🇪🇹 ኢትዮ Students

Description
Our Bot :
@EthioExamBot

Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 Monat, 1 Woche her

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 Monat, 2 Wochen her

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 4 Wochen, 1 Tag her

2 weeks ago
**በስለት የተወጉት የኦርቶዶክስ ጳጳስ ጥቃት አድራሹን …

በስለት የተወጉት የኦርቶዶክስ ጳጳስ ጥቃት አድራሹን “ይቅርታ ብያለሁ” አሉ

ባለፈው ሰኞ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በቀጥታ በሚተላለፍ ሰብከት ላይ ሳሉ በስለት ጥቃት የደረሰባቸው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በፍጥነት እያገገሙ እንደሆነ ገልጸው ጥቃቱን እንዳደረሰ ለተጠረጠረው ግለሰብም ይቅርታ እንዳደረጉ ተናግረዋል።

ጳጳሱ በተቀረጸ ድምጽ ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡ እንዲረጋጋም ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ሳምንት በተፈጸመው ጥቃት አራት ሰዎች ተጎድተዋል። ፖሊስ ጥቃቱ ሃይማኖታዊ መነሻ ያለው የሽብር ድርጊት ነው ብሏል።

ከክስተቱ በኋላ ጳጳሱ በሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሁከት ተፈጥሯል። ጥቃቱን እንዳደረሰ የተጠረጠረ እና ራሱም የተጎዳው የ 16 ዓመት ታዳጊ በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም እስካሁን ክስ አልተመሰረተበትም። ባለስልጣናት የታዳጊውን እምነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ታዳጊው በአረብኛ ሲጮህ እና “ነብዩ” የሚልበትን ቪዲዮ የሀገሪቱ የስለላ ቢሮ እየመረመረው እንደሆነ የተቋሙ ኃላፊ ተናግረዋል። አራት ደቂቃ ርዝማኔ ባለው እና በቤተክርስትያኑ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው ድምጽ ላይ ጳጳሱ “ማንም ይሁን ማን” ይህንን ላደረገው ግለሰብ ይቅርታ አድርጌያለሁ ሲሉ ይደመጣሉ።

“እናም ለአንተ ሁልጊዜ እጸልያለሁ። ይህንን እንድታደርግ የላኩህ ማንም ይሁኑ ማን በኃያሉ ኢየሱስ ስም ይቅርታ አድርጌላቸዋለሁ” ብለዋል። “የክርስቶስን ተግባር እንድትፈጽሙ እፈልጋለሁ። ጌታችን ክርስቶስ እንድንጣላ በፍጹም አላስተማረንም። መጥፎ ስራ እንድንሰራ አላስተማረንም” ብለዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

2 weeks, 2 days ago
በአውስትራሊያ በቀጥታ ስርጭት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ …

በአውስትራሊያ በቀጥታ ስርጭት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ጳጳስን ጨምሮ አራት ሰዎች በስለት ተወጉ፡፡

በጩቤ ከተወጉት መካከል የአሶራውያን ኦርቶዶክስ ጳጳስ ብጹዕ ቢሾፕ ማር ማሪ ይገኙበታል፡፡

በዋክሌይ በሚገኘው የክርስቶስ በጎ እረኛ ቤተክርስቲያን ድንገተኛ ሁከት ከተከሰተ በኋላ ውጥረት ነግሷል ተብሏል፡፡

ክስተቱ የተፈጸመው በምዕራብ ሲድኒ ዋክሌይ በሚገኘው የክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ሲል Anadolu Agency ዘግቧል።

የጥቃቱ ዝርዝር ሁኔታ እስካሁን አልተረጋገጠም ያለው ፖሊስ ነገር ግን ብቻውን እንደፈፀመ የሚታመንበት ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል ሲል አስታውቋል። (ቪዲዮው ከላይ ተያይዟል)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

2 weeks, 6 days ago

**በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ ፖሊሶች ቆሰሉ

👉🏼 ተጨማሪ ሌላ አንድ መንገደኛ ግለሰብም ተገድሏል**

በዛሬዉ እለት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ ሰዎች ዉስጥ ሁለቱ ሲገደሉ ሌላኛዉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የአዲስአበባ ፖሊስ ፤ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት ሰዎች በአዲስአበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን ተኩስ ከፍተዋል ብሏል።

ግለሰቦቹ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም  ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል ብሏል ፖሊስ፡፡

ሌላዉ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ተመልክቷል፡፡ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸዉንም ፖሊስ አረጋግጧል።

ሌላዉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ታጣቂዎቹ  በመኪናቸው እንዲጭኗቸው  ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በታጣቂዎቹ ተገድለዋል ሲል ፖሊስ ወንጅሏል፡፡  አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ  ጨምሮ ገልጿል ፡፡

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

2 months, 1 week ago

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው ገለፀ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል። አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ ያለው ባንኩ ለተፈጠረው…

2 months, 1 week ago

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው ገለፀ

በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ ያለው ባንኩ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

2 months, 1 week ago
ኢየሱስ ወደ ኢትዮጲያ መልዕክት ልኳል፦ Pastor …

ኢየሱስ ወደ ኢትዮጲያ መልዕክት ልኳል፦ Pastor Tee

👉 አንድ ዓመት ብቻ ነው የቀራቹም ብሏል

የጌታ ታናሽ ወንድም ነኝ ,እናቴ ማርያም ናት አባቴ ዮሴፍ ነው ሲል የሰነበተው ኬንያዊ ናይሮቢ እና ዋንጅራ ከተሰኙት ሁለት የኬንያ ከተሞች ተልዕኮዬን ጨርሼ አዲስ አበባ ልመጣ ነውም ብሏል

ይህ ኬንያዊ ከኢየሱስ ለኢትዮጲያዊያን መልዕክት ይዤያለው ያለ ሲሆን ፤ይህንንም መልዕክት በቀጣይ ወር ይዞ እንደሚቀርብና እስከዛው ግን ምዕመኑ ፀሎት እንዲያደርግ አሳስባለው ሲል በx ገፁ አጋርቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ማለትም 2025 ማርች ወር ላይ ወደ ዓለም እንደሚመጣ'ና የዓለም ፍፃሜም እንደሚያደርግ
ገልጿል።

ከዚያህ በፊት ግን አንድ ዓመት ብቻ ለቀራቸው ሀበሾች መልዕክት አድርስ ተብያለው ብሏል።
🤔🤔

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months, 2 weeks ago
🇪🇹 ኢትዮ Students
4 months, 2 weeks ago
***‼️******❌******❌******❌******‼️***

‼️‼️
ኢትዮጵያ🇪🇹በቅርቡ ግብረሰዶማዊነት፣የጾታ መቀየር፣ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የቀረበን ሰነድ
ፈርማለች። 😭
ይህም ሰነድ በዚህ አንድ ወር
ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ይጠበቃል።🤯
ለዚህም መቃወሚያ Petition በትንሹ 50,000 ፊርማዎችን ለማሰባሰብ በዚህ Link እንሳተፍ።🇪🇹Say NO!!
ታሪክ የማይረሳውንና  እስከትውልድ ጥግ  በመልካሞቹ የሚዘከረውን ይህን movement በደስታ ተቀላቀሉ!!!

ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት በቀላሉ መፈረም ትችላላችሁ

🛑Petition ለመፈረም
https://keap.page/gq193/.html

🛑Tiktok
https://vm.tiktok.com/ZM66xSPCn/

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months, 2 weeks ago

ብሔራዊ ሎተሪ የ8 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እድለኛ እንደጠፋበት ገለጸ

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር በየጊዜው ለሽፓጭ ከሚያውላቸው የእድል ሎተሪዎች መካከል የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንዱ ነው።

20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ይህ እጣ ባሳለፍነው ጷግሜ 2015 ዓም እጣው የወጣ ሲሆን 1820259 ደግሞ የመጀመሪያ እድለኛ ቁጥር እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ንዋይ ለዓልዐይን እንዳሉት "ባሳለፍነው ጷግሜ ላይ ከወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከሶስት እጣ አሸናፊ በስተቀር የሁለት እጣ አሸናፊዎች እስካሁን አልመጡም" ብለዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months, 3 weeks ago

💰የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ100 ሺህ ዶላር ሊመነዘር እንደሚችል ተገለጸ፡፡ 💰

በፈረንጆቹ 2009 ላይ ጃፓናዊው ሶታሺ ናካሞቶ እንደተፈጠረ የሚታመነው ቢቲኮይን የተሰኘው የድጅታል መገበያያ ገንዘብ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

ይህ መገበያያ ገንዘብ ዋጋው በየጊዜው ከፍ እና ዝቅ ሲል የቆየ ሲሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዋጋው ዝቅተኛ ምንዛሬን አስመዝግቦ ነበር።

ይሁንና በዓለም ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት እያጋጠመ ባለው የዋጋ ግሽበት እና ሌሎች የኢኮኖሚ ችግሮች ምክንያት የቢትኮይን ዋጋ እየጨመረ እንዲመጣ ማድረጉ ተገልጿል።

እንደ ሲኤንቢሲ ዘገባ ከሆነ የዓለም ምናባዊ ወይም ክሊፕቶከረንሲ መገበያያ ገንዘብ ከዓመታት በኋላ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

በዚህ ምክንያት አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን በ44 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም ከዓመታት በኋላ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል። (AlAin)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 Monat, 1 Woche her

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 Monat, 2 Wochen her

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 4 Wochen, 1 Tag her