Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

Description
ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው።
(ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል።
(إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 month, 1 week ago
***ከረመዳን ጾም በኃላ ከሸዋል ወር ስድስት …

**ከረመዳን ጾም በኃላ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን መጾም ምንዳው ምን ያህል ነው?

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- “ረመዳንን ጾሞ ከዛም በኃላ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን (በመጾም) ያስከተለው አንድ አመት የጾመ ያህል ነው።” ሙስሊም ዘግበውታል

ጣሀ አህመድ

🌐** https://t.me/tahaahmed9

1 month, 1 week ago

**ተክቢራን ማድረግ ከኢስላም ሀይማኖታዊ ምልክቶች (ሸዓኢር) ነው !!

በዒደል-ፊጥር ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰአት አንስቶ ሰላቱ እስኪጀመር በኢደል-አድሀ ደግሞ ከዙል-ሂጃ የዘጠነኛው እለት ፈጅር ሰላት አንስቶ የአስራ ሶስተኛው እለት ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ተክቢራን ማድረግ ከኢስላም ሀይማኖታዊ ምልክቶች (ሸዓኢር) ነው፡፡
ከዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር-ረዲየላሁ ዓንሁማ- እንደተላለፈው:- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የዒደል-ፊጥር እለት ከቤታቸው ወጥተው እስከመስገጃው ድረስ ተክቢራን ያደርጉ ነበር::" (አል-ሃኪም እና በይሃቂይ ዘግበውታል) አልባኒ ኢርዋእ-አልገሊል ላይ ሰሂህ ብለውታል::
አል ኢማም አነወዊይ እንዲህ ብለዋል:- "በሁለቱ ዒዶች ተክቢራን ማድረግ ለሁሉም የተደወደደ መሆኑን ዑለማዎች የተስማሙበት ጉዳይ ነው::"(ሸርህ ሙስሊም)

ጣሀ አህመድ

🌐** https://t.me/tahaahmed9

Telegram

🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

***ተክቢራን ማድረግ ከኢስላም ሀይማኖታዊ ምልክቶች (ሸዓኢር) ነው !!*
1 month, 1 week ago
***በዒድ እለት የመልካም ምኞትን መግለጽን በተመለከተ*

**በዒድ እለት የመልካም ምኞትን መግለጽን በተመለከተ

«የመልእክተኛው ባልደረቦች የዒድ ቀን በሚገናኙበት ወቅት አንዳቸው ለሌኛው "ተቀበለ አላሁ ሚና ወሚንከ" ይባባሉ ነበር።» (ኢብኑ ሀጀር ፈትሁልባሪ ላይ ዘግበውታል አልባኒም ሰነዱ ትክክለኛ ነው ብለዋል)
ትርጉሙም: ‐ "አላህ ከእኛም ከአንተም መልካም ስራችንን ይቀበልን" ማለት ነው።

እንኳን አደረሳችሁ በመባባል የመልካም ምኞትን መግለጽ እና ዱዓእ መደራረግ በሸሪዓ መሰረት ያለው ለመሆኑ ይህ ግልፅ መረጃ ነው።

ጣሀ አህመድ

🌐** https://t.me/tahaahmed9

1 month, 1 week ago

**ታድያ ዱዓእ እናብዛ ማለት ነዋ?!

አቡ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየ አላሁ ዓንሁ) እንዳስተላለፉት:- “ማንኛውም ሙስሊም በወንጀል ወይም ዝምድናን በመቁረጥ ዱዓእ ካላደረገ አላህ ከነዚህ ሶስት ነገሮች አንዱን ቢሰጠው እንጂ አይቀርም:- ወይ በዱንያ ላይ የለመነውን ይሰጠዋል አልያም ለወድያኛው አለም (አኺራ) ያቆይለታል ወይም በዱዓው ልክ መጥፎ ነገርን ያርቅለታል” አሉ:: ሰሀቦቹም ታድያ (ዱዓእ) እናብዛ ማለት ነዋ?! በማለት ጠየቁ:: መልእክተኛውም “ አዎን! የአላህ (ስጦታ) ብዙ ነው ” አሉ::
(ኢማሙ አህመድ፣ አቡ ያዕላ እና ቡኻሪ አል-አደቡል ሙፍረድ ላይ ዘግበውታል) አልባኒም ሀዲሱ ሰሂህ ነው ብለዋል::

ጣሀ አህመድ

🌐** https://t.me/tahaahmed9

Telegram

🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

***ታድያ ዱዓእ እናብዛ ማለት ነዋ?!*
1 month, 1 week ago
***ዱዓእ ተቀባይነት የሚያገኝባት ሰአትን በተመለከተ*

**ዱዓእ ተቀባይነት የሚያገኝባት ሰአትን በተመለከተ

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– "የጁመዓ ቀን ለአስራ ሁለት ሰአታት የተከፋፈለ ነው፤ ታዲያ ከነዛ ሰአታት መካከል አንዲት ሰአት አለች፣ በዚያች ሰአት ማንኛውም ሙስሊም ባሪያ አላህን አንዳች ነገር ቢጠይቅ የለመነውን ቢሰጠው እንጂ፣ ያቺን ሰአት ከዓስር በኃላ በመጨረሻው ሰአት ፈልጓት።"
ሀዲሱን አቡ–ዳውድ እና ነሳኢ ዘግበውታል አልባኒ ሰሂህ ብለውታል

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐** https://t.me/tahaahmed9

1 month, 2 weeks ago

👆👆👆

📚 1. የዘካተ'ል ፊጥር ትርጉሙ፣ ጥበቡ እና ሸሪዓዊ ፍርዱ

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አህመድ የትምህርት መድረክ
https://www.facebook.com/ustathilyas
@ustazilyas

4 months ago

*📌 በተከበሩት ወራቶች ነብሳችንን ከመበደል እንጠንቀቅ!!

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በተከበሩት መልእክተኛ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይሁን። በመቀጠል፤

ያለንበትን የረጀብ ወር በማስመልከት የሚፈፀሙ የቢድዓ ተግባራት ተበራክተዋል። የረጀብን የመጀመሪያ እለት፣ የመጀመሪያ ጁምዓ፣ አስራ አምስተኛውን እለት እንዲሁም ሀያ ሰባተኛውን ቀን ማክበር ቢድዓ መሆኑን፤ በሌሎች ወሮች  እንደሚፈፀሙት የሰኞና ሀሙስ ወይም አያመልቢድ ፃሞች ካልሆነ ወሩን አስመልክቶ የተደነገገ ልዩ ፆምም ይሁን ሰላት እንደሌለ ገልጫለሁ።   ይህ ማለት ግን ረጀብን ከሌሎች ወራቶች የሚለየው ምንም ነገር የለም ማለት አይደለም። 

የረጀብ ወር፤ በሱረቱል ተዉባህ ቁጥር 36  ከተጠቆሙት የተከበሩ አራት ወራት (አሽሁሩል ሁሩም) አንዱ  ነው።

አላህ እንዲህ ይላል፤ 

[إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِنْدَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْراً فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ذَلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ فَلا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنْفُسَكُمْ] التوبة/36 

« አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር፤  በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ (በጥብቁ ሰሌዳ ለውሀልማህፉዝ) ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን (የሰየመው) ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤» አልተውባህ 36

عَنْ أَبِي بَكْرَةَ رضي الله عنه عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ , ثَلاثٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ , وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ) رواه البخاري ومسلم.

ከአቢ በክራህ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «አመት አስራ ሁለት ወራት ነው፤ ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ”ረጀብ” ወር ነው።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ዙልሂጃ የታወቀው የሀጅ ወር ነው፤ 
ዙልቂዕዳ ደግሞ ሁጃጆች ወደ መካ የሚያቀኑበት ወር ሲሆን፤ 
ሙሀረምም ከሀጅ ስነስርአት በኋላ ሰዎች ወደቀያቸው የሚመለሱበት ወር ነው።  አላህ ረጀብንም ከእነዚህ  የረከበሩ ወራት  አድርጎታል። 

እነዚህ ወራት (የተከበሩ) ናቸው ስንል፤

1- እነዚህ ወረሰቶች ጦርነት የተከለከለባቸው ወራት ናቸው።  
ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ከፈፀመባቸው እራሳቸውን ለመከላከል ብቻ ካልሆነ በስተቀር ውጊያ አይፈቀድም።

2- በነዚህ ወራት አላህ ክልክል ያደረጋቸውን ነገሮች መፈፀም በሌላ ወራት ወንጀልን እንደመፈፀም አይደለም። ስለዚህም አላህ እነዚህን ወራቶች ለይቶ ነብሳችንን እንዳንበድል አሳስቦናል፤ «በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ» ። 

እራስን መበደል አስከፊ መሀይምነት ነው። በአንድ ሰውና በጌታው መካከል የሚፈፀም እራስን መበደል ለአላህ መፈፀም የሚገባን ሀላፊነት አለመወጣት ነው። በራስ ላይ ከሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ትልቁ  በአምልኮ ፍጥረታትን ከአላህ ጋር ማጋራት “ሽርክ" ነው። ሰዎች ላይ የሚፈፀም በደልም ቢሆን የሚጎዳው ሰሪዉን ነውና እራስን መበደል ነው። ለራሱ ያወቀ በማንኛውም ጊዜ ከበደል ይርቃል። 

ኢባደላህ!
አላህ እነዚህን ወራቶች አክብሯቸዋልና እኛም ከፍተኛ ክብር መስጠት ይገባናል። 
እነዚህ ወራቶች ሲገቡ፤ አላህ ክብርን እንደለገሳቸው ልናስታውስና ከወንጀል ለመራቅ ያለንን ቁርጠኝነት ልናድስ ይገባል። ይህ ልባዊ ኢባዳ ነው። 

ወንጀልን በማንኛውም መፈፀም የተከለከለ ቢሆንም በነዚህ ወራት ግን ክልክልነቱ የበረታ ነው።

ስለዚህም ከምንም አይነት ወንጀሎች መጠንቀቅ እና ወደ አላህ መመለስ ያስፈልገናል።   ከትናንሽም ይሁን ከትላልቅ ወንጀሎች በአላህ እንጠበቅ። 

ሸይጣንን እናሸንፍ!
አላህ ከጥፋት ይጠብቀን..

አሚን!!

አኹኩም ፊላህ አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ

http://t.me/abujunaidposts

Telegram

🗞 የ አቡጁነይድ መልዕክቶች Abujunaid posts

ይህ በአቡ ጁነይድ ሳላህ አህመድ የቀረቡ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክቶች የሚሰበሰቡበት ቻነል ነው። አላህ ጠቃሚ እውቀትን ከመልካም ስራ ጋር ያግራልን! You can contact me here @salehom100

*****📌*** በተከበሩት ወራቶች ነብሳችንን ከመበደል እንጠንቀቅ!!**
6 months, 1 week ago

#እንድታውቁት

የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን !

አንድ ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው ፦

- በተሽከርካሪው ዓይነት (የቤት አውቶሞቢል፣ የህዝብ ማመላለሻ ወይም የዕቃ ማመላለሻ፣ ልዩ ልዩ)

- የተሸከርካሪዉን የመጫን አቅም (የሰው ብዛት፣ የጭነት ኪሎ መጠን)፣

- ጉልበት (ለቤት አውቶሞቢሎች) መሰረት በማድረግ እንዲሁም ClF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡

#ተገጣጥመው_ወደ_ሀገር_ውስጥ_የሚገቡ አዲስ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ጉልበታቸው እስከ 13ዐዐ ከሆነ 75.67% ሲሆን ጉልበታቸው ከ1301 እስከ 1800 ደግሞ 116.79% እንዲሁም ከ18ዐዐ በላይ ጉልበት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ 231.9% አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

ሹፌሩን ጨምሮ እስከ 16 የመቀመጫ አቅም ያላቸው የሰው ማጓጓዣዎች እና እስከ 1.5 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው የእቃ ማጓጓዣዎች አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ 52.5% ሲሆን ከ16 ሰው በላይ የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻዎች እና ከ1.5 ቶን በላይ እቃ የሚጭኑ ተሸከራካሪዎች ደግሞ 29.5% አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ለመገጣጠም በአምራች ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚገቡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተበተኑ (CKD/SKD) የሆኑ ተሽከራካሪዎች በተመለከተ በአዲስ ይዞታ ተገጣጥመው ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በተለየ በዝቅተኛ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ የሚስተናገዱ ሲሆን በተቃራኒው #ያገለገሉ (USED) ተሽከራካሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በአዲስ ይዞታ ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በአንፃራዊነት በጣም ከፍተኛ አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ አላቸው፡፡

የተሽከርካሪው ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡

እንደ ተሽከርካሪው አይነት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የተሸከርካሪዎች ላይ እስከ #አራት_ዓይነት የቀረጥና ታክስ ዓይነት የሚጣልባቸው ሲሆን ከአምራች ድርጅቶች ውጪ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ከሆኑ ደግሞ በተጨማሪነት #የዊዝሆልዲንግ_ታክስ ይሰበሰባል፡፡

የቀረጥ እና የታክስ ማስከፈያ መሠረት (Tax base) የሚሆነው የእቃው ዋጋ (CIF) እና በቅድም ተከተል የሚሰላው የቀረጥ ወይም ታክስ መጠን ፦
የጉምሩክ ቀረጥ፣
ኤክሳይዝ ታክስ፣
የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣
ሱር ታክስ ድምር ይሆናል፡፡

የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት ተደርጎ እንደሚታሰብ ለምሳሌ ሁሉም ዓይነት ታክስ በሚመለከተው በቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ በምሳሌነት እንመልከት፡፡

የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 4ዐዐ,ዐዐዐ፣ የሲሊንደር አቅሙ 13ዐዐ የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ወደ ሀገር ሲገባ ፦

🚘 በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 400,000 × 3ዐ%(ከፍተኛው መጣኔ) = 12ዐ,ዐዐዐ ይሆናል፡፡

🚘 ቀጥሎ ኤክሳይዝ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (400,000 + 120,000) 5%= 26,000 ብር ይሆናል፡፡

🚘 በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት thn (400,000 + 120,000 + 26,000) 15% = 81,9ዐዐ ብር ይሆናል፡፡

🚘 በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (400,000 + 120,000 + 26,000 +81,900) 10% = 86,190 ብር ይሆናል፡፡

🚘 ተሽከርካሪው በመደበኛ አስመጪ (ከአምራች ድርጅት ውጪ...) የሚመጣ ከሆነ በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 4ዐዐ, 000 × 3%= 12,ዐዐዐ ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት 120,000 + 26,000 + 81,900 + 86,190 + 12, 000= 326,090 ብር ይሆናል፡፡

#ማሳስቢያ ፦ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው መሠረት በማድረግ የተለያየ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸዋል።

ይህ መረጃ የገቢዎች ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia

7 months, 1 week ago

Edit, Sign and Share PDF files on the go. Get Acrobat Reader for mobile: https://adobeacrobat.app.link/Mhhs4GmNsxb

7 months, 1 week ago

شرف المكان والمكانة
لعموم المسلمين

📢 تعلن كلية المسجد النبوي عن بدء التسجيل في الدورة التأهيلية للعلوم الشرعية المستوى الأول
عن بعد
التسجيل متاح للرجال والنساء👇🏼

📜الملف التعريفي للدورة
https://drive.google.com/drive/folders/1iIfG4eUDAt4VrkxQyDxvcS5sdalVxPpe

📝رابط التسجيل في المنصة:
https://ethraa-cmn.alamlms.com/register
📚رابط الدورات:
https://ethraa-cmn.alamlms.com/sub_category/46/almsto-alaol

Alamlms

منصة إثراء | كلية المسجد النبوي

*شرف المكان والمكانة*
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago