የሀድራው ❤️ ወዳጅ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️??

Description
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week, 2 days ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months ago

6 months, 3 weeks ago
[***?***ሀላል ፈገግታ***?***

[?ሀላል ፈገግታ?

የዘምዘም ባንክ ?
ኤቲኤም ብር ስጨርስ ???

?ኑ በሃላሉ ይዝናኑ?](https://t.me/addlist/3agyuIn4l7IxYTg0)

6 months, 3 weeks ago

?የመጨረሻው ፓርት ሊለቀቅ ነው ?

7 months ago

•┈┈• ❀°•?•°❀•┈┈•
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
#ፀሀፊ ሂክማ #የእናት ሆድ ━━━━━━✦✿✦━━━━━━
    •┈┈• ❀°•
?•°❀•┈┈• ?* #ክፍል_6?

ብድግ ብላ ቆመችና "ቁማርተኞቹ" ብላ ዘላ ወጣች ለሷም አልታወቃትም በምን ፍጥነት እቤት አጠገብ እንደደረሰች ስትደርስ የቤታቸው በር ተከፍቷል ልቧ ማራቶን እንደተወዳደር አትሌት በጣም ይመታል
?*** ከበሩ እንደገባች ደም አየች በደበሩ ጋር ይንጨለጨላል ልቧን ልትተፋው ነው ሁሉም ዘሪቱ ሱመያ እና የዘሪቱ ባል ተከትለዋት በኋላ ከኋላዋ ያይዋታልያይዋታልልክ ሳሎኑ መሀል እንደፈራችው አባቷ ተዘርግቷል እያለቀሰች ዙሪያውን አየችው ሱመያ ስታየው አልቻለችም በጣም ጮኸች ሰአዳ "ኢናሊላህ" አለች መቋቋም አቃታት ከአባቷ አጠገብ ተዘረረች ሰፈሩ ህብረተሰብ ተጥለቀለቀ መጮህ ጀመረ ሱመያ በድን ሆነች ግድግዳውን ተደግፋ ሸርተት ብላ ወደቀች በዛች ትንሽ ደቂቃ ውስጥ በጣም ብዙ ነገር አሰበች ያወሩት ነገር ጆሮዋ ላይ አቃጨለባት የዘሪቱ ባል ሰአዳን አንስቶ አልጋ ላይ አደረጋትና ወጣ ህዝቡ መጮህ ጀመረ " ደግ ሰው ነበርክ ደግ ሰው ነበርክ ልጆችህን ለማን ጥለህ " ያደረገውንም ያላደረገውንም ይቀባጥራሉ ሱመያ አሁንም ድረስ በድን ሆናለች ሰአዳ አባትዋ ከተቀበሩ በኋላ ነበር የነቃቸው እየቃዠች ነበር "አባበይ" ብላ ብድግ አለች ሱመያ እገሯ ስር ተቀምጣ " አውፍ ብዬሀለው " እየደጋገመችው ታለቅሻለች ሰአዳ እንደነቃች ሰዎች ከበቧት እሷ አላህ በራህመቱ ያያት ነበርችና ሰብር ለማድረግ እያጣጣረች ወደ ሱመያ ጋር ሄዳ አቀፈቻት ሳግ እየተናነቃት " የኛ ያልሆነ ነገር የኛ አይደለም ለምን ወሰዳችሁብኝ ተብሎ ችክ አይባልም ሰብር አድርጊ አባትን የሚተካ እንደሌለ አቃለሁ ግን በቃ ዱአ አድርጊለት" እሷንም የሚያፅናናት ያስፈልጋታል እኮ የተናገረችው ነገር ጆሮዋ ላይ ጭውውውው ይልባታል ይደጋገማል አባቷ ለነሱ የነበረው ፍቅር በቦታው እንደነበረ ተገነዘበች
ነገሩ በረድ አለ ለቀስተኛውም ቀነሰ ከነሰአዳ ጋር ደሞ አንዲት የእናታቸው ጓደኛ የነበረች ሴት ተደፍራ ከቤት ስላባረሯት ከነሱ ጋር ለመኖር ተቀላቅላቸው ነበር  ሁለቱም ትምህርታቸውን አቁመዋል። ከአባታቸው ህልፈት ከአራት ወራት ቆይታ በኋላ ዘሪቱ እንደ አዲስ ባለፈው ስለጠየቀቻት ጉዳይ ድጋሚ አወራቻት "አንቺው ስለትምህርቱ ምንም አላሰብሽም ወይ ሱመያም ትምህርት ትግባ ለምን ይቅርባት ወንድሜ ከሳምንት በኋላ ሊመጣ ነው በፈለግሽው ሰአት እየመጣሽ የቤተሰቦችሽን እርስት መንከባከብ ትችያለሽ እኛም ልክ እንዳንቺ ሆነን የምንጠብቀው ይሆናል "አለቻት የናትና የአባቷን ንብረት ጥላ መሄድ ቢከብዳትም ዘሪቱን ስለምታምናት እና ሱመያን ማስተማር ለሷ ከምንም በላይ ስለሆነ ሆዷን ባር ባር እያላት ለመሄድ ተስማማች ሱመያ እንኳን አባቷ የቅርብ ጎረቤት የሞተባትም አትመስልም ምን አልባት ከነበራት ጥላቻ አንፃር ይሆናል።
ከሳምንት በኋላ እንደተባለው የዘሪቱ ወንድም መንሱር ወደነ ሰአዳ ሀገር መጣ ሰአዳ እምባ እየተናነቃት ነው አሁንም አሁንም አባቷ ይተኛበት የነበረውን አልጋ ታያለች ሱመያ ደሞ በተቃራኒው ደስታዋ ወደር አልነበረውም ከእናቷ ለቁርዐን መስሚያ የተሰጣት እሷ እጅ ከገባ በኋላ ደሞ የሙዚቃ ማጠራቀሚያ የሆነ ትንሽዬ ጅፓስ አለቻት ለመሄድ ሶስት ቀን ሲቀራቸው ነበር ቻርጅ ያደረገችው በቃ ደስታዋ ከፊቷ ላይ ይነበብ ነበር ዘሪቱ ልብሳቸውን በማውጣት እያገዘቻት ሰአዳን እንዲህ አለቻት"...

ይቀጥላል━━✦✿✦━━━━━━
    •┈┈• ❀°•
?•°❀•┈┈•

ይቀጥል የምትሉ ????

❤️መቶ ላይክ መሆን አለበት❤️

7 months, 1 week ago

•┈┈• ❀°•?•°❀•┈┈•
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
#ፀሀፊ ሂክማ #የእናት ሆድ ━━━━━━✦✿✦━━━━━━
    •┈┈• ❀°•
?•°❀•┈┈• ?* #ክፍል_5?

ሱመያ"
?**?*? አሁን እኛ ላይ እጁን ሲያነሳ ወንድ አይመስልም ይሄ የወንድ አልጫ ? ለስሙ ጠመንጃን የሚያህል ክብር ያለው ጉድ ተቀምጧል አይ እንደው የሰው ከንቱ" በመሀል በመሀል እየሳቀችሰአዳም እኮ ሳቋ መጥቷል ግን ለመሳቅ አልደፈረችም የተበላበትን አነሳስታ ለባብሰው እየሄዱ ዘሪቱ ጠራቻት "ሠአዳዳዳዳዳዳ"አስረዝማ ጠራቻት "ወይይይይይ"ሰአዳም ልክ እንደሷ አስረዝማ "ተትምህርት ስትመለሺ ድረሽ እኔጋ የማዋይሽ ጉዳይ ነበረኝ "ሰአዳ ነገሩ ስለገባት ፈገግ ብላ እሽ እቴ"እየተፍነከነከች እህቷን ይዛ ጉዞ ወደ ትምህርት ቤት ክፍላቸው ተማሪው ሞልቶ ነበር የደረሱት ሁለቱ እህትማማቾች ታዋቂ ነበሩ ሰአዳ በጉብዝናዋ ሱመያ በራባሽነቷ ሰአዳ ከእህቷ ጋር የመቀመጥ ፍላጎት ቢኖራትም ትረብሻታለች ተብሎ ስለሚታሰብ አብረው አይቀመጡም ዛሬም ወደ ክፍል ሲገቡ ሱመያ ወደ በጥባጭ ጓደኞቿ ሰአዳ ደሞ ከፊት ለፊት ሄደው ተቀመጡ ሱመያ በጣም የምትወደው ፍቅረኛ አላት ፋሩቅ ይባላል ሰአዳ በዚ ጉዳይ ላይ ጎትጉታት ጎትጉታት እምቢ ስላለቻት "በራስሽ አይን ታይዋለሽ ብላ ትታታለች ዛሬም ገና ከመግባቷ አፍ ለአፍ ገጥመው እያወሩ ነው ሙሉ ቀኑን ተምረው እንደጨረሱ ወደ ቤት መንገድ ከጀመሩ በኋላ ሱመያ የምሳ መያዣዋን ረስታ ነበር "ውይ ሰአዳ እህል መያዣውን እክፍል ትቼ ነው የመጣሁት እዚሁ ቆዪኝ እሩጬ መጣለሁ "እየሮጠች ወደ ክፍል አመራች ልክ በሩን በርግዳ ስትገባ የሷው ጉድ ፋሩቅ ከሴት ጋር ተቃቅፎ ተቀምጦ ሲሳሳቅ አየችው ምንም ሳትል የምሳ እቃዋን ይዛ ወጣች ተከተላት" አለሜ ቆይኝማ" አላት ማስተባበያ ነበር "ምን ልስማህ ያየሁትን ልተደግምልኝ ነው እስቲ ተናገር እሺ" እጇን አጣጥፋ ቆማ አይን አይኑን ማየት ጀመረች "አለሜ ያው ሰውም አይደለሁ ስሜቴ ገፋፍቶኝ ነው እንጂ ተነፍሴ አብልጬ እንደምወድሽ አንቺም ታውቂያለሽ" አላት ከት ከት ብላ ሳቀችና "አንተ ከሰሙህ ብዙ ታወራለህ ዛሬ ለሷ ያልተመለስክ ነገ ለኔም የምትመለስ አትሆንም" ብላ ጥላው ሮጠች ልክ ሰአዳ ጋር ስትደርስ ተናዳ ስለነበር ፊቷ ቀልቶ ነበር" ምን ሁነሻል አንቺው"ሰአዳ ግራ ስለገባት ጠየቀቻት "ስሚማ ፋሩቄን እኮ ? የምን አባቱ ፋሩቄ ማለቴ ፋሩቅን እኮ ከከንፈር ጓደኛው ጋር ተዛዝሎ እክፍላችን አየሁት"አለቻት እዝን ብላ? "አየሽ አይደል ነግሬሽ ነበር አይደል ወንዶች ካንቺ ጋር የሚሆኑት የሆነ የሚፈልጉትን ነገር እስከሚያገኙ ነው ከዛ ለደቂቃም ካንቺ ጋር መቆየት አይፈልጉም ሌላ ሴት ይፈልጋሉ ወስላቶች ስሚማ አንቺ አሁን ትምህርትሽ እና ቁርአንሽ ላይ ትኩረት አድርጊ እሺ የምትፈልጊውን ነገር ጠይቂኝ" ለማፅናናት ሞከረች ተቃቅፈው ወደቤት ሄዱ ልብሷን ቀየረች ወደ ዘሪቱ ጋር ለመሄድ ቸኩላ ነበር ለዛ ለሱመያ መክሰስ ሰጠቻትና መድረሳ ፍቃድ እንድትጠይቅላት ነግራት ዘሪቱ ጋር ሄደች "ሰላም አለይኩም እናቴዋ" ሰአዳ ነበረች ወደውስጥ ስትገባ "አለይኩመሰላም አለሜ ነይ ዝለቂማ እናቴ"አለች ከዛ ምግብ አቀረበችላትና "አንድ ጉዳይ ላማክርሽ ነበር ምን መሰለሽ እኸተማ ያለው ወንድሜ  ስለጉዳያችሁ ነግሬው ያውውውው እኔ ቤት መጥተው ትምህርታቸውን መከታተል ይቻላሉ ብሏል ምን ትያለሽ እዝህ ይሄ ሁሉ ጭቆና ሲደርስብሽ እያየሁ አንጀቴ አልችል አለ እቴ"አምርራ አለቀሰች ሰአዳም የደስታ አለቀሰች የአባቷም ነገር አሳሰባት "ተይኝ እቴ ጠዋት ቁማርተኞች መጥተው ብር ካልከፈልክ ብለው ሽንቱን አስለቅቀውት ነው የሄዱት ጭራሽ ካልከፈለ ብሩን እስኪመልስ እኛን እንዲያስይዝ አስጠንቅቀውት ነው የሄዱት ቢጨንቀኝ እኮ ነው ቆይ እኛ ሳንኖር ቢያዳፉትስ?" ተነፈሰች ጭንቀቷን"አላሁሁሁሁ አክበር በሞትኩት ልጆቹን በብር ሊለውጥ ነው አላህ ነጃ ይባላችሁ በይ እሺ በቃ ይቺን ወጥ ይዘሽ ህጂ ይቺንም ፍራንክ ያዣት ለአንዳንድ ነገረ ትሆንሻለች " ብላ 800 ብር ሰጠቻት የተለመደ ስለሆነ ሳትግደረደር ተቀበላቻት እቤት ገብታ እህቷንና አባቷን መጠባበቅ ጀመረች እህቷ በጊዜ ተመለሰች መሽቶ አብዱም መጣ ዛሬ አልሰከረም "ሰአዳ" ከረጅም ጊዜ በኋላ በስሟ ጠራት "አቤት አበይ "የተሰማት ደስታ ይሁን ምን እሷም አታቀውም ደስ ብሏት ነበር "ሱመያን ጥሪያት መአድ ቅረቡ" እንደዚ ሲላት ጭራሽ አባቷ አልመስል ብላት ከጓዳው ወጣ ብላ አየችው ሱመያም ነገሩ ግራ ስለገባት ሄደችና ቀስ ብላ "ማነው ?" አለች በመገረም" ወጥተሽ እይው " እያንሾኳሾከች ከዛ ምግቡን አቀራርበው አብረው በሉ ከደስታዋ ብዛት ቡና ሁላ አፈላችለት አብረው ጠጡ ካለቀ በኋላ ለማውራት ጉሮሮውን ጠራርጎ "ልጆቼ አውፍ በሉኝ ለዚ ምክንያቴ የእናታችሁ ምት ነው "አለ እና ቀጠለ"እና ዛሬሬ እእእ ስራ አለብኝ እና ዘሪቱ ጋር እደሩ" ሰአዳ በደቂቃዎች ውስጥ ፊቷ ተቀያየረ " አረረረረ ተው በእናቴ ቤት አንሶላ ልትጋፈፍ እውነትህን ነው ይሄንን ጉድ አላይም እኔ እኮ የተቀየርክ መስሎኝ እእእ " ወደ ጓዳ ሮጣ ገባችና ፌስታሏን ሰብስባ ሱመያን አስነሳቻት ሱመያ እያለቀሰች" መቼም አውፍ አልልህም እሺ" ወጣች ቀድማት "ይኸው ፈረሱም ሜዳውም ያንተ ነው እንደፈለክ ሁንበት በሩን በርግዳ ወጣች እነ ዘሪቱ ቤት እንዴት እንደደረሰች አታቅም በሩን ከቆረቆረች በኋላ ነበር ያሸማቀቃት ሰአቱ ብዙም ስላልመሸ አልተኙም ነበር ዘሪቱ በሩን ከፍታ "አኡዙቢላህ አንቺው ምነው በማታ ነይ በይ ግቡ ከብርድ ላይ "እራት ለማቅረብ ብትጠይቃትም አሻፈረኝ አለች እያወሩ እስከ 4 ሰአት ገደማ ቆዩ አራት ሰአት ላይ ሶስት ጊዜ የተኩስ ድምፅ ተሰማ አንድኛው ሲተኮስ ጩኸት ነበረው ሌሎቹ ሁለቱ በተከታታይ ነበር የተተኮሱት እነዘሪቱ ከቅርብ ስለተተኮሰ ደንግጠው ነበር ግን ያው የሰከሩ ሰዎች ይሆናሉ ብለው ተዉት እና ትንሽ ከቆዩ በኋላ ሰአዳ ብድግ ብላ ቆመችና "...

ይቀጥላል━━✦✿✦━━━━━━
    •┈┈• ❀°•
?•°❀•┈┈•

ይቀጥል የምትሉ ????

❤️መቶ ላይክ መሆን አለበት❤️

7 months, 2 weeks ago

•┈┈• ❀°•?•°❀•┈┈•
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
#ፀሀፊ ሂክማ #የእናት ሆድ ━━━━━━✦✿✦━━━━━━
    •┈┈• ❀°•
?•°❀•┈┈• ?* #ክፍል_4?***

ተንደርድሮ ሄዶ በጥፊ ሞላት"ትበላው የላት ትከናነበው አማራት አለ ያገሬ ሰው አንች ወጠምሻ ጭራሽ በብሬ እእእ በማናባሽ ጎጆ ነው ተጠልለሽ ነው ያለሽው አንቺ ወናፍ እናንተ ከተፈጠራችሁ በኋላ ዱንያዬም ጠፋ ቡዳዎች የልጅ ቡዳዎች" ቀበቶውን ፈቶ መጠፍጠፍ ጀመረ ሰዐዳ አቃታት "ወግድ አን ጨካኝ ለምንድነው የምትወቅሳት አረ አላህን ፍራ"ሲቃ ተናነቃት "አረገኝኝኝኝኝ እ ጭራሽ ተባብራችሁ ልትመቱኝ አርበኛ የአርበኛ ዘር ነኝ እኮ ወስላቶች ወደ ሰአዳ ተቀይሮ እሷ ሆነች ተረኛ በጣም ሲበዛ ምቱ ሱመያ ጮኸች የሰፈሩ መንደርተኛ ተሰበሰበ ገላገሏቸው ጓደኞቹ አብዱን ይዘውት ሲወጡ "ዲቃሎች" ገላምጧቸው ወጣ ሁሉም ሰዎች ተጠራርገው ሲሄዱ ከነሱ ቤት ቀጥሎ ሶስተኛ ቤት ላይ የምትገኘው ጎረቤታቸው ዘሪቱ ቁጭ ብላ በሀዘኔታ ማየት ጀመረች "ዘሪቱ ህጂ በቃ እቴ እኛ እንጨራርሰዋለን ትምህርቱም ይቅር ምን አደርጋለው ሀድያ አላህ መለኛውን አዞብናል"ሠዐዳ ናት ለመሳቅ እየሞከረች ዘሪቱ ተናደደች "እንዴት እንዴት ነው ምታስቢው አንቺው ዛሬ እንዲ ያደረጋቹ ነገ ተነገ ወድያ ምን እንደሚያደርግ ማን ያቃል እኔማ ዝም ብዬ አላያችሁም የሆነ መላ እናበጃለን "እያለቀሰች ጥላ ወጣች
   ዘሪቱ ከነሰዐዳ ሶስተኛ ግቢ የምትኖር ጎረቤታቸው ናት እነሱ መንደር ካሉ ሀብታሞች ትጠቀሳለች ልጅ የላትም በቅርቡ ነው ያገባችው አዲስ አበባ የሚኖር ወንድም አላት በየጊዚው ጠቀም ያለ ገንዘብ ይልክላታል ባለቤቷም ደህና የሆነ የእርሻ መሬት አለው እና ጎበዝ ገበሬም ጭምር ነው ሠዐዳ አብዛኛውን ጊዜ ዘሪቱ ጋር ነው ስራ የምትሰራው ዘሪቱም የሚደርስባትን ጫና ስለምታቅ ትንሽ ስራ ከሰራችም በዛ ያለ ገንዘብ ትሰጣታለች
   አንድ ዕለት እንዲሁ እንደተለመደው ቁርስ በልቶ ሊወጣ ሲል በራቸው ተበረገደ እና 3 ሽጉጥ የያዙ ሰዎች ተከታትለው ገብተው አነጣጠሩበት ባለበት ቁጢጥ አለ
"አን ወስላታ ብራችንን በልተህ የት አባክ ልትሄድ ህህህህ ከኔ ከአንበርብር አንድ የሚያመልጥ ሰው የለም"የፌዝ ሳቅ ሳቀበት እና ወዲያው ተኮሳተረ "ትሰማ እንደሆነ ስማ ወይ ተበላከውን ገንዘብ አንጣ ወይምምምምም" እነሰዐዳን አያቸውና "አስይዝና ስትከፍል ይመለስልሀል"አጉረጠረጠበት
"እሽ እሽ እከፍላለው ጌታው እባኮትን ትንሽ ጊዜ ይስጡኝ የዛሬን ይማሩኝ" እግሩ ስር ሆኖ ተማፀነው ምራቁን መሬት ላይ ለጥፎ እነሰዐዳን ገላምጧቸው ወጣ ሁለቱም ተከተሉት ሱመያ የአባቷ ሁኔታ አስቋታል አፏን አፍና እስኪወጣ ትጠባበቃለች ሰዐዳ ደሞ ምንም ያህል ብትጠላውም እንዲ የድመት አፍ ውስጥ እንደገባ አይጥ ሲወተረተር አንጀቷ ተላወሰ አብዱ ይርበተበታል በረጅሙ ተነፈሰ "እፎይይይይይይይ" ሱመያ መቆጣጠር አቃታት ሳቋን ለቀቀችው ድንግጥ ብሎ ዞሮ አፈጠጠባቸው ሰዐዳ አፏን ቶሎ ብላ ያዘቻት ተነስቶ ከመሮጥ ባልተናነሰ እርምጃ በሩን በርግዶ ወጣ

ይቀጥላል━━━✦✿✦━━━━━━
    •┈┈• ❀°•
?•°❀•┈┈•

ይቀጥል የምትሉ ????

❤️መቶ ላይክ መሆን አለበት❤️

9 months, 1 week ago
ፎቶዋቹ ባማረ መልኩ [#edit](?q=%23edit) እንዲደረግ ከፈለጋቹ

ፎቶዋቹ  ባማረ መልኩ #edit እንዲደረግ ከፈለጋቹ

photo editing

9 months, 1 week ago
የኸው ለተማሪዎች ብቻ ምርጥ ቻናል የዤ …

የኸው  ለተማሪዎች ብቻ ምርጥ ቻናል  የዤ መጥቻለው ያልተቀላቀላችው ከስር ጆይን ሚለውን በመንካት ተቀላቀሉ??
school meme  join ብቻ

9 months, 1 week ago
ይሄን ፎቶ ያነሳችው አንድት የሆስፒታል ነርስ …

ይሄን ፎቶ ያነሳችው አንድት የሆስፒታል ነርስ ነች።

"ሰውየው ሆስፒታል ውስጥ ከሞተ ቢሰነብትም ቤተሰቤ ነው ብሎ መጥቶ የጠየቀው አልነበረም።
ይች ምስሉ ላይ የምትታየው እርግብ ግን ባልተለመደ መልኩ በመስኮት እየሾለከች ትገባና ትንሽ ቆይታ ተመልሳ ትሄዳለች፣
በቀናት ለብዙ ጊዜ ትመላለሳለች በዚህ ሁኔታ ቀናቶች ካለፉ በሇላ
[ሰውየውን አውቃለሁ የሚል አንድ ሰው ተገኘ"
ትላለች ነርሷ
ሰውየውም እንድህ አለ............ Read more

ሙሉውን ለማንበብ ? ይጫኑ](https://t.me/addlist/z0echrVJEw9jMTY0)

9 months, 1 week ago
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week, 2 days ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months ago