Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

مدرسة الإصلاح (አል ኢስላሕ መድረሳ)

Description
ይህ ቻናል ከፉሪ ሕይወት ፋና ወደ ዑመር ኢብኑ ዓብዱልዐዚዝ መስጂድ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ኑሪ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የአል ኢስላሕ መድረሳ ኦፊሺያል የቴሌግራም ቻናል ነው። በአላህ ፍቃድ በመድረሳው የሚሰጡና በተለያዩ የሰለፊያህ ዱዓቶች፣ ኡስታዞችና መሻኢኾች የሚተላለፉ መልዕክቶች (በድምፅም ይሁን በፅሑፍ) ይተላለፉበታል።
https://t.me/medresetulislah
We recommend to visit

Books only!

This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !

Join and share @Books_worldd

አስተያየት @BooksWorlddd_bot !

@books_worlddd መወያያ ግሩፕ

#share

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Last updated 3 months, 1 week ago

Last updated 1 year, 4 months ago

1 month, 1 week ago

ጉድ እኮ ነው! የሸይኽ አብድልሀሚድ ቢን ያሲን አልለተሚይ የዛሬ ቀን 7/07/16 ከዝሁር በኋላ በበድረዲን መስጂድ ያደረጉት ዳዕዋ ለሙመይዓዎችና ለኢህዋኖች ባይመቻቸውም ህዝቡ ግን ከዚህ በፊት ዳዕዋ ተደርጎ የማይታወቅ በሚመስል መልኩ ተገርሞና አፋን ከፍቶ ሲሰማ ነበር። 🪐 በህዝቡ አዕምሮ ላይ የሆነች ነገር ቀረፀው የሄዱ ይመስላል ለዚህም መጨረሻ ላይ ህዝቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሁነው ነበር። ረጅም እድሜ…

1 month, 1 week ago

አስደሳች ዜና 🎤🎤 ታላቅ የሙሓዶራ ፕሮግራም 🎤🎤    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ነገ እሑድ ረመዳን 07 1445 ዓ.ሂ በቀን 08/07/2016 ታላቅ የሙሓዶራ ፕሮግራም በአል-ኢስላሕ መድረሳ  ከወትሮው ለየት ባለና ባማረ ሁኔታ ስለተዘጋጀ ይህ እድል እንዳያመልጠዎት ስንል እርሰዎን  ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር  በአክብሮት ጋብዘንዎታል። 🪑 ተጋባዥ እንግዶች፡-       ▬▬▬▬▬▬▬ 1️⃣ኛ. ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ…

1 month, 1 week ago

👉 በዱዓእ ላይ ድንበር ማለፍን የሚዳስስና ጠቃሚ ጥቆማዎችና ማስጠንቀቂያዎች ያሉበት ድንቅ ኪታብ ነው።

👉 ዱዓእ ዒባዳ እንደመሆኑ ማጠን ተውቂፊይ ስለሆነ በቁርኣን ላይ በተገለፁትና ከነቢዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በተገኙት ላይ መገደብ ያስፈልጋል።

👉 ዐረብኛ በደንብ የምትረዱ ብታነቡት በአላህ ፈቃድ በጣም ትጠቀሙበታላችሁ።
* የኪታቡ ፀሐፊ ዶ/ር ሸይኽ ሙሐመድ ቢን አሕመድ አልፊፊ ናቸው።*

https://t.me/medresetulislah

1 month, 2 weeks ago

🚫 ሙአዚኖች አላህን ፍሩ

ኢስላም ለኢማምና ሙአዚን ትልቅ አክብሮት ችሯል ። የሙአዚን ሚናው ከተሸከመው ሀላፊነት አንፃር ከባድ ነው ። እንዳጠቃላይ የሙስሊሞች ሶላት በተመይ ዑዝር ኖሯቸው እቤት የሚሰግዱ ሰዎች ፣ የሴቶች ፣ ሶላት በሙአዚኑ ጫንቃ ላይ የወደቀ ነው ።
የረመዳን ወር ፆም መያዣና መፍቻም በሙአዚኑ ጫንቃ ላይ ነው ። ሙአዚን እንዲህ አይነት ሀላፊነት የተሸከመ ሲሆን አብዛኞቹ የኛ ሀገር ሙአዚኖች አዛን ማለት ትርጉሙም ሆነ አላማው የገባቸው አይመስልም ። አንዳንዱ ከ15 ደቂቃ በፊት ሌላው ሌላው ከ20 ደቂቃ በኋላ አዛን ያደርጋሉ ። ይህ ማለት ሰዎች ያለ ሳአቱ እንዲሰግዱ እንዲያፈጥሩ ያደርጋል ።
ሶላታቸው ውድቅ የሆነባቸውና ፆማቸው የተበላሸባቸው ሰዎች ወንጀል እነርሱ ላይ ነው የሚሆነው ። በመሆኑም ሙአዚኖች አላህን ፈርተው አዛንን በጊዜው በማለት የሙስሊሞችን ዒባዳ ጠብቀው በአዛን የሚገኘውን ምንዳ እንዲያገኙ ማድረግ አለባቸው ። የየመስጂዱ ኮሚቴዎች ሙአዚኖችን በማስታወስና ወቅቱን ጠብቀው አዛን እንዲያደርጉ በማድረግ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል እላለሁ ።
አላህ በመልካም ከሚተዋወሱት ያድርገን ።

