The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 month, 2 weeks ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
?? https://donorbox.org/zemedemedia እና
?? https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 months, 1 week ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 10 months, 1 week ago
ጥር 22 2017
የሀገሪቱ ህጎች ሁሉ የበላይ ነው የሚባለው ህገ መንግስቱን ይቃረናል የሚል የሰላ ትችት የቀረበበት የአጠቃላይ የትምህርት አዋጅን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፅድቆታል፡፡
ምክር ቤቱ ያጸደቀው አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ የምክር ቤት አባላት ህገ መንግስቱን ይቃረናል ሲሉ ተችተውታል፡፡
የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ(ዶ/ር) አዋጁ የአንድ መግባቢያ የሀገራዊን ቋንቋ አስፈላጊነት የዘነጋን ይመስለኛል ብለዋል፡፡
ህፃናትን በአፍ መፍቻቸው ቋንቋ ማስተማር መሰረታዊ የህፃናት መብት መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ደሳለኝ ህፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የማስተማር አስፈላጊነት ያክል ደግሞ አንድ አስተሳሳሪ የሆነ ሀገራዊ ቋንቋ አስፈላጊነት መርሳት የለብንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የ1986 የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ አማርኛ ቋንቋ በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት አይነት መስጠትን ይፈቅድ ነበር፡፡
ባለፈው ዓመት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው አዲሱ የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ ግን ይህንን ጉዳይ እንዲለወጥ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡
እንደ እኔ አማርኛ ቋንቋ ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ በነበረችው የታሪክ መስተጋብር ውስጥ በጥሩ እና በመጥፎ የታሪክ ዘመናቸው ውስጥ አነሰም በዛም መስተጋብር ማስተሳሰሪያ ሆኖ ያገለገለ ቋንቋ ነው ብለዋል፡፡
የሰሜኑ ከደቡቡ የምስራቁ ከምዕራቡ ከራሱ ቋንቋ በተጨማሪ ሚግባባት ቋንቋ አማርኛ ነው፡፡ ይህን ቋንቋ በተለይ ከ1960ዎቹ እንቅስቃሴ ጀምሮ ቋንቋውን የአንድ ህዝብ ብቻ አድርጎ በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን ድልድይ ፈጣሪ ቋንቋ የማሳነስ ሁኔታ እስከ ዛሬ ድረስ ይስተዋላል ብለዋል፡፡
‘’እኔ አማራ ስለሆንኩ አይደለም ይህን ጥያቄ የማነሳው’’ ያሉት ደሳለኝ ቢያንስ ልጆቻችን የሚነጋገሩበት ሚግባቡበት ቢጣሉ የሚታረቁበት አንድ የጋራ ቋንቋ ቢኖራቸው ለዚህም አማርኛ ቢያንስ ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ በመደበኛ አስከ 12 ክፍል ድረስ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲሰጥ በአዋጁ ቢካተት ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት በምክር ቤቱ የሰው ሃብት ቴክኖሎጂ ስራ ስምሪት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ የሆኑት ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)አንድ ሀገራዊ ቋንቋ ቢሰጥ ለሚለው የትኛው ነው አገራዊ ቋንቋ? እስከዛሬ ድረስ በቋሚ ኮሚቴም ስንወያይበት ይሄ ነው ተብሎ አልተነገረንም ብለዋል፡፡
እኔም የትኛው ነው? አገራዊ ቋንቋ የሚለውን ጥያቄ ሳነሳ ነበር ዛሬ ግን ያነሱት የምክር ቤት አባል አማረኛ ቋንቋ ነው ብለዋል በግልጽ የተቀመጠው ግን አማርኛ ቋንቋ የፌደራል የስራ ቋንቋ እንደሆነ ነው ብለዋል፡፡
ሌላው አቶ ጋሻነው ዳኛው የተባሉ የምክር ቤቱ አባል የትኛውም ህግ የሚመነጨው ከህገ - መንግስቱ መሆን አለበት ይላሉ፡፡ አሁን የወጣው አዋጅ ግን ህገመንግስቱ እስኪሻሻል ይላል፤ እስኪሻሻል ብሎ ህግ ማውጣት ይቻላል ወይ የሚል ጥያቄን ጠይቀዋል፡፡
ሌላው አዋጁ ከህገ መንግስቱ ጋር ይጣረሳል የሚለው ጥያቄ ያነሱት የምክር ቤቱ አባል አበባው ደሳለው(ዶ/ር) ናቸው፡፡
ዶ/ር አበባው የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ አማርኛ ነው ይላል ህገመንግስቱ ደግሞ አንድ ህግ ሲወጣ ከህገ መንግስት ጋር ከተጣረሰ ተፈፃሚነት አይኖረውም ይላል ለምን የማይፈጸም ህግ እናወጣለን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አዋጆች ሲወጡ የህብረተሰቡን ችግሮች ለመፍታት ነው ችግር የማይፈታ ነገር በአዋጁ ላይ ለምንድነው ለማስቀመጥ የተገደዳችሁት ሲሉ ዶክተር አበባ ጠይቀዋል፡፡
ነገሪ ሌንጮ(ዶ/ር) አዋጁ ከህገመንግስቱ ጋር የሚጣረስ ነገር የለውም ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/4bszwkej
ያሬድ እንዳሻው
ቴሌግራም: https://t.me/ShegerFMRadio102_1
ዌብሳይት: https://shorturl.at/yCz7q
ጥር 21 2017
ፍርድ ቤቱ በእነዮሃንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመስማት ለፊታችን ጥር 29 ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
አቶ ዮሃንስ ቧያለውና አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ 51 ግለሰቦችን ባካተተው የክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 16ቱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
በትላንትናው እለት ስለዋለው ችሎት የጠየቅናቸው ከተከሳሾች ጠበቆች መካከል የሆኑት አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ተከሳሾቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ቀርበዋል ብለዋል።
ጠበቃው ስለ ችሎቱ ሲያስረዱ ችሎቱ ከዚህ ቀደም ዐቃቤ ሕግ ክሱን እንዲያሸሽል ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፣ ዐቃቤ ሕግም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በመጠየቁ ጉዳዩ ለአራት ወራት ሳይንቀሳቀስ ቆይቷል፤
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የከፍተኛውን ወይም የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማጽናቱ እና ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በማዘዙ በትላንቱ ችሎት እገዳው ተነስቶ መዝገቡ ተንቀሳቅሷል ብለውናል፡፡
አቃቢ ህግ ክሱን እንዲያሻሽል በእስር ፍርድ ቤት በቀደመው ችሎት የታዘዘው ተጠርጣሪዎቹ ፈጽመውታል ተብሎ በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ብቻ ሳይሆን ስም ዝርዝራቸውን፣ የደረሰውንም የንብረት ጉዳት ዘርዝሮ እንዲያቀርብ መሆኑን ጠበቃው ነግረውናል፡፡
ይህንን የእስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ማፅናቱን በማቅረባችን እግዱ ተነስቶ መዝገቡ ተንቀሳቅሷል፤
ፍርድ ቤቱም የተከሳሾቹን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለጥር 29 ቀን 2017ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከጠበቃው ሰምተናል፡፡
ከተከሳሾቹ መካከል የሆኑት አቶ ዮሃንስ ያለውና አቶ ክርስቲያን ታደለ የወደመውን ንብረትና የጠፋውን የሰው ህይወት በተመለከተ ከዚህ ቀደም በሌላ መዝገብ ከቀረበው የተለየ መረጃ ሊቀርብ አይችልም፤በዚህ መንገድ ለ5 ወራት መቆየት አልነበረብንም፣የተፋጠነ ፍትህ ይሰጠን ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል ሲሉም ነግረውናል፡፡
በተጨማሪም ተከሳሾቹ አዋሽ አርባ በታሰሩበት ወቅት ደረሰብን ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለፍርድ ቤቱ አመልክቶ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን ልኮ ጉዳዩ እንዲጣራ ተደርጓል፤ኮሚሽኑም ስለ ጉዳዩ አጣርቶ ለፍርድ ቤቱ ሪፖርት ማቅረቡን ተከትሎ ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው ሪፖርቱ ደርሶን አስተያየት እንድንሰጥበት ውሳኔ ይሰጥልን ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ማመልከተቸውን ከጠበቃው ከአቶ ሰለሞን ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/39s6kttc
ምንታምር ፀጋው
547 - በውጭ ጉዳይ መስሪያቤት
በአምባሳደርነት በተለያዩ ሀገራት ሀገራቸውን ያገለገሉት እና በአሁኑ ወቅት የህዝብ እንደራሴ ከሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ!
ህዳር 4፣2017
ባሳለፍነው ሰኞ ህዳር 2 ቀን 2017ዓ.ም በመርካቶ ገበያ ያሉ ነጋዴዎች ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው የመጣነው ያሉ ሰዎች ያለ ደረሰኝ ለምን ሸጣችሁ በሚል እቃችንን ወርሰውብናል ማለታቸው ይታወሳል፡፡
በዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በእለቱ በመርካቶ ያሉ በርከት ያሉ ሱቆች ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በሰጠው መግለጫ የተባለው ችግር በመርካቶ እንደተፈጠረ አምኖ ነገር ግን የነጋዴዎችን እቃ ወርሰዋል የተባሉት ግለሰቦች ከገቢዎች ቢሮም ይሁን ከየትኛውም የመንግስት አካል ያልተወከሉ ህገ ወጦች ናቸው ብሏል፡፡
በቢሮው የታክስ ኢንቴሌጀንስና ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ነጋሽ እኛ ምንም አይነት ንብረት የመውረስ መብት የለንም መወረስ ካለበትም ይህንን የሚሰራው የጉምሩክ ኮሚሽን ነው ብለዋል፡፡
ግለሰቦቹ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ባዘጋጁት ተሽከርካሪ እቃዎችን ጭነው ሄደዋል፤ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ደግሞ ገንዘብ ተቀብለው ተሰውረዋል ያሉት ኃላፊው ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ነጋዴዎቹ ለፀጥታ አካላት መረጃዎችን በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡
በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች መንግስት ከመርካቶ ገበያ የነጋዴዎችን እቃ መውረስ ጀመረ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ያሉት ኃላፊው ውዥምብሩ የተፈጠረው በዚህ ምክንያት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ኃላፊው የተፈጠረውን ሲያስረዱም የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ከዚህ ቀደም ይሰራ እንደነበረው ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይፈፀም ለማድረግ ያለመ የቁጥጥር ስራ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ይህ ስራ ሲሰራ የነበረው በአለፍ ገደም ነበር፤ አሁን ምንም ዓይነት ግብይት ያለ ደረሰኝ እንዳይከወን ለማድረግ ከህዳር 1 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ መልክ የጀመርነውን ስራ ከመርካቶ በመጀመራችን ይህንን ነው ያደረግነው ብለዋል፤ አቶ ተስፋዬ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመርካቶን የንግድ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠሩ ባለሙያዎች ያለ እጅ መንሻ የማሰሩ መሆኑን አረጋግጫለሁ ያለው ቢሮው ሁሉንም የመርካቶ ተቆጣጣሪዎችን በማንሳት በአዲስ መተካቱንም ተናግሯል፡፡
ቢሮው እየሰራሁ ባለው የቁጥጥር ስራ ያለ ደረሰኝ ሲገበያይ የተገኘን ማንኛውም ሰው 100 ሺህ ብር እንደሚቀጣ እወቁልኝ ብሏል፡፡
መርካቶን ጨምሮ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ያሉ አምራቾች፣ አስመጪዎችና ቸርቻሪዎች የትኛውንም ግብይት በደረሰኝ እንዲፈፅሙ ይገደዳሉ ተብሏል፡፡
በመርካቶ አካባቢ ያለው በነጋዴዎች ዘንድ የተፈጠረው ውዥምር ረግቦ ነጋዴዎች ወደስራቸው እየተመለሱ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ በያዝነው 2017 ዓ.ም 230 ቢሊዮን ብር ከገቢ ግብር ለመሰብሰብ ውጥን ይዞ በ3 ወር ውስጥ 47 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡንና ከዚህ ቀደም ገቢ በቁጥጥር ማነስም ይሁን በሌላ ገቢ የማሰበሰብባቸው የነበሩ ዘርፎችን ወደ ግብር ሥርዓቱ እያስገባሁ ነው ማለቱ ይታወሳል፡፡
ምንታምር ፀጋው
ህዳር 4፣2017
በአዘርባጃን እየተካሄደ በሚገኘው በኮፕ 29 ጉባኤ ላይ የተገኙ ፕሬዘዳንት ታዬ አፅቀስላሴ “ከጉባኤው የምንጠብቀው ቃል መግባትን ሳይሆን ተጨባጭ የሆነ የፋይናንስ አቅርቦትን ነው” ማለታቸው ተሰማ፡፡
የኢፌድሪ ፕሬዘዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፕ 29 ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር በተለይም ታዳጊ ሀገራት የሚያስፈልጋቸው ቃል ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ የሆነ የፋይናንስ ድጋፍ ነው ማለታቸው ተነግሯል፡፡
የአፍሪካ ሀገራትና ሌሎች በተመሳሳይ ታዳጊ የሆኑ ሀገራት በየጊዜው በሚደረጉ የአየር ጠባይ ለውጥ ጉባኤዎች ላይ የሚገባው ቃል ወደ ተግባር እንዲቀየር እና ተጨባጭ የፋይናንስ ድጋፍን ይፈልጋሉ ያሉት ፕሬዘዳንት ታዬ ይህ ካልሆነ ግን ችግሩን ለብቻቸው መጋፈጥ ይከብዳቸዋል ሲሉ መናገራቸውን የአዘርባጃን የወሬ ምንጮች ተናግዋል፡፡
ባለፉት ሶስት አመታት ኢትዮጵያ በረሃማነትን ለመከላከል በሰራቸው ስራ የደን ሀብቷን ከ17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ማሳደጓንና በ2030 እድገቱን ወደ 30 በመቶ ከፍ ለማድረግ እየሰራች ነው ሲሉ ፕሬዘዳንት ታዬ ተናግረዋል፡፡
በየጊዜው በሚደረጉ ጉባኤዎች ላይ ሀገራት ተስፋ ከመስጠት እና ቃል ከመግባት ወደ ኋላ ባይሉም ተጨባጭ የሆነውን የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት ላይ ግን ችግሮች አሉ ሲሉም ፕሬዘዳንት ታዬ ተናግረዋል፡፡
በአዘርባጃን ኮፕ 29 ጉባኤ ላይ የቻይናና የአሜሪካ እንዲሁም ከፍተኛ ካርቦን አመንጭ የሆኑ ሀገራት መሪዎች አለመገኘታቸው ታውቋል፡፡
በፓሪሱ የአየር ጠባይ ለውጥ ጉባኤ መሰረት ከፍተኛ የካርቦን ጋዝ አመንጭ የሆኑ ሀገራት የጋዝ የልቀት የሙቀት መጠናቸውን ከ2 ከዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንዲያደርጉ እንዲሁም ከፍተኛ ካርቦን አመንጭ የሆኑ ሀገራት የፋይናንስ የቴክኒክና ሌሎች ድጋፎችን ለታዳጊ ሀገራት እንዲሰጡ እ.ኤ.አ 2015 በኮፕ 21 ፓሪስ ላይ ስምምነት መደረሱ ይታወሳል፡፡
የኔነህ ሲሳይ
#ተጨማሪ ሪፖብሊካዊው የአሜሪካ ፕሬዘዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ ሀገሮች መሪዎች እንኳን ደስ ያለዎ እየተባሉ ነው፡፡ ትራምፕን እንኳን ደስ ያለዎ ካሉት መካከል የብሪታንያ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ይገኙበታል፡፡ ትራምፕ በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው አሸናፊነታቸው ከምናልባትም በላይ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ በፍሎሪዳ ፓልም ቢች ለደጋፊዎቻቸው ታላቅ ድል ተቀዳጅተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አሜሪካውያን…
ሪፖብሊካዊው የአሜሪካ ፕሬዘዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ ሀገሮች መሪዎች እንኳን ደስ ያለዎ እየተባሉ ነው፡፡
ትራምፕን እንኳን ደስ ያለዎ ካሉት መካከል የብሪታንያ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ይገኙበታል፡፡
ትራምፕ በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው አሸናፊነታቸው ከምናልባትም በላይ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡
በፍሎሪዳ ፓልም ቢች ለደጋፊዎቻቸው ታላቅ ድል ተቀዳጅተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አሜሪካውያን ታላቅ ሀላፊነት ሰጥተውኛ ማለታቸውም ተሰምቷል፡፡
ትራምፕ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ ዋይት ሐውስ የመመለሳቸው ነገር እንደተለየ አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡
ሪፖብሊካውያኑ በህግ መወሰኛው ምክር ቤት አብላጫነቱን መቆጣጠራቸው እንደማይቀር መገመቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ትራምፕን እንኳን ደስ ያለዎ ሲሏቸው፤ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር በፊናቸው አብረን ተባብረን እንሰራለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ጥቅምት 20፣2017
ኢሼሎን ግሩፕ ከአሊ ኤክስፕረስ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያን ገበያ ሊሰሩ ነው፡፡
ኩባንያዎቹ ለዚሁ ስራ አንዲሆን በአዲስ አበባ ጌቱ ኮሜርሻል ህንጻ ላይ ምርት ማሳያ ቦታ ከፍተዋል፡፡
ኢሼሎን ግሩፕ የኢትጵያዊያን እና ካናዳዊያን ድርጅት ሲሆን በኢኮሜርስ፣ መጋዘን፣ ሎጅስቲክስ፣ ግብርና እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ የሚሰራ ኩባንያ ነው፡፡
ኢሼሎን ግሩፕ ከአሊ ኤክስፕረስ በፈጠሩት ጥምረት በኢትዮጵያ የኦንላይን ግብይት የበለጠ ተደራሽ፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ ማድረግ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
በዚህ አጋርነት፣ ኢሼሎን ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን ልምድና ስም በመጠቀም የሀገሪቱን የኢ-ኮሜርስ እድገትን ለማፋጠን ይሰራል ተብሏል፡፡
የሁለቱ ኩባንያዎች ትብብር አዲስ አበባ ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ግብይትን ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበትና ድንበኞችም በአካል ሄደው የሚያዩት የምርት ማሳያ ክፍል ማቋቋምን ያካትታል ተብሏል።
ይህም ደንበኞችን፤ ምርቶችን መፈተሽ እና በቦታው ላይ ድጋፍ የሚያገኙበት አዲስ ሁኔታን ስለሚፈጥር በባህላዊ እና የዲጂታል ንግድ መካከል ያለውን ልዩነት ያጠባል ተብሎ ተነግሮለታል።
ኢሼሎን ግሩፕ ከአሊ ኤክስፕረስ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያን ገበያ ስራ መጀመራቸው
ከውጪ ሀገር እቃ የሚያስመጡ ነጋዴዎች ውጪ ሀገር መጓዝ ሳይጠበቅባቸው በኦልላይን የሚያዙትን እቃ አዲስ አበባ በተከፈተው ማሳያ ቦታ አይተው ትዕዛዝ መስጠት ያስችላቸዋልም ተብሏል፡፡
"የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ሞያውን በጠበቀ፣ በታማኝነት እና በብቃት ለማበርታት ቁርጠኛ ነን። ከከአሊ ኤክስፕረስ ጋር ያለን አጋርነት ከዚህ ራዕይ ጋር የተጣጣመ ነው፣ ለኢትዮጵያዊያን ስራ ፈጣሪዎች ብዙ እድሎችን እና ለተጠቃሚዎች የበለጠ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል”ሲሉ የኢሼሎን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚካኤል ማሞ ተናግረዋል።
ከኢሼሎን ግሩፕ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ውስጥ የገባው አሊ ኤክስፕረስ በኢባባ ግሩፕ ስር ያለ ድርጅት ሲሆን ዋነኛ ስራውም የኦንላይን ግብይት ነው፡፡
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 month, 2 weeks ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
?? https://donorbox.org/zemedemedia እና
?? https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 months, 1 week ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 10 months, 1 week ago