Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

የሰለምቴዎች ቻናል

Description
وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago

5 days, 9 hours ago

"ግድያ በባይብል"

◁ አቅራቢ

◍ ወንድም ሳላህ

5 days, 10 hours ago

የአሳማ ሥጋ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ

"ኺንዚር" خِنزِير ማለት "አሳማ" ማለት ሲሆን የአሳማ አስተኔ ምድብ ውስጥ የሚመደቡ ጉንደ እንስሳ "እሪያ" እና "ከርከሮ" ናቸው፥ አሳማ ሴረም ፕሮቲኖችን ስለያዘ ሥጋው በሰውነት ውስጥ የአለርጂን ሂደት የሚያነቃቁ አልቡሚን እና ኢሚውኖ ግሎቡሊን አላቸው። በዚህም ግልጽ ምክንያት አካላችንን በጣም ብዙ ጎጂ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተውሳኮች ይይዛል፥ በአሳማ የጡንቻ ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ የሚገኙ ጎጂ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተውሳኮች ሰው የአሳማ ሥጋ ሲበላ ወደ ልቡ ጡንቻ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ይራቡና በዚህም ለሕይወቱ አስጊ ሁኔታን ያስከትላል። አምላካችን አሏህም ሰውን የሚጎዳው ይህንን የአሳማ ሥጋ መብላት ክልክሏል፦
2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ሥጋን እና በእርሱ ማረድ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ
16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋን እና ያንን በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ
6፥145 በላቸው፡- «ወደ እኔ በተወረደው ውስጥ በክት፣ ወይም ፈሳሽ ደምን፣ ወይም የአሳማ ሥጋን እርሱ ርኩስ ነውና፣ ወይም በአመጽ ከአላህ ስም ሌላ በእርሱ ላይ የተወሳበት ካልኾነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የኾነን ነገር አላገኝም፡፡ قُل لَّا أَجِدُ فِي مَا أُوحِيَ إِلَيَّ مُحَرَّمًا عَلَىٰ طَاعِمٍ يَطْعَمُهُ إِلَّا أَن يَكُونَ مَيْتَةً أَوْ دَمًا مَّسْفُوحًا أَوْ لَحْمَ خِنزِيرٍ فَإِنَّهُ رِجْسٌ أَوْ فِسْقًا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ

"ሐርረመ" حَرَّمَ ማለት "የተከለከለ" ማለት ነው፥ ይህ ክልከላ እኛን ስለሚጎዳን እንጂ አንድ ሰው በረሃብ ምክንያት ሞት አፋፍ ላይ ቢሆን መብላቱ ሙባሕ ነው። ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አምላካችን አሏህ ለነቢያችን"ﷺ ኡማህ ካነሳው ሦስት ነገሮች አንዱ የገተደዱበትን ነገር ነው፦
2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፥ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
16፥115 አመጸኛም ወይም ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥145 አመጸኛ እና ወሰን ያለፈ ሳይኾንም የተገደደ ሰው ከተወሱት ቢበላ ኃጢአት የለበትም፡፡ ጌታህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ رَبَّكَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ

ነገር ግን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ውጪ ያሉት የክርስትና እምነት ተከታዮች የአሳማ ሥጋ መብላትን ሐላል አርገዋል፥ ቅሉ ግን በባይብልም ቢሆን የአሳማ ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦
ዘሌዋውያን 11፥7 እርያም ሰኮናው ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
ዘዳግም 14፥8 እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስላላመሰኳ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፥ ሥጋውን አትብሉ! በድኑንም አትንኩ።

"ሥጋውን አትብሉ" የሚለው ክልከላ ይሰመርበት! የእሪያን ሥጋ የሚበሉ ግን በጀሃነም በአንድነት ይጠፋሉ፦
ኢሳይያስ 66፥17 "የእሪያን ሥጋ፣ አስጸያፊ ነገርን፣ አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ" ይላል ያህዌህ።

የክርስትና እምነት ተከታዮች እነዚህን አናቅጽ ስንሰጣቸው፦ "የእሪያን ሥጋ በአዲስ ኪዳን ተፈቅዷል" ይላሉ፥ ነገር ግን መፈቀዱን የሚያሳይ አንድም ጥቅስ አያመጡም፦
ማቴዎስ 15፥11 ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው" አላቸው።
1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥4 እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም"።

እነዚህ ሁለት አናቅጽ ላይ አንጻራዊ ንግግር እንጂ ወደ አፍ የሚገባ የሚያረክሱ ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ ሐራም ናቸው፦
1 ቆሮ 10፥28 ማንም ግን፦ "ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው" ቢላችሁ ከዚያ ካስታወቃችሁና ከሕሊና የተነሣ አትብሉ"።
ራእይ 2፥14 ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ እና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።
የሐዋርያት ሥራ 15፥20 ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰት፣ ከዝሙት ከታነቀም፣ ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።
የሐዋርያት ሥራ 21፥25 አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም ነፍሳቸውን እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል።

ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ አያካትትምን? ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት ለጣዖት የተሰዋ ምግብ፣ ደም መብላት፣ የታነቀ እንስሳ የሚጣል የለምን? አይ፦ "ኢየሱስ አያረክስም ያለው እጅ ሳይታጠቡ መብላትን እንጂ እርኩስ ነው የተባሉትን ምግብ አይደለም፥ ጳውሎስ የሚጣል የለም ያለው መልካም ምግብን ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ የአሳማ ሥጋ የተፈቀደበት አንድም ጥቅስ መቼም ልታመጡ አትችሉም። የማታውቁትን ነገር መናገር ዳፋው እና ጦሱ ለራስ ነው፥ ስለዚህ ጨርቄን እና ማቄን ሳትሉ የአሳማ ሥጋ ሐራም መሆኑን ብትቀበሉ ይሻላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

6 days, 14 hours ago

ሌላን አትገዙ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

ሚሽነሪዎች ኢየሱስ እንደሚመለክ ለማስመሰል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም፥ "በ"ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ" የሚለውን ሐረግ "ለ"ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ" በሚል እያንሸዋረሩ ይረዳሉ ያስረዳሉ። ነገር ግን ጳውሎስ ያስቀመጠው በዚህ መልኩ አይደለም፥ እስቲ ከኢሳይያስ ኃይለ-ቃል እንጀምር! ፈጣሪ፦ "ጕልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል" እያለ ይናገራል፦
ኢሳይያስ 45፥23 ጕልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል።

"ለእኔ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "ለ" እና "በ" ሁለት የተለያዩ መስተዋድዶች ናቸው፦
ፊልጵስዩስ 2፥10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ "በ"-ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ።

"በ" የሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ ያለ መስተዋድድ በኢየሱስ ስም ለአብ መንበርከክን ያሳያል እንጂ ለኢየሱስ መንበርከክን አያሳይም። ለምሳሌ፦
ኤፌሶን 5፥20 "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንን እና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።

አምላክና አባት የተባለው እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ይመሰገናል፥ አሁንም ኢየሱስ "በ" በሚል መስተዋድድ አስመላኪ እንጂ "ለ" በሚል መስተዋድድ ተመላኪ አይደለም፦
ቆላስይስ 3፥17 እግዚአብሔር አብን "በ"-እርሱ እያመሰገናችሁ።

የሚመሰገነው አብ በማን ነው? ስንል "በ"-ኢየሱስ ነው። "በ" የሚለው መስተዋድድ አስምሩበት! እግዚአብሔር አብ "በ"-ኢየሱስ ይመሰገናል፦
ሮሜ 1፥8 አምላኬን "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።

ጳውሎስ አምላኩን እግዚአብሔርን በኢየሱስ ክርስቶስ ያመሰግናል። ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ የምስጋናን መሥዋዕት የሚቀርበው "ለ"እግዚአብሔር "በ"ክርስቶስ እንደሆነ ይናገራል፦
ዕብራውያን 13፥15 እንግዲህ ዘወትር "ለ"-እግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ "በ"-እርሱ እናቅርብለት።

"በ" አስመላኪ ሲሆን "ለ" ደግሞ ተመላኪ ነው። ብቻውን ጥበብ ላለው "ለ"-እግዚአብሔር ክብር የሚሰጠው "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፦
ሮሜ 7፥25 "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን "ለ"-እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
ሮሜ 16፥27 ብቻውን ጥበብ ላለው "ለ"-እግዚአብሔር "በ"-ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን።

"በ" የሚለውን "ለ" ብሎ ከተረዱት እንግዲያውስ "በ"-ጽዮን" የሚለውን "ለ"-ጽዮን" ብለው መረዳት ይኖርባቸዋል፦
መዝሙር 65፥1 አቤቱ "በ"-ጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል።  לַמְנַצֵּ֥חַ מִזְמֹ֗ור לְדָוִ֥ד שִֽׁיר׃ לְךָ֤ דֻֽמִיָּ֬ה תְהִלָּ֓ה אֱלֹ֘הִ֥ים בְּצִיֹּ֑ון

ዋናው ነጥብ ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክ ለኢየሱስ ስም ሳይሆን በኢየሱስ ስም ለፈጣሪ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ አስመላኪ እንጂ ተመላኪ አይደለም፥ ለፈጣሪው ተንበርክኮ የሚያመልክ አካል ተመልሶ ተመላኪ አይሆንም። ኢየሱስ እራሱ በጉልበቱ ተንበርክኮ እና በፊቱ ተደፍቶ ወደ ፈጣሪ ይጸልይ ነበር፦
ማቴዎስ 26፥39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀ እና ሲጸልይ።
ሉቃስ 22፥41 ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ ተንበርክኮም።

ሸብረክ እና ብርክክ ብሎ ለፈጣሪው ሡጁድ የሚወርድ ኢየሱስ እራሱ አምላኪ መሆኑን ይህ ጥቅስ ጉልኅ ማሳያ ነው። እናንተም እንደ ኢየሱስ አሏህን እንጂ ሌላን አትገዙ፦
11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ፡፡» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

2 months ago
2 months ago

***ረመዳን (6)

ስድስተኛው ጁዝእ

የቻልን ቀርተን ያልቻልን አዳምጠን በየ ኮዳችን እጅ እናዉጣ

الله يكتب لنا الأجر والثواب جميعاً
وكل عام وأنتم الى الله أقرب وعلى طاعته أدوم 🌸***

2 months ago

●▯ውይይት ▯●

"የፈጣሪ መኖር"

◍ ኡስታዝ አቡ ሙዓዊያህ
◍ ወንድም ዑስማን
🆅🆂
◍ ወገናችን ጃህ ዓቢር
እና ሌሎችም

2 months, 1 week ago

●▯ውይይት ▯●"

◍ወንድም ኢምራን
◍ወንድም አህመድ

🅥🅢
◍ ከወገኖች ጋር

2 months, 1 week ago

መደምደሚያ
ነፍስ የሚለው ቃል “ነፍስያ” نفسيه ማለትም “የራስ ዝንባሌ” ለማመልከት ይመጣል፤ ይህ ዝንባሌ በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ነው፤ ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር ”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡
6፥164 በላቸው «እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን
ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ዝንባሌ አደገኝነቱ ይህንን ያህል ከታወቀ በጊዜ ወደ አላህ መመለስ ግድ ይላል፤ አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፣ በማስተካከል፣ በማሳመርም ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፦
16:90 አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፤ ከአስከፊም፣ ከማመንዘር፤ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፤ ትገነዘቡ ዘንድ ይገሥጻችኋል።
7:28 መጥፎንም ስራ በሰሩ ጊዜ፦ በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን፣ አላህም በርሷ አዞናል ይላሉ፤፦አላህ “በመጥፎ ነገር አያዝም”፤ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?በላቸው።
17:32 ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!

ስለዚህ ስራችንን በኢኽላስ ማለትም ለአላህ ውዴታ ተብሎ ከሙገሳ እና ከወቀፃ ነፃ የሆነ ስራ ከሰራን እና በአላህ መንገድ እውነትን ለማንገስ ሀሰትን ለማርከስ በምናደርገው ትግል ዝንባሌ ይገታል። አላህ ዝንባሌአቸውን ከማይከተሉ ባሮቹ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

2 months, 1 week ago

ነጥብ ሶስት
“ዝንባሌ”
“ዝንባሌ” የሚለው እሳቤ ቢድዓ፣ ኩርፍ፣ ሽርክ እና ኒፋቅ ምንጭ የሆነለት የሸይጧን እርምጃ መሆኑ እሙንና ቅቡል ነው፤ “ሸይጣን” شيطان የሚለው ቃል “ሸጠነ” ش ط ن ማለትም “ራቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ከአላህ ራህመት የራቀ” የሚል ፍቺ አለው፣ “ሸያጢን” شياطين ደግሞ የሸይጣን ብዙ ቁጥር ነው፡፡ ይህ የባህርይ ስም ሲሆን ሸይጣን የሰውም የጅንም አለ፦
6:112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጂንን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን፡፡
23:97 በልም «ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ፡፡
114:4-6 ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጎት ከኾነው፤ ከጂንዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ በል።

“ወስዋስ” وَسْوَاس ከሰይጣናት ወደ ልብ የሚመጣ “ጉትጎታ” ወይም “ማንሾካሾክ” ሲሆን ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው ያሾከሹካሉ፦
6፥121 በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ፡፡ እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው፡፡ ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ “ያሾከሹካሉ” لَيُوحُونَ ፤ “ብትታዘዙዋቸውም” እናንተ በእርግጥ “አጋሪዎች” ናችሁ፡፡

“ያሾከሹካሉ” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “ለዩሑነ” لَيُوحُونَ የሚለው ግስ “አውሃ” أَوْحَىٰٓ “ገለጠ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ቀልብ ላይ የሚወሰውሱት ወስዋስ ነው፤ ይህም ወስዋስ ሰይጣናት በመጥፎ፣ በሚጠላ ነገር፣ በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር ማዘዝ፣ በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችን ጠብንና ጥላቻን መጣል፣ አላህን ከማውሳትና ከስግደትም ማገድ፤ እንዳንለግስ በድኽነት ማስፈራራት፤ በአላህ ላይ የማናውቀውን እንድንናገር ያዛል፦
24:21 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! የስይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፤ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ፤ እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዝዛል
5:91 ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፣ አላህን ከማውሳትና ከስግደትም ሊያግዳችሁ፣
2:268 ሰይጣን እንዳትለግሱ ድኽነትን ያስፈራራችኋል፡፡ በመጥፎም ያዛችኋል፡፡
2:169 እርሱ “የሚያዛችሁ” በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር በአላህም ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ብቻ ነው፡፡
35:6 ሰይጣን ለእናንተ ጠላት ነው፤ ስለዚህ ጠላት አድርጋችሁ ያዙት፤ “ተከታዮቹን” የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲኾኑ ብቻ ነው።

ሚስጥር እና አሻጥር አመሳጥሮና አመሰጣጥሮ የሚወሰውሰው ሸይጣን ነው፤ እርሱ ለእኛ ግልጽ ጠላት ነውና፤ የሰይጣን እርምