ዳና🐾

Description
👉 ከዘረኝነት እና ከሀይማኖት ትንኮሳ ፍፁም የፀዳ ፍቅር ቁምነገር እና ተዝናኖት የሚፈጥሩ የተመረጡ እጅግ ውብ ሀሳቦች ብቻ የሚንፀባረቁበት የእናንተው ቻናል ነው።

👉 ለብዙዎች ደርሶ ሰፊ ለውጥ ያመጣ ዘንድ ለወዳጅ ጓደኞቻቹ ማገራት አይርሱ።
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 9 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 months ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 3 months, 3 weeks ago

2 months, 1 week ago

☕️☕️☕️

ገና አንድ ስኒ ቡና ስጠጣ ያየሁትን ሰው ሁላ የመውደድ መግነጢሳዊ ሀይል ይቆጣጠረኛል ..... እንደ እናት ልጅ እሳሳላቸዋለሁ የኔ ቢጤወች መተው ስለእመብረሀን ካሉኝ ኪሴን ገልብጬ ምንም እስከማይቀረኝ እባርካቸዋለሁ

ከፍተኛ ትህትና ይጠናወተኛል የገፋኝን ሰው ሲቃ እየተናነቀኝ ይቅርታ እጥይቀዋለሁ ......የሆነ ጉዳይን የምረዳት አቅሜም ከወትሮው በሀምሳ ፐርሰንት ከፍ ይላል የተምስጦዬን ነገር ተውት 😌

🤎🤎

©Lamri

2 months, 2 weeks ago

ከጦርነትም በላይ የሚገርመኝ ምድራችን ላይ የፍቅር እድሜ አስተጣጠር ነው። ስናፈቅር ደግሞ ግነቱ! ተመልከቱ ከስድስት አመት በፊት እንዴት ልብስ የሚያስጥል ፍቅር ውስጥ እንደነበርን። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲያስል ሁሉ ይደገም ብለናልኮ። ቀልድ አይደለም ሚሊኒየም አዳራሽ ጉሮሯቸውን ለመጠራረግ እህህ ሲሉ (አማርኛ ማውራት ተናንቋቸው) ይደገም ይደገም ...😀 ዶ/ር ዓብይ ሁለት ቀን ከግማሽ ቲቪ ላይ ጠፉ ብለን ተጨንቀናልኮ በኋላ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት "ደህና ናቸው አብረን ነው በአውሮፕላን የመጣነው" ብለውን ተረጋጋን። የምንግዜም ምክትል ጠ/ሚንስትር የነበሩት ደመቀ መኮነን በላይ ዘለቀ ናቸው ብለንም ነበር። ዝርዝሩ ትዝ አይለኝም! እና ይሄን ሁሉ የሚያደርገን ፣ ገመና የሚያሸፋፍነን ፍቅር እንደንጥሻ ውልብ ብሎ ጦርነት ግን ለዓመታት የሚቆይልን እንዴት ነው?

#ዳና

2 months, 3 weeks ago

ለደህንነቱ ስል ስሙን የማልጠቅሰው አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት (ወገኛኮ ነኝ😄) በቲሸርት ገባሁ… ቀና ብሎ ያየኝ እንኳን አልነበርም። ችላ አሉኝ። ተመልሼ ወጥቼ ጃኬት ለብሼ ገባሁ። "ምን እንታዘዝ ጌታዬ" ብሎ አንድ ልጅ ቆሞ እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ… ጃኬት በጣም የተናቀ ግን ጠቃሚ ነገር ነው።

እንዴት ብላችሁ ያለ ጉቦ… የጉቦ መስተንግዶ እንደምታገኙ መረጃ ልስጣችሁ ብዬ ነው… ቁልፍ ያላችሁ ደሞ በእጃችሁ ብትዪዙት ነገሩን ያፋጥነዋል… ማንኛውም ቁልፍ መሆን ይችላል 😄

#ዳና

4 months, 2 weeks ago

ጠበቃው

∞ ∞ ∞ ∞

ጠበቃው ሚስቱ ሞተችበት። የተዝካሯ ዕለት ያሠራላትን ሀውልት ሊያስመርቅ ወዳጆቹን ሰብስቦ ሃውልቱ የተሸፈነበት ጨርቅ ሲገለጥ ሃውልቱ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ተጽፎበት ነበር፣

"የአሸብር ሸንቁጤ ሚስት እዚህ አርፋለች። አሸብር ሸንቁጤ በማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና አማካሪ ። ውዴ ነፍስሽ በሰላም ትረፍ"

ይህንን ያየው ጓደኛው ሲመለከተው አሸብር ሸንቁጤ ተንሰቅስቆ እያለቀሰ ነበር። ጓደኛው በንዴት ጠየቀው፣

"እንዲህ ዓይነት ርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ለምን ፈለግህ? አሁን ምን ያስለቅስሃል?"

"የሚስቴ መሞት ብቻ አይደለም የሚያስለቅሰኝ"

"ታዲያ ምንድነው"

"ይሄ ሀውልት ሲሰራ ለሀውልት ሠሪው ቢዝነስ ካርዴን ሰጥቼው ነበር። ስልክ ቁጥሬን ሳይጽፈው ረስቶታል። እሱ ነው የሚያስለቅሰኝ"

#ዳና

4 months, 2 weeks ago

እናንተ… ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ ሰዎች

∞ ∞ ∞ ∞

ልብስ ሳትለኩ የምትገዙ፣ ነፍፍ ቁጥር በቃላችሁ የምትይዙ፣ አስተማሪ "እስቲ አንተ ይሄንን ጥያቄ መልስ" ብሏችሁ የማያውቅ እና ጭራሽ ደግሞ ተከራክራችሁ የፈተና ማርክ የምታስጨምሩ አላችሁ፣ ከኤክሳችሁ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ያላችሁ፣ የተተበተበ ኤርፎን ቶሎ የምትፈቱ፣ እጅ ፅሁፋችሁ የሚያምር፣ ሂሳብ ቶሎ የምትደምሩና የምትቀንሱ፣ ቤቲንግ የምትበሉ፣ ስልክ የማይጠፋባችሁ፣ ጉዳይ ቶሎ የምታስፈፅሙ፣ ጫማ የማይቆሽሽባችሁ፣ ATM ካርዳችሁን ወስዶባችሁ የማያውቅ…

∞ ∞ ∞ ∞

ከሁለት ደቂቃ በላይ የሆነ ቪዲዮ ሳታቋርጡ የምታዩ ሰዎች ምን ጉድ ናችሁ?… እንዴት ቻላችሁበት… የጥልቁ አባል ከእናንተ በላይ ይኖራል?

∞ ∞ ∞ ∞

አላርም Snooze ሳታደርጉ ሲጮህ ብድግ ብላችሁ የምትነሱ፣ በሰርጋችሁ ቀን በተደረገ ወሲብ አርግዛችሁ ያስረገዛችሁ፣ ስማችሁን ሰው ሲፅፈው spelling የማይሳሳትባችሁ፣ የመረጣችሁት መንግስት የሚገዛችሁ (የእናንተ ደሞ ይለያል)፣ ቶሎ ቶሎ የማይርባችሁ፣ በልታችሁ ጠጥታችሁ ሂሳብ ልትከፍሉ ስትሉ የሞባይል ባንኪንግ እምቢ ብሏችሁ የማያውቅ፣ የተገኘውን ቢራ የምትጠጡ፣ እስኪሪብቶ የማትበሉ፣ ስልካችሁ ላይ password የሌላችሁ...

∞ ∞ ∞ ∞

በrelationship 4 አመት ምናምን የምትቆዩ፣ መጥፎ ነገር ሆኖባችሁ ሲያበቃ ተመስገን የምትሉ ምዕመናን፣ ጀርባችሁ ላይ የሚያሳክካችሁ ቦታ ደርሳችሁ የምታኩ፣ የማታውቁት ሰው ለቅሶ ላይ ሄዳችሁ ንፍርቅ የምትሉ…

∞ ∞ ∞ ∞

የቤት ኪራይ በቀኑ የምትከፍሉ፣ Diet ላይ የምትቆዩ ሰዎች፣ ልብስ ተኩሳችሁ የምትለብሱ፣ ክብሪት በአንድ ሙከራ የምትጭሩ፣ ዝርዝር ብር እና ካሽ ኪሳችሁ ውስጥ የማይጠፋ፣ ከሰል ቶሎ የምታያይዙ፣ መንገድ ላይ ገንዘብ ወድቆ የምታገኙ፣ ፀጉራችሁን ያገኛችሁበት ገብታችሁ የምትሰሩ፣ ሻይ እና ቡና በትኩሱ የምትጨልጡ፣ ጨጓራ እና ፈርስ የምታጣጥሙ እና…

በተለይ በተለይ ደግሞ… ከውጭ ገንዘብ የሚልክ ዘመድ ያላችሁ ሰዎች…

ሁላችሁም በጣም ነው የምታስፈሩኝ…ኢሉሚናቲ ናቹ እንዴ ቆይ?

#ዳና

4 months, 2 weeks ago
(ፈጣሪ ምስክሬ ልጁን አላውቀውም ግን ስላሳዘነኝ …

(ፈጣሪ ምስክሬ ልጁን አላውቀውም ግን ስላሳዘነኝ ነው፡፡የልጅ ህመም ያሳዝናል፡፡የቻላችሁ አግዙ ያልቻልን ደሞ ሼር እናርግ)

የእርዳታ ጥሪ

የ14 አመቱ ታናሽ ወንድማችን ያቤጽ ሰለሞን የመጨረሻ ደረጃ የተራዘመ የኩላሊት በሽታ ህመም እየተሳቃየ ይገኛል። በዚህ እድሜ ከእኩዮቹ እኩል ትምህርቱን መከታተል ሲገባው በስቃይ ላይ ማሳላፉን ማየት ለወላጆቹ ልብ የሚሰብር ነው። ያቤጽ ህክምናው በሀገር ውስጥ ማድረግ እንደማይችል እና ወደ ውጪ ሄዶ መታከም እንዳለበት ሀኪሞች ለቤተሰቹ አሳውቀዋቸዋል። ልጃችን ያቤጽን ለመታደግ ይረዳ ዘንድ እንዲሁም የተለያዩ ወጪዎች ይረዳቸው ዘንድ ቤተሰቦቹን ለማገዝ ትንሽም ትልቅም የአቅማችሁን እንድትረዱን በፈጣሪ ስም እንጠይቃችኋለን።

ለመርዳት
አካውንት ባለቤት: ሰለሞን አለማየሁ

አካውንት ቁጥር:
ንግድ ባንክ: 1000057164143
አዋሽ: 01320037587500
አቢሲኒያ: 102845781
Coop: 1000072492677

ቤተሰቦቹን ለማውራት
0962157832
09116704076

4 months, 3 weeks ago

አልበም ወ ፌስቡክ

∞ ∞ ∞ ∞

በድሮ ዘመን fb ስላልነበር ሰዎች ፎቷቸውን ፖስት የሚያደርጉት አልበም ውስጥ ነበር ፤ ከዛም እንግዳ ሲመጣ ከለስላሳ መጠጥ ጋር ያቀርባሉ ፤ እንግዳውም "ይህንን ፎቶሽን እንዴት እንደወደድኩት!" ብሎ Like እና comment ያደርጋል ፤ የሆነ ሰው ቤቱ ሆኖ ስቅ ካለው mention ተደርጓል ማለት ነው ፤ እንግዳው የሚወደውን ፎቶ ከአልበም ውስጥ ካገኘ share ያደርጋል (ሰርቆ ይወስዳል) ፤ ፎቶ እየተሰረቀባቸው የሚቸገሩ ሰዎችም አልበሙን ቁም ሳጥን ውስጥ ቆልፈው only me ያደርጉት ነበር።ፎቶ አብሮ የተነሳው ሰውዬ ጋር ፀብ ከተፈጠረ ደግሞ block ይደረጋል ፎቶው ከሁለት ይቀደድና የሰውየው ምስል ያለበት ወደ ጋርቬጅ ይጣላል፣አልበም ውስጥ ፎቶ ካለው ጓደኛ ጋር ከተደባበሩ ደግሞ un follow ይደረጋል ፎቶው ላይ ሌላ ፎቶ ይደረባል።

#ዳና

4 months, 4 weeks ago
ዳና🐾
4 months, 4 weeks ago
በነገራችን ላይ የኑሮ ደረጃህን ሁልጊዜ የአለም …

በነገራችን ላይ የኑሮ ደረጃህን ሁልጊዜ የአለም ባንክ እስኪነግርህ አትጠብቅ።

∞ ∞ ∞ ∞

የድህነት ወለል ጣራ እያልክ አትድከም። መለኪያው እጅህ ላይ ነው። ይሄ ፎቶው ላይ የሚታየው ምንድነው? አየህ! መልስህና አጠቃቀምህ ደረጃህን ይነግርሃል ....