http://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***🚫*** ሙአዚኖች አላህን ፍሩ
1 month, 2 weeks ago

🟢ጨረቃ ታየች
‏عاجل:

‏رؤية هلال رمضان في سدير..
‏وغدا الإثنين أول أيام رمضان بالسعودية.
በሱኡዲያ እና ተመሳሳይ ሀገሮች ነገ ሰኞ የመጀመሪያው የረመዳን ቀን ይሆናል።
ኢን ሻእ አላህ።
https://t.me/Abuhemewiya

1 month, 3 weeks ago

🟦 የፆም ትርጉሙና ህግጋቱ
❴በጉራጊኛ ቋንቋ❵

👉 የካቲት 24/2016 በእነሞር ወረዳ ጎንደሬጨ ቀበሌ ቢላል መስጂድ ላይ የፆም ትርጉሙና ህግጋቱ በሚል ርእስ በጉራጊኛ ቋንቋ የተደረገ ሙሓደራ በቁጥር ሁለት ቻናል ላይ ተለቋል ቋንቋውን ለሚችሉ በማድረስ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።

🎙 የድምፅ ፋይሉን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka2/96

Telegram

Bahiru teka 2

5 months, 2 weeks ago

👉   የሐቅና ባጢል ትግል መጨረሻው

      ስራው ረቂቅ የሆነው አምላካች ይህን ፍጥረተ – ዐለም እሱ በሻውና ሒክማው ባስፈረደው መልኩ እንዲጓዝ አድርጎታል ። ሒክማው ካስፈረደውና የፍጥረተ – ዐለሙ ጉዞ ሚስጢር ከሆነው ስራው አንዱ የሐቅና ባጢል ትግል ነው ። ከዚህ ውስጥ ቁርኣን ትኩረት ሰጥቶ የዳሰሰውና ለአማኞች በሚገጥማቸው ፈተና ሁሉ ፅናት እንዲኖራቸውና የመጨረሻው ድል የእነርሱ እንደሆነ የተስፋ ብርሀን እንዲፈነጥቅላቸው የሚያደርገው በነብያቶችና በተከታዮቻቸው እንዲሁም በባጢል ሀይሎችና በሐቅ ሰዎች መካከል ያለው ትግል ነው ።
     ይህን አስመልክቶ አላህ የዚህ አይነቱ ትግል የሱ ጥበብ ያስፈረደውና ፍጥረተ – ዐለሙ የሚጓዝበት መስመር መሆኑና ማንም እንደማይቀይረው ሲነግረን እንዲህ ይለናል : –

« سُنَّةَ مَن قَدْ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ مِن رُّسُلِنَا ۖ وَلَا تَجِدُ لِسُنَّتِنَا تَحْوِيلًا »
               الإسراء  ( 77)
" ከመልክተኞቻችን ካንተ በፊት በእርግጥ እንደላክናቸው ሰዎች ልማድ ብጤ (ይጠፉ ነበር) ፡፡ ለልማዳችንም መለወጥን አታገኝም ፡፡"

