Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

Description
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 days, 16 hours ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 3 weeks, 2 days ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 8 months, 3 weeks ago

3 weeks, 2 days ago
"…እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ …

"…እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፉማል። የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ። ኢሳይ 41፥ 10-12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

3 weeks, 2 days ago
"…አላችሁ አይደል…?

"…አላችሁ አይደል…?

• አንደዜ ገባ ገባ በሉማ…!

3 weeks, 3 days ago

"ርእሰ አንቀጽ"

• ጥያቄ ፩

"…የፌዴራል መንግሥት ተብዬው የ "ሀ ገደሉ" ማይም ወጠጤ ዱርዬ ስብስብ ባለፈው ሰኔ ላይ በምክር ቤት አቅርቦ የ2017 ዓም 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት መጸደቁ ይታወቃል። መልካም…

"…ታዲያ ይሄ የተበጀተ በጀት መስከረም ወር ላይ ይጨመራል ለተባለው ደሞዝ እንኳ ሳይጨመር፣ ከኮሪደር ልማቱ መብራትና የብሽክሊሊት ማሽከርከሪያ መንገድ በቀር ሌላ ምንም ዕቅድ በሌለበት ገና በወርሀ ህዳር ተጨማሪ 583 ቢልዮን ብር ያስፈልገኛል በማለት በትናንትናው ዕለት ማስጨመሩ ይታወቃል።

"…በዐማራ ክልል የኦሮሚያ አምባሳደር ዶር ለገሰ ቱሉም በፌስቡክ ገጹ ላይ "የፌዴራል መንግስት የ2017 አጠቃላይ በጀት 1.5 ትሪሊየን ብር ደረሰ።  በትላንትናው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት 582 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል። ኢትዮጵያ ከፍ ከፍ እያለች ነው።" በማለት ተሳልቋል።

"…ወደ ኋላ ሄደን በ2015 ዓም በጀት 786.6 ቢሊዮን ብር ወይም 14.64 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2016 ዓም ጭማሪ አሳይቶ 801.65 ቢሊዮን ብር ወይም 14.2 ቢሊዮን ዶላር፣ ዘንድሮ በ2017 ዓም 971 ነጥብ 2 ቢልዮን ብር ሆኖ ከጸደቀ በኋላ ወዲያው አነሰኝ በማለት 582 ቢልዮን ብር አስጨምሮ 1.5 ትሪልየን ብር አጽድቋል። ይሄንንም በወቅቱ ምንዛሬ በዶላር ስንመታው 12 ቢሊዮን ዶላር ይመጣል ብለው የጻፉ አይቻለሁ።

"…እሺ በ2015~ 14.64 B$፣ በ2016~14.2 B$ ከሆነ የዘንድሮ…የዘንድሮው የ2017~12 B$ ዶላር ከመጣ ለስሙ 1.5 ትሪልየን ብር ተባለ እንጂ በወቅቱ ምንዛሬ በዶላር ሲመታ ከ2015 እና ከ2016 ዓም በጀት ያነሰው የዘንድሮው የ2017 ዓም ዓመታዊ በጀት እንዴት ቢሆን ነው "ምእመናን እልል በሉ ኢትዮጵያ አደገች፣ ከፍ ከፍም አለች" ተብሎ በመንግሥት አፍ በድፍረት የሚነገረው…? በቃ እነዚህን ደናቁርት የማይም ስብስቦችን ሃይ የሚል ወንድ ጠፋ ማለት ነው? ሀገሩን እንዴት ቢንቁት ነው ግን እንዲህ የተጸዳዱበት…? ከምር እንዴት ያለን ሾርት ሚሞሪያም እንደሆን አድርገው ቢቆጥሩን እንዲህ የሚያላግጡብን።

"…እነዚህ ማይም፣ ደናቁርት ትሪልዮን በጀቱ ገና በህዳር ወር ምን ቢያደርጉት ነው ያነሳቸው? በምንስ ነው የጨረሱት? ታህሳስና ጥር፣ ሚያዚያና ግንቦት ሲመጣስ ምን ሊሆኑ ነው? ኧረ ሌላው ይቅር ኢትዮጵያ ከፍ ከፍ አለች እልል በሉ የሚያሰኘው የምሥራች ምኑ ላይ ነው?

• መልሱልኝ… ሁለተኛው ጥያቄዬ ሌላ ሦስተኛ ጥያቄ ስለወለደ እንዲሁ እየቆየሁ እጠይቃለሁ። ምሑራን መልሱልኝ በማርያም፣ በናታቹ፣ ባባታቹ…? 

4 weeks, 1 day ago

👆⑤ ከላይኛው የቀጠለ… …የሚገኙ ዐማሮችንና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችን ዘልዝለው የበሉት ኃይሎች ለይተው የጨፈጨፉ ያረዱ ያቃጠሉ አራጆች፣ በትግራይ ቤንዚን አርከፍክፈው ትግሬን አርደው ያወደሙ፣ ቅርስ የዘረፉ፣ ንፁሐን በድሮን የፈጁ፣ ሰላማዊ ሰዎችን በአደባባይ እንደ አማንኡኤል ወንድሙ ያሉትን የሚረሽኑ ሰዎች አሁን አንድ ማንነቱና ምንነቱ ያልታወቀ አሰቃቂ እርድ ጓ አሉ? በቴ ኡርጌሳን በገዛ ሀገሩ የኋላ የፊጥኝ አስሮ የረሸነ ኦሮሙማ ደራ ላይ አዝኖ ሰልፍ ሲያስወጣ ታየኝ እኮ።

"…ለማንኛውም በዚህኛውም የብልፅግና አጀንዳ ዐማራ አሸናፊ ሆኗል። በኦሮሚያ ሚሊሺያ የዛሬ ዓመት የተገደለን ወጣት የዐማራ ፋኖ ነው ያረደው ብሎ ማጯጯህ ነውረኝነት ነው። የሟቹ ልጅ ቤተሰቦችስ ምን ይሉናል አይባልም ወይ? ከኤርትራ ድራማ ፊልም ላይ የተወሰደ አንዲት ሴት በመጥረቢያ ስትቆረጥ የሚያሳይ ፎቶ ለጥፎ ዐማራ ነው እንዲህ የሚያደርገው ማለትስ ምን ማለት ነው። ሌላውንስ ሸውዱት እኔ ዘመዴን በየት በኩል ትሸውዱኝ? እንዴት እኮ? እንዴት አድርጋችሁ ነው የምትሸውዱኝ? ቀሽሞች። አሁንም የብልፅግና የሚዲያ ፔጆችን አውቀንበታል። የጎንደር ስኳዱ ጎንደሬው ፀረ ጎጃም የጉርሻ ቲዩብ ባለቤት አቶ ዳዊት ቢያሰልፍ አበበም እንድ ሕፃን ፌቨን አጀንዳ አድርጎ ፋኖ ላይ ዘመቻ ለመክፈት ሻርጂያ ዱባይ ተቀምጦ ቢንደፋደፍም ለአሁኑ አልተሳካለትም። ከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካና ራሱ ከዱባይ ሆኖ በሚያስተዳድረው ፔጅ ላይ የብልጽግናን ቅርሻት ለመትፋት ቢሞክርም የፔጁን ባለቤት ስሙን ጠርቼ በማጋለጤ የግል ፌስቡኩን መጀመሪያ ፎቶውን፣ ቀጥሎ ፌስቡኩን ራሱ ዲአክቲቬት ነው የደረገው። ዳዊት የሸራተኑ ጋርድ አሁን ተንፍሷል። ስደውልለትም ስልኬን አላነሣ ብሎኝ እንጂ እነግረው ነበር። አሁንም አድርሱልኝ። አላርፍ ያለው ያሬድ ያያ ዘልደታ ነው እሱም ቢሆን ወድዶ አይመስለኝም እንግዲህ እስኪገባው ድረስ መጠበቅ ነው።

"…በመጨረሻም የሰሞኑ የደራን አጀንዳ በተመለከተ በእለተ እሁዱ የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ ላይ እውነታውን አፈርጠዋለሁ። ይሄ ድራማዊ አጀንዳ ግን ለጊዜው ለዐማራ ሁለት ጥቅም እና በረከት ይዞለት ነው የመጣው። አንደኛው አብዛኛው  የኦሮሞ ኤሊት ጃዋርን ጨምሮ በወንጀሉ ብልፅግናን ነው የከሰሱበት። ከትግሬ አክቲቪስቶች በቀር አብዛኛው የኦሮሞ አክቲቪስቶችም የዐማራ ፋኖን እንደ ማባያ አድርገው ጠቀስ ያድርጉታል እንጂ በብዛት ይሄ አጸያፊ ተግባር የአቢይ አሕመዱ ብልፅግና ተግባር ነው ብለው በሃላል መስክረውበታል። እነ ጂጂ ኪያ ሳይቀሩ ትግሬዎቹን አታባሉን፣ እረፉ በማለት አፋቸውን አስይዘውበታል። እናም ይሄ ለዐማሮች በእጅጉ ጠቃሚ ነገር ነው። ደግሞም እውነት ከመመስከር በቀር ሌላ አማራጭ የላቸውም። ስለዚህ የራሳቸውን ሕዝብ ኦሮሞው በተወሰነ መልኩ ያረጋጋዋል። ሁለተኛ ጥቅም ደግሞ የዐማራ ፋኖ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ በይፋ ጠይቆበታል። በዚህም በራሱ በብልፅግና የከሰረ ቀሽም አጀንዳ ዕድሉን ተጠቅሞበታል። የሕዝብ ሓላፊነት እንዳለውም አስመስክሮበታል። ይሄም ጥቅም ነው። በተለይ በተለይ ደግሞ ከዐማራ ክልል ውጪ ለጥ ብሎ የተኛውን ዐማራ በሚገባ አነቃቅቶታል። ይሄም ጥሩ ነው። በዚያ ላይ አገዛዙን ወደ ስሁት ቀሽም አጀንዳ ያንደረደረው፣ የዳያስጶራ አንድነትና ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፣ ምድር ላይ የፋኖ አንድነት ወሬዎች፣ የሸዋ ፋኖዎች ከእነ እስክንድር የመለየት መግለጫዎች ተከታትለው መምጣት ነው ይሄን ጮማ የሆነ የዐማራ ፖለቲካ ሲሳይ የሆነ አጀንዳ ከሰማይ እንደ መና ያወረደው።

"…በነገራችን ላይ ትዊተር ስፔስ ሄጄ ያፈረስኩት ግምብም ቀላል አልነበረም። እነ ሲሳይ ሙላውን ወደ ቤተሰብ፣ ወደ ልጆቹ ነው የመለስኩት። አንድ ቀን ላይቭ ላይ እያለ ሚስቱ ስትቆጣው አስታውስ ነበር። ስልኩን ቀምታው ስትወረውር፣ እናም ያንን ቤተሰብ ነው ሰላም ያወረድኩለት። የደርግ ገዳይ፣ ኋላ ቅንጅት፣ ከዚያ ግንቦት 7፣ ከዚያ ባልደራስ፣ ቀጥሎ ግምባሩ፣ ሠራዊቱ፣ አሁን ደግኖ ድርጅቱ የነበረውን አቶ ክንፉ ወዳጄን፣ የጴንጤዋ ባል፣ ሰካራሙን የኒውዮርክ ቡፋሎውን ጠጪ ነው ከትዊተር ስፔስ ድራሹን ያጠፋሁት። የአዋሽ ነው የዳሽን ባንኩን የጎንደር ስኳድ፣ የመላኩ አለበልን ዘመድ አሁን ተሰድዶ ኡጋንዳ የገባውን ጥላሁን ጽጌን ነው ያስነጠስኩበት፣ እነ ጄ ብሩ፣ እነ ዳማከሴን የመሰሉ የአራዳ ልጆች፣ የፍሕ ሰዎችን ነው ያፈራሁበት። ሀብታሙን በቀለን የመሰለ የምሥራቅ ሰው የሀረርጌ ልጅ ስክን ብሎ ግራ ቀኙን እንዲያይ ነው ያደረግኩበት። እና ለእኔ ትልቅ ድል ነበር የትዊተር ስፔሱ ቆይታዬ።

"…የዋን ዐማራው ሮቤል ይሄ የደራው ድራማ ከመምጣቱ በፊት ወለጋ ላይ ታርደው አንገታቸው በእንጨት ላይ ስለተንጠለጠለ ሸኔዎች በተደጋጋሚ እኔ እንዳልለጠፍኩት፣ ዩቲዩብም እንደሌለኝ እየታወቀ ሁሉ አውቆት የነበረውን ነገር እነዚህ የብልፅግና ደብል ኤጀንቶች "በወለጋ ዘመዴ የተቆረጠ አንገት አሳይቶ ኦሮሞን አስቆጥቶታል" በማለት አጀንዳ ፈጥረው ነበር። የስፔሱ ሪከርድም አለኝ። እነ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመድኩን በሃይማኖት በኩል በወሎ ግጭት ሊያስነሣ ነው ብለው ከእነ ጃል ሀብታሙ ጋር መንበጫበጭ ጀምረው ነበር። በዚያውም እኔም ጓ ብዬ ከሁለት ዓመት በፊት ሆነ ከተባለው ጋር አያይዘው በሟጯጯህ ማኖ ሊያስነኩኝም አስበው ነበር። እንዲያውም መልሰው እነ ዘርያዓቆብም፣ ኦሮሞቹም አጀንዳውን ነቄ ብለው የለም ፌክ ነው በማለት ሲዳረቁ ነበር። ቀሽሙ ስክሪፕትም፣ ቀሽሞቹም ተዋናዮች አፈር ደቼ በልተው ዐማራው አጀንዳውን በዝረራ አሸንፏል። 

"…ዐማሮች የተኛችሁ ንቁ። የነቃችሁ የበለጠ ንቁ። የዐማራ አክቲቪስቶች ከቧልት፣ ከጥድፊያ ውጡ። የግድ ተቀባብታችሁ አሰስ ገሰሱን ሁላ ወደ አደባባይ አታምጡ። በእውቀት ተንቀሳቀሱ። ንቁ፣ ቆቅ ሁኑ። ለወሬ አሊ፣ ለሥራ ጥንቸል አቦሸማኔ ሁኑ። የኦሮሞም፣ የትግሬም አክቲቪስቶችን በዕውቀት ብለጡ። የጅብ ችኩል አትሁኑ። የጓዳ ወሬ ቲክቶክ ላይ አታምጡ። እንደኔ እንደ ዘመዴ ብስል፣ ሙክክ በሉ። አስሬ ለክታችሁ አንዴ ቁረጡ። ለጠላት በር አትክፈቱ። እኔ የሀረርጌ ቆቱ ስለሆንኩ ብትሰድቡኝኝ አልቀየምም እናንተ ግን ተከባበሩ። ተዋደዱ፣ ተፈቃቀሩ። በየትኛውም አጀንዳ አትበርግጉ። ልክ እንደ ፋኖ የተረጋጋጋችሁ ሁኑ። ከዚያ ታሸንፋላችሁ። አለቀ፣ አከተመ፣ ሃላስ።

• ቅድም ስታልፉ የመታችሁ የደርግና የወያኔ እንቅፋት አሁንም የብልፅግናው እንቅፋት እንዳይመታችሁ ዐማሮች ተጠንቀቁ።

• ዳይ ዛሬም ትናንት ያፈረስነውን የኦሮ ብልፄን ቀሽም አጀንዳ ወደመቅበሩ እናመራለን። ዕድርተኞች አንዳችሁም እንዳትቀሩ። 🎺🎺🎺🎤🎤🎤🔨🔬🔬🔑🗝💚💛❤️🚫❗️⛔️◻️🟢🟡🔴📢🔔

•••

ሻሎም…!   ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ሕዳር 13/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

4 weeks, 1 day ago

👆④ ከላይኛው የቀጠለ… "…በነገራችን፣ በጨዋታችን መሃል የወያኔው አሮጌ አለቃ አይተ ደብረጽዮን መጀመሪያውኑ ሲጀመር እንዴት ወደ አዲስ አበባ ሊመጣ ቻለ? መጥቶስ ከአቢይ ጋር ምን ተመካከሩ? ከተገናኙ በኋላ በሀገሪቷ እየተፈጸሙ ያሉትን ድርጊቶችን ምስሎቹን ገጣጥማችሁ ስታዩ ምን ዓይነት ምሥል ዓያችሁ? ከደብረ ፂ እና ከ4ተኛ ጨው የምክክር ውጤት በኋላ ሰው ሲታረድ የሚያሳይ የቆየ  ድራማ አምጥተው ኦሮሚያ ውስጥ የሕዝብ ቁጣ ለመቀስቀስ የሄዱበትን ርቀትስ አያታችኋል? ወያኔን ለመውጋት ወለጋ ውስጥ በቶሌ ቀበሌ ዐማሮችን ጨፍጭፎ፣ በፓርላማ ውስጥ የፓርላማ አባላትን እምባ አራጭቶ፣ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ በእልህ አስነሥቶ ትግራይ ክተት እንዳሳወጀው ሁሉ አሁንም የፈለገው ኦሮሚያ ውስጥ እሳት አስነሥቶ ዐማራ ላይ ለመቀወጥ እንደዚያ ነበር። ግን አልተሳክቶም። ከዚያስ ከዚያ አጀንዳውን ወደ ትግራይ አዞሩና ከዚህ በፊት የትግሬ ወታደር ትጥቁን ፈትቷል ብለው ዐዋጅ እንዳላሳወጁ ያንን ረስተው የትግሬ ጎረምሶች የተራቡ፣ ሥራ አጥ ስልችት ያለ የመረረ፣ የጨፈገገ ፊት ያላቸው ወጣቶች የቡድንና የግል መሣሪያ አምጥተው ለሀገር መከላከያ ሲያቀርቡ በቪድዮ ሲሠራጭ ወለ። ከተረሳ ዓመት ያለፈውን የፌክ ስምምነታቸውን እንደ አዲስ ፈልፍለው አመጡት። ህውሓት ትጥቅ ፈታ፣ የአፍሪካን ኅብረትም ምስክር ሆኖ ታየ። እግርህንም፣ ሞኝህንም ብላ። ወዲያው ደግሞ ተቃውሞ ከትግሬ ዲያስፖራ ሲበዛ አንዱ የትግሬ ባለሥልጣን ወጥቶ "ተረጋጉ መሣሪያው ከትግራይ አይወጣም፣ እዚሁ ትግራይ ውስጥ ነው የሚቀመጠው ብሎ እርፍ" (ቪድዮው አለኝ)

"…ስለዚህ ጨው እና ደፂ ቢሳካላቸዉ ኖሮ ኦሮሞና ትግሬን በብርሃን ፍጥነት አደራጅተው በማስነሣት፣ በሕዝብ ማዕበል ዐማራዉን በመጨፍጨፍና በመውረር ታሪክ ሊሠሩ ነበር የፈለጉት ብለን ብንጠረጥር አይፈረድብንም። ከኦሮሞው ይልቅ የትግሬዎቹ እኮ ባሰባቸው። ተናደዱ አይገልጸውም። አንዷማ ምን አለች "ዐማራ እንጂ ኦሮሞ አራጅ አይደለም" አላለችም። አይ ትግሬ አሳዘኑኝ ከምር። ያ ቢሳካላቸው ኖሮ ነገም የሚያደርጉት ቢሆንም ምን አልባት ኦሮሚያ ውስጥ በሚልዮን የሚቆጠር ዐማራ ጉዳት ይደርስበት ነበር። አንዱም በቪድዮ ወጥቶ እኔም በሀገሬ አንድ አሳርጃለሁ ብሎ እናንተም ጀምሩ እንጂ እያለ በቪድዮ ሲያወራ ይዤዋለሁ። የሆነው ሆኖ መዘናጋት አያስፈልግም። ሕወሓት ትጥቅ ፈታች ተብሎ ከተነገረህ ህወሓት ልትወርህ ነው ማለት ነው። ባታደርገውም ህወሓትንም በዓይነ ቁራኛ መከታተሉ አስፈላጊ ነው። ህወሓት ለመደች ተብሎ በኪስ አትያዝም። ነግሬሃለሁ።  አሁን ግንቦቴውም፣ እስክንድራውያንም አይተባበሩም ማለት አይቻልም። ገፍቶ የሚመጣውን ምሱን መስጠት፣ በዚያውም ከሚገባው በላይ ራስን ማጠናከር፣ አንድነቱን ማፍጠን ያስፈልጋል።  ዳያስጶራውም በጨዋ ደንብ ከግንቦቴና ከፌክ ኢትዮጵያኒስቱ የጸዳ የተቃውሞ ሰልፉን አጠንክሮ መቀጠል አለበት።

"…አይታችሁልኛል ግን ከተትናንት ጀምሮ ብልጽግናዎች በግልፅ ጭንብላቸውን አውልቀው ቲክቶክ ላይ እየተንጫጩ ነው። የሰላሌው ኦሮማይዝድ የተደረገው ዐማራው መስፍን ፈይሳም እንዲሁ ሲያቀረሽ ነው ያመሸው። ብልጽግና ከወደቀ አብሬ እወድቃለሁ እንጂ ዓይኔ እያየ ጎፈንድሚ ሰብስቦ የረዳኝ ዐማራ አራት ኪሎ አይገባትም ሲል ነበር ያመሸው። NO WAR ሲል የከረመው ፓስተር አያና እና ሌሎችም ብልጽግና ሰዎች ጂጂ ኪያ ቤት ከፍታላቸው ስታስለፈልፋቸው ነበር የመሸችው። እነዚህ ጎጋዎች የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ መሆኑን ረስተዋል። ድርጊቱን ማንም ቢያደርገው እኮ ይሄ የሚያሳየው መንግሥት የሚባለው ተቋም አለመኖሩን፣ ሕግና ፍትህ መጥፋቱን፣ ሀገር በሴተኛ እና ወንድኛ አዳሪዎች እጅ መውደቋን ነው የሚያሳየው። እና መንግሥት ተብዬውም በሕይወት ካለም ተጠያቂው ራሱ መንግሥት መሆኑን ነው የዘነጉት። የኦሮሞ መንግሥት ውድቀት፣ ኦሮሞ ሀገር አረጋግቶ መምራት አይችልም የሚባለውን ይትበሃል እያረጋገጡ መሆናቸውም አልገባቸውም። ወናፍ ሁላ ጭንብሉ ነው የተገፈፈው። ያ አላህ በስማም ብለህ እረደው እያለ፣ የሚታረድ የተባለውም ሰው ጥርት ባለ አማርኛ የእናንተው ወገን ነኝ እያለው እየተሰማ፣ ቀሽም ድራማ ሠርተው፣ ከሠሩትም በኋላ ደንግጠው አጥፍተው አፍረው ካፈርኩም አይመልሰኝ ብለው ዋይ ዋይ የሚሉት ሁላ ናቸው የተገለጡት። አይ እነ ኖ ዋር። ደራ ላይ እኚያ የመስጊድ ኢማም ከነቤተሰባቸው ሸኔ ሲያርዳቸው ሲሳለቅ የነበረ ሁላ አሁን አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆኖ ቢዘበዝብ ማን ይሰማዋል? መርጦ አልቃሽ ሁላ። ወንጀለኛ አራጁን ለፍርድ ማቅረብ እንጂ የምን በዘብዘብ ነው። አንተ እጨርሳለሁ ስትል አንተንስ የሚጨርስ ይጠፋልብለህ ነው እንዴ? ገተት ሁላ።

"…አሁን እነ ሽመልስ አብዲሳ መንዳት የሚችሉት የኦሮሞን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ብቻ ነው። የኦሮሞን የሃይስኩልና የመዋዕለ ሕፃናትንም ሊያሰልፉ ይችላሉ። አዎ መንዳት፣ ሆሽ ማለት የሚችሉት እነሱን ብቻ ነው። ያ ደግሞ መብታቸው ነው። የትግሬ ተማሪ ትምህርቱን አቁሞ፣ የዐማራ ተማሪ ትምህርቱን አቁሞ በጦርነት እየነደደ የኦሮሞ ተማሪ ተረጋግቶ መማሩ ራሱ አስቂኝ ነበር። እናም ጥሩ ነው። ደጋግመው ቢወጡ እንደውም ሸጋ ነው። ተምሮስ ሥራ የለ። ስለዚህ ቢሰለፉ መልካም ነው። ቆይቶ ያው ሰልፍ ብለው የወጡትን ብልጽግና መልሶ እየረበሹ ነው ብሎ አፍሶ ወስዶ መከላከያ ነው የሚያድርጋቸው። የናዝሬት፣ ሞጆ፣ ዱከም፣ ደብረዘይት አፈሳ በቂ አልሆነም። አሁን ይሄን ሀገር ተርቦ ዳቦ እየወረወረ አድማ የጀመረን የኦሮሞ ጥጋበኛ ተማሪ ራሱ ብልጽግና ሸክሽኮ ልክ ያገባዋል። በፌክ አጀንዳ መነዳት ትርፉ ይሄው ነው።

"…በደቡብ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ ስላልተክፈላቸው ሥራ መሄድ አቁመዋል። ለመንግሥት ሠራተኞች መስከረም ላይ ይጨመራል የተባለው ደሞዝ ይኸው የገና ጾም ገባ ወፍ የለም። ድሮን የሚገዛው የአቢይ አገዛዝ ነዳጅ ማስገባት አቅቶት በክልል ነዳጅ የለም። ቤት ፈረሳው ለጉድ ነው። እናም ይሄን ይሄን ሁሉ ትኩረት ለመበተን ያመጡትን አጀንዳ ተሸክመህ ብታዘጠዝጥ ትርፉ ራስህን የባሰ የሞት አደጋ ውስጥ መክተት ነው። ዐማራ እንኳን ሊያርድ የማረካቸውን የብራኑ ጆላን ጦር ነጭ ማኛ የጤፍ እንጀራ እንደሚያበላ ማን በነገራቸው። ማረድ የማን እንደሆነ በዚህ 6 ዓመት ታየ እኮ። ዋነኛው አታጅ የአራጆች አለቃ አቢይ አሕመድ ብትነኩኝ 100 ሺዎችን በአንድ ሌሊት አርጄላችሁ ነው የምወርደው አለላችሁ እኮ። ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድለው በዐማራ አሳበው፣ ለፖለቲካቸው ትርፍ ሻሸመኔን ጨምሮ መላ ኦሮሚያ ውስጥ …👇④ ከታች ይቀጥላል…

4 weeks, 1 day ago

👆③ ከላይኛው የቀጠለ… "…ይሄ አሁን በትግል ያለው የዐማራ ብሔረተኛ ገና ጀማሪ ብሔረተኛ ነው። እንደ ትግሬ ብሔረተኛ በብሔረተኝነት ጥርሱን የነቀለ ብሔርተኛ አይደለም። እንደ ኦሮሞ ብሔረተኛ እንደ ዳውድ ኢብሳ በብሔረተኝነት የሸመገለ፣ እንደ ስብሃት ነጋም የጃጀ አይደለም። ከነ ተግዳሮቶቹ አሁን ያለው የዐማራ ብሔረተኛ የዐማራ ብሔረተኝነትን በቅርብ የጀመረ እና ብሔረተኝነቱም ገና ዳዴ በማለት ላይ ያለ ብሔረተኝነት ነው። እናም ከህወሓትና ከኦሮሞ ብሔረተኝነት ተሞክሮና ልምድ እየወሰደ ይሄዳል ማለት ነው። ኦነግ ኦሮሞን ህወሓት ትግሬን ነፃ ለማውጣት በይፋ በሕጋዊ መልኩ እንደሚንቀሳቀሱት ፋኖም የዐማራን ሕዝብ በትግሬና በኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ከደረሰበት ግፍ ነፃ ለማውጣት ይታገላል ማለት ነው። ኦሮሞና ትግሬ በኦሮሞው መንግሥቱ ኃይለማርያም ደረሰብን የሚሉትን ግፍ በመታገል ዐማራን እንደሚከሱት የዐማራ ፋኖም በትግሬዋ ህዋሓት፣ በኦሮሙማው ደርግና ብልፅግና የደረሰበትን ግፍ ፕሮሞት እያደረገ፣ እያስተዋወቀ ይታገላል ማለት ነው። ትግሬና ኦሮሞ ነፃ ለመውጣት ሲታገሉ ዐማራም ነፃ ለመውጣት የማይታገልበት ምክንያት የለም። ለኦሮሞና ለትግሬ ነፃ አውጪዎች የተፈቀደ መጨማለቅ ለዐማራ ነፃ አውጪዎች የሚከለከልበት ምክንያት የለም። ትግሬና ኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ብረት አንሥተን ታግለን ነው እዚህ የደረስነው እንደሚሉት ዐማራም ብረት አንሥቶ ያቀደበት፣ ያለመበት የማይደርስበት ምንም ምክንያት የለም። እነሱ ሺዎችን ገብረን ነው ዛሬ የተከበርነው እያሉ እንደሚፎገሉት ሁሉ ያለ መስዋእትነት ስርየት የለም እንዲል መጽሐፍ ዐማሮችስ ደም ገብረው፣ ሞተው፣ ተጋድለው፣ በብላሽ ከመሞት ወጥተው ድልን የማይጎናፀፉበት ምንም ምክንያት የለም። ሌሎች ሲሠሩት ጽድቅ ዐማራ ሲሠራው ኩነኔ፣ ርግማን የሚሆንበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም።

"…ዐማራ አሁን እንቅፋቶቹን ሁሉ በሚገባ ዐውቋል። ለይቷል። እንኳን መንገድ ላይ የኦሮሞ ነፃ አውጪ፣ የትግሬ ነፃ አውጪ፣ ሻአቢያና ግብፅ ያስቀመጡትን ይቅርና፣ አማሪካና እንግሊዝ፣ አውሮጳና አረብ ያስቀመጠውን ወጥመድ ዐውቋል። አይደለም የውጪው የውስጡን የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላዎች በሚገባ ዘአውቋል። ለይቷል። ለዚህ ነው የውስጥ የበግ ለምድ የለበሱትን ተኩላዎች እነ ግምባሩንና እነ ስኳድን ለይቶ የገንዘብ ምንጫቸውን አድርቆ እንደ በለስ አድርቆ ያስቀራቸው። የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ዐማራን እየከሰሱ ግማሽ ምዕተ ዓመት ፈጅተውም ማፈራረስ ያልቻሉትን የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በአንድ ዓመት ትግል እንኩትኩቱን አውጥቶ ያፈራረሰው ዐማራ ዐማራ ስለሆነ ነው። ጥቂት ሲቆይ ደግሞ ታየዋለህ። ይሄ መሃይሙ፣ ደናቁርቱ፣ ደንታ ቢሱ፣ አጋሰሱ፣ ርጥብ ፋራ ሰገጤው፣ ሆዳሙ፣ አጋሰሱ፣ ለዐማራነቱ ደንታ የሌለው፣ ክብሩን በቲክቲክ ላይ ያወረደው፣ ጆሮ ጠቢው፣ ደንቆሮው፣ እንደ እከ ለሽ ብሎ የተኛው ዐማራ ነቅቶ ሲነሣ ደግሞ በዚያች ሀገር የሚፈጠረውን ዕድሜ ሰጥቶን አብረን ለማየት ያብቃን። ከፋፋዩ ስኳድና ፌክ ኢትዮጵያኒስቱ የእነ እስክንድር ነጋ ጋሬጠናት አብቅቶ በጫካ ያለውም ዐማራ ወደ አንድነት መጥቶ አንድ ሲሆን ብላችሁ ደግሞ አስቡት።

"…ወያኔና ኦህዴድ፣ ኦነግ አንድ ላይ እየሠሩ፣ ብልፅግና ኦህዴድ እና ኦነግ፣ ኦነግ ሸኔና ኦፌኮ አንድ ላይ እየሠሩ። በድኑ ብአዴን ህወሓትን እየናፈቀ፣ ለኦነግ እየተገረደ፣ የዐማራ ሚሊሻን፣ የአድማበታኝ ፖሊስን የገዛ ወገኑ ላይ እያዘመተ። እስክንድር ነጋ የተባለ ደንቃራ ፀረ ዐማራ ፌክ ኢትዮጵያኒስት የሆነ ሾተላይ ሰውዬ ከጎጃም በቀር ሸዋን ሁለት ቦታ፣ ወሎን ሁለት ቦታ፣ ጎንደርን ሦስት ቦታ ከፍሎ የዐማራን አንድነት ከፋፍሎ፣ ዳያስጶራ ዐማራው አሁንም የግንቦት 7፣ የፌክ ኢትዮጵያኒስቶቹ መንፈስ ሳይጠፋለት እንዲሁ በደመ ነፍስ እየቃተተ፣ እንደ ትግሬና ኦሮሞ አንድ ላይ መቆም አቅቶት እንደ ገበቴ ላይ ውኃ፣ እንደ ባህር ላይ ኩበት እየዋለለም እንኳ ዐማራው በነቁት ጥቂት ልጆቹ ወደ መስመር እየገባ ነው። ይሄ ነው መሬት ላይ ሂዊንና ኦነግን ያስደነገጠው።

"…ዐማራ የሰሞኑም የደራ ሁኔታ ለፖለቲካ የበላይነት ነው እየተጠቀመበት ያለው። የሳይበር ላይ ዐማራው እንደ ድሮ አይደለም። በቶሎ አይደነግጥም። እነ ቤተልሄም ዳኛቸው ሳይቀር ነጠላ ዘቅዝቀው የሚያስለቅሱት ዐማራ አሁን ላይ የለም። እነ ሞጣ ቀራንዮ የሚመሩት የሳይበር ላይ ውጊያም የለም። ዐማራው ብልህ ሆኗል። ይሄ ረጋ ማለቱ፣ ይሄ አለመደንገጡ፣ በሚሰጠው አጀንዳ ያለመረበሹም አሸናፊ አድርጎታል። አጀንዳ ተፈጥሮ ተበትኖ እንኳ ዐማራው ኬሬዳሽ ሆኖ እየሳቀ ሳያራግብ መቆየቱዛሬ ላይ አሸናፊ አድርጎታል። ዐማራው አስሬ ለክቶ አንዴ መቁረጡ ጠቅሞታል። ብልህ ሆኗል። ለዚያ ነው ተደራጅተው መጥተው የነበሩት የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የጴንጤና የአክራሪ የወሃቢይ እስላሞችን የበከተ፣ የሻገተ፣ ቀሽም ፕሮፓጋንዳ አፈር ከደቼ ያስጋጠው። ያበላው። እነ ሎዛ አምቼ ትግሬዋ፣ ለኦሮሞ በመገረድ እልል በሉልኝ እያለች ያለችዋ፣ እነ ደሩ ዘሀረሩ፣ እነ ማንትስ ሊያ ወዘተን ዱቄት ያደረገው ዐማራው ቀድሞ ወሬውን እንደሰማ ነጠላዬን አቀብሉኝ እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ስላቆመ ነው። የበፊቱ የሳይበር ዐማራ የጠላት አጀንዳ በጅምላ ገዝቶ በችርቻሮ ይሸጥ የነበረ ስለነበር ነው አድካሚ የነበረው። የአሁኑ ዐማራ ነቄ ሆኗል። እንደ ድሮው ሞጣ ምን አለ? ዮኒ ማኛ ምን አለ? ብሎ ሳይሆን "በዚህ ጉዳይ ላይ ዘመዴ ምን አለ? ያ የሀረርጌ ቆቱ መራታው ዘመዴ ምን ብሎ ጻፈ? ያ የሥላሴ ባርያ፣ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው ባለ ማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ አክሊለ ገብርኤል ምን አለ? ብሎ ጠብቆ ነው። ባይገርምላችሁ ሃገር ታምሶ የእኔ ቤተሰቦች፣ የቲክቶክም የመረጃ ቲቪ ቤተሰቦቼ በሙሉ እኔ እስክናገረው ድረስ አንኳ በውስጥ መስመር እንኳ መጥተው አይጨቀጭቁኝም። በቃ መብሰል ማለት እንዲህ ነው። አንድ ሰው ከተረጋጋ ሕይወቱ የሰመረ ይሆናል። የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል እንዲሉ የሸኖ ቅቤ ነጋዴዎች። ኢንዴዢያ ኖ።

"…ዐማራው ሥራው ላይ በማተኮሩ ምክንያት፣ ዓለም የሚያየው ሥራ እየሠራ ሥለሆነ ይሄን የዐማራ ፋኖ አላደረገውም ብለው መነስከር የጀመሩት ራሳቸው የኦሮሞ አክቲቪስቶች ናቸው። ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋቢሳ፣ እነ መስፍን ፈይሳ ጭምር ይሄ ነገር ልክ አይደለም በማለት፣ ፊልሙም የቆየ ነው። ቦታውም ደራ አይደለም የሚሉ ሁላ ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። እነ ትግሬው ሴቭ ኦሮሚያ ጭምር የለጠፉትን ቪድዮም አወረዱ። ዐማራው ለጉዳዩ ትኩረት ነፍጎ ኬሬዳሽ ሲሆንበት አጀንዳውን የሚያራግብ ጠፋ። ድሮም አጀንዳ ተሸክሞ አራጋቢው ዐማራ ነኝ ባዩ አንዳንድ ገተት ዐሞራ መሳይ ስለነበር አሁን ማን ያራግበው? ከሰሩ። ራሱ አገዛዙ ገበባበት። የሚያጯጩህለት ሲያጣ አገዛዙ ራሱ በለገሰ ቱሉና በኮሬ ነጌኛው ኃይሉ ጎንፋ አማካኝነት ዘለው ገቡበት። እነ እስታሊን ሳይቀሩ ይሄን አጀንዳ ባለማራገባቸው ተሰደቡ፣ የትግሬ የቲክቶክ አክቲቪስቶች እንደ ከፍት፣ እንደ እንስሳ የሚነዷቸውን የኦሮሞ የቲክቶክ ላይ አክቲቪስቶች ወረዱባቸው። (ቬድዮው አለኝ) ዐማራው ግን ጆሮ ዳባ ልበስ አለው። ይሄ የደራው አጀንዳ ለዐማራው ያመጣለትን በረከት መጨረሻ ላይ አስቀምጠዋለሁ።👇 ③ ከታች ይቀጥላል…

1 month ago
መልካም…

መልካም…

"…ውይይቱ ይቀጥላል። በወልቃይት ጉዳይም አሁን አሁን ማንንም ሳትፈሩና ማንንም ሳታፍሩ ደፈር ብላችሁ መነጋገር መጀመራችሁም ያስመሰግናችኋል።

"…ነገ የተቀበል መርሀ ግብራችን የሚቀርብብት ዕለት ነው። ቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብር የሚሆኖ ግጥም፣ ቅኔ፣ አጫጭር አስቂኝ ቪድዮዎችን አዘጋጅታችሁ ጠብቁን።

• ማሳሰቢያ፦

"…ፎቶው ባልተዛር ጋር ከሚባለው ሶዬ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ደግሞ ክፉ ነገር እያሰባችሁ እንዳታስቀስፉኝ።

• እየጸለያችሁ…🙏🙏🙏

1 month ago

👆② ከላይኛው የቀጠለ… "…ሌላው የወልቃይት ጉዳይ ነው። እኔ ኮሎኔል ደመከ ዘውዱን በግልጽ ጥያቄ ሳነሣበት ጎንደሬ ነኝ የሚል ዐማራውም፣ የትግሬ ዲቃላ ስኳዱም እሪሪ ብሎ ነበር የጮኸብኝ። ደመቀ ትግሬ ነው። ፕላን ቢ አድርገው ትግሬዎቹ ለክፉ ቀን ያስቀመጡት ልጃቸው ነው። ደመቀ ከወልቃይት ዐማራን ያጸዳ ሰው ነው። ወልቃይትን ጎንደሬ ዳግም ይበላል። መከላከያ ከወልቃይት እየተነሠሣ ነው የጎንደር ዐማራን የሚጨፈጭፈው። ደመቀ ዘውዱ ብልጽግና ነው። ደመቀ ዘውዱ አሳልፎ ወልቃይትን ለወያኔ ይሰጣል ብዬ ስለፈልፍ አፈር ከድሜ የምግጥ አይደለሁም እንጂ አፈር ከድሜ እኔን ለማስጋጥ የተሰለፈውን ሕዝብ ታስታውሳላችሁ። አይደል ምእመናን።

"…ይኸው ትናንት ዐማራው ጎንደሬ በወልቃይት ምክንያት የወጣውን ዜና ተመልክቶ ምንድነው ነገሩ? ምን ጉድ ነው የመጣብን? ምን ዓይነት ነገር ነው? what's going on, ምንድነው የምንሰማው ነገር፣ ምንድነው የምናየው ነገር በማለት ዋይዋይ ሲሉ ነው የዋሉት። የትግራይ አክቲቪስቶች እንደ ትልቅ ድል ቆጥረውት "ተመዛበልቲ ወደ ገዛኦም ተመሊሳ" እያሉ ሲዘግቡ፣ በማይካድራ ጭፍጨፋ፣ በወልቃይት ጭፍጨፋ ተሳትፈው የነበሩ የወያኔ የጦር መኮንኖች አቢይ አሕመድ በላከላቸው አውሮጵላን ተሳፍረው ወልቃይት ሲደርሱ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አውሮጵላን ጣቢያ ድረስ ሄዶ ሲቀበላቸው የተለቀቀው ፎቶ የጎንደርን ዐማራ ጆሮ ጭው ሲያደርግ ነው የዋለው።

"…ባይገርምላችሁ ጎንደሬ ሆነው ሁል ጊዜ ስለወያኔ ብቻ የሚጽፉ ፔጆች ላይ ሄድኩኝ። እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ፔጅ ላይ ገባሁ ምንም ወፍ የለም። የወልቃይት ጉዳይ፣ የኮሎኔል ደመቀም ጉዳይ ቀይ መስመራችን ነው ብሎ በሚታወቀው ፉከራው የሚታወቀው ባህርዳር አድጎ ፀረ ጎጃሜ የሆነው የደቡብ ጎንደሩ አያሌው መንበር ፔጅ ገባሁ። እንደውም የዛሬ ስድስት ቀን የማይካድራን ጭፍጨፋ ከለጠፈ በኋላ ምን እንደሰማ አይታወቅም ድራሽ አባቱ ነው የጠፋው። ሙላት አድኖ ቤት ገባሁ ወፍ የለም። ሙላት የፈራ ይመለስ ዛሬም ጎጃሜን ነው የሚወቅሰው። አረጋ ከበደ ብራኑ ጁላን ሸለመው ብሎ ነው የሚያለቅሰው። ሲሳይ አልታሰብ የአሸቦ ዕቃው ወዳጄ ቤት ገባሁ። ወፍ የለም። ሙሉዓለም ገረ መድህን ኡጋንዳ ሆኖ ትንፍሽ አላለም። ብቻ what's going on የሚል ብቻ ነው የበዛው። ኮሎኔል ርስተይ ተስፋይ እና አስፋው አብርሃ ብቻ ናቸው ደፍረው እንኳን በደኅና መጻዕኮም ኮሎኔሎታት ብጻይ አሐወይ ብለው የተነፈሱት።

"…የጎንደር የዐማራን ፋኖ ለ3 የከፈሉት ሁሉ ዛሬ ጮቤ እየረገጡ ነው። ወልቃይትን ነጻ ለማውጣት የሞቱ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎ እና የጎንደር ዐማሮችን ነፍስ ይማር። ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይከፋሽ ነው አይደል የሚባለው? ጎንደር ለዳግም ስደት ተዘጋጅ አልያም አንድ ሆነህ ጠላትን ለመጋፈጥ ተዘጋጅ። ባርነት ወይም ነፃነት ምርጫው የአንተው ነው። ዳግም ከመጡ ግን ለዘር አያስተርፉህም። ይሄን በደንብ ዕወቅ። ተረዳ። ወልቃይት ላይ አያቆሙም። ከአክሱም እንዳባረሩህና ጎንደር እንደወሸቁህ አሁን ከጎንደርም ድራሽ አባትህን ነው የሚያጠፉህ። አዲስ አበባና ኡጋንዳ መሰደድ አያዋጣም። ወደ አሜሪካና አውስትራሊያ፣ ወደ አውሮጳም መሰደድ አያዋጣም። ትግሬውን ኮሎኔል ደመቀ በጎንደር ዐማራ ስም ሲሸውድህ ፋራ ዥል፣ ዥልጥ ሆነህ ከተሸወድክ በኋላ አሁን ማለቃቀሱ ዋጋ የለውም። የፈሰሰ ውኃ አይታፈስም። በዚሁ ከቀጠለ በቅርቡ ወልቃይት የወያኔ ይሆናል። መዝግቡልኝ።

"…ስኳዶች አትደበቁ። ውጡና ተናገሩ። የእኔ ጦማር ያበሳጫል፣ ደም ያፈላል፣ ይጎረብጣል። ግን ኮሶ ነው ያሽራችኋል። ግን መድኃኒት ነው ይፈውሳችኋል። አትደበቁ። የማይነጋ መስሏችሁ ነው ቋት ውስጥ ያራችሁት እናንት በጠጣም ፀረ ጎንደሬ፣ ፀረ ዐማሮች። አሁን የት ትደበቁ? የት ትገቡ? ውጡና ተንፍሱ። ተናገሩ። በአፄ ቴዎድሮስ ስም እየማሉ፣ በጎንደር ሙዚቃ እየደነሱ፣ በፋሲል ግንብ እያጌጡ ወልቃይትን አደንዝዘው ያሳጧችሁን ለይታችሁ ውቀሱ። ጎንደሬዎች ትደነዝዙ ዘንድ የመገጭ ግድብ ይሠራላችኋል። የፋሲል ግንብ፣ የከተማዋ አውራ መንገድ በኮሪደር ልማት ቀለም፣ በመብራት ይሸቆጠቆጥላችኋል። እሱን እያያችሁ ወልቃይትን ይረከቡአችኋል። ይሄን ስላልኩ ፎክር፣ አቅራራ አሉህ አንት እስኳን ፀረ ጎንደር ዐማራ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው። ፎክር።

"…በመጨረሻም ዐራቱም የዐማራ ፋኖ ዕዞች ወደ አንድ ለመምጣት የጀመሩትን ጉዞ ዐውቃለሁ። የወሎው በምሬ ወዳጆ፣ የጎንደሩ በባዬ ቀናው፣ የጎጃሙ በዘመነ ካሤ እና የሸዋው በኢንጂነር ደሳለኝ የሚመሩት ዕዞች ማለት ነው። ብዙ መንገድ ሄደዋል፣ ለፍተዋል፣ ደክመዋል። እየጣሩም ነው። ነገር ግን አሁን ላይ እነዚህ ዕዞች ወደ አንድነት እንዳይመጡ አንደኛው ዕዝ ላይ ሴራ እየተሴረ እንደሆነ እየሰማሁ ነው። ይኸውም ዕዝ የጎንደሩ የእነ ባዬ ቀናው ዕዝ እንደሆነም እየሰማሁ ነው። ይሄን ወደ አንድነት እንዳይመጡ የመጎተት ሴራው ደግሞ በጎንደሩ በእነ ባዬ ቀናው የጎንደር ፋኖ በኩል ይመስላል። ምክንያቱ ደግሞ አንድነቱን እያዘገየው ያለው በሴራ ነው ተብሏል። ሴራውም የተጎነጎነው የእነ ሀብቴ ወልዴ ቡድን ከእስክንድር ነጋ ድርጅት መውጣቱን በይፋ በግልፅ ሳይናገሩ፣ በጎን የጉንደር እዝ ወደ አንድ ልንመጣ ነው እያሉ የእነ ባየ ቀናው ዕዝ ከእነ ዘመነ፣ ከእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ፣ ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር ሊመሰርቱ ያሰቡት የፋኖ ኃይል ላይ እንቅፋት እየሆኑ መሆናቸው ነው የተሰማው። ለማንኛውም ጥንቃቄ ያስፈልጋል። እስር ቤት ያሉትም ከእስርቤት መልእክት እየላኩ አንድነቱን ባያዘገዩት ይመረጣል።

"…ለጊዜው ሊመጣ ከጫፍ የደረሰውን አንድነት አርበኛ ዘመነ ካሤን በመግደል ለማስተጎገል ታስቦ ነበር። እሱን እግዚአብሔር አከሽፎታል። ቀጣዩንም ሴራ እግዚአብሔር ያከሽፈዋል። ዝርዝሩን የምጽፈው ጉዳዩ አደገኛ አዝማሚያ ሲይዝ ብቻ ነው። መቼም የምለው ይገባችኋል። አለቀ።

• በዐማራ ትግል ላይ ደንቃራ የሆኑትን ሾተላዮች በሙሉ በጋራ ሆነን በእውነት ሰፌድ እናበጥራቸዋለን…!

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 6/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

1 month ago

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ሰሞኑን ታዝባችሁልኝ ከሆነ በሸዋ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ስር የሚተዳደረው የእነመከታው ፋኖ ቡድን በተደጋጋሚ ወደተለያዩ ሚዲያዎች እየወጣ ስለፋኖ አንድነት፣ ከአንድነት ውጪ ሌላ ምርጫና አማራጭም እንደሌለ፣ ሳይጠየቅ እየለፈለፈ ነው። ከእነ ምሬ ወዳጆ ጋር፣ ከእነ ዘመነ ካሤ ጋር፣ ከእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ጋር በጋራ ለመሥራት እየተነጋገርን፣ በደንብ እየሄድንበት ነው የሚል መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል። ይሄንኑ መግለጫም በጎንደሩ ስኳድ በፓስተር ምስጋናው ሚዲያና በመሳይ መኮንን ሚዲያ ላይ በመቅረብ አቤ ጢሞና መምህሩ ሲደሰኩሩም ተሰምቷል። አለቃቸው ፋኖ መከታውም በቪድዮ መልእክት ወጥቶ ከወንድሞቻችን ጋር በግድ ከመታረቅ፣ አንድ ከመሆን በቀር ሌላ አማራጭ የለንም ሲል ተሰምቷል።

"…ምኞቱ ጥሩ ነው። ጥሩም ነበር። ነገር ግን ምንድነው ዛሬ እንደዚህ ታስሮ እንደተፈታ ሰው እንደ ግሪሳ ወፍ ከነ ወጥተው ዋይዋይ ያስባላቸው? ምን ሆነው? ምን አግኝተው ነው እንዲህ አደባባይ አውጥቶ የፍቅር፣ የአንድነት ሰባኪ ያደረጋቸው? ድንገቴው ነገር ምንድነው? ይሄንን ለመመርመር ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መልስ ግን እነርሱ ከሚያወሩት በእጅጉ የተለየ ነው። መሬት ላይ ያለው የኃይል አሰላለፍ ነው እነ መከታውን የአቡኤን መገበሪያ እንደበላ ሰው ያስለፈልፋቸው የጀመረው። ብዙ ሰዎች በሸዋ ጉዳይ የሸዋን ፖለቲካና የሸዋ ፋኖን እንቅስቃሴ የሚከታተሉ አካላት ነገሩ በደንብ ይገባቸዋል። ለምን የእባብ መርዝ እንደቀመሰ ፍየል ማርከሻውን ፍለጋ እንደሚንጠራወዙ ይገባቸዋል።

"…እነመከታው በእስክንድር ምክንያት ደጋፊ አጥተዋል። በእስክንድር ምክንያት በሳምንት ይፈስላቸው የነበረውን 20 እና 30 ሺ ዶላር አጥተዋል። እነ መከታው ከተዋጊ ፋኖዎቻቸው በእስክንድር ጉዳይ ለሚነሳባቸው ጥያቄ ምንም ዓይነት ምላሽ ባለመስጠታቸው ከእነ መከታው የፋኖ አደረጃጀት የሚወጡ ብርጌዶች፣ ተዋጊዎች ዕለት ዕለት እየጨመሩ መምጣት፣ ክፍለ ጦሮችም ከጠቅላይ ዕዙ ለመለየት መግለጫ ማውጣት መጀመራቸው፣ እነሱ ተንፈላሰው ይኖሩበት የነበረው ቀጠና በተዋጊ ዕጦት መሳሳት መጀመሩ አሳስቧቸዋል። እስክንድርን ይዘው ሚልዮን ዶላሮችን ለማፈስ፣ እስክንድርን ይዘው በድርድር በአቋራጭ ሥልጣን ለማግኘት በመጓጓት የሠሩት ስህተት ከባድ አርታኢሌ የሆነ ስጋት ውስጥ ከትቷቸዋል። እናም ስለዚህ ያላቸው አማራጭ ሳይጠየቁ መለፍለፍ፣ ሳይለመኑ የሰላም፣ የአንድነት ሰባኪ መሆን ብቻ ነው። ግን ረፍዷል።

"…እነመከታውን ነግሬአቸው ነበር። የሸዋ ተወላጅ ግማሽ ሚልዮን ዶላር የረዷቸው ሰዎችም ነግረዋቸው ነበረ። ከጎንደር ስኳድ ከፖለቲካው ቅማንት ከትግሬ ዲቃሎች ጋር ያላችሁን ግኑኝነትም አቁሙ ተብለው ነበረ። እስክንድርን ከመካከላችሁ አውጡት፣ ወይም በእናንተ ስር ገብቶ ይታገል፣ ሸዋ ተቀምጦ፣ በመከታው ጀሌ እየተጠበቀ፣ በሸዋ ግንባሩ፣ ሠራዊቱ፣ እያለ እንደ ኢንኪዩቤተር የፖለቲካ ጫጩት፣ ያውም የማያድጉ፣ ካካቸው የበዛ የፖለቲካ ድርጅት አይፈልፍል ቢባሉም አልሰሙም። ምክር ናቁ። በሽምግልናው ወቅት እነ መከታው የወከሉት ፓስተር ዮናስን ነበር። እነ ደሳለኝ የወከሉት ደግሞ ዶር አብደላን ነበር። እነ ዶር አብደላ የጠየቁት አንዲት ጥያቄ ብቻ ነበር። እነ መከታው የወሰዱብንን አንዲት የግላችን ንብረት መልሱልን። እነ መከታው የወከሉት ፓስተር ዮናስ ግን ስለዚህ ነገር የማውቀው ነገር የለም። እነ አሰግድ በእኛ ስር ከገቡ ይግቡ፣ ካልገቡ ግን አንለማመጣቸውም። እነሱን ለመደመስስ ግማሽ ሰዓት አይፈጅብንም ነበር ያለኝ። በሁለቱም በኩል መሬት ላይ የተመደቡትን ሽማግሌዎች ይሄ የእነ መከታው ፓስተር ነው አፈር ከደቼ ያበላው እና በትእቢት ነገርየውን እንዳይሆን ያደረገው። አሁን እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም የሸዋ ፖለቲካ የእነ መከታው ደጋፊ ሆነው ሲመጡ ነጥቦቹን ስገጣጥም ያገኘሁት ሥዕል የሚያሳየኝ የሸዋ፣ የእነ መከታው ትግል በብልፅግና ወንጌል ፓስተሮች ጭምር መጠለፉን ነው።

"…የሆነው ሆኖ የዐማራ ትግል የግዱን እየጠራ ይመጣል። በረሀ ወርጃለሁ ብሎ ጺምን ኦ እየተቆረጡ፣ ሁሌ ሥጋ፣ ሁሌ ፍየል እየበሉ፣ ስቴኪኒ ይዘው እየዞሩ፣ ሚስቶቻቸውን እና ገርል ፍሬንዶቻቸውን አቅፈው እየተኙ፣ አንዲት ከተማ ሳያስለቅቁ፣ የገበሬ ከብትና ፍየል፣ ሙክት ብግ ዳያስጶራ ደም ተፍቶ የሚልከውን በሸነና እያሉበት መቀጠል አይቻልም። እንደ ላስታ፣ እንደ የዐማራ ፋኖ በወሎ ልጆች ያለ ውጭ እርዳታ ሙጫና በለስ፣ አጋምና ቀጋ እየበሉ በመታገል ጠላትን ድል ማድረግ ይቻላል። እንደነመከታው እና እስክንድር ገጠር ተቀምጦ በዐማራ ፋኖ ትግል ቦርጭን አንዘርጥጦ ጽድት ብሎ መንገማሸር ፌር አይደለም። ሊወገዝ ይገባል። የህልውና ትግል ያለበት ፋኖ ዶላር ሲቀርበት ዋይዋይ አይልም። ፋኖነትን ለኑሮ ማሸነፊያ ማድረግ ስህተት ነው። ትልቅ ጥፋትም ነው። ደያስጶራው በዚህ በኩል ስሜታዊ፣ ደንታቢስ ሆኖ ሳይሆን መርምሮ፣ አጥንቶ፣ በዐማራ የፋኖ ትግል ውስጥ በተጨባጭ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚጨበጥ ትግል በማድረግ ላይ ያሉትን ፋኖዎች ለይቶ በማውጣት እርዳታ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት። የሸዋ ተወላጅ የዐማራ ዳያስጶራዎች ያደረጉትም ይሄንኑ ነው። እነመከታውን ይረዱ፣ ይደገፉ ነበር። እነመከታው ጠገቡ፣ ወበሩ፣ የእስክንድርን ሚልዮን ብር ሊቀራመቱ ምራቃቸውን ዋጡ። ስለዚህ ቋሚ ደጋፊዎቻቸውን አሳዘኑ። የሸዋ ተወላጆችም እነመከታው ትእቢታቸው ጣሪያ ሲነካ ሽፍት አደረጉ። ወደ እነ ደሳለኝ ፊታቸውን አዞሩ። ወደከሰም፣ ወደ ቡልጋ ፊታቸውን አዞሩ። አሁን የእስክንድር የለመንለት ዶላር ሲጠር እነመከታው ኪሳቸው ባዶ ሲሆን፣ ሲራቆት፣ እነ ፓስተር ምስጋናውም ዱዲ ሳንቲም እንደማይሰጧቸው ሲያውቁ በየሚዲያው ወጥተው ከዘመነ ካሤ ጋር ልንታረቅ ነው። ከነ ምሬ ወዳጆ ጋር አንድ ልንሆን ነው፣ ከእነ ደሳለኝ ጋር ልንተቃቀፍ፣ ልንሳሳም ነው… ብላ ብላ…  ፓስተር ዮናስን ምን አልኩት። ታያለህ ዮኒዬ ኃይል የእግዚአብሔር ነው። እንዲህ እንደታበያችሁ ቀን መጥቶ ዘጭ ብላችሁ አፈር ደቼ ባትግጡ ምናለ ዘመዴ በለኝ ብዬ ነው እቅጩን የነገርኩት። የሆነውም የተናገርኩት ነው። ትእቢት እንዲህ ብርድ ብሎ ሲታይ ደስስ ሲል።

"…ከዚህ ሁሉ በኋላ በዛሬው ዕለት የእነ መከታው ቡድን በሸዋሮቢት ከመከላከያ ጋር እየተዋደቀ መሆኑን ይፋ አድርጎ በእነ መዓዛ መሀመድ ሮሀ ሚዲያ ሲዘገብ ታይቷል። በአካባቢው ምንድነው የሆነው? የእነ መከታው ጦር መከላከያ ላይ ለምን ተኮሳችሁ እያለ ፋኖዎችን የሚቀጣው ቡድን እንዴት ደፍሮ ተዋጋ ብዬ ወደ አከባቢው ደውዬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ የሚያሳየው እነመከታው እንዳልተዋጉ፣ ወደ መጨረሻው አካባቢ ሕዝቡ አስገድዶ ዲሽቃ እንዲሰጥ እንዳስደረገና፣ ቅር እያለው ዲሽቃ ይዞ የእነ መከታው ቡድን ወደ ስፍራው እንደሄደ ነው የተነገረው። የጦርነቱም መነሻ በአካባቢው ያለ የመከላከያ ኃይል በሸዋሮቢት ዙሪ ዝም ብሎ በዘፈቀደ የተኮሰው መድፍ አንድ ደገኛ የዐማራ ገበሬ ይገድላል። በሁኔታው የተበሳጨው የሸዋ ሮቢት ዙሪያ ገበሬ መከላከያን ባለው መሳሪያ ይገጥመዋል። ከዚያም መከላከያው ያልጠበቀው ዱብ ዕዳ ይገጥመዋል። መከላከያው ተረፈረፈ። ከዳር ቁጭ ብሎ የሚያየውም የመከታው ጦር በአስቸኳይ እንዲቀላቀላቸው ጥሪ ገበሬው አቀረበ። ሳይወዱ በግዳቸው ዲሽቃ ይዘው መጥተዋል። የሆነው ይሄው ነው ብለዋል የአካባቢው የመረጃ ምንጮቼ። …👇① ከታች ይቀጥላል…

1 month, 1 week ago
ተቀበል…2

ተቀበል…2

"…የቅዳሜ ከሰዓት ተቀበል መርሀ ግብራችን እንደቀጠለ ነው። አድማጭ ተመልካቾቻችንም ከያሉበት ሆነው ተዋዱጁን የተቀበል የግጥም መርሀ ግብራችንን እየተከታተሉ መሆናቸውን በሚያደርሱን የፎቶና የቪድዮ መረጃ እያሳወቁን ነው።

• ተቀበል… እየገጠማችሁ…

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 days, 16 hours ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 3 weeks, 2 days ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 8 months, 3 weeks ago