The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 2 Monate, 1 Woche her
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 11 Monate her
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 Wochen, 6 Tage her
❤️ተማሪዋ❤️
?…………ክፍል 50 ………..?
የመጨረሻ ክፍል
" ምን እያልሽ እንደሆነ እንኳን ለኔ ለራስሽም የሚገባሽ አይመስለኝም ቃልዬ ፣ ዛሬም ዛኪን እንደምታፈቅሪው ብቻ ነው የገባኝ አሁን ያልሽኝን ልረዳውም ላምንሽም አልችልም ።
መቼም እንዳላምንሽ አርገሽ ልቤን ሰብረሽዋል አሁን የምፈልገው ከዚህ በላይ ምንም ክፍ ቃል ካፌ ሳይወጣ እንድትሄጅልኝ ብቻ ነው" አልኳት። ቀና ብዬ ቃልዬ ስትሄድ ላለማየት እንዳቀረቀርኩ።
ረጅም ደቂቃ እያለቀሰች ቆየች። ከዝምታ ውጪ ምንም አላልኩም።
"ኤፍዬ ይቅርታ እሺ" ብላኝ እያለቀሰች ቤቱን ለቃ ወጣች።
እኔም ወጣሁ። ታምሜ ተኛሁ።
አስር ቀን ሙሉ ምን እንወሆነ በማይታወቅ በሽታ ታመምኩ ስራ አልሰራሁም ። የቃልዬ ምርቃት ቀን እንደምንም ተነስቼ ቀደም ብዬ የገዛሁላትን ስጦታ እና አበባ ይዤ ወደ ግቢ ሄድኩ።
ከቤተሰቦቿ መሀል ሆና ከግቢ እንደወጡ ከጀርባ ጠጋ አልኩና
"ቃልዬ" ብዬ ጠራኋት።
ዘወር ብላ እንዳየችኝ ከቆመችበት አልተንቀሳቀሰችም ። ቤተሰቦቿ ወደፉት እየሄዱ ነው። ቃልዬ እዛው ቆማ እያየችኝ በዝግታ እየተራመድኩ አጠገቧ ስደርስ እነዛ አይኖቿ ላይ ያቀረረው እንባ በጉንጯ ላይ ቀልቀል ወረደ።
ስጦታዋን ሰጠኋት። ተቀበለችኝ። አመሰግናለሁ ሳይሆን ምናልባትም ለአስረኛ ግዜ•••
"ኤፉዬ ይቅርታ እሺ" ነበር ያለችኝ።
ፉቴን መልሼ ካጠገቧ ሄድኩ። ምናልባት ቃልዬም ከአንድ ከሁለት ቀን በሁዋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አዲስ አበባ ትሄዳለች።
ህይወት ፣ ምኞት፣ ደስታ ፣ ስራ፣ ተስፋ ሁሉ ፣ እራሱ መኖር ትርጉሙ አልገባህ አለኝ። ለምን እንደምኖር እራሴን ስጠይቅ ለመኖር የሚያስገድደኝ አንድ ምክንያት ብቻ ነበር ያገኘሁት።
እሷም እህቴ ነች።
የምኖረው ልኔ ብዙ ለደከመችው ለእህቴ ስል ብቻ ነበር።
የናትና ያባቴ ምትክ እህቴ እኔን ብታጣ ምን እንደምትሆን ማሰብ አልችልም። ለሷ ስል እኖራለሁ። ሂወት ቀጠለ።
ለወራት የክቡር ዶክተር አርቲስ ጥላሁን ገሰሰን ሳላስብ ትተሽኝ የሚለውን ሙዚቃ ሳላዳምጥ ተኝቼ አላውቅም።
ከስምንት ወር በሁዋላ አይቼው የማላውቀውን የፌስቡክ አካውንቴን ከፍቼ ስመለከት መጀመሪያ ላይ የመጣው ፎቶ ቃልዬ ከሁለት ቀን በፊት የለጠፈችው ቀለበት ስታስር የተነሳችው ፎቶ ነበር። ቀለበት ያሰረችው ግን ከዛኪ ሳይሆን ከሌላ ወንድ ጋር ነው።
"ቃልዬ ከተመረቅን በሁውላ ከዛኪ ጋር አብረን እንደማንቀጥል እርግጠኛ ነኝ " ያለችው እውነት ነበር ማለት ነው አልኩ። ስልኬን ወርውሬ ግርግዳው ላይ ለጠፍኩት ፣ ብትንትኑ ወጣ።
ከተበታተነው የስልኬ ስብርባሪ መሀል ግን የቃልዬ የቀለበት ፎቶ ቅዳጅ አልነበረም።
ዳግም ህመም ዳግም ግርሻት ፣ ዳግም ስቃይ። አወይ ፍቅር ግርሻቱም አይጣል ነው ለካ።
ስልኬን ከሰበርኩት ከአንድ ወር በሁዋላ እህቴ ከወራት በፉት በገዛችልኝ ሚኒባስ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሰው እስኪሞላ መሪው ላይ ተደፍቼ እየጠበኩ ነው።
መኪና ውስጥ የሚለጠፉ ጥቅሶችን እያዞረ የሚሸጥ አንድ እድሜው ከአስራ አራት የማይበልጥ ልጅ እግር በጋቢናው በኩል መጥቶ ምርጥ ምርጥ ጥቅሶች በቅናሽ ዋጋ እያለ የያዛቸውን ጥቅሶች ተራ በተራ እያነበበ ነው ። አራት ጥቅሶችን አንብቦ አምስተኛው ላይ ሲደርስ እንደመባነን ብዬ ከመሪው ላይ በፍጥነት ቀና አልኩና•••
"እስቲ ቆይ ቆይ አሁን ያልከውን ድገመው !" አልኩት። ደገመው ከጠየቀኝ ሂሳብ በላይ እጥፉን ከፍዬ ጥቅሱን ገዛሁትና መኪናዬ ዳሽ ቦርድ ላይ ለጠፍኩት።
ወረቀቱ ላይ የተፃፈው ••••
"ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ ቢልም ፣ ለባልጀራህ ሁሉን ሚስጥርህን ንገረው ግን አይልም"
የሚል ጥቅስ ነበር ። መታሰቢያነቱ ለኪያ። .
.
.
.
•••••••ተፈፀመ ••••••••
.
.
.
.
ለነበረን ቆይታ ከልብ አመሰግናለሁ ❤❤
.
.
ቤተሰቦቼ በሌላ ልብ ወለድ እንገናኛለን። በአጠቃላይ በታሪኩ ላይ ጠቅለል ያለ ሀሳብ አስተያየታችሁን ፣ ወደፊት ቢስተካከል የምትሉትን ነገር ሁሉ በኮሜንት መስጫው ስር እንደምታስቀምጡ ተስፋ እናደርጋለን ??
https://vm.tiktok.com/ZMkkFephM/
❤️ ተማሪዋ ❤️
❤️….. ክፍል 49 …….❤️
"ምን እሚሉት ጥያቄ ነው እስከዛሬ ምን ያህል እንደማፈቅርህ አታውቅም እና ነው ቆይ ምንድን ነው የሆንከው ፊትህ እኮ ልክ አይደለም?"
"ፉቴ ብቻ አይደለም ሁሉ ነገሬ ልክ አይደለም ቃል እባክሽ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ብቻ መልስ ስጪኝ አንቺ ምንም ነገር አትጠይቂኝ"
"እሺ"
"ታፈቅሪኛለሽ ቃል"
"አዎ ኤፍዬ አፈቅርሀለሁ"
"ዛኪንስ ታፈቅሪዋለሽ ቃል?" ስላት ፊቷ ላይ ያየሁት ድንጋጤ እኔኑ አስደነገጠኝ።
ያ ድንጋጤዋ ነበር የመጨረሻውን መርዶ ያረዳኝ። በቃ የቃልዬን መልስ ድንጋጤዋ ውስጥ አየሁት።
ቃልዬ ብዬ ጠራሁዋት አይን አኗን እየተመለከትኩ።
ወዬ ማለት አልቻለችም። በቃ አቃታት። የኔም የሷም አይኖች እኩል እንባ አቀረሩ።
" ቃልዬ!" ብዬ ደግሜ ጠራኋት።
አይን አይኔን ከማየት ውጪ አቤትም ወዬም ማለት ተሳናት ቃል አፏ ተለጎመ። የስረኛው ከንፈሯ ይንቀጠቀጥ ጀመር።
ጣቴቻን በጣቶቿ እያፍተለተለች ተለጎመች የኔ ቃል።
ሁሉን ነገር እንደደረስኩበት ውስጧ ነግሯታል።
ይህን ሳስብ አመመኝ ።
ቃልዬ ሁኔታዋ አንጀት ይበላል።
የሚታዘንልኝ እኔ ሆኜ ሳለሁ ቃልዬ በዛ ልክ ጭንቅ ጥብብ ሲላት ሳይ አሳዘነችኝ።
ያን ሲተናነቀኝ የነበረውን እውነት መናገር ጀመርኩ•••
ቃልዬ አውቃለሁ ሁሉን አውቃለሁ። ከቀናት በፊት ሀረር እስከሄዳችሁባት አስቀያሚ ቀን ድረስ ይቺ ቅፅበት በኔና ባንቺ መሀል እንዳትፈጠር ስሸሻት ኖሪያለሁ።
ነገር ግን እውነትን መሸሽ ከሞት እንደማያድነኝ ተረዳሁ። አዎ ቃልዬ አንቺን ከማጣ ሞቴን እመርጣለሁ፣ መሞት አልፈልግምና አንቺን ማጣት እፈራለሁ።
እኔ ስለፈራሁት እኔ ስለሸሸሁት የሚቀር ነገር የለም።
ሁሌም አፈቅርሻለሁ። ምንም ብትበድይኝ ምንም ብትጎጂኝ አንቺን አለማፍቀር እስክችል ድረስ አፈቅርሻለሁና ዛሬም ቢሆን አንቺን ክፉ የምናገርበት አንደበት የለኝም።
ክፉ ይናገረኛል አልያም ይጎዳኛል ብለሽ እንዳታስቢ እሺ? ፣ እኔ አንቺን የማፈቅርሽ የእውነት ነው ፣ የማፈቅርሽ ግን የኔ ስለሆንሽ ብቻ አይደለም።
ዛሬም የማልፈልገው አንቺን አለማፍቀር ሳይሆን እየታመምኩ፣ እየተረበሽኩ፣ እንቅልፍ እያጣሁ፣ የተበዳይነት፣ የተገፊነት ስሜት እያንገላታኝ ማፍቀርን ነው።
ነገ ከነገ ወድያ ላጣሽ ልትለይኝ እንደምትችይ እያሰብኩ ማፍቀር ደከመኝ ቃልዬ።
አብሬሽ ሆኜ የተሰቃየሁት ስቃይ አጥቼሽ ከምሰቃየው ጠናብኝ ቃልዬ ።
ሀለቱም ለኔ ህመም ቢሆንም ከእውነት ጋር መታመም ይሻላል እውነትን ሸሽቼ የማላመልጥበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁና የምደበቅበት የምሸሽበት የለኝም እውነቱን ልጋፈጠው የተገደድኩት ሁሉ ነገ ካቅሜ በላይ እስከሚሆን ታግሼ ነውና በውሳኔሽም በውሳኔዬም እንደማልፀፀት ተስፋ አደርጋለሁ።
አንድም ቀን በዚህ ልክ ትጎጂኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ቃልዬ።
ዛሬ እውነቱን ካንቺ አንደበት ሰምቼ ሀቁን ልጋፈጠው ወስኛለሁ። ስለትናንት አልወቅስሽም፣ ስለነገም አላውቅም አሁን የምፈልገው በራስሽ አንደበት እውነቱን እንድትነግሪኝ ብቻ ነው ቃልዬ።
" ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል ቃል?"
"እ ቃል እባክሽ ንገሪኝ ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል?"
ቃልዬ መልሷ ማልቀስ ብቻ ሆነ። ከጎኔ ቁጭ ብላ ስታለቅስ ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ። እራሴን ፈራሁት። ስሜታዊ ሆኜ ቃልዬ ላይ እጄን እንደማልሰነዝር ባውቀውም እራሴን ፈራሁት ከአጠገቧ ተነስቼ በመራቅ ፊት ለፉቷ ተቀመጥኩ።
አቀርቅራ ስታለቅስ ቆየችና ድንገት ቀና ብላ
"ኤፍዬ ይቅርታ!" አለችኝ። ሰማይ ተደፋብኝ። ቤቱ የሚሽከረከር መሰለኝ። ከተቀመጥከበት እንዳልወድቅ አይኔን ጨፍኜ ግርግዳውን ተደገፍኩ።
"ኤፍዬ ይቅርታ !" አለች በድጋሚ። መልስ አልሰጠኋትም።
ቃልዬ ቀጠለች ••••
"እኔና ዛኪ እዚህ ግቢ ትምህርት እንደጀመርኩ የዛሬ ሶስት አመት ነው በፍቅር አብረን የሆነው ፣ " ስትል ገና ከግር ጥፍሬ ጀምሮ ሁለመናዬን ወረረኝ። እያየኋት ልሰማት አቅም አጣሁ። ጭንቅላቴን ጉልበቶቼ መሀል ደፍቼ አቀረቀርኩ ። ቃልዬ ቀጠለች...
"ፍቅር ጀምረን ወራት ያህል እንደቆየን ስለሱ ብዙ ነገር እሰማ ጀመር ከብዙ ሴት ጋር እንደሚቀራረብ ባውቅም አምነው ነበር። ሁሉንም ነገር የምሰማው በውሬ ነው። ስጠይቀው ይክደኛል ። ያን ቀን አንተና እኔ በተገናኘንበት ምሽት አንዷ ሴት ጋደኛዬ ዛኪ ከሌላ የግቢ ሴት ጋር የለበትን ሆቴል ነግራኝ ነበር ሳንቲም እንኳን ሳልይዝ አለ ወደተባለበት በርሬ የሄድኩት።
ግን አጣሁት መመለሻ ሳንቲም እንኳን ልነበረኝም ። ዛኪን ከዛ በኋላ አብሬው ላልቀጥል ወስኜ ነበር። ለምን በዛ ሰአት እዛ ሆቴል በር ላይ እንደቆምኩ አንተ ስጠይቀኝ ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ ነበር ያልኩህ። ዛኪን አየሁት ብላ የደወለችልኝ ሴት ያንን አጋጣሚ ተጠቅማ አብረዋት ከነበሩ ሁለት ወንዶች መሀል ከአንደኛው ጋር ልታቀራርበኝ ስትሞክር ተናግሪያት ወጣሁ። በዛ ሰአት ነበር አንተ መጥተህ ፊት ለፉቴ የቆመከው ። ይህንን ደሞ በመጠኑም ቢሆን ነግሬሀለሁ። ኤፍዬ የኔና ያንተ ነገር ከተዋወቅንባት ምሽት ጀምሮ መቀራረባችን እና ወደ ፍቅር መግባታችን እንዴት እንዴት እንደፈጠነ ታውቃለህ።
እኔና አንተ ወደፍቅር በገባንባት ሁለት ወር ውስጥ ከዛኪ ጋር ተኮራርፈን ነበር ።ድጋሚ የምታረቀውም አልመሰለኝም ነበር።
ነገር ግን ልጅቷ ሆን ብላ እኔን ለሌላ ወንድ ለማጣበስ ስለሱ መጥፎ እያወራች እንዳጣላችን በየቀኑ እየመጣ ይነግረኝ ነበር። መውጫ መግቢ መቆሚያ መቀመጫ አሳጣኝ። ካንተ ጋር ሆኜ እንኳን ስንቴ እንደሚደውልና ስንቴ ተነስቼ ካጠገብህ እየሄድኩ እንደማዋራው ታስታውሳለህ።
በቃ ታረቅን። እኔና እሱ ስንታረቅ በጣም ተጨነቅኩ። ዛኪን የታረቅኩት ትምህርቴን ተረጋግቼ ለመጨረስ ብቻ ነበር።
አንተን ልጎዳ ብዬ ያደረኩት ምንም ነገር የለም ። ከዛኪ ጋር እዛ ግቢ ውስጥ እስካለሁ ድረስ መውጫ መግቢያ ስለሚያሳጣኝ መለያየት ከባድ ቢሆንም አብረን እንደማንዘልቅና ከተመረቅን በኋላ እንደምንለያይ እርግጠኛ ነኝ። አንተን •••ብላ ልትቀጥል ስትል መስማት አቅለሸለሸኝ።
የመጨረሻ ክፍል ረቡዕ ማታ 2:00 ላይ ❤️??
https://www.instagram.com/reel/DD6fkUSu_mv/?igsh=MWRkNjA2dWFvMzg1eg==
❤️❤️ተማሪዋ❤️❤️
.
??…….ክፍል 48 ……??
.
አላወቅኩም ቆይ እስቲ ጥበቃውን ልጠይቅልሽ " ብያት ወደ ጥበቃው ስመለስ አሁንም እማርኛ እና የነጮቹን አፍ እየቀላቀለች ስላስቸገርኩህ ይቅርታ አይነት ነገር አለች ። መልስ ሳልሰጣት ሄጄ ጥበቃውን...
"አባባ የሚላላከው ልጅ አለ እንዴ ? ዲያስቦራዋ ፈልጋው ነበር?'' አልኳቸው።
"ውይ ፈለገችው እሱማ መሄጃ ሰአቱ ደርሶ ወጣኮ ምሽት ሁለት ሰአት ወደ ቤቱ ሄደ። ምን ፈልጋ ይሆን ?" እያሉ አብረውኝ ተመለሱና ልጁ እንደለለ ነገሯት።
እዛው ቆም ብዬ እኔ ከወጣሁ በኋላ የተያዙና መብራት የበራባቸውን ክፍሎች ገልመጥ ገልመጥ እያልኩ ስቃኝ። ዲያስቦራዋ ልጁን የፈለገችው ቢራ ከውጪ ገዝቶ እንዲያመጣላት እንደነበር ስትነግራቸው ጥበቃው አንዴ እሷን
አንዴ እኔን አንዴ በሩን በየተራ እየተመለከቱ።
"አይይይ ግድ ከሆነና ካስፈለገሽ እኔው ሄጄ ላምጣልሽ ይሆን የኔ ልጅ?••• ልጁማ ሰአቱ ደርሶ ወጣኮ ቀደም ብትይ ደግ ነበር?'' አሏት። አሳዘኑኝ። ለሷ ሳይሆን ለሳቸው ስል አንዳፍታ ገዝቼ ላቀብላትና ገብቼ ልተኛ አሰብኩና
"ችግር የለውም አባቴ እርሶ ከሚሄዱ እኔ አመጣላታለሁ"
ስላቸው ገና መርቀውኝ ሳይጨርሱ ለሳቸው ጉርሻ መቶ ብር ጨምራ የቢራ መግዣውን ብር ሰጠቻቸው ።
የሳቸውን ለሳቸው ሰጥቼ ቢራውን ልገዛላት ስንቀሳቀስ ከዳግም ምርቃታቸው አስከትለው ቆይ የኔ ልጅ ጠርሙስ ካልያዝክ ማስያዣ ይጠይቁሀል ጠብቀኝ ጠርሙስ ላምጣ ብለውኝ ግቢ ውስጥ ወዳለ አንድ ክፍል አምርተው አራት የቢራ ጠርሙስ ይዘውልኝ መጡ።
ተቀብያቸው ልወጣ በሩን ከከፈትኩ በኃላ እዛ አከባቢ በግራም በቀኝም ሆቴል አለማየቴን አሰብ አድርጌ••••
"እታች ወርጄ ነው የምገዛው አደል አባባ እዚህ አከባቢ በቅርብ ሆቴል የለም አደል?" ስላቸው •
"ውይ የኔ ነገር የምትገዛበትን ሳላመላክትህ ሰደድኩህ አደል የኔ ልጅ ፣ ለካ አታውቀውም እያሉ ከግቢ ወጡና ካለንበት በቀኝ በኩል ትንሽ ሄደት ብዩ ወደ ግራ ቁልቁል የምትወስድ ቀጭን
መንገድ እንዳለችና ገባ እንዳልኩ ሆቴል እንደማገኝ ነገሩኝ። ከዚህ በፊት አላውቀውም ሆቴሉን ምናልባት በቅርብ የተከፈተ ይሆናል እያልኩ ወደ ሆቴሉ አቅንቼ ግቢ ውስጥ ስገባ ግቢው ጭር ያለ ነው ። ወደ ሆቴሉ ከሩቅ ሳማትር አለፍ አለፍ ብለው ወንበር ይዘው በተከፈተው ለስላሳ ሙዚቃ የሚዝናኑ ውስን ሰዎች ይታያሉ።
ራመድ ራመድ እያልኩ ወደሆቴሉ ዘው ብዬ እንደገባሁ ፊት ለፊት ባየሁት ነገር ልቤ ስንጥቅ አለች። ወይኔ አምላኬ ምንድን
ነው የማየው ? ጭራሽ እኔ የገዛሁላትን አዲሷን ልብስ••• እያልኩ በሁለቱም እጆቼ ሁለት ሁለት ባዶ የቢራ ጠርሙዝ እንዳንጠለጠልኩ ድንጋጤዬ አብረክርኮት አልራመድ ያለኝን እግሬን በግድ እየጎተትኩ በቀስታ ወደ ተቀመጡበት ወንበር ተጠጋሁ በሆቴሉ ውስጥ ጭልም ደሞ ብርት የሚሉ ሲበሩም ደብዛዛ ብርሀን የሚፈነጥቁ ጌጣማ አንፖሎች እዛም እዛም ተሰቅለዋል ፣
ቀረብ ስል ግራ ገባኽ አብሯት ያለው ወንድ ፊቱ በደንብ ታየኝ። ዛኪ አይደለም።ገዘፍ ያለ ነው። አስተያየቱ ደሞ ያስፈራል። ገልመጥመጥ ሲያደርገኝ እነሱን እያየሁ በቀጥታ ወደነሱ መሄዴን ቀየር አደረኩና እንደማለፍ ብዬ አየት ሳደርግ ልጅቷም ቃልዬ አይደለችም። ቀሚሱዋም ዲዛይኗ የቃልዬ አይነት ቢሆንም ' ከለሯ 'በተወሰነ መልኩ ይለያል።
የስራሽን ይስጥሽ ቃልዬ፣ ግራ የገባኝ ደግሞ ተከትያት ሀረር ከመጣሁ በሁዋላ የተጠናወተኝ በቅርብ ርቀት ያየኋት ሴት ሁሉ ቃልዬን የምትመስለኝ በሽታ ነው ፣ ይሄ መታመም ካልሆነ ምን ይሆናል ? እያልኩ ቢራውን ገዝቼ ተመለስኩ።
የግቢው ጥበቃ የቀራቸውን ምርቃት ሁሉ አሟጠው መረቁኝ።
"የእኔን እድሜ ያድለህ ፣ ጧሪ አያሰጣህ፣ የማታ እንጀራ ይስጥህ፣ የልጅ ልጅ ያሳይህ•••••" ሌላም ሌላም ብዙ ምርቃቶች።
"አባባ " አልኳቸው እንደጨረሱ።
"ወዬ የኔ ልጅ"
"ፍቅር ይዝለቅልህ!" ብለው ይመርቁኝ አልኳቸው እንባ እየተናነቀኝ።
"ፍቅር ይዝለቅልህ ፣ የወድድካትን ያፈቀርከትን ክፉ አይይብህ ፣ ትዳርህን ይባርክልህ !
" አሜን አሜን አሜን አባቴ" አልኳቸው ዋናው እሱ ነው ። እኔ የልጅ ልጅ ማየት የምፈልገው ከቃልዬ ነው። ከቃልዬ ከነጠለኝ በሁዋላ ረጅም እድሜ ምን ሊጠቅመኝ። እያልኩ ቢራውን ሰጥቻት ወደ ክፍሌ ገባሁ።
ቃልዬ ከዛኪ ጋር ማደሯን ማሰብ አስፈሪ እንደሆነብኝ ድካምና ረሀቡ ነው መሰለኝ የወደቅኩበትን ሳላውቅ ነጋ።
ጥዋት ወደ ድሬ ዳዋ ስመለስ ቃልዬ እራሷ እስክትደውል ላልደውልላት በናቴ ማልኩ።
ሳትደዉል መሸ፣ ሳትደውል ነጋ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ቀንም እንደዛው ልደውል ስልኬን ካወጣሁ በሁዋላ በናቴ መማሌ ትዝ ሲለኝ ስልኬን ወደ ኪሴ እመልሰዋለሁ።
በአራተኛው ቀን ደወለች ።
"ይቅርታ ኤፍዬ በዚህ ምርቃት ሰበብ ተዋክቤ፣ ቻርጀሬ ጠፍቶ ፣ ባትሪ ዘግቶ••••" ብዙ ብዙ አለች ፣ ለመጥፋቷ ብዙ ምክንያት ብዙ ሰበብ ተናገረች ቃል። ዝም ብዬ ሰማኋት።
ስትጨርስ አንድ ነገር ብቻ ተናገርኩ ። አንድና አንድ ነገር ብቻ አልኳት።
"ችግር የለውም ቃልዬ በጣም ላገኝሽ እፈልጋለሁ መች ይመችሻል?" የሚል ጥያቄ ብቻ ሰነዘርኩላት። ድምፄ መሰባበሩ ለኔ ቢታወቀኝም ለሷ አላታወቃትም አልያም አላስተዋለችውም።
"ኤፍዬ አብረን ለመዋል ከሆነ ነገ ፣ ለማደር ከሆነ ግን ከነገ ወድያ"
"አይ ችግር የለውም አብረን ውለን ትሄጃለሽ"
"በቃ ነገ ከሰአት ደውልልኝ "
የቃልን ስልክ እንደዘጋሁ ጌትነት ስልክ ላይ ደወልኩ።
እቤቱን ለአንድ ቀን እንደምፈልገው ነገርኩት።
"ችግር የለውም ኤፍዬ ማደርም ትችላለህ እኔ ጀለሶቼ ጋር እሄዳለሁ" አለኝ።
ቃልዬን ላመጣት ስሄድ ለጌትነት ደውዬ ልመጣ ነውና ቁልፉን አስቀምጠህልኝ ሂድ አልኩት።
ደረስኩ ተገናኘን ። ስማኝ ከጀርባ ገባች። ደንዝዣለሁ። ምንም አላወራም ቃልዬ ግን ምን ያህል እንደናፈቅኳት ፣ ስለሰሞኑ የምርቃታቸው ወከባ ምን ያህል ግዜ እንዳሳጣት እያወራችልኝ የማውራት እድል ሳትሰጠኝ እነ ጌትነት ቤት ደረስን።የማውራት እድል ብትሰጠኝ ምን እንደማውራ አላውቅም።
ገብተን ትንሽ እንደቆየን ከምን እንደምጀምር ምን እንደምላት ጨነቀኝ።
ካንድም ሁለት ሶስቴ ልጀምር እልና የሆነ የሚረብሽ ስሜት እየተናነቀኝ አቋርጠዋለሁ። ተነስቼ ወደ መታጠቢያ ቤት እሄድና በቀዝቃዛ ውሃ ፊቴን ታጥቤ እመለሳለሁ።
ቃልዬ ቡና ለማፍላት እየተንጎዳጎደች ሁኔታዬን ማስተዋል አልቻለችም።
አቦሉን እንደጠጣን •••
"በቃ ሁለተኛውን አታፍይ ይቅር " አልኳት።
"ለምን ኤፍዬ?" አለችኝ ፊት ፊቴን እያየች።ፊቴ ልክ እንዳልሆነ ያስተዋለችው ያኔ ነበር። መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች።
"ምን ሆነሃል ኤፍዬ ችግር አለ?" አለችኝ አገጬን ይዛ ወደግራም ወደቀኝም ገልበጥ ገልበጥ እያደረችኝ።
"አዎ ችግር አለ ቃል"አልኳት አገጬ ላይ ያለውን እጇን ይዤ ከአገጬ ላይ እያወረድኩት።
"ምንድን ነው እሱ?" አለችኝ ልቧን በግራ እጇ ደገፍ አድርጋ እየተመለከተችኝ። ልቧ ነገራት ብዬ በውስጤ እያሰብኩ ዝም አልኩ።
"ኤፊዬ!" ብላ ተጣራች።
"ወዬ ቃል"
"ምን ሆነሀል ?" ምን ሆንኩ እንደምላት ቸገረኝ።
"ቃልዬ" አልኳት።
"ውዬ"
"ታፈቅሪኛለሽ?"
.
.
ክፍል 49 ከ150 ላይክ ቡሀላ ይቀጥላል
♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
?...ክፍል 35...?
.
.
.
.
ኤፍዬ"
"ወዬ ቃል"
"ልቀቀኝ እኔ መጨፈር እፈልጋለሁ አልኩህ እኮ አሰማም ? ቆይ እኛ ዶሮ ነን እንዴ በዚህ ሰአት ገብተን የምንተኛው?
እንብየው እንብየው እኔ መግባት አልፈልግም ልቀቀኝ "
እያለች እቅፍ አድርጌ የመሸከም ያህል ይዣት ስወጣ•••
"ቆይ እንቅልፍ ምን ያደርጋል? እንቅልፋም ነገር ነህ እሺ ኤፍዬ እንቅልፍም፣ ኪኪኪኪ ቆይ ቆይ ፣ አቅም ግንባታ ፣ያልጋ ላይ ጫወታ፣ እግዞዬታ ኡኡታ እያልክ ስትፎክር የዋልከው ገብቶ ለመተኛት ነው እንዴ ? እስቲ ወንድ ዛሬ ገብተህ ትተኛና እንተያያለና ኪኪኪ ቆይ ቆይ ቆይ ኤፊዬ. "ድብድቡ ሳይጀመር አንድ ቢራ" ያለው ማን ነበር. ኤፊዬ ? እኛም ድብድቡ ሳይጀመር የምንጠጣው አንዳንድ ቢራ ይዘን መግባት አለብንኮ ባዶ እጃችንን ልንገባ ነው? ቆይ እሺ ልቀቀኝና ሁለት ቢራ ይዘን እንምጣ"
"ቃልዬ በጣም መሽቷል እኮ ስድስት ሰአት አልፏል"
"ይለፋ ገና አሁን አይደል እንዴ የወጣነው ፣ ስማ ስማ ኤፍዬ ቆይ የሰከርኩ መስሎህ ነው አደል ? እሄው እይ ባንድ እግሬ ስቆም እሺ ብሰክር ባንድ እግሬ እቆማለሁ ልቀቀኝ ቆሜ ላሳይህ "
ትልና አንድ እግሯን ብድግ አድርጋ ሳጨርስ ተንገዳግዳ እኔው ደረት ላይ ዘፍ ትላለች።
"ካካካካካ " በቃ ሳቋ ማቆሚያ የለውም።
"እሺ እሺ በናትህ ኤፍዬ ስሞትልህ በዚች ዘፈን ብቻ እንደንስና እንገባለን ሰማው ዘፈኑን እዚህ ድረስ ይሰማል እኮ ይሰማሀል ኤፍዬ የፀሀዬ ዮሀንስ ዘፈን••
ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲሄዱ ባይ
ሳጣሽ የኔን ሲሳይ ፣ ቀናሁ በሰዎች ላይ
ዛሬም ሳላይሽ ላድር ነው ወይ እባክሽ ነይ
ዝርያዬን ባስስ ባስስ አንቺ እንደሁ የለሽም
ባንጋጥጥ ወደሰማይ ዘፈኑን ፍቅረኛው አጠገቡ የለለች ሰው ይመሰጥበት እኛ እንግባ እኛ እኮ ጥንድ ነን ቃልዬ "
"ምን አልክ ኤፊ? ጥንድ ነን ነው ያልከው? መስሎህ ነው ባክህ እኛማ ጥንድ ብቻ አይደለንም። ከጥንድም በላይ ነን። ቆይ ከጥንድ በላይ የሆኑ ፍቅረኛሞች ግን ምንድን ነው የሚባሉት ?
ታውቃለህ እንዴ? ባክህ አታውቅም እኔ ነኝ እንጂ ማወቅ የነበረብኝ አንተ ምን በወጣህ ፣ ግን እስከዛሬ ፍቅረኛሞች ከጥንድ በላይ ይሆናሉ ብለህ አስበህ ታውቃለህ ኤፊዬ?
" አላውቅም"
"እኔም አስቤ አላውቅም ነበር ግን ሆነ አይገርምን ኤፊ"
"አይገርምም" አልኳት ምን እያለች እንደሆነ ስላልገባኝ ።
"ኪኪኪኪኪ አይገርምም ይላል እንዴ ፣ ባክህ አንተ ስለማታውቅ ነው ያልገረመህ "
ስትለኝ ምን እያወራችልኝ ነው? ምን ማለቷ ነው? ከጥንድ በላይ የሆኑ ፍቅረኛሞች ማለት ስንት ነው? ስስት ነው አራት? ወይስ ከዛ በላይ። አራት ከሆኑ ያው ሴትና ወንድ ሴትና ወንድ ሁለት ጥንዶች ማለት ነው ። ሶስት ከሆኑስ እንዴት ነው የሚሆነው?
ሁለት ሴት እና አንድ ወንድ ነው ? አይ እንደዛማ አይሆንም እሺ ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት ቢሆንስ ብዬ ሳስብ ወረረኝ።
ቃልዬ ስለምን እያወራች ነዉ በሷ በኩል ሌላ ወንድ ይኖር ይሆን ብዬ ከማሰብ በላይ ምን የሚወር ነገር አለ?
እና ቃልዬ ምን እያለችኝ ይሆን ይሄ ነገር "ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል " ይሉት አይነት ንግግር ነው እንዴ?
"ስማ ኤፊዬ "
"እ ምንድን ነው?"
"ኤፊዬ አንተኮ ታማኝ፣ ንፁህ፣ደግ፣ ግልፅ ፣ ተጫዋች በቃ የሆንክ ፍቅር የሆንክ ልጅ ነህ ፣ የኔ የዋህ፣ አፈቅርሀለሁ እሺ ?"
አለችኝ። ቃልዬ ያን ያህል ብዙም አልጠጣችምና ከሞቅታ ውጪ የለየለት ስካር ውስጥ አልገባችም።
በምትናገረው ነገር ግን የተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ እየከተተች እኔኑ አሰከረኝ።
እንደምንም መንገድ ለመንገድ እየተጓተትን ክፍላችን ገባን።
አልጋው ላይ አረፍ እንዳለች እኔ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባሁና ልብሴን ውልቅልቅ አድርጌ ይሄን የሀረር ቀዝቅልዛ ውሃ አናቴ ላይ ለቀቅኩት።
ኳኳኳ " ክፈት ኤፊ" ከፈትከላት።
"ለምንድን ነው ብቻህን የምትታጠበው እኔም መታጠብ እፈልጋለሁ "
ብላ ከነልብሷ ልትነከር ስትል ያዝ አደረኩና ከላይ የለበሰችውን አውልቄ ፀጉሯ እንዳይበላሽ ቦርሳዋ ውስጥ የያዘችውን የተለየ ስም ይኑረው አይኑረው ባላውቅም ብቻ ሴቶች ድንገት መንገድ ላይ ሆነው ዝናብ ሲመጣ እና ሲታጠቡ የሚያጠልቁትን ከፍያ መሳይ ላስቲክ ነገር ጭንቅላቷ ላይ አጠለኩላት ።
"አመሰግናለሁ እሺ የኔ አሳቢ !" ብላ ብላ ሳመችኝና አብረን መታጠብ ጀመርን።
እየተሳሳቅን ተጣጥበን እንደወጣን ለቀቃት ቀዝቀዝ አለች። ጋደም ብለን ስንጨዋወት ቆየን። ውስጤ ጥያቄ ቢፈጥርብኝም ቅድም በጥንዶች ዙርያ እንዲህ ብለሽ ነበር ምን ለማለት ፈልገሽ ነው? ብዬ በመጠየቅ ሌላ ውዝግብ ውስጥ እንድንገባና ያንን ደስ የሚል የሀረር ቆይታችንን ላደበዝዘው ስላልፈለኩ ተውኩት።
መብራቱን ሳየው አይኔን እያጭበረበረኝ ነው የሚቀነስ ከሆነ ሀይሉን ቀንሰው ያለበለዚያ አጥፋው አለችኝ።
በጣም እንዳይጨልም በጣምም ቦግ እንዳይል አድርጌ አደበዘዝኩት። እድሜ ለቴክኖሎጂ። ትንሽ ቆይቶ በኔ እና በቃልዬ መሀል መነካካት ተጀመረ። ቀስ ነቀስ መሳሳም ቀጥሎም ወደ ወናው ወደ ጥሎ ማለፍ ጫወታው ሰተት ብለን ገባን።
የመጀመሪያው ግብግብ በኔና በቃልዬ መሀል ብዙ የጎላ ልዩነት ሳይኖር ተመጣጣኝ በሆነ የሀይል ሚዛን ተጠናቀቀቅ።
"ሽንቴን ልሽና መጣሁ ኤፍዬ መተኛት አይፈቀድም ብላኝ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ሳቅ እየተናነቃት እንደሆነ አነገገሯ ያስታውቅ ነበር።
ከአንደበቷ ባይወጣም "እንደፎከርከው አልሆነልህም ምን ትሆን እንግዲ ድንቄም ጥሬ ስጋ ?" እያለች ያላገጠችብኝ ያህል ነው ተሰማኝ።
በእረፍት ሰአት የታክቲክ እና የቴክኒክ ለውጥ ማድረግ እንዳለብኝ ሳስብ ቆየሁ። ሁለተኛው ዙር ላይ አዲሱን ስልት መተግበር ጀመርኩ።
ቅልጥ ያለ የፍቅር ጦርነት ውስጥ ከመግባታችን እና ቃልዬ እንደእንዝርት ከመሾሯ በፊት ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ እና መላ አካሏን በመውረር ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን በመሳም፣ በዳበሳ እና በዳሰሳ ማጥቃት ጀመርኩ ።
ወደ ወሳኙ ጦርነት ሳንገባ ቃልዬ አተነፋፈሷ እየተቀየረ የልብ ትርታዋ እየጨመረ መጣ።
ለደቂቃዎች በተደረገባት የጣት እና የከንፈር ወረራ መላ አካላቷ ላይ በሚርመሰመሱት ጣቶቼና እና ካንገት በላይ የስራ ድርሻውን በሚወጣው ከንፈሬ ገና ሳይጀመር የጋለችው ቃልዬ በፍቅር ጫወታው ትግበራ ላይ የጫወታውን አይነት ፣የጫወታውን ቦታ፣ የጫወታውን ፍጥነትና ሁኔታ የመወሰኑን ስልጣን ለኔ ለማስረከብ ተገደደች።
ሁሉም ነገር በኔ ስልጣን በኔ ቁጥጥር ስር ዋለ። እስካሁንም የጫወታው ቁልፍ ቅድመ ጫወታ ላይ ያለው የማሟቂያ ግዜ መሆኑን አለማስተዋሌ ነው የጎዳኝ አልኩ ለራሴ ። ቃልዬ እኔ በምልክትም በቃላትም ሁኚ የምላትን መሆን ብቻ ሆነ እጣ ፋንታዋ።በዚህ መልኩ የደስታን ጥግ እያጣጣም ደቂቃዎች አለፉ።
ወደ ማሳረጊው አከባቢ ቃልዬ ስሜት ውስጥ ሆና የተናገረችው ነገር በሚሳኤል የተመታሁ ያህል ጆሮ ግንዴን አደባየው።
ቃልዬ ድክም በለ ድምፀት በስሱ "ዛኪዬ የኔ ፍቅር አልቻልኩም" የሚሉ ቃላቶች ብትናገርም ወደ ጆሮዬ ሲደርሱ ግን ጩኸታቸው የመብረቅ ያህል አስደንጋጭ ነበር።
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 36 ይለቀቃል?
https://vm.tiktok.com/ZMh9xdBnV/
♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
?...ክፍል 34...?
.
.
"አመረርክ እንዴ ትናንት እኮ እኔን ለማሳቅ ብለህ እኔን አሸናፊ አንተን ተሸናፊ አድርገህ እንደቀለድክ እንጂ ከልብህ እንዳልሆነ ነበር ያሰብኩት፣ ኤፊዬ ሙት እኔ ትናንት በነበረው ነገር በጣም ደስተኛ ነኝ፣ ምንም ያጎደልክብኝ ነገር የለም ተመችቶኛል"
"ገሎ ማንሳት፣ ጠብሶ ማሸት የሚባል ነገር ታውቂያለሽ"
"ገሎ ማንሳት አላውቅም ጠብሶ ማሸት ግን ለበቆሎም ሊሆን ይችላል ለሰውም ይሆናል ያው ጠብሰክ እያሸኸኝ አይደል እንዴ ኤፊዬ?"
"ካካካ አንቺ ነሻ ገለሽ የምታነሽው ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ ብለሽ ከገደለሽኝ በሁዋላ አይደለም በሽንገላ በክሪክ አልነሳም።
ያለው አማራጭ ወንድነቴን ማሳየትና ማስመከር ብቻ ነው"
"ክሪክ ምንድን ነው ኤፊ ?"
"የተሽከርካሪ ጎማ ለመቀየር ለሌላም ጉዳይ ብቻ መኪናው ከፍ የምናደርግበት ነዋ " አልኳት በቃ ወሬህ ዞሮ ዞሮ ከትራፊክ ህግና ከተሽከርካሪ አይወጣም አይደል እንዳትለኝ ውስጥ ውስጡን እየተሳቀቅኩ።
"እኔ እንግዲህ ወንድነትህን አይቼዋለሁ ሌላ የምታሳየኝ አዲስ ነገር አለ?"
'አዎ አለ"
"እና አሳየኛ "
"አሁን አይደለም ስንመለስ " ብዬ እጇን ይዤ በመጎተት ከአልጋው ላይ አነሳኋትና ይዣት ወጣሁ።
እየሄድን መንገድ ላይም "አይ ኤፊ" እያለችና ዝም ብላ እያየችኝ ትስቃለች።
"ለምንድን ነው የምትስቂው ቃልዬ?"
" ኤፊዬ ግልፅነትህ በጣም ደስስስስስ እንደሚለኝ ታውቃለህ ግን?"
"አላውቅም ነበር ይሄው አሁን ነገርሽኝ። እና ግልፅነቴ ብቻ ነው ደስ የሚልሽ?"
"ሌላውን ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ"
"በጣም የሚገርመኝ ባህሪሽ የሆነ ነገር ለማውራት ቀጠሮ የምትይዥው ነገር ነው"
"ሁሉም ነገር እኮ ባንድ ግዜ አይወራም ኤፍዬ"አለችኝ ወገቤን አቀፍ አድርጋ ወደሷ በመጎተት በዳሌዋ ገጨት እያደረገችኝ።
ተንገዳግጄ ልወድቅ ነበር ። የሴት ቀጭን የለውም አለች አያቴ። ቃልዬ በርግጥ የሰማዩ ንጉስ ክብሩ ይስፋና ከወገቧ ቀጠን ከዳሌዋ ሰፋ አድርጎ ስላስዋባት በዛ ዳሌ ተገጭቼ ብንገዳገድ በኔ አይፈረድም። ቃልዬ
" ና በደንብ ልግጭህና ውደቃ በቃ ነጋ ሳረግህ ተንገዳገድክኮ መውደቅ አምሮህ ነው" እያለች ድጋሚ ልገጨኝ ስትሞክር አንገቷን አቅፌ ተረፍኩ።
ለጥሬ ስጋ እስከዚህም ብትሆንም አንተ የበላኸውን ነው የምበላው ሌላ ምግብ አላዝም ብላ አብራኝ በላች።
በልተን እንደጨረስን እዛው በስሱ ማወራረጃውን እየተጎነጨን ቆየን። እንደትናንትናው ከዚህ በላይ እንዳትጠጣ በቃህ አላለችኝም። እኔም በነፃነት በላይ በላይ እልፈው ጀመር።
ነገር ግን ቃልዬም እንደስከዛሬው ከሁለት በላይ አልጠጣም የምትለውን ረስታው ይሁን ትታው ደገም ደገም ስታደርግ ኦኦ ሁለታችንም ከሰከርን ማን ማንን ሊጠብቅ ነው ? አልኩና የኔን መጠጣት ገታ ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩ።
ጭራሽ " ጠጣ እንጂ ኤፊዬ" ስትለኝ እየጠጣሁ ነው ጠጪ እያልኩ ከንፈሬን እያረጠብኩ መመለስ ጀመርኩ።
እንዲሁም በትንሽ በትልቁ ሳቅ ሳቅ የሚላት ቃልዬ ምንም ሳናወራ ሁላ ዝም ብላ እያየችኝ መሳቅ ጀመረች።
ይውጣላት አልኩና ከምግቤቱ ይዣት በመውጣት ቅልጥ ወዳለ ጭፈራቤት ይዣት ሄድኩ።
እንደገባን ጭፈራውን ታቀልጠው ጀመር ። ጭፈራው ላይም የዋዛ አልነበረችም። እኔ ደከመኝ ብዬ ጥግ ጥግ ላይ ወዳሉ
"ባለጌ ወንበሮች" ሄጄ ለመቀመጥ ስሞክር እየጎተተች ታስነሳኛለች።
ያልጨፈረችበት የዘፈን አይነት የለም። ወደጆሮዋ ጠጋ ብዬ•••
"ቃልዬ ያ የውዝዋዜ ዳኛው ትናንት ያደነቀሽ የእውነት መሰለሽ እንዴ? አቀለጥሽው እኮ" ስላት
ሙዚቃውን ያስናቀም ያሳቀቀም ሳቅ ሳቀች ። መቀመጥ የሚባል ነገር የማይሞከር ሆነ ።
"ተነቅቶብሻል ባክሽ ወይ በዳንስ አድክመሽ ልታስተኝኝ አስበሻል ወይ ትናንት የጀመርሽውን ወገብ ሰበራ በዳንስ ልትጨርሽው ፈልገሻል " አልኳት።
ቃልዬ እኔ ባወራሁ ቁጥር ስትስቅ በተለይ ቀዝቀዝ ያለ ዘፈን ሲሆን የሷ ሳቅ ጎልቶ እየወጣ በቤቱ ያሉ የተወሰኑ ሰዎችን ትኩረት መሳባችንን እንዳስተዋልኩ ማውራቴን ተውኩት።
ቃልዬ ግን እኔ ማውራት ባቆምም ከዚህ ቀደም ከወር እና ከሁለት ወር በፊት ያወራነውን ሁሉ እያነሳች በትዝታ መሳቅ ጀመረች።
ከምሽቱ አምስት ሰአት አለፍ እንዳለ ሌላ ቦታ የተሟሟቁና የሰከሩ ወጣቶች ወደ ጭፈራ ቤቱ በብዛት መግባት ጀመሩ። ሰው እየበዛ ቤቱም እየሞላ መጣ። ይዣት ለመውጣት ብወስንም ቃልዬን ከዛ ቤት ይዞ መውጣት ቀላል ስራ አልነበረም።
በብዙ ውትወታ እና ልመናም እሺ ብላ አልወጣ አለችኝ። በግድ ተሸክሜም ቢሆን ይዣት መውጣት ነበረብኝ።
"እንግባ ይበቃናል ቃልዬ ነገ ጥዋት አራት ሰአት ክላስ አለሽ እኮ በጥዋት ስለምንሄድ ገብተን መተኛት አለብን"
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 35 ይለቀቃል?
Like አርጉ እኛም ቶሎ እንልቀቀው ?
https://vm.tiktok.com/ZMh9xdBnV/
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
[ምን አይነት ፊልም መመልከት ይፈልጋሉ?????????????
▶️የቱርክ ፊልም JOIN ? ይንኩ
▶️የአሜሪካ ፊልም JOIN ? ይንኩ
▶️ የህንድ ፊልም JOIN ? ይንኩ
▶️የቻይና ፊልም JOIN ? ይንኩ
▶️የአማርኛ ፊልም JOIN ? ይንኩ
▶️ተከታታይ ፊልሞች JOIN ? ይንኩ
▶️ አኒሜሽን ፊልሞች JOIN ? ይንኩ
▶️አክሽን ፊልሞች JOIN ? ይንኩ
▶️የጫካ ፊልሞች JOIN ? ይንኩ
▶️የፍቅር ፊልሞች JOIN ? ይንኩ
▶️የsex ፊልሞች JOIN ? ይንኩ
✅ እንደ ምርጫው መርጦ ይቀላቀሉ ✅
JOIN
ይቀላቀሉ ይቀላቀሉ](https://t.me/addlist/V90Z_jti1TU1ZmQ0)
♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
?...ክፍል 32...?
.
"ልክ እኔ እና አንቺ የአልጋላይ ጫወታውን እንደጨረስን
ያ ጠይሙ የውዝዋዜና የዳንስ ዳኛ ብድግ ብሎ አንቺን አንቺን ብቻ እያየ
"ዋው ዋው ዋው " እያለ ያጨበጭብና ቁጭ ይላል።
ቁጭ እንዳለ ማይኩን ብድግ አድርጎ•••የሚገርም ኬሮግራፊ፣ የተጠናና እና ውበት ያለው እንቅስቃሴ፣ የሚገርም ወገብ ፣ ዋው በአስር ደቂቃ ውስጥ ሁሉንም የጭፈራ አይነቶች ማሳየት መቻል ድንቅ ብቃት ነው።
ለብዙዎች እስቴጁን ተጠቀሙበት ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ ነው በተግባር ያሳየሽልን።
አልጋውን ማለቴ መድረኩን አጠቃቀምሽ ልዩ ነበር፣ ያልጨፈርሽበትን የአልጋ ክፍል ማግኘት ይከብዳል።በተለይ መሀል አከባቢ እሱ ቁጭ እንዳለ አንቺ እሱ ላይ ተቀምጠሽ ያሳየሽን እንቅስቃሴ ገራሚ ነው።
እንደዛው እንደተቀመጥሽ ወደላይ ወደላይ እያልሽ የአፋሮችን ባህላዊ ውዝዋዜ ስትስትጫወቺው ያየ ሰው አልጋውን ማለቴ መድረኩን አጠቃቀምሽ ልዩ ነበር፣ ያልጨፈርሽበትን የአልጋ ክፍል ማግኘት ይከብዳል።በተለይ መሀል አከባቢ እሱ ቁጭ እንዳለ አንቺ እሱ ላይ ተቀምጠሽ ያሳየሽን እንቅስቃሴ ገራሚ ነው።
እንደዛው እንደተቀመጥሽ ወደላይ ወደላይ እያልሽ የአፋሮችን ባህላዊ ውዝዋዜ ስትስትጫወቺው ያየ የሰው ልጅ ቁጭ ብሎም መዝለል ይችላል እንዴ? ማለቱ የማይቀር ነው።ወድያው ከአፋርኛ ወደ ሸጎዬ ቢት ቀይረሽ ግራ ቀኝ ዘንበል ቀና ስትይ ልዩ ትእይንት ነበር ።
እሱን አይተን ሳንጠግበው እንቅጥቅጥን ታስነኪው ጀመር፣ እዛ ላይ እንደተመሰጥን ወደ ጀርባሽ ድንገት ዝንጥፍ ብለሽ ስትታጠፊ እኔ በእውነት ወገብሽ ቅንጥስ ያለ ሁላ መስሎኝ ልጮህ ነበር።
ቃልዬ ሳቋን መቆጣጠር እያቃታት እያቃረጠች ብታስቸግረኝም ስቃ ጋብ እስክትል እያረፍኩ የዳኛውን ማብራሪያ ቀጠልኩ•••
አንድ ሳልነግርሽ ማለፍ የማልፈልገው ድንቅ እንቅስቃሴ መጨረሻ አከባቢ አንቺ ከስር ሆነሽ እሱን ከላይ ካደረግሽው በኋላ እግሮችሽን ወገቡ ላይ አጠላልፈሽ ያሳየሽው አለም ነው ።
እሱን አላላውስ ቢለውም ድንቅ ፍትወቶግራፊ የታየበት የዳኞቹን እና የ ተመልካቾችን ስሜት ሰቅዞ የሚይዝ ድንቅ ፐርፎርማንስ ነበር።
በዚሁ ቀጥይ ነገ ትልቅ ቦታ እንደምትደርሺ አልጠራጠርም ።
ይልና ባንዴ ፊቱን ዘፍዝፎት ወደኔ ይዞራል ከዛ እንዲህ ይለኛል •••
" ወዳንተ ስመጣ በጥቅሉ የሷ እንቅስቃሴና ፍጥነት ከጠበቅከው ውጪ የሆነብህና ግራ የተጋባህ መሆኑን ነው ያስተዋልኩት።
ለዚህ ማሳያው ዙሩ እየከረረ እና እየተጋጋለ ሲመጣ አንተም እንደኛው በሷ ሁኔታ የተገረምክ በሚመስል ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴያችሁን ቁጥጥር አንቺ እንዳሻሽ እንደፈቀድሽ አድርጊኝ ብለህ ለሷ በመተው ለመሳተፍ ሳይሆን እንደኛው ለመዳኘት የመጣህ ይመስል በአድናቆት ስትመለከታት ማየቱ በቂ ነው" ይለኛል ።
ከዛ የድምፅ ዳኛው ማይኩን ይቀበልና
ማነሽ ቃልኪዳን እኔ ላንቺ አድናቆቴን የምገልፅበት ቃል የለኝም።
በጥቅሉ ስታሰሚን የነበረው በስሜት የበለፀገ ድምፅ እንደ እንቅስቃሴው የሚፈጥን እና የሚረግብ ሪትሙ ልክክ ያለ ፣ ቴምፖው የተመጠነ ለጆሮ የሚጥም ድምፅ ነበር።
ወደ ኤፍሬም ጋር ስመጣ እእእ ኤፍሬም አንተ ጋር የነበረው ነገር በጣም ግራ የሚያጋባ ግራ የገባው ድምፅ ነው ።
እኔ የምታወጣው ድምፅ ማጓራት ይሁን ማቅራራት በፍፁም ሊገባኝ አልቻለም። እንቅስቃሴው ትንሽ ከበድ ብሎህ ስለነበር ድምፅህን አዛብቶታል።
ላንተ ያለኝ ምክር ሰፈራችሁ ጫካ አልያም ተራራ ካለ ባይኖርም ከከተማ ወጣ ብለህ ሰው ወደማይኖርበት ጫካ በመሄድ ጮክ ብልህ የድምፅ (ቮካል ) ልምምድ በመስራት ይህንን አባጣ ጎርባጣ ድምፅህን ልትሞርደው ይገባል " ይለኛል።
"ካካካካ አባጣ ጎርባጣ ድምፅ ግን ምን አይነት ነው ቃልዬ?" ስላት ቃልዬ እየሳቀች ስለነበር መልስ አልሰጠችኝም።
"ከዛ ሶስተኛው ዳኛ ደሞ•••" ብዬ ልቀጥል ስል•••
"ኧረ ኤፍዬ በቃህ መሳቅ ደከመኝ ኪኪኪኪ በእውነት ሆዴን አመመኝ በቃህ" አለችኝ።
ከወንበሬ ላይ ተነስቼ ወደ አልጋው በመሄድ ቃልዬን አቅፊያት ተኛሁ።
እሁድ አመሻሹ ላይ ወደ ድሬ ተሳፈርን። የሚኒባሱ የመጨረሻ ወንበር ላይ ያለነው እኔና ቃልዬ ብቻ ነን።
ሚኒባሱ ገና አልሞላም ከመናሀሪያ ቢወጣም ከመንገድ ላይ ለሞሙላት
"የሞላ የሞላ አወዳይ፣ ሀሮማያ ፣ደንገጎ ፣ ድሬ ዳዋ ሁለት ሰው" እያለ ይጣራል።
ውስጤ እርብሽብሽ አለብኝ ። ከቃልዬ ጋር ድሬ ስንደርስ መለያየታችን ግድ መሆኑን ሳስበው አ
ስጠላኝ።
"ቃልዬ ተነሽ እንውረድ !" አልኳት እጇን ያዝ አድርጌ እየተነሳሁ።
"ምነው ኤፍዬ ምን ረስተህ ወጣህ " እያለች ተከተለችኝ።
"ሀይ በቃ ሊነሳ ነውኮ ግቡ እንጂ አለ ረዳቱ"
"ዝም ብዬው የቃልዬን ክንድ ይዤ እየጎተትኩ ትንሽ እንደተራመድን
" አንተ ልበ ቢስ ምን ረስተህ ነው ? ለምንድን ነው የወረድነው?" አለችኝ።
"ምንም አረሳሁም ቃልዬ"
"እና ለምን ወረድን ይሄም በግድ ነው የሞላው ሌላ እናገኛለን ኤፍዬ ?"
"ወደድሬ መሄድ አስጠላኝ ቃልዬ ! ድሬ ዳዋ ገና ግብት እንዳልንባት አንቺን ከኔ ነጥቃ በመውሰድ እዛ ግቢ ውስጥ እንደምትወረውርሽ ውል ሲልብኝ መሄድ ቀፈፈኝ! "አልኳት አይን አይኗን እያየሁ።
ቃልዬ ማውራት ብትፈልግም ማውራት አልቻለችም እንባ እየተናነቃት ሲፈታተናት ዝም ብላ አቀፈችኝ። አጥብቃ አቀፈችኝ።
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 33 ይለቀቃል?
♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
?...ክፍል 31...?
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ=- ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍
.
.
በተለያየ አጋጣሚ ሁለቴ ከሞሞካከር በስተቀር እኔ በዚህ ዙርያ ብዙ ልምዱ እንዳልነበረኝ ባልክድም ያ ሙከራ እንጂ ትግበራ ለመባል እንኳን የማይበቃ መተሻሸት እንደነበረ ያመንኩት አሁን ነው።
ቃልዬ እያገለበጠች ስታንገላታኝ በተለይ አንደኛዋ ከዚህ ቀደም ያጋጠመችኝ ሴት ትዝ አለችኝ ። ምን ሆና ነው ግን እንደዛ አይኗን ጨፍና የተጋደመችው? ማደንዘዣ መርፌ ተወግታ ነው እንዴ የመጣችው? አልኩ።
ቃልዬ ትለያለች ። ወንድ ነኝ እኔ መብለጥ ነበረብኝ እንዴት እበለጣለሁ ብዬ በአጉል ትእቢት ደስታዬን መቀነስ አልፈለኩም።
ሁልግዜ ወንድ መብለጥ አለበት የሚል ነገር በአንዳንዶቻችን ወንዶች ጭንቅላት ውስጥ ያለ ኩፈሳ እንጂ ከተግባሩ ጋር ሲነፃፀር እውነቱ ሌላ የሚሆንበት አጋጣሚ እንዳለ እንደቃልዬ አይነት ተውረግራጊ የአልጋ ንግስቶች ያጋጠሟቸው ወንዶች መች ይክዳሉ።
እኔም መበለጤን አምኜ ስታጋድመኝ ስጋደም ፣ ስታስቀምጠኝ ስቀመጥ፣ ስታስቆመኝ ስቆም ፣ ስትንጠለጠልብኝ ስሸከም፣ ስትጨፍርብኝ ሳስጨፍር ወገቤ ተንቀጠቀጠ፣ ጉልበቴም ተብረከረከብኝ።
ሁለት እጄን ወደላይ ሰቅዬ •••
" ቃልዬ ገደልሽኝኮ የዕረፍት ሰአት የለም እንዴ ?"ልል ትንሽ ነበር የቀረኝ። እየተሽከረከረችና እያሽከረከረች ልኬን ስታሳየኝ እኔም እሷም ውስጥ የነበረው የደስታ ሲቃ ልዩ ነው።
እና እኔ ነኝ ቃልዬን ለምን ልጃገረድ አልሆንሽም ብዬ ለመደንፋት ሞራል ያለኝ?። ከድንግልናዋ ምን ጉዳይ አለኝ። ኧረ ምንም ። ብራንባር ቅብርጥሴ ኧረ የታባቱ ። ደሞ እሱ ኖረ አልኖረ ብዬ ልጨነቅ እንዴ። ጥንቅር ይበል ።
ብር አንባር ድሮስ ምን ያደርጋል ?እንደዉም ድንግልናኮ የወንዶች ባላንጣ ነው፣ የምሬን ነው ድንግልና ምቀኛ ነገር ነው።
እንደአመፀኛ ሚዜ በር ዘግቶ አላስገባም ሰርገኛ አርፈህ ተኛ እያለ ከመከላከል በቀር ምን ስራ አለው? ምንም።
እና እባክህ አሳልፈኝ በሞቴ ልግባ አልግባ እያልኩ ከሱ ጋር ግብግብ መግጠም ምን ያደርግልኛል? ምንም።
ኧረ እንኳንም አልኖረ ፣ ድንግል ሆና ዝም ብላ በጀርባዋ ተንጋላ በል ከቻልክ ግባ ካልቻልክ ስራህ ያውጣህ ብትለኝና ነገር አለሙን ሁሉ ለኔ ብትተወው ምን ይውጠኛል?እንደዛች ማደዘዣ መርፌ የተወጋች እንደምትመስለው ልጅ ሳትገላበጥ ሰትላወስ አይኗን ጨፍና በመጋደም ኧረ አሳመምከኝ ቀስ በል እንጂ ኤፊ አመመኝ እኮ እያለች የአልጋ ላይ ትራፊክ ሆና ብታሳቅቀኝ መሳቀቅ እንጂ ምን አተርፋለሁ?።
ልጃገረድ ብትሆን ለሷ ትልቅ ነገር ሊሆን ይችላል። ለኔ ግን ከሱ ጋር ትግል ገጥሜ ላቤን ከማንቆርቆር በስተቀር ምንም እንደማይሰራልኝ ያሳመነችኝ እራሷ ነች ።
ድንግል ከምትሆን ይልቅ እንዲህ እላዬ ላይ እንደቬንትሌተር እየተሽከረከረች አለሜን ብታሳየኝ እንደሚሻለኝ ያወቅኩት በሌላ በማንም ሳይሆን በቃልዬ ነው።
ይህንን ደስታ ድንግልና ኬት አባቱ አምጥቶ ይሰጠኛል።
ትርፉ ድካምና ሰቀቀን ብቻ ።ኧረ ወደዛ እንኳንም ቀረብኝ ።
ቃልዬ ፍቅር ሲይዝ እንዴት እንዴት እንደሚያደርግ ብቻ ሳይሆን ፍቅር እንዴት እንደሚሰራም ዛሬ አስተማረችኝ።
ቃል ለኔ የ ፍቅር አስተማሪዬ ነች ። እኔ ደሞ ተማሪዋ ።
ይህን ሁሉ የምለው ቃልዬ መታጠቢያ ቤት ገብታ እኔ ደግሞ ዝብርቅርቁ የወጣው አልጋ ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ያንቃቃችውን ወገቤን እያሸሁ ነው ።
ታጥባ እንደጨረሰች አጠገቤ መጥታ ጋደም አለችና
"ምን እያሰብክ ነው ጣራ ጣራ የምታየው ?" አለችኝ አንገቴን እየሳመችኝ።
"ያሯሯጥሻት ልቤን እስክትረጋጋ እየጠበኳት ነው"
"ኪኪኪ እሺ ሌላስ?"
"ሌላስ ምን ቃልዬ?"
"ሌላስ ምን እያሰብክ ነበር?"
"ሌላ ሌላ ሌላ ደሞ ያንቺ ፍቅረኛ በመሆኔ ምን ያህል እድለኛ እንደሆንኩም እያሰብኩ ነበር"
"ሌላስ?"
"ሌላማ ቃልዬ እንዲህ ስብርብር ያደረግሽውን ኤፍሬም እንዴት እንደምታድኝውና ይዘሽው ወደድሬ እንደምትመለሽ እያሰብኩ ነበር"
"ኪኪኪ•••ስንደጋግምበት ይለቅሀል እሺ ኤፍዬ" ብላኝ እርፍ።
"በለው በለው ያልቅልሃል ነው ይለቅሀል?" አልኩ የእውነት ደንግጬ።
ቃልዬ ከልቧ ሳቀችና
"እና ሌላስ ምን አሰብክ ምን ተሰማህ ደስ ብሎሀል ኤፊዬ?"
እየደጋገመች ሌላስ ሌላስ የምትለኝ ድንግል ነሽ ብዬ ጠብቄ ነበር እንድላት ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ።
ብላት ምን ሊሰማት እንደሚችልም አሰብኩ።ባይከፋትም የጠበኩትን ስላጣሁ ቅር ያለኝ ሊመስላት ስለሚችል እንደዛ ማለት አልፈለኩም።
"በጣም ደስ ብሎኛል ቃልዬ. ፣ ሌላ ነገር ግን ምን እንዳስብኩ ልንገርሽ?" አልኳት።
" እስቲ ንገረኝ ምንድን ነው እሱ?" አለችኝ ቀና ብላ በመቀመጥ አይን አይኔን እያየች
"የዳንስ፣ የውዝዋዜና፣ የመዝፈን ተሰጥኦ ያላቸውን በየቴሌቭዥኑ የሚዳኙት ዳኞች አሁን እኔና አንቺ እዚህ አልጋ ላይ ከደቂቃዎች በፊት ያደረግነውን ግብግብ
ተመልክተው የዳኝነት አስተያየት እንዲሰጡ ቢጠየቁ ምን ሊሉ እንደሚችሉ እያሰብኩ ነበር ስላት•••
" ኪኪኪ ምን ስትል አሰብከው በጌታ ! ፣ እስቲ ምን የሚሉ ይመስልሀል ኤፍዬ? አለችኝ እየሳቀች።
"ምን እንደሚሉ ልንገርሽ? ••• ቆይ ልክ እንደነሱ ፊት ለፊት ወንበር ላይ ተቀምጬ ነው የምነግርሽ እንደውም" እያልኩ ገና የቀጨችውን ወገቤን ደግፌ ስነሳ ነበር ሁለት ትራስ ደራርባ እግሮቿን ወደፊት ዘርግታ ግርግዳውን በመደገፍ መሳቅ የጀመረችው።
ክፍሉ ውስጥ ያለውን ወንበር ወደ ክፍሉ በር አከባቢ ወስጄ በቃልዬ ትይዩ ተቀመጥኩና•••
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 32 ይለቀቃል?
https://vm.tiktok.com/ZMhPw4syW/
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 2 Monate, 1 Woche her
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 11 Monate her
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 Wochen, 6 Tage her