Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 weeks ago

3 weeks, 2 days ago
የኢራን መከላከያ ሚኒስትር መሀመድ ሬዛ ቀሬይ …

የኢራን መከላከያ ሚኒስትር መሀመድ ሬዛ ቀሬይ አሽቲያኒን ጨምሮ የኢራን አብዮታዊ ሰራዊት ከፍተኛ ጄነራሎች በምሽቱ የአጸፋ ጥቃት ዙሪያ መግለጫዎችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ
..
ሀሩን ሚዲያ፥ ሚያዝያ 5/2016
...
ሚንስትሩ በመግለጫቸው እስራኤል የትኛውንም አይነት ጥቃት እፈጽማለሁ ካለች ሌላ የከፋ ዙር አጸፋ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ሚንስትሩ ከእስራኤል በተጨማሪ ኢራንን ለማጥቃት እና እስራኤልን ለመርዳት የአየር ክልሏን ወይም ግዛቷን የከፈተች ሀገር ሁሉ የኢራን ቆራጥ ምላሽ ይጠብቃታል ሲሉ ዝተዋል።
...
የአብዮታዊ ሰራዊቱ ጄኔራሎች በሰጡት መግለጫም የተጠቀሙት ክሩዝ ሚሳኤልና ድሮን የእስራኤልን ጠንካራ የሚሳኤል መከላከያ እንዲያልፉ ተደርገው የተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከታቀደው በላይ ኢላማቸውን መምታታቸውንም አያይዘው ጠቅሰዋል። በአጽንኦት የገለጹት ጉዳይም እስራኤል ምንም አይነት እርምጃ ዜጓቿ ላይ ብትፈጽም አጸፋውን ለመመለስ አሁንም ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ ነው።
..
ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሀገሮች ሀይፐርሶኒክ የተሰኘውን አውዳሚ መሳርያ ጨምሮ የኒውክለር ሀይል ጋር ስሟ ተያይዞ የሚጠቀስ ሀገር እንደመሆኗ ይህ ጦርነት አደገኛ ምዕራፍ እንዳይዝ ተሰግቷል። የእስራኤል አጋር የሆነችው አሜሪካም በፕሬዝዳንቷ በኩል እስራኤል የአጸፋ ምላሽ እንዳትሰጥ መጠየቋን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ አልጀዚራ ዘግቧል።
...
© ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j

1 month, 4 weeks ago

የሀሩን ሚዲያ የዛሬው አስደማሚ ዕለታዊ ውሎ

የሀሩን ሚዲያ የዝግጅት ክፍል በዛሬው እለት ብቻ በርካታ ቦታዎች ላይ ተከፋፍሎ በመገኘት የሚከተሉትን ስራዎች ከውኗል፦

  1. ሀሩን ሚዲያ በየአመቱ በረመዳን ወር የሚያዘጋጀው "ጀዛከላህ" ልዩ ፕሮግራም ዘንድሮም የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው ዕለት በአወሊያ መስጂድ ከሰላሳ አመት በላይ በኢማምነት ያገለለገሉትን ሼኽ ኡመርን ጀዛከላህ ብሏል።

2.ዳሽን ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት "ሸሪክ"ያስጀመረበትን ስድስተኛ አመት በዋና መስሪያ ቤቱ አክብሯል።ሀሩን ሚዲያ በመድረኩ የተገኘ ሲሆን ሙሉ ፕሮግራሙን ወደናንተ ያደርሳል።

3.የ1445ኛው አመተ ሂጅራ የረመዳን ወርን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ "የእንኳን አደረሳችሁ" መግለጫ በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ሆቴል ሰጥቷል።ሙሉ መግለጫውን የምናደርስ ይሆናል።

4.በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት አዘጋጅነት በሱማሌና በአፋር ክልሎች  መካከል  የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ የዕርቀ ሠላም ኮንፈረስ የመጀመሪያ ዙር ወይይት በሸራተን አዲስ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በስኬት መጠናቀቁ ተገልጿል።ዝርዝር መረጃውን የምናደርስ ይሆናል።

5.ኑር ኢስላሚክ ሴንተር የምስጋና እና አዲስ ፕሮጀክት የማብራሪያ መርሀግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እያካሄደ ነው። ሀሩን ሚዲያ በቦታው ተገኝቶ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ ይገኛል።

6.በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ አቦኪቾ ከተማ በኡስታዝ አቡሀይደር አማካኝነትና በሀጂ ሱልጣን ናስር አስተባባሪነ የተገነባው በታላቁ የሀላባው አሊም ሀጂ አህመዲን ሼህ ኡስማን ስም የተሰየመው መስጂድና መድረሳም ተመርቋል፣ በዚህም ዝግጅት ላይ የሀሩን ሚዲያ የደቡብ ስቱዲዮ የተገኘ ሲሆን ሙሉውን ፕሮግራም ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

  1. በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለከተማ ርቼ አካባቢ በመገኘት የአካባቢው ሙስሊሞች የመስጂድ ጥያቄን አስመልክቶ ልዩ ዘገባ ሰርተናል

8/ ባቡል ኸይር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ፓኬጅ አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል። ሙሉ መግለጫውን ሀሩን ሚዲያ ተከታትሏል።

9/ የ1445ኛው አመተ ሂጅራ የረመዳን ወርን አስመልክቶ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ "የእንኳን አደረሳችሁ" መግለጫ በዛሬው ዕለት አስተላልፏል። ሙሉ መግለጫውን የምናደርስ ይሆናል።

© ሀሩን ሚዲያ
___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j

1 month, 4 weeks ago
Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
2 months, 3 weeks ago
Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
2 months, 3 weeks ago

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

ተፈላጊ - ጋዜጠኛ

ብዛት - 2

የስራ ልምድ - 0 አመት

ጾታ - አይለይም

የስራ ቦታ - ጀሞ 3 ሰይድ ያሲን ህንጻ፣ የሀሩን ሚዲያ ስቱዲዮ

ሀሩን ሚዲያ ከዚህ በታች ያሉ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾችን ተቀብሎ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል።

1/ በጋዜጠኝነትና ተያያዥ የትምህርት ዘርፍ ለመስራት ተሰጥኦውና በመስኩም ለመስራት ፍላጎት ያለው

2/ ሚዲያው በሚያሰማራው ስራዎች ላይ ለመስራት ተነሳሽነት ያለው

3/ ፕሮግራም የማዘጋጀት፣ ቃለ መጠይቅ የማድረግና መድረክ የመምራት አቅሙና ዝግጁነቱ ያለው

4/ የስነ- ጹሁፍና የንግግር ክህሎት ያለው

እነዚህን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች በዚህ የቴሌግራም አድራሻ መልዕክት በማስቀመጥ መመዝገብና መወዳደር የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን፦

ኢሜል፦
Harunmedia09@gmail.com

ቴሌግራም፦
+1 (202) 931-8685

2 months, 4 weeks ago
Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
5 months ago
Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
5 months, 1 week ago

ሀሩን ሚዲያ በአዲስ እና ልዩ አቀራረብ፣ በአዳዲስ ተጨማሪ የዩቲዩብ ቻናሎች
....
በሶስት ስቱዲዮዎች ማለትም በዋሽንግተን ዲሲ በአዲስአበባ እና በሀላባ ስቱዲዮዎች የተለያዩ ስራዎችን ወደናንተ እያደረሰ የሚገኘው ሀሩን ሚዲያ እነሆ አሁን ደግሞ ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋፋት እና አዳዲስ ዝግጅቶችን በተለያዩ አማራጮች ወደናንተ ውድ ተመልካቾች ለማድረስ ተሰናድቷል። በዚህ መሰረትም ሶስት የዩቲዩብ ቻናሎችን ከፍቶ ፕሮግራሞችን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል።
...
1ኛ "ሀሩን ወቅታዊ" ሀሩን ሚዲያ ትኩረት አድርጎ በሚሰራበት ሙስሊም ማህበረሰብን የተመለከተ የሚቀርቡ የተለያዩ ወቅታዊ ዝግጅቶች ወደተመልካች የሚደርስበት አዲስ የዩቲዩብ ቻናላችን ነው።
2ኛ "ሀሩን ዳዕዋ" በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች እንዲሁም በባህር ማዶ በታላላቅ ዳኢዎች እና መሻይኾች የሚቀርቡ የዳዕዋ ፕሮግራሞች "በሀሩን ዳዕዋ "ወደተመልካች ይደርሳሉ።
3ኛ "ሀሩን ፕላስ" ከህፃናት እስከ አዋቂ እያዝናኑ ቁምነገር የሚያስጨብጡ የወጣቶችን ህይወት የሚዳስሱ እንድሁም ከስፖርት አለም ያሉ ኢስላማዊ ታሪኮች የሚዳስሱበትና የሚቀርቡበት አዲስ ሶስተኛው የሀሩን ሚዲያ የዩቲዩብ ቻናል ነው። እርሰዎም እንደተለመደው ሰብስክራይብ፣ ላይክ እና ሼር በማድረግ አጋርነታችሁን ትቀጥሉ ዘንድ አክብሮታዊ ግብዣችን ነው።
...
📌 ሀሩን ወቅታዊ ቻናል
https://www.youtube.com/channel/UCdqBrJIL5sm0XiDQzLRC-Og
📌 ሀሩን ፕላስ ቻናል
https://youtube.com/@HarunPlus

📌 ሀሩን ዳዕዋ
https://youtube.com/@HarunDaewa
©ሀሩን ሚዲያ

5 months, 1 week ago
6 months, 3 weeks ago

በሀላባ ቡርዓቲቾ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት 510 በማምጣት 2ኛ ደረጃ ላይ የቀመጠችው ኒቃብ ለባሿ ነጅዋ አብራር
....
ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ ጥቅምት 4/2016 ዓ/ል
...
ከሴት ተማሪዎች መካከል ከትምህርት ቤቱ 531 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገበችው ኢንቲሳር መመሀድ በመቀጠል ከሴቶች 510 በማምጣት 2ኛ ደረጃ ላይ የቀመጠችው ኒቃብስቷ ነጅዋ አብራር ስትሆን ኒቃብ አድርጋ በመማሯ ምንም አይነት ችግር እንዳልፈጠረባትና ኒቃብ የሚሸፍነው ውጫዊ የሰውነታችንን ክፍል እንጂ የምናስብበትን አዕምሮ አይሸፍንም በማለት አለባበሷ ትምህርቷ ላይ ምንም ተጽእኖ አለመፍጠሩን ገልጻልናለች ።
....
በኒቃባቸው ምክኒያትም ሴቶች ምንም አይነት ጫና ሊደርስባቸው አይገባም ስትል አጽዕኖት ሰጥታ ገልጻልናለች። እንዲሁም በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች ስላልቻሉ ብቻ ሳይሆን የመፈተኛ ቦታ ከተለመደው ቦታ ውጭ መሆኑ በቂ የስነ-ልቦና ዝግጅት ባለማድረጋቸው ነው ሲሉ የሀላባ ቡርዓቲቾ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ወደ ዩኒቨርሲቲ ያለፉ ተማሪዎች ለሀሩን ሚዲያ ገልጸዋል።
...
ተማሪዎቹ እንዳሉት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በማለፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባቸውን ማለፊያ ውጤት ያላመጡ ጓደኞቻቸው በመኖራቸው እንዳዘኑ የገለጹ ሲሆን ለዚህም ፈተናውን ላለማፋቸው ምክኒያት የመፈተኛ ቦታ ከተለመደው ቦታ ውጭ መሆኑ በቂ የስነ-ልቦና ዝግጅት ባለማድረጋቸው ነው ሲሉ ገልጸዋል።
...
ተማሪዎቹ እንዳሉት ከሆነ ወደ መፈተኛ ዩኒቨርስቲ በሄድንበት ወቅት ፈተናውን እናልፋለን እንወድቃለን በሚል በከባድ ፍራቻና ውጥረት ውስጥ ገብተን ነበር ብለዋል። ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ በሀላባ ቡርዓቲቾ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ት ቤት ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች እና ከትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ጋር ልዩ ቆይታ አድርጓል።

◾️ ሙሉ ፕሮግራሙ እንደደረሰን የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

© ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ

___
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 weeks ago