🇪🇹 ኢትዮ Students

Description
Our Bot :
@EthioExamBot

Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months ago

2 weeks ago
🇪🇹 ኢትዮ Students
2 weeks ago
[#Update](?q=%23Update)

#Update

🚨 “ ግብረሰዶም ወደ ሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል” -  በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ

**➡️ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር**

ኑሮን ለማሻል በሚል ወደ ታይላንድ የሄዱና በኃላም ወደ ማይናማር የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን በጋንግስተሮች እጅ ወድቀው ከውላቸው ውጪ  ህገወጥ የዶላር ማጭበርበር ሥራ ለመስራት እንደተገደዱ ቤተሰቦቻቸው ጭምር መግለጻቸው ይታወሳል።

የታጋቾቹ ወላጆች ያቋቋሙት ኮሚቴም፣ “ ልጆቻቸን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርል ” ሲል በቅርቡ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ማሳሰቡ አይዘነጋም።

በወቅቱ ምላሽ የጠየቅነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ፣ ቶኪዮ ባለው ኤምባሲ አማካኝነት ንግግር እየተደገ መሆኑን ገልጾ፣ “ ልጆቹ የማይናማር መንግስት የሚቆጣጠረው ቦታ ላይ አይደለም ያሉት ለዛ ነው ችግሩ እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ” ብሎ ነበር።

የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
የኢትዮጵያዊያኑ ወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ግብረሰዶም ወደሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል ” ሲል ገልጿል።

ኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?

*“ ልጆቻችን ገና አልወጡም። ወደ ሦስት ሀገራት ዜጎቻቸውን አስወጥተዋል። የ18 የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ልጆች ናቸው እየተሰቃዩ ያሉት።

ሦስቱ ሀገራት ከእነዛ ጋንግስተር ቡድን ተነጋግረው አቅጣጫዎችን አስቀምጠው የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለው ነው ልጆቻቸውን ያስወጧቸው። 

በአጋጣሚ ከወጡት ከፊሊፒን ዜጎች ወክሎ ሲንቀሳቀስ የነበረን ሰው አድራሻ አግኝተን (የታይላንድ ፓሊስ ኮማንደር ነው) በምን አይነት ሁኔታ ልጆቻቸውን እንዳስወጡ ኮንታክት እያደረግን ነበር። ያንን ኢንፎርሜሽን ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመስጠት ሞክረናል።

ሌሎች ዜጎች ስለወጡ በአሁኑ ወቅት ልጆቻችን ብቻቸውን በግላጭ ስለቀሩ ስቃዩ በርትቷል። ጭራሽ እንዲያውም በግብረሰዶም ወደምታትታወቀው ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል። ፈጣሪ ይጠብቅልን እንጂ።

እጅ በእጅ ነው ልጆቹን አስተላልፈው የሚሸጡትና ይሄ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ስለሆነ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ትኩረት በመስጠት ልጆቻችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሌሎችንም ሀገራት ወዳሉበት ቀርቦ በተለይ ከታይላንድ መንግስት ጋር ተነጋግሮ መፍትሄ ይስጠን።

ማይናማርን ማነጋገር እንዳለ ሆኖ የታንላንድን መንግስት ማነጋገር ለሁለት ነገር ይጠቅማል። ለክፍያ የሚጠይቁትን ገንዘብ በማስቀረት እንዳይታሰሩ ለማድረግና ካሉበት መከራ እንዲወጡ ለማድረግ።

ከጋንግስተሮቹ ጋር ቀረቤታ አለው ተብሎ ነው የሚታሰበው የታይላንድ መንግስት። ሌሎች ሀገራትም ይህንኑ ሲስተም ነው የተጠቀሙት የኢትዮጵያ መንግስትም ይህን መንገድ ተጠቅሞ ልጆቹ የሚወጡበትን መንገድ እንዲያመቻች በአጽንኦት እንጠይቃለን”* ሲል አሳስቧል።

ወደ 111 ወላጆች ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለአንድ አመት ተመላልሰው መፍትሄ ባለማግኘታቸው ትላንት ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባነር ይዘው ከሚኒስትሮች መፍሄ እንደጠየቁ፣ ሚኒስቴሩም ከኢትዮጵያ ሰዎችን ለመላክ እንደተወሰነና በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ቃል እንደገባ ኮሚቴው አስረድቷል።

ምን አዲስ ነገር አለ? ጉዳዩ ከምን ደረሰ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ “አዲስ መረጃ ካለ አጋራለሁ” ብሏል። (ጉዳዩን እስከመጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

2 weeks, 2 days ago

" የዘንድሮው ቅዝቃዜ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጠንከር ያለ ነው " - ባለሙያዎች

አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ አብዛኛው ስፍራዎች ሰሞኑን የተከሰተው ጠንከር ያለ ብርድ ከዚህ ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ እየተዳከመ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

" ዘንድሮ ህዳር መጨረሻ አከባቢ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ነው ያለው፡፡ አሁን ደግሞ ያለንበት ታህሳስ ወር በጣም የባሰበት ቅዝቃዜ እያስተዋልን ነው " ብለዋል አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ።

አዲስ አበባ ውስጥ በተለይ ካለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ አሁን እስካለንበት ታህሳስ ወር ከተለመደውም ጠንከር ያለ ከፍተኛ ብርድ ተስተውሏል፡፡

በኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ከጥቅምት እስከ ጥር ወራት ያሉትን የሚሸፍነው አሁን የምንገኝበት በጋ ተብሎ የሚጠቀሰው ወቅት ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች ደረቅና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋልበት ነው ብለዋል።

" ይህ ወቅት ለአብዛኛው የአገራችን አከባቢዎች፤ ለአብነትም ለትግራይ፣ አፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አብኛው የኦሮሚያ እና ማዕከላዊና ምስራቃዊ የኢትዮጵያ አከባቢዎች በዚህ በበጋ ወቅት የበጋ ደረቃማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታዎች የሚያመዝንበት ወቅት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ዘንድሮ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ አከባቢዎች ከባለፈው ዓመት እንኳ ሲነጻጸር ጠንከር ያለ የማለዳ ቅዝቃዜ አሁን መስተዋሉን አንስተዋል፡፡

" በተለይም አዲስ አበባን ከባለፈው በጋ 2016 ዓ/ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር አነጻጽረን ስንመለከተው የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ10 ወደ 6.6 ድግሪ ሴንትግሬድ ዝቅ ብሎ ተመልክተናል " ብለዋል።

ይህ ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ ወር አጋማሽ ድረስ እንደሚቀጥልና ከታህሳስ 13 በኋላ ግን የቅዝቃዜ መጠኑ እየተዳከመ እንደሚሄድ አስረድተዋል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS

3 months ago
በአሜሪካ ኒዮርክ የአይጦችን ቁጥር ለመቀንሰ የእርግዝና …

በአሜሪካ ኒዮርክ የአይጦችን ቁጥር ለመቀንሰ የእርግዝና መከላከያ እንክብል ሊስጣቸው ነው

አይጦቹን ቁጥር ለመቀነስ በመርዝ መግደል ቢታሰብም ከእንሰሳት መብት ጋር አብሮ የሚሄድ ስላልሆነ በእርግዝና መከላከያ እንክብሉ ቁጥራቸውን ለመቀነስ መታቀዱን ተነግሯል::

በኒዮርክ ከ3 ሚልየን በላይ አይጦች አሉ::

3 months ago
**የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ እስራኤል …

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ እስራኤል ለኢራን ጥቃት ምላሽ ከሰጠች "አስከፊ ጥቃት" እንደሚደርስባት አስጠንቅቋል

3 months ago
**እስራኤላውያን የኢራንን ጥቃት በመስጋት ቤት የተሸሸጉ …

**እስራኤላውያን የኢራንን ጥቃት በመስጋት ቤት የተሸሸጉ ሰዎች  ለቀው እንዲወጡ ተፈቅዶላቸዋል።ከእንግዲህ ኢራን ስጋት አይደለችም  - ወታደራዊ ቃለ አቀባይ

ሀገሪቱ የአየር ክልሏንም ከፍታለች።**

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months ago