    ይህ አላህ ለነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ሙሽሪኩል ዐረብ ከሀገር ሊያስወጡዋቸው ያሴሩ በነበረ ጊዜ ከዛ በፊት የነበሩትም ነብያት ህዝቦች ነብያቶችን ለማስወጣት እንደሞከሩና አላህ ያጠፋቸው መሆኑን ያመላከተበት አንቀፅ ነው ።
     በመሆኑም የመልእክተኞችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም የባጢል ሀይሎች ትግል አዛ በማድረግ ጀምሮ በትችት ስድብና ድብደባ ተሻግሮ ወደ መግደል ካልሆነ ከሀገር ማባረር መሆኑን በተለያዩ የቁርኣን አንቀፆች ተወስቷል ። ከዚህ ውስጥ በፊርዓውንና በነብዩላሂ ሙሳ መካከል ስለነበረው ትግል አላህ ሲነግረን እንዲህ ይለናል : –
« فَأَرَادَ أَن يَسْتَفِزَّهُم مِّنَ الْأَرْضِ فَأَغْرَقْنَاهُ وَمَن مَّعَهُ جَمِيعًا »
                 الإسراء   ( 103 )
" ከምድርም ሊቀሰቅሳቸው አሰበ ፡፡ እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ሰዎች ሁሉንም አሰጠምናቸው ፡፡"
      ፊርዓውን በኒ ኢስራኢሎች የመከራና ግፍ መጨረሻ የደረሰ ስቃይ ካደረሰባቸው በኋላ ይህ አልበቃ ብሎት ነብዩላሂ ሙሳን ከሀገር ሊያስወጣቸው በፈለገ ጊዜ የደረሰበትን ውድቀት ነው አላህ የነገረን ። 
    ሙሽሪኩል ዐረብ በነብዩና በተከታዮቻቸው ላይ የሚችሉትን ሁሉ መከራ ካደረሱና ስቃይ ካቀመሱዋቸው በኋላ በተለያየ መንገድ ነብዩን ለመግደል ቢያስቡም ሳይሳካላቸው ሲቀር ከሀገር ለማስወጣት ማሰባቸውን አላህ በሚቀጥለው አንቀፅ ይነግረናል : –

« وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ ۚ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ اللَّهُ ۖ وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ »
               الأنفال ( 30 )
" እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ይመክራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፡፡ አላህም ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው ፡፡"
      በሌላ የቁርኣን አንቀፅም እንዲህ ይለናል : –
" وَإِن كَادُوا لَيَسْتَفِزُّونَكَ مِنَ الْأَرْضِ لِيُخْرِجُوكَ مِنْهَا ۖ وَإِذًا لَّا يَلْبَثُونَ خِلَافَكَ إِلَّا قَلِيلًا "
                   الإسراء   ( 77 )

" ከምድሪቱም (ከዓረብ ምድር) ከርሷ ያወጡህ ዘንድ ሊያሸብሩህ በእርግጥ ተቃረቡ ፡፡ ያን ጊዜም ከአንተ በኋላ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር ፡፡"

ይህ የአላህና የነብያት እንዲሁም የአማኞች ጠላቶች የአላህ መልእክተኛችንና አማኞችን ከሀገር የማስወጣት አዛቤ ከመጀመሪያዎች ነብያት አመፀኛ ህዝቦች ጀምሮ የመጣ ነው ። ይህንንም አላህ ሲነግረን እንዲህ ይለናል : –

« وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِرُسُلِهِمْ لَنُخْرِجَنَّكُم مِّنْ أَرْضِنَا أَوْ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَا ۖ فَأَوْحَىٰ إِلَيْهِمْ رَبُّهُمْ لَنُهْلِكَنَّ الظَّالِمِينَ »
             سورة إبراهيم  ( 13 )

" እነዚያም የካዱት ለመልክተኞቻቸው «ከምድራችን በእርግጥ እናወጣችኋለን ፤ ወይም ወደ ሃይማኖታችን በእርግጥ ትመለሳላችሁ» አሉ ፡፡ ወደእነርሱም ጌታቸው እንዲህ ሲል ላከ «ከሓዲዎችን በእርግጥ እናጠፋለን ፡፡"
           ይሁን እንጂ እነዚህን የአላህ መልእክተኞችንና አማኞችን የሚያሰቃዩትንና ከሀገር የሚያስወጡትን እንደሚያጠፋ አላህ ቃል ገብቷል ። ይልቁንም ያን ሲቋምጡለት የነበረ ምድር ለአማኞች እንደሚያደርገውም ነው እንዲህ ብሎ የሚነግረን 

« وَنُرِيدُ أَن نَّمُنَّ عَلَى الَّذِينَ اسْتُضْعِفُوا فِي الْأَرْضِ وَنَجْعَلَهُمْ أَئِمَّةً وَنَجْعَلَهُمُ الْوَارِثِينَ »
                 القصص ( 5 )
“በእነዚያም በምድር ውስጥ በተጨቆኑ ላይ ልንለግስ፣ መሪዎችም ልናደርጋቸው ወራሾችም ልናደርጋቸው እንሻለን ፡፡ ”
      ለዚህም ማሳያ አላህ ማን አለብኝ ባዩን ፊርዓውንና ሰራዊቱን አጥፍቶ ለበኒ ኢስራኢሎች የሱን ምድር አወረሰ ይህንንም አላህ እንዲህ ብሎ ይነግረናል :
« وَقُلْنَا مِن بَعْدِهِ لِبَنِي إِسْرَائِيلَ اسْكُنُوا الْأَرْضَ فَإِذَا جَاءَ وَعْدُ الْآخِرَةِ جِئْنَا بِكُمْ لَفِيفًا»

الإسراء  ( 103 )
“ ከእርሱም በኋላ ለእሰራኤል ልጆች «ምድሪቱን ተቀመጡባት የኋለኛይቱም (ሰዓት) ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትኾኑ እናመጣችኋለን» አልናቸው ፡፡"
     የመካ አጋሪያኖች ነብዩንና ተከታዮቻቸውን አሰቃይተው ከሀገር ያስወጡዋቸው የነበረ ቢሆንም መጨረሻ ላይ እነዚያን አመፀኞች የውርደት ልብስ እንዲለብሱ አድርጎ የመካን ምድር ለነብዩና አማኞች አደረጋት ።
      አሁንም ማን አለብን ባይ ምእራባዊያንና ሰው በላዎቹ አይሁዶች ፍልስጢናዊያንን ከሀገራቸው ቢያስወጡዋቸውም መጨረሻው አላህ እነዚህን ተምክህተኛችን የውርደት ልብስ አልብሶ ምድርዋ ለአማኞች መሆኗ አይቀርም ። ለዚህ የድል ቀን ፍሊስጢናዊያንን ቶሎ እንዲያደርሳቸው ሁላችንም ዱዓእ እናድርግ አንዘናጋ ።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***👉*** **የሐቅና ባጢል ትግል መጨረሻው**
5 months, 2 weeks ago

🆕 አድስ አፕ ተለቀቀ

*📚 النحو المستطاب*

📚 አነህዉል _ሙስተጧብ

🎁ቁጥር ⓵➢

🎙 በሸይኽ አቡዘር ሀሰን አቡ ጦልሓ ሀፊዘሁሏህ

ለሌሎች ሼር በማድረግ ላልደረሳቸው እናዳርስ

ሊንኩንም ሼር ማረግን አትርሱ
👇👇👇👇👇
https://t.me/salfy_App

https://t.me/+hIxxXxIRhGU5NzM0

📨 መሰል  ቂራአት እና ሙሀደራወች ለማሰራት የሚከተልውን አድራሻ ይጠቀሙ
👇👇👇👇👇
@selfy_app_developer

5 months, 2 weeks ago

👉 አል ኢኽዋኑል ሙስሊሙን ከኸዋሪጆች የባሱ ናቸው።

👉 መነሻቸው የኸዋሪጅ ፊክራ ሆኖ ሸራቸው ግን የባሰ ነው። ሸራቸው ጨምሯል።

👉 ኸዋሪጅ ብሎ ከመጥራት ተሳሁል (ተፍሪጥ) ማድረግ አይበቃም።

👉 እንዲያውም በጣም የሚመሳሰሉት በቀራሚጧዎች ነው።

🎤 የተከበሩ ሸይኽ ሷሊሕ ቢን ፈውዛን ቢን ዐብዲላህ አልፈውዛን ሐፊዘሁሏህ

https://t.me/medresetulislah

5 months, 3 weeks ago

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ማሳሰቢያ፡-
       ▬▬▬
መጀመሪያ የተለቀቀው ክፍል 1 የኮርሱ መጀመሪያ ኢዲት/Edit/ ያልተደረገውና ያልተስተካከለው ስለሆነ ይህ የድምፅ ፋይል Edit የተደረገውና የተስተካከለው ስለሆነ የመጀመሪያውን ሼር ያደረጋችሁ የቻናል ባለቤቶች በዚህ በተስተካከለው እንድትቀይሩት ስናስታውሳችሁ ከታላቅ ይቅርታ ጋር ነው*
👆**👆*👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

We recommend to visit

Books only!

This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !

Join and share @Books_worldd

አስተያየት @BooksWorlddd_bot !

@books_worlddd መወያያ ግሩፕ

#share

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Last updated 3 months, 1 week ago

Last updated 1 year, 4 months ago