Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

🇪🇹 ኢትዮ Students

Description
Our Bot :
@EthioExamBot

Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 3 weeks, 4 days ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 2 weeks, 3 days ago

1 month, 4 weeks ago

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው ገለፀ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል። አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ ያለው ባንኩ ለተፈጠረው…

1 month, 4 weeks ago

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው ገለፀ

በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ ያለው ባንኩ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

2 months ago
ኢየሱስ ወደ ኢትዮጲያ መልዕክት ልኳል፦ Pastor …

ኢየሱስ ወደ ኢትዮጲያ መልዕክት ልኳል፦ Pastor Tee

👉 አንድ ዓመት ብቻ ነው የቀራቹም ብሏል

የጌታ ታናሽ ወንድም ነኝ ,እናቴ ማርያም ናት አባቴ ዮሴፍ ነው ሲል የሰነበተው ኬንያዊ ናይሮቢ እና ዋንጅራ ከተሰኙት ሁለት የኬንያ ከተሞች ተልዕኮዬን ጨርሼ አዲስ አበባ ልመጣ ነውም ብሏል

ይህ ኬንያዊ ከኢየሱስ ለኢትዮጲያዊያን መልዕክት ይዤያለው ያለ ሲሆን ፤ይህንንም መልዕክት በቀጣይ ወር ይዞ እንደሚቀርብና እስከዛው ግን ምዕመኑ ፀሎት እንዲያደርግ አሳስባለው ሲል በx ገፁ አጋርቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ማለትም 2025 ማርች ወር ላይ ወደ ዓለም እንደሚመጣ'ና የዓለም ፍፃሜም እንደሚያደርግ
ገልጿል።

ከዚያህ በፊት ግን አንድ ዓመት ብቻ ለቀራቸው ሀበሾች መልዕክት አድርስ ተብያለው ብሏል።
🤔🤔

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months ago
🇪🇹 ኢትዮ Students
4 months ago
***‼️******❌******❌******❌******‼️***

‼️‼️
ኢትዮጵያ🇪🇹በቅርቡ ግብረሰዶማዊነት፣የጾታ መቀየር፣ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የቀረበን ሰነድ
ፈርማለች። 😭
ይህም ሰነድ በዚህ አንድ ወር
ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ይጠበቃል።🤯
ለዚህም መቃወሚያ Petition በትንሹ 50,000 ፊርማዎችን ለማሰባሰብ በዚህ Link እንሳተፍ።🇪🇹Say NO!!
ታሪክ የማይረሳውንና  እስከትውልድ ጥግ  በመልካሞቹ የሚዘከረውን ይህን movement በደስታ ተቀላቀሉ!!!

ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት በቀላሉ መፈረም ትችላላችሁ

🛑Petition ለመፈረም
https://keap.page/gq193/.html

🛑Tiktok
https://vm.tiktok.com/ZM66xSPCn/

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months, 1 week ago

ብሔራዊ ሎተሪ የ8 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እድለኛ እንደጠፋበት ገለጸ

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር በየጊዜው ለሽፓጭ ከሚያውላቸው የእድል ሎተሪዎች መካከል የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንዱ ነው።

20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ይህ እጣ ባሳለፍነው ጷግሜ 2015 ዓም እጣው የወጣ ሲሆን 1820259 ደግሞ የመጀመሪያ እድለኛ ቁጥር እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ንዋይ ለዓልዐይን እንዳሉት "ባሳለፍነው ጷግሜ ላይ ከወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከሶስት እጣ አሸናፊ በስተቀር የሁለት እጣ አሸናፊዎች እስካሁን አልመጡም" ብለዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months, 1 week ago

💰የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ100 ሺህ ዶላር ሊመነዘር እንደሚችል ተገለጸ፡፡ 💰

በፈረንጆቹ 2009 ላይ ጃፓናዊው ሶታሺ ናካሞቶ እንደተፈጠረ የሚታመነው ቢቲኮይን የተሰኘው የድጅታል መገበያያ ገንዘብ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

ይህ መገበያያ ገንዘብ ዋጋው በየጊዜው ከፍ እና ዝቅ ሲል የቆየ ሲሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዋጋው ዝቅተኛ ምንዛሬን አስመዝግቦ ነበር።

ይሁንና በዓለም ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት እያጋጠመ ባለው የዋጋ ግሽበት እና ሌሎች የኢኮኖሚ ችግሮች ምክንያት የቢትኮይን ዋጋ እየጨመረ እንዲመጣ ማድረጉ ተገልጿል።

እንደ ሲኤንቢሲ ዘገባ ከሆነ የዓለም ምናባዊ ወይም ክሊፕቶከረንሲ መገበያያ ገንዘብ ከዓመታት በኋላ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

በዚህ ምክንያት አሁን ላይ አንድ ቢትኮይን በ44 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም ከዓመታት በኋላ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል። (AlAin)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months, 1 week ago

#ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ :-
• የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

• የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

🌐Website: https://placement.ethernet.edu.et 
✈️Telegram : https://t.me/moestudentbot

ትምህርት ሚኒስቴር

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months, 2 weeks ago

የ16 አመት ታዳጊ በማገት 2 ሚሊዮን ዶላር ጠይቀው ስላልተከፈላቸው ግድያ የፈፀሙ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

<hr>

በሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክፍለ ከተማ መልካ ገፈርሳ ወረዳ ሳብር ሬዲዋን የተባለ የ16 ዓመት ታዳጊን በማገት  ገንዘብ ጠይቀው ስላልተከፈላቸው ያገቱትን ታዳጊ የገደሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

ስለ ጉዳዩ የፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር ብርሃኔ ሁንዴሳ እንደተናገሩት  ህዳር 2 ቀን 2016 ዓ. ም ከቀኑ 11:00 ላይ የታዳጊው አባት የወንድም ልጅ ከጓደኛው ጋር ሞተር ይዘዉ በመምጣት በሞተር እንሂድ  ማለታቸውንና ታዳጊው በጣም ጠንቃቃ ስለነበር በሞተር ሂጄ ስለማላወቅ አልሄድም እንዳላቸው  በመግለፅ ነገር ግን የታዳጊው አባት የወንድም ልጅ ጓደኛውን አንተ ሂድ በቃ እኔ ይዤዉ እመጣለሁ በማለት ተያይዘዉ ወደ ቡራዩ ክፍለ ከተማ መልካ ገፈርሳ በ20 ሽህ ብር ወደ ተከራዩበት ቤት ይዞት መሄዱን ጠቁመዋል።

ቤቱ ውስጥ ከገባ በኋላ ታዳጊውን ከወሰዱት በኋላ ማጅራቱን በመምታት መሬት ላይ በመጣል አፉን በፕላስተር  እጁንም ወደኋላ በማሰር የምንጠይቀዉን ገንዘብ ካልተከፈልን እንገልሃለን ማለታቸውን የገለፀው ፖሊስ ታዳጊዉ አትግደሉኝ አባቴን ጠይቁት ገንዘብ ይሰጣችኋል ማለቱንም ጠቁሟል።

ተጠርጣሪዎቹ 11:45 ላይ ወደ ታዳጊው አባት በመደዎል ልጁን እንዳገቱትና 2 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውንና  የታዳጊው አባት ይህን ያህል ገንዘብ የለኝም 500 መቶ ሺህ ልከፈላችሁ በማለት ለመደራደር ይሞክራሉ።

አጋቾቹ ግለሰቦች በድጋሚ  ህዳር 3 ቀን ዳግመኛ ይደዉሉና እንዲከፍሉ ይጠይቃሉ ፣አባትም የለኝም በቃ 1 ሚሊየን ብር ልክፈል ሲላቸዉ እኛ የጠየቅነዉን ገንዘብ ካልተከፈለን ልጁን በህይወቴ አያገኙትም ብለዉ ዝተዉ  ስልኩን ይዘጉታል።

ተጠርጣሪዎቹ ገንዘብ እንደማያገኙና ጉዳዩም ለፖሊስ ሪፖርት ይደረጋል ብለዉ ስለፈሩ ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም ታዳጊውን ደብድበው መግደላቸውንና ስልካቸውን ማጥፋታቸውን የገለፀው ፖሊስ ስልክ መዝጋታቸዉን በመጠራጠር ቤተሰቦቹ ጉዳዩን ለፖሊስ እንዳመለከቱና ፖሊስም በደረሰዉ ጥቆማ መሰረት ክትትል ሲጀምር አንደኛዉ ተጠርጣሪ መልካ ገፈርሳ አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉንግለሰቡም ምርመራ ሲደረግበት ጓደኛዉም ወደ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እንደሄደ መረጃ ይሰጣል።

ፖሊስም ከጉራጌ ዞን ፖሊስ ሚስጥራዊ ግንኙነት በማድረግ ሁለተኛዉን ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር እንዳዋለዉ የቡራዩ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር ብርሃኔ ሁንዴሳ ተናግረዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

4 months, 2 weeks ago

🇨🇦 ካናዳ በቀጣዩ የፈረንጆቹ አመት  50,000 ኢትዮጵያንን  ወደ ሀገሯ ለስራ ለትወስድ ትችላለች 🛫🛫

ፊደል ፖስት   ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው  ሰዎች የሰማው መረጃ ይሄን ይመስላል;

እነማን ነው የሚሂዱት?

ዘጠኝ ሙያዎች የተለዩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ፣ የምግብ ምርት  ማምረትና ማቀነባበር እና ማሸግ፣  አናጢነት ፣ የኤሌትሪክ ባለሙያ ፣ ነርሲንግ ፣ የኤርፖርት አስተናጋጅ ፣  ኮምፒዊተር ሳይንስ እና አይቲ  የሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚፈለጉ ይሆናል።

ለመሄድ ምን ያስፈልጋል ?

በነዚህ ሙያዎች የሰለጠነ ባለሙያ   በኦንላየን እና  በአካል  ፈተና እዚሁ ኢትዮጰያ ውስጥ  ይፈተንና  ፈተናውን ካለፈ / ች  ካናዳ ካሉት ከቀጣሪ ድርጅቶቹ ጋር ወደ ሚያገናኙት፣ የፓስፖርትና አስፈላጊ ፎርም  ወደ ሚሞሉለት የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር ተልኮ  የጉዞው ሂደት ተጀምሮለት በአጭር ጊዜ ይሄዳል።

መቼ ይጀመራል?

የወረቀት ስራዎች የተጀመሩ ሲሆን በቅርቡ በኢትዮጵያና በካናዳ መንግስት በኩል  የሰለጠነ ባለሙያ ወደ ካናዳ በመላክ ጉዳይ ላይ  የመግባቢያ ሰነድ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።

በካናዳ ያለው  Ministry of Labour, Training and Skills Development,  የኢሚግሪሽን  ቢሮ እና የካናዳ መንግስት   በጉዳዩ ላይ ማብሪሪያ ተሰጥቷቸው ጉዳዩንም አምነውበታል። 

በኢትዮጵያ በኩል  የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር  ስራውን ተግባራዊ ለማድረግ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ጋር እየሰራ ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 3 weeks, 4 days ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 2 weeks, 3 days ago