∞ ∞ ∞ ∞

ሐብታሞች በብዛት ገዝተው በብዛት ለብር ማስያዣነት ይጠቀሙበታል። ደሀ ሴቶች ለፀጉር ማስያዣ ፣ ደሀና ከይሲ ፈላወች ወስፈንጠር ሰርተው አላፊ አግዳሚ ለመነጀስ ይጠቀሙበታል። አንድ የሀብታም ልጅ በወስፈንጠር ሲጫወት አታገኝም። ይሄን ላስቲክ "ለቁርጥማት ጥሩ ነው" ብሎ እንደብራዝሌት እጁ ላይ የሚያስር ቁርጥማታምም አለ። ምን ላይ ነን ?? ((ከለጠፍኩት በኋላ ብዙ ሰው ፓስታ መስሎን ብሏል እያዛጋ፣ ካሰብኩት በላይ ነው እንዴ የራበን??))

#ዳና

5 months ago

አንዳንዱ አባት ፀልዮ ነው የሚሳሳተው?!

አንድ አብሮን የተማረ ጓደኛችን ወደአውሮፖ በሊቢያ በኩል ልወጣ ሞክሬ ለአንድ አመት ከዳከርኩ በኋላ ነገሮች ተበላሹብኝ፣አሁን ወደኢትዮጵያ መመለሻ የተወሰነ ብር ፈልጌ ነበር ፣ይልና ለአንዱ ጓደኛችን ይነግረዋል። ልጁ የተረጋጋ ከተመረቅን በኋላም አሪፍ ስራ የነበረው ልጅ ስለነበር በነገሩ አዘንን። በቃ ሁላችንም የቻልነውን እናድርግ ተባለና የተወሰነ ብር ተዋጣላት፣ በሰላም ኢትዮጵያ ገባ። ከስድስት ወር በኋላ አንድ አስገራሚ ነገር ተፈጠረ።

እንዳለ የተዋጣለትን ብር አመስግኖ ላሰባሰበው ልጅ ይመልሳል። ነገሩ ብድር ስላልነበር ሁላችንም ተገረምን። እና ምን እንደገጠመው ስንጠይቅ ከነመኖራቸው የማያውቃቸው ሁለት የአባቱ ልጆች አፈላልገው አግኝተውት እህቶችህ ነን ለዓመታት ስናፈላልግህ ነው የኖርነው። አባታችን አባትህ ነበር። የኑሮ ችግር የለብንም  ምናምን ይሉታል። በአጭሩ የሞላ የተረፋቸው ሃብታም እህቶች በአንድ ጀምበር ያውም ከሆነ አውሮፓ አገር ሄደው ያንን ከርታታ ኑሮውን ቀያየሩት። እሱም ሰበብ ነበር የሚፈልገው መስመሩን ይዞ "ስትመጡ ወጭ በኔ ነው " ብሏል አለኝ። አንዳንድ አባቶች ፀልየው ነው መሰል የሚሳሳቱት ብሎ ቀለደ አንዱ ወዳጃችን።

ገንዘብ ያሰባሰበው ወዳጃችን በነገሩ ውስጡ ተነካ፤ እኔምኮ ላገኛቸው ፈርቸ እንጅ አባቴ ከመሞቱ በፊት ከሌላ የተወለዱ ሁለት እህቶችና አንድ ወንድም እንደነበሩኝ ነግሮኛል ይለኛል። እንዴ ምን አስፈራህ ዘመድ ጥሩ ነው፣ አግኛቸው በማለት አበረታታሁት። መከርኩት። በሞራል የሶስት ወር ረፍት ወስዶ ሄድና አፈላልጎ አገኛቸው። ታሪኩን ሳሳጥረው ወደአሜሪካ ሲመለስ በቦሌ ሄዶ በሊቢያ በኩል በእግሩ የተመለሰ እስኪመስለኝ ከስቶ በአንዴ ሽበት ሁሉ ወሮት ሳገኘው ደነገጥኩ።

ምን እንደገጠመው በሰፊው አጫወተኝ። እህቶቹን አገኛቸው። አንዷ ባሏን በሊጥ መዳመጫ  ገድላ እስር ቤት ነበር ያገኛት፣  ወንድሟ እንደሆነና ከአሜሪካ እንደመጣ ሲነግራት  «እስከዛሬ አሜሪካ በርገርህን እየገመጥክ  ነው እንዲህ ስንቸገር ዝም ያልከው? ብላ ካፈጠጠችበት በኋላ ፣ከእስር ቤት እስከምትፈታ አምስት የቲም  ልጆቿን እንዲንከባከብ አስጠንቅቀዋለች። ዘጠኝ አመት ነው የተፈረደባት ሁለቱን ጨርሳለች። "ሰባት ዓመት እሩቅ እንዳይመስልህ፣ አትወጣም ብለህ በዛው ትጠፋና እንደገና ወደኢትዮጵያ ዙረህ አታይም" ብላ ሁሉ ዝታበታለች።

ሌላኛዋ እህቱ ጫት ቤቷ በልማት ፈርሶባት ያገኛታል። ከሚከስር ብላ የተረፈውን ጫት እዛው ፍርስራሹ ላይ ፈርሻ እየቃመች ፣ሁለት ጉንጯ ተወጥሮ የየመን ወታደር መስላ ነበር። እንኳን የአባቷን ልጅ ከአባት መወለዷን ሁሉ በብዙ ማብራሪያ ነው ያስታወሰችው! ለዚያውም «ኦ አስታወስኩ አባቴ በሱማሊያ ወረራ ጊዜ ነው የሞተው፣ ተረግዠ ነበር ወደጦርነት የሄደው » ትለዋለች። የተወለደችው ግን 19 89 ነበር። ይሄ ማለት እንደሰው ዘጠኝ ወር ሳይሆን በ1969 ተረግዛ ከ20 ዓመት በኋላ የተወለደች ልዮ ፍጥረት። አይ ጫት...እዚህ ኑሮ ላይ ሲደመር ይሰራዋል ስራ! የሆነ ሁኖ የስድስት ወር የቤት ኪራይ ከፍሎ፣ ወረት ሰጥቶ ነበር የተመለሰው። ገና ከመመለሱ ደወለች። ሰላም መግባቱን ለማረጋገጥ መስሎት ነበር፣ ግን የተከራየችው ቤት እንደገና ለልማት መፍረሱን ነገረችው።

ሶስተኛው ወንድሙ እንኳን ደህና ነበር። ዝንጥ ያለ ፈገግታ የማይለየው አካውንታት። መላጣ። እና ምን አለው «ዋናው ወንድምነቱ ነው! ፈልገኸን ስለመጣህ አመሠግናለሁ። ትልቅ ሰው ነህ።  እንኳን ተገናኘን! ብዙ ላስቸግርህ አልፈልግም፣ አሜሪካም ቢሆን ገንዘብ ከመሬት አይታፈስም ወንድም አለም ! ብቻ ይችን ፀጉሬን ቱርክ ሄጀ ማስተከል የዘወትር ህልሜ ነበር። እንዲሁ ትንሽ ዶላር ከላክልኝ ይበቃኛል። ስትመለስ ይደርሳል ብዙ አያስቸኩልም?

አንዳንድ አባት ስህተቱ መራር ነው። ስህተትም እነደሎተሪ ዕድል ይጠይቃል መሰለኝ። እና በመጨረሻ  ደሜ መራር ነው መቸም ምናለኝ ? «ባትመክረኝ ኑሮስ አብርሽ . . .ተው ብትለኝስ...»

አሁን ደግሞ ለእርሱ እያዋጣን ነው።

#ዳና

We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 9 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 months ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 3 months, 3 weeks ago