው እንደውም ብዙ ሰዎች በአድናቆት መመልከት ሁሉ ጀምረዋሉ፤

ቆይ ደስታ ሱቅ ውስጥ እየተለመመደ ነው እንዴ የሚውለው? ብቻ ችሎታው በጣም ገርሞኛል! ደስታ እና መቅዲ ሞቅ ብለው እየጨፍሩ አንዲት እብድ የሆነች ልጅ መጥታ ለደስታ የሆነ ምልክት ሰጥታ ከቦታው ዞር አለች፣
ደስታም ይበልጥ መቀወጥ ጀመረ.... ልጅቷ ለደስታ ምንድነው ያለችው ብዬ የደስታን ሁኔታ ማጥናት ጀመርኩኝ፣
ከዛ በኋላ ብዙም አልቆየም በፍጥነት መጥቶ አንተስ ለምን ቁጭ ትላለህ ለጫወታ አይደል እዚህ የመጣነው? ተነስ ዘና ፍታ እንበል ብሎ እጄን ይዞኝ አንስቶኝ ለሦስት መቀወጥ ጀመረን...
ለካ እሱ እኔን ያነሳኝ እሱ ዞር ለማለት ስለፈለገ ነው፣
ሽንት ቤት ደርሼ መጣሁ ብሎ ሲሄድ እኛ ሁለታችንም ሞቅ ብለን ቤቱን ቀውጥ ማድረጉን ቀጠለን...
በዚህ መሃል ሁሉ ግን የደስታን መምጣት እየጠበቅን ነው፣
መቅዲ ደስ ብሏታል ስለ የደስታን መሄዱንም መምጣቱንም እንደ ቁም ነገር አላየችም፤
የኔን ውስጥ ግን የቅድሟ ልጅ የሰጠችው ምልክት ሰላም ነስቶታል በዚያ ላይ ልጅቷ ቤት ውስጥ የለችም!
ቆይ ነገሩ ምንድነው? ደስታ እስከአሁን የት ነው ብዬ ወደ ሽንት ቤት ሄድኩኝ....
የወንዶች ሽንት ቤት እና የሴቶች ሽንት ቤት ለየ ብቻ ነው ያለው፣ በመጀመርያ ወደ ወንዶች ሽንት ቤት ሄድኩና ሁሉንም ማንኳኳት ቀጠልኩኝ
እንደ አጋጣሚ ሆኖ ግን በሁሉም ሽንት ቤቶች ሰው አልነበረም:
የሴቶች ሽንት ቤት መሄድ ደሞ ያው ክልክል ነው ምን ብዬ እሄዳለሁ ብዬ ልመለስ ስል ውስጤ የሴቶችንም ሽንት ቤት ደርሰህ ተመለስ እያለ ትእዛዝ መስጠት ሲጀምር በምን ምክንያት እንደሚሄድ ባለውቅም በቀጥታ ወደ ሴቶች ሽንት ቤት ሄድኩኝና ሁሉንም ዞር ዞር ብዬ ማንኳኳት ቀጠልኩኝ፣

አሁንም ምንም አዲስ ነገር የለም!
ጥግ ላይ ወዳለው ወደ መጨረሻው ክፍል ስደርስ ግን በሩን ከማንኳኳቴ ቀድሞ በጆሮዬ ላይ የሆነ ድምፅ መጥቶ ገባ🤔🤔🤔
ብቻውን የሚያወራው ሰው ግን ጤነኛ ነው ወይ ብዬ ልሄድ ስል በሽክሹክታ የሚያወራ የወንድ ድምፅ በጆሮዬ ላይ መጥቶ ወደቀ። ምን?😆😃😛በስህተት የወንድ ሽንት ቤት ነው እንዴ የመጣውት ብዬ በድጋሚ ወጣ ብዬ ሳነበው አሁንም የሴቶች ሽንት ቤት ይላል🤔🤔🤔
ይኼ ወንድ በሴቶች ክፍል ምን ያደርጋል ብዬ ሄጄ በር አጠገብ ቆምኩኝ፣
ባልመጣ ይሻል ነበረ😬😬😬😬😬
እዚህ ክፍል የአሜሪካን የፍቅር ፊልም እየተሰራ ነው😬😬😬
መዝናናት ማለት እንደዚህ ነው እንዴ? እኔኮ ጠጥቶ ደንሶ መሄድ ብቻ መስሎኝ ነበረ ለካ ሌላም ነገር አለ😛😆😃😆😃
አሁንም ምንም የወንድ ድምፅ የለም ብቻ የሆነች ሴት ያዘኝ ልቀቀኝ ሞትኩኝ እያለች ነው፣
እውነትም ችግር ውስጥ ትሁን ወይ ብዬ በሩን ለማንኳኳት ስል የኔ ንጉስ እንደዛ እንደዛ ደስ ይላል ስትል ሰምቼ አምላኬ ምን ቤት ነው የመጣውት ብዬ ተመልሼ ወደ መቅዲ ሄድኩኝ
አንተ ከየት ነው የመጣው? ቆይ ሁለታችውም ጥላችውኝ ትሄዳላችሁ? ሁለተኛ ከእናንተ ጋር አልመጣም በቃ ወደ ቤት ውሰደኝ አለች፣ በዚህ ጭቅጭቅ ውስጥ እያለን ደስታ መጣ....
.
መቅዲ አንተ ደስታ ከየት ነህ ስትለው ሽንት ቤት እኮ ነው የሄድኩት ምነው ቆየሁ እንዴ ሲላት ከመቅዲ ቀድሜ ኧረ ምንም አልቆየህም መቅዲ እኮ ትንሽ ሞቅ ብላለች የእሷን ነገር አትስማ አልኩት፤ እሱም ትንሽ ስቆ አንተም ትንሽ ሞቅ ያለህ ትመስላለህ አሁን ወደ ቤት እንሂድ አለኝ
ጨረስክ እንዴ አልኩት😆😛😃
ደንግጦ እንዴ ምኑን ሲለኝ
አይ ጨዋታ በቃህ ወይ ለማለት ነው አልኩት
አዎ በእናትህ በጣም ድክም ብሎኛል ቀን ስራ ላይ ነው የዋልኩት ሲለኝ ሰው የማታ ስራ ጨምሮ እየሰራ አይደል አልኩት የሽንት ቤቱን ልጅ በልቤ እያሰብኩት😆😃😛😃
መቅዲ እና ደስታ ምንም ሙድ የሌለው ምሽት አብረው አሳልፈው እኔም ሰምቼ የማላውቀውን የሴት ድምጽ ሰምቼ😬😬ወደ ቤት መጣን፣ እኔ ለሽንት ከመኪና ውስጥ ቀድሜ ወጣሁኝ ለካ በዚህ አጋጣሚ ደስታ የመቅዲን ከንፈር ለመሳም ሙከራ እያደረገ ነበረ😆😛😃
ሙዱ ያልገባት መቅዲ ተቆጥታ ከመኪና ውስጥ ወጣች ቆይ እሷ ደስታም እንደ'ኔ ወንድሟ እንዲሆን ትፈልጋለች እንዴ ነው ወይስ ከንፈሯም በድንግልና እንዲቆይ ትፈልጋለች😆😃😬

ደስታ ከመኪና ወርዶ ቤቱ ገባ፣
እኔም መኪና ውስጥ ገብቼ መቅዲን ይዣት ቤት ስመጣ መንገድ ላይ አንተ ጆን ቆይ ደስታ የወንድ እና የሴት ሽቶ ለይቶ አያውቅም እንዴ የሆነ ሴታ ሴት ነገር ነው ደግሞ እሱም ወንድ ሆኖ ከንፈሬን ሊስመኝ ይሞክራል?አቦ  ምን አይነቱ ዱቄት ነው ስትለኝ አንቺ ፍቅረኛሽ እኮ ነው ለምን እምቢ አልሺው አልኳት
ባክህ ወደዛ ሂድ በለው የምን ሩጫ ነው? ቀስ አይልም ታድያ አለችኝ
የኔ እህት ዘመኑ እኮ የሩጫ ነው ብዬ እተሳሳቅን ቤት ደረሰን😆😃

ሁለታችንም ድክምክም ብለናል፣
እንደምንም ሆነን የግቢውን በር ከኪሴ ቁልፍ አውጥቼ ከፍቼ ገባን፤
ከዛ በኋላ ሁለታችንንም የት እንደወደቅን አላወቅንም ነበረ😛😆😃
ጠዋት ላይ የክፍሌ በር ሲንኳኳ ደንግጬ ከእንቅልፌ ስነሳ አጠገቤ ሌላ አስደንጋጭ ክስተት ተፈጥሯል፣ መቅዲ ደረቴ ላይ ለጥ ብላ ለራሷ በህልሟ ነው መሰለኝ የፍቅር ግጥም ምናምን በማንበብ ላይ ቢዝ ሆናለች😛😛😛
እሺ ቤቱን የሚያንኳኳ ሰው ማነው?
እናቷ ወይስ አባቷ? ምን ብዬ ቤቱን እከፍታለሁ? ምክንያቱም መቅዲ በእኔ አልጋ ላይ ናት!
ለዚህች የዋሀ መቅዲ ተነሽ ብላት ምናልባት እሷም ቤቱን በአንድ እግሯ ልታቆም ሁሉ ትችላለች😩
ወይኔ ጉዴ ብዬ በሩ አጠገብ ሄጄ ማነው አልኩት
አንተ ጆን በሩን ክፍት አሉኝ
የመቅዲ እናት ናቸው፣
እሺ እማማ መጣሁ መጣሁ ብዬ ዝም አልኩኝ
የኔን ድምጽ ሰምተው ሰላም ናቸው ብለው ነው መሰለኝ ትተውኝ ሄዱ
ተመስገን አምላኬ!
ጥያቄ አሁን ይቺን እብድ መቅዲ ምን ብዬ ነው ከእንቅልፏ ተነሺ የምላት?

ክፍል አስራ ሁለት ማክሰኞ ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄
♥️ የክብር እስፖንሰር ♥️
      ‌   https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
••●◉Join us share

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@yefkrtarik @yefkrtarik

┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄┄

Telegram

ሳሎዳ ትሬዲንግ ️

***📣*** ለቤቶ ቢሉ ለመስርያ ቤቶ የሚሆኑ ህይወቶን ቀለል የሚያደርጉ ቁልፎች | እጀታዎች | ማጣበቂያዎች | ኤምዲኤፎች እኛ ጋር ያገኛሉ ይጎብኙን ***🌐*** :: ስልክ +251914855557

‍ ​​***💟******🌹***ሚስጥራዊ ሚስት***💟******🌹***
3 weeks, 1 day ago

‍ ​​​​​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹

በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

ክፍል 5⃣

አቤት የውሸት መጨረሻ ገና ከጅምሩ ተይዤ ነበረ እኮ🙉🙊🙈
እነ መቅዲ ቤት ልዩ ክብር እና ቦታ እየሰጡኝ ነው እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጣቸው ለኔ ከሚገባ በላይ ብዙ ነገሮችን እያደረጉልኝ ነው ቤተሰቦቼም እንደበፊቱ ብዙ እየተቸገሩ አይደለም ምክንያቱ ደሞ የመቅዲ እናት እና አባት ናቸው።
ሁሌም ልብህ ንጹህ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ሰውን አንዴ ከፈጠረ እንዴት አድርጎ እንደሚያኖር ራሱ ያውቃል የሰው ልጅ ብዙ ስለሮጠ ስኬታማ አይሆንም መስራት መሮጥ መጥፎ ነው እያልኩ አይደለም ግን አንድ አንድ ሰዎች አለን አይደል በመሮጥ ብቻ ስኬት የሚገኝ መስሎን የሰውን ሃቅ ጭምር በእጃችን ለማስገባት ቀን በእግር ማታ በሃሳብ እየሮጥን ውለን የምናድር!
ብዙዎች አለን አይደል ለገንዘብ ብለን ጓደኛን የምንክድ💔💔
ብዙዎች አለን  አይደል ለራሳችን ስኬት ብለን ቤተሰቦቻችን ሲቸገሩ አይተን ዝም የምንለው😢😢
ዛሬ ብር መሰብሰብ ብቻ ሀብታም አያደርግህም ምን አይነት ንግግር ነው ብር ከተሰበሰበ እንዴት ሀብት አይሆንም ልትሉኝ ትችላላችሁ ግን እውነታው ብር ስለሰበሰብክ ብቻ ሀብታም መሆን አትችልም!
ሀብታም መሆን የምትችለው የምትሰበስበው ብር ላይ ምንም እንከን የማይደርስ ከሆነ ነው እንከን የሚደርስ ከሆነ አንተ ዝም ብለህ ትሮጣለህ አንተ ለብዙ አመታት ሮጠህ ያጠራቀምከው ሁሉ በአንድ አጋጣሚ ተበትኖ ታያለህ ለዚህ ነው መሮጥ ብቻ ስኬታማ አያደርግም ያልኩት
ስኬታማ መሆን የምትችለው
በቅንነት
በታማኝነት
በእምነት መሮጥ ስትችል ነው
•ቅንነት ሲኖርህ ለሌሎች መልካም ነገር ማድረግ ትጀምራለህ ለሌሎች መልካም ነገር እያደርክ ነው ማለት ደሞ ለፈጣሪ ብድር እየሰጠህ ነው እንደማለት ነው ስለዚህ ፈጣሪ ለአንተም ይሰጣል ማለት ነው

•ታማኝነት ሲኖርህ አንተ ለሌላ ሰዎች ታማኝ እንደሆንክ ሁሉ ፈጣሪ ደሞ ለአንተ ታማኝ ይሆናል ማለት ነው

• እምነት ሲኖርህ በፈጣሪ በሙሉ ልብ ማመን ትጀምራለህ በሙሉ ልብህ ፈጣሪን ማመን የምትችል ከሆነ ደሞ ፈጣሪ በእሱ የሚያምኑትን መቼም ቢሆን አይጥልም ማለት ነው
ስለዚህ የስኬት ቁልፍ መሮጥ መስራት ብቻ ሳይሆን ከስራ እና ከሩጫ ጋር ቅንነት ታማኝነት እና እምነት ጭምር ይዞ መሮጥ እና መስራት ነው
እዚህ ቤት በጣም ጥሩ የሆነ ጊዜ እያሳለፍኩ ነው መቅዲን በመኪና ት/ቤት አድርሼ መልሼ ቤት የማመጣት እኔ ነኝ
መቅዲ ቀበጥ ለሁሉም ነገር ችኩል እና የዋሀ ልጅ ናት
ከማንም በላይ የማውቃት እኔ ነኝ ብል ውሸት አይሆንብኝም፤
በርግጥ የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ አውቃለሁ ማለት ስህተት ነው እናትም ብትሆን ልጇን ሙሉ በሙሉ ማወቅ ላትችል ይሆናል ሰውን ሙሉ በሙሉ ማወቅ የሚችለው አንዱ ፈጣሪ ብቻ ነው።
ቢሆንም ግን ሰው ሰውን በሚያውቀው ልክ ከሌላ ሰዎች ይልቅ መቅዲን አውቃታለሁ ምክንያቱ ደሞ በነገሮች ላይ ግልጽ መሆንዋ ነው
በቃ መቅዲ በሁሉም ነገር ግልጽ ናት😗😗😗
ለምን ይሁን ብቻ አላውቅም የትኛውንም ነገር ከእኔ መደበቅ አትፈልግም አንድ አንድ ጊዜ ጭራሽ የሌላ ቤት ልጅ እንደሆንኩ ሁሉ ትረሳለች መሰለኝ ልክ እንደ ወንድም ሁሉ አድርጋ ትቆጥረኛለች😍😍
የዋሀ ሴቶች ግን ደስ አይሉም?
ወንድ ልጅ የዋሀ ሲሆን ሞኝ ይመስላል ሴት ልጅ የዋሀ ስትሆን ግን አንጀትን ነው የምትበላው
መቅዲ እኔ ደስታ ነኝ እያልኩ በምልክላት ግጥም ፍቅር ውስጥ ገብታለች🙊🙈😍😗
ጭራሽ ለጠዋት ቁርስ እና ለማታ እራት የአንተን ግጥም በልቼ ውዬ ባድር እያለችኝ ነው😅😆😅😛
የዋሀ ስለሆነች ማስመሰል ምናምን አታውቅም የምታወራው ነገር ሁሉ ከልቧ ነው😍😗

ትልቅ ችግር ውስጥ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል ውሸት እንደሆነ ጊዜ ይፈልጋል እንጂ የትኛውንም ጉርጓድ ቆፍረው ማውጣቱ አይቀሬ ነው🙈🙊🙉
መፍትሄው ምን ይሁን እያልኩ ጭንቅ ውስጥ ገባሁ
የስስስ አንድ ሃሳብ መጣልኝ

ክፍል ስድስት ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄

‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@yefkrtarik @yefkrtarik

┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄┄

2 months, 2 weeks ago

​​​​═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

🌹የፍቅር ንቅሣት

ፀሀፊ፡ኮዜት ዳንኤል

ክፍል 7⃣

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ

ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ።<ሁላችሁም እንዳከበራችሁን እግዚአብሔር ያክብራችሁ፤ይሄንን ዝግጅት እንዲህ የተሟላ እንዲሆን በሀሣብም ሆነ በስራ ስለረዳችሁን በጣም አመሠግናለሁ በተለይ ሚም ለሊቱን ሙሉ ሳትተኚ ሁሉንም ስራ ሸፍነሽ ስትሠሪ ነበር በእኔና በእናቴ ስም ምስጋናዬን አቀርባለው። አባቴም ነብሱን በአፀደ ገነት ያኑርልኝ።>ብሎ ተቀመጠ።ማስተዋል በተሞላበት ንግግሩ ኮራሁበት።እናቴ ቡና አፍዪ ብላኝ ቡና እያፈላው ብዙ ስነወራ ካመሸን በኀላ ሁሉም ወደ ቤት መሄድና የቀሩት መተኛት ሲጀምሩ እኔና ሮቢ ቁጭ ብለን እያወራን እጄን የሡ እጅ ላይአድርጎ ጣቴን መለካት ጀመረ፤ሮቢ ምን እየሠራህ ነው ስለው ደሞ ሠፊ ቀለበት ገዝቼልሽ የሠው መሣቂያ እንዳልሆን ነዋ አለኝ።ሁለታችንም እየተሣሣቅን እናቴ ድንገት መጥታ እናንተ ከተገናኛቹ በቃ ወሬ አያልቅባችሁም አይደል ነገ እኮ ት/ት አለ ነይ በይ ተኚ አለችኝ እየሣቀች አንተም ደክሞሀል ሮቢ ከትላንት ጀምሮ አልተኛህም በል ተኛ አለችው።አቅፌው ቻው አልኩትና ወደ ቤት ሄድኩኝ።መጋቢት ሰባት ማታ ላይ የኔ ቤተሠቦች አስት የሮቢ ጓደኞች ሌሎች ተከራዮችና እኔና ሮቢ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለን እራት እየበላን እየተጨዋወትን ነበር።ሁሉም እራት በልቶ ጨርሶ የየራሡን ወሬ ማውራት ሲጀምር እኔና ሮቢም ከጓደኞቹ ጋ ማውራት ጀመርን።ሁሉም ቀስ በቀስ ወደ ቤት ሲገባ የሮቢ ሁለቱ ጓደኞቹ ደሞ በ pc film ማየት ጀመሩ እኔና ሮቢ ፊልሙ ስላልተመቸን የራሣችንን ወሬ ማውራት ጀመርን።ከሮቢ ጋ ቁጭ ብለን የባጥ የቆጡን ስነሠወራ ለካ ሠአቱ ሄዶ ነበር፤ከሡ ጋ ስሆን በጣም ነው ደስ የሚለኝ ልክ እንደ ሁል ጊዜው እጄን ይዞኝ እያወራን   ጓደኞቹ ተነስተው በቃ እንሂድ ሲሉ አስትም ወጣችና አው መሸባቹ ሂዱ እናንተም ግቡና ተኙ መቼም እናንተን መለያየት ችግር ነው አለችን።ቅር እያለንም ቢሆን ተነስተን ገባን።ፍቅር ለኔም ሆነ ለሮቢ የመጀመሪያችን ነው። ለኔ በጣም ለብዙ ነገር መጀመሪያዬ ሮቢ ነው።ብዙ ነገሮችን በሡ አይቻለው፤ተምሬያለው።ደስ የሚል እና ሁሌም ቢያስቡት የሚያስቀና የማይሠለች የፍቅር ጊዜ አብረን አሣልፈናል።ቅዳሜ ቀን እኔ ግቢ ውስጥ ለማፍላት እቃ አቀራርቤ ቡናውን እየቆላው አጠገቤ መጥቶ ቁጭ አለና earphone አድርጎልኝ ላንቺ ነው ውዴ ስሚው አለኝ።የናቲ ማን የመጀመሪያዬ ሚለው ዘፈን ነበር።ዘፈኑ ገና መውጣቱ ነው ተነሣሁና ጉንጩን ስሜው ቁጭ አልኩኝ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር።እንዴ ቆይ ሌላም አለ ድጋሜ ትስሚኛለሽ ብሎኝ አሁንም የናቲ ማን track 01 <ተነፋፍቆ ለተገናኘ ሠው
ለጨዋታ ቀን ሌቱም አይበቃው>ሚለውን ዘፈን ከፈተልኝ።ሀሣባችንን በደንብ ሚገልፅ ግጥም ስለነበረው በጣም ነው የወደድኩት ቅዳሜን በጣም ደስ ብሎን አሣለፍን።ማታ ላይ እናቴ የኔና የሮቢ ቅርበት በጣም በዝቶባት ስላጠራጠራት ያለንን ግንኙነት እንድነግራት ጠየቀችኝ።እኔም ምንም ሣልደብቅ ሁሉንም ነገር ነገርኳት፤ሁሉንም ስለነገርኳት ደስ ብሏት ሮቢንም ስለምታውቀው ምንም አላለችኝም።ሁሉም ነገር ሲመቻች እንዴት ደስ ይላል ከሮቢ ጋ ያለን ፍቅር በጣም እየጨመረ መጣ በቃ ሁሉም እስኪቀናብን ነበር ምንፋቀረው፨ሮቢ ከጋበዘኝ ዘፈኖች ውስጥ የናቲ ማን(የመጀመሪያዬ እና ተነፋፍቆ)፤የያሬድ(ዘለላዬ)፤የታሜ(ሀኪሜ ነሽ)፤የሳንቾ(አታሣዩኝ) ሁሌ ስሰማቸው እስካሁን እሡን ነው የሚያስታውሱኝ ግን ከምንም በላይ የብስራት ሱራፌል(ቃል በቃል)ብሎ ያዜመውን ሙዚቃ ስሰማው ሮቢ አብሮኝ ያለ አጠገቤ የተቀመጠ ነው ሚመስለኝ ሁሌ ከሮቢ ጋ አብረን ስንሆን ስለምንሠማው ነበር።አንድ ቀን እንኳን ሣንኮራረፍ ሁለተኛ ወራችን እየቀረበ መጣ።መጋቢት 21/2010አ.ም ነበር ሠማይ የተደፋብኝ እስኪመስለኝ የጨለመብኝ በጣም ከባድ ቀን  ነበር

✎ ክፍል ስምንት (8) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
         ••●◉Join us share

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@yefkrtarik @yefkrtarik

┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄┄

2 months, 3 weeks ago

🌹የፍቅር ንቅስት ❤️

📌 ክፍል 4 ማታ 2:00 ሲል ይለቀቃል :: ሁሌም ከጎናችን ስላላችሁ ብርታታችን ናችሁ 🙏

••● ሼር እንደሁሌው አይለይን ••●
ሃሳብ አስተያየት @Rominya_1
💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@yefkrtarik @yefkrtarik
        ┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄┄

2 months, 3 weeks ago

🌺🌺 የንስር አይን  🌺🌺

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺

ክፍል 13

ደራሲ - በፍቅረማርቆስ ደስታ

🎙ተራኪ አማኑኤል አሻግሬ 🎙

የሰአት ፍጆታ፦58:30ደቂቃ
📁የፋይል መጠን፦ 3.4MBMB

••●◉Join us share

♡ ㅤ  ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲            
ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ  ˢʰᵃʳᵉ

ይከታተሉን | Follow us፡
@Yefkrtarik    @Yefkrtarik

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺

4 months, 2 weeks ago

🌺🌺 የንስር አይን  🌺🌺

🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ 🌺

ክፍል 8

__ ደራሲ - በፍቅረማርቆስ ደስታ _ _

🎙ተራኪ አማኑኤል አሻግሬ 🎙

የሰአት ፍጆታ፦58:30ደቂቃ
📁የፋይል መጠን፦ 3.7MB

••●◉Join us share

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌

@Yefkrtarik    @Yefkrtarik

🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ 🌺

5 months ago

🌺🌺 የንስር አይን  🌺🌺

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺

ክፍል 7

__ ደራሲ - በፍቅረማርቆስ ደስታ _ _

🎙ተራኪ አማኑኤል አሻግሬ 🎙

የሰአት ፍጆታ፦48:30ደቂቃ
📁የፋይል መጠን፦ 2.6MB

••●◉Join us share

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@Yefkrtarik    @Yefkrtarik

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺

5 months ago

🌺🌺 የንስር አይን  🌺🌺

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺

ክፍል 6

__ ደራሲ - በፍቅረማርቆስ ደስታ _ _

🎙ተራኪ አማኑኤል አሻግሬ 🎙

የሰአት ፍጆታ፦58:30ደቂቃ
📁የፋይል መጠን፦ 3.6MB

••●◉Join us share

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@Yefkrtarik    @Yefkrtarik

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺

6 months, 1 week ago

እኔ አንተን ስወድህ

ትጠፋ ትኖረው ምኑንም ሳላውቀው
ዝም ብዬ የማፈቅርህ❤️

እኔ አንተን ስወድህ

አስበኝ ወይ እርሳኝ ለሱ ሳልጨነቅ
ነው የምናፍቅህ😐

እኔ አንተን ስወድህ

ሁሉም ነገር ተንቀሳቅሷል ብቻዬን ነው
ምጠብቅህ🧍‍♀

እኔ አንተን ስወድህ

አዲስ ዘመን ተቆጥሮ አልቆ ሌላ ዘመን
ያው መጣልህ📆

እኔ አንተን ስወድህ

እንደ አዝማሪ ያደርገኛል ዜማ ፈለኩ
ልዘፍንልህ🎤

እኔ አንተን ስወድህ

አይንህን ሳላይ ነው ቃልህን የማምንህ😌

እኔ አንተን ስወድህ

አለም ቅጧ ይጥፋ ምንም አይገደኝም
አንተ ጎኔ እስካለህ🤗

እኔ አንተን ስወድህ

ልክ እንደ ፈጣሪ ከልቤ ማኖርህ🥰

እኔ አንተን ስወድህ

እንደ ጨረቃዋ በኮኮብ ላጅብህ

እኔ አንተን ስወድህ

ጥላ ልሁን እና ሁሌም ልከተልህ🚶‍♀

እኔ አንተን ስወድህ

እንዲህ ያደርገኛል ብዙም
እንዳይገርምህ😉

ላንተው📝ነው

✍️Fikir3021

📌 ምንጭ በእውቀቱ ስዩም እና ስነ-ፅሁፍ
✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺

••●◉Join us share

💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@Yefkrtarik    @Yefkrtarik

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month, 2 weeks ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month ago