لـ تمويل 💜 🔚 @vssss
✹ القناة الرسمية عالتلڪرام استمتعو بالمشاهده 📮♥️
•┊رمزيات 📷
•┊اقتباسات 📖
•┊فيديوهات 📽
•┊اغاني 🎧
• رابط القناة 💙🔚 @ssssv
✹ القنـاه الاولئ علئ التليڪرام والباقي تقليد 💞💞
Last updated 1 month, 2 weeks ago
- انتِ جميلة كشيّء مُقتبس من ملاذ الحياة..
للإعلانات المدفوعه t.me/dddlb
رابط القناة t.me/dlIIIIl
Last updated 2 months ago
الفَارس لِنقل المُبـٰاريات.
Last updated 5 months, 2 weeks ago
በመጀመሪያ፦
እንደ ጥያቄ ለጸህፊዋ እና ፖስቷን ለሚጋሩ ፤ ከነዚህ ሃሳቦች ዉስጥ አንድ ከቁርአን ወይንም ከሓዲስ ማስረጃ ያለው ሃሳብ አለን? ካለ -
قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ )
፡ «እውነተኞች እንደኾናችሁ አስረጃችሁን አምጡ በላቸው፡፡
1ኛ ነጥብ - በድብቅ 2ኛ፣ 3ተኛ፣ 4ተኛ ሚስት መሆን- የተፈለገበት ለሷ ቅርብ የሆኑ ወልዮች ሳይፈቅዱና የሚገባቸውን ሳይፈፅሙ ማግባት ከሆነ አንደኛም ሚስት ሆና ይሁን ሁለተኛ ያሰረችው ኒካሕ በነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሐዲሶች ሚዛን ወድቅና ተቀባይነት የሌለው ነው። ከዚህ ውጭ ሸሪዓዊ መስፈርቶችን አሟልተው ከአንደኛ ሚስቱ ድብቅ መሆንን ከሆነ ይህ መስለሓን የሚመለከት ጉዳይ ነው።
በመሠረቱ - ሁለተኛ ማግባት የፈለገ ወንድ ጉዳዩን ለመጀመሪያዋ የማሳወቅ ግዴታ የለበትም ! ጥቅሙንና ጉዳቱን በማመዛዘንም መጥጠበቅ ያለባቸውን መስፈርቶች እስከ ጠበቀ ድረስ ሁለተኛውን ትዳር መደበቅ እንደሚችል ዑለማእ ያወራሉ ! በምትሉት ነገር ላይ መረጃን መሠረት ማድረግ አይታይምና አላህን ፍሩ ! አላህን ፍሩ !
2/ ባል ሁለተኛ ሲያገባ የመጀምርያ ሚስቱ ከሱጋ ችግር ያላየች…….“ የሚለውን በተመለከተ
አንድ ባል የመጀመሪያ ሚስቱ አመታትን ከሱ ጋር ስለወጣችና ስለወረደች በሷ ላይ ሁለተኛ ከማግባት የሚከለከልበት አሳሪ የሆነ ሸሪዓዊ ህግ የለም ። ይህንን በማድረጉም በመጀመሪያ ሚስቱ ላይ በደልን እንደፈፀመ ታስቦ ሊኮነን አይገባውም ። ነውሩ ይህንን ሸሪዓ የፈቀደውን ትዳር ማነወሩ ነው !!! አንዳንድ ሴቶቻችን ወዴት እየሄዳችሁ ይሆን እንዴህ አይነቱን ነገር በድፍረት አደባባይ ላይ እስከማነወር የደረሳችሁት ?!
ይሄ التقييد ወይንም التخصيص ከየትኛው የቁርአን አያት ወይንም ሓዲስ ኢስቲንባጥ(استنباط) ተደርጎ ይሆን? እስኪ
( قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ) ፣
قال الله تعلى
فَٱنكِحُواْ مَا طَابَ لَكُم مِّنَ ٱلنِّسَآءِ مَثۡنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَۖ فَإِنۡ خِفۡتُمۡ أَلَّا تَعۡدِلُواْ فَوَٰحِدَةً أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡۚ ذَٰلِكَ أَدۡنَىٰٓ أَلَّا تَعُولُواْ )
ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
3/ 3ተኛ ላይ የተነሳው ሃሳብ “ምነው ባልተነሳ”። እንደተጻፈው “ የስሜት ማራገፊያ “ እዚህ የተፈቀደ ቦታ ላይ ልቅ በሆነ መልኩ መጠቀም የሚጠበቅበትን ሀያእ ካራገፈ ሰው እንጂ ከደጎች ፣ ንግግራቸውን ከሚመዝኑ ሰዎች አይጠበቅም ።
አላህ የፈቀደው ቦታ ላይ እንዲህ አይነቱን ፀያፍ ቃል መጠቀም ሐያኡን ካራገፈ ሰው ብቻ ይጥጠበቃል !
እንዲህ አይነቱን አገላለፅ ከኢስላም ጠላቶች ነበር የምናውቀው !
ተፈጥሯዊ ፍላጎቶችን በተፈቀደ ነገሮች ላይ ማዋል እንዲህ አይነቱ ፀያፍ ቃል የሚገባው አይደለም
وفي بضع أحدكم صدقة
ብለው ነቢዩ ሰደቃ በማለት ገልፀውታል ።
4/ አራተኝውና የመጨረሻው ሃሳብ፤ ሁለተኛ ሚስት መሆን መቆጨትን ማስከተሉ ነው።
ለመሆኖኑ እንደ ሙስሊም የሚያስቆጭና የሚስለቅስ ነገር ምንድን ነው? _ ሽርክ መስራት፤ በዲን ላይ መፍጠር፤ መልክተኛውን አለመታዘዝ፤ በዲን ላይ ያለ እውቀት መናገር፤ ዝሙት……’’
قُلۡ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ ٱلۡفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنۡهَا وَمَا بَطَنَ وَٱلۡإِثۡمَ وَٱلۡبَغۡيَ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَأَن تُشۡرِكُواْ بِٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ سُلۡطَٰنٗا وَأَن تَقُولُواْ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ )
«ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው» በላቸው፡፡
የመሳሰሉት ወንጀሎች። አላህ ሁለተኛ ሚስት መሆንን በድብቅም ይሁን በግልጽ ከልክሏን?
በመጨረሻም በዚህም ጉዳይ ይሁን በሌሎች የዲን ጉዳዩ እንደነዚያ አላህ
مُّذَبۡذَبِينَ بَيۡنَ ذَٰلِكَ لَآ إِلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِ وَلَآ إِلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِۚ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ سَبِيلٗا (143)
በዚህ መካከል ወላዋዮች ኾነው (ያሳያሉ)፡፡ ወደእነዚህም ወደእነዚያም አይደሉም፡፡ አላህም ያሳሳተውን ሰው ለእርሱ (የቅንነት) መንገድን በፍፁም አታገኝለትም፡፡
የተዓዱድ ጉዳይም እንዳይከለክሉት ከአላህ ዘንድ የሆነ ግልጽ ፍርድ ሆነባቸው እንዳይቀበሉት ስሚትና ኩራት አሸነፋቸው። ምነው ይሄን ትተው ሁሉም ከአላህ ዘንድ ነው ተቀብለናል ባሉ ኖሮ።
ማመንታት አይበጅም ከአላህ ዘንድ የመጣ ሁሉ ሃቅ ነው ልባችን ባይፈልገውም።የሰዎች ሁሉ ምርጥ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሁ ወሰልም ከ1 በላይ ሚስት ነበራቸው የአላህ ኸሊል ኢብራሂም ዓለይሂሰላም ከአንድ በላይ ሚስት ነብራቸው ኹለፋኡ ራሺዲን፤ በርካታ ሶሓቦችም ከአንድ በላይ ሚስቶችን አግብተዋል። ሚስቶቻቸው አልትቃወሙም።
በዚህ ላይ ከላይ የተጠቀሱት 4 ነገሮች ለሁለተኛ ወይንም 3ተኛ ሚስት ብቻ ሳይሆን በመጀመርያዋም ሚስትም ላይ ሊባል ይችላልና ትዳሩን ጠቅልሎ ትቶ ወደ ምንኩስና ወይንም ዝሙት ማምራቱ ሳይሻል አይቀርም ማለትን ያስይዛል።
በየዩኒቨርሲቲው ያለ ሰርግ በቤተሰብ ፍቃድ ብቻ (የኒካሕ መስፈርቶችን አሟልቶ)ኒካህ ማድረግ በዝቷል ወጣቱም ስራ ኖራት አቅም እያጠረው ኒካህ አድርጎ በድብቅ መኖርን ተያይዟል …. እናም አንቺ የዚህ ሰው ሚስት ሆይ ይሄን ጸያፍ ተግባርሽን ተይ ቤተሰቦቹ እስከ እዚህ እድሜው ድረስ በውጣ ወረድ አሳድገው አንቺ ተንሰፍስፈሽ ስታገቢው አያሳፍርሽም ወይ በያት…. ፍቺዋንም ጠይቂላት! የሱ ስሜት ማራገፍያ ከመሆንም ውጪም ምንም ጥቅም እንደሌላት ንገሪያት። እንደው በምን ማስረጃ ይሆን የመጀመርያዋ የስሜት ማራገፍያ ሳትሆን የሁለተኛዋ የስሜት ማራገፍያ የሆነችው?
አሁንም እህቶችሽን - አንዳድንድ ወንዶች ገብዘባችኁን ሊበሉ ይችላሉና ትዳር ይቅርባችሁ አታግቡ። ባል ገንዘባችሁን ይበላል ያስለቅሳችሃልም በያቸው። መፍትሄው ይሄ ከሆነ። ከዚያም ከምንኩስና ወይንም ዝሙት ሌላ አማራጭ ካላቸው አመላክቻቸው።
ልብ እንበል - የተፈለገው በተዓዱድና በትዳር ስም የሚፈጸመውን ግፍንና በደል ማጽደቅ ሳይሆን በነዚህ አይነት ግፈኞች ተዓዱድንና ትዳርን መሸሽ ትክክል አለመሆኑን ማሳታወስ ነው!!
አቡ ሙዓዊያ ሰኢድ ሙሐመድኑር ሐፊዘሁሏህ
`የሰዉን ልጅ ብዙ መካሪ ቢኖራቸዉም
ለአንድ አማኝ ግን ከቁረአን በላይ
መካሪ የለዉም!!!
إِذَا زُلْزِلَتِ الْأَرْضُ زِلْزَالَهَا
(ሱረቱ አል-ዘልዘላህ - 1)
ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤
وَأَخْرَجَتِ الْأَرْضُ أَثْقَالَهَا
(ሱረቱ አል-ዘልዘላህ - 2)
ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤
وَقَالَ الْإِنسَانُ مَا لَهَا
(ሱረቱ አል-ዘልዘላህ - 3)
ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤
يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا
(ሱረቱ አል-ዘልዘላህ - 4)
በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡
بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا
(ሱረቱ አል-ዘልዘላህ - 5)
ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡
يَوْمَئِذٍ يَصْدُرُ النَّاسُ أَشْتَاتًا لِّيُرَوْا أَعْمَالَهُمْ
(ሱረቱ አል-ዘልዘላህ - 6)
በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ
(ሱረቱ አል-ዘልዘላህ - 7)
የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ
(ሱረቱ አል-ዘልዘላህ - 8)
የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል`
لـ تمويل 💜 🔚 @vssss
✹ القناة الرسمية عالتلڪرام استمتعو بالمشاهده 📮♥️
•┊رمزيات 📷
•┊اقتباسات 📖
•┊فيديوهات 📽
•┊اغاني 🎧
• رابط القناة 💙🔚 @ssssv
✹ القنـاه الاولئ علئ التليڪرام والباقي تقليد 💞💞
Last updated 1 month, 2 weeks ago
- انتِ جميلة كشيّء مُقتبس من ملاذ الحياة..
للإعلانات المدفوعه t.me/dddlb
رابط القناة t.me/dlIIIIl
Last updated 2 months ago
الفَارس لِنقل المُبـٰاريات.
Last updated 5 months, 2 weeks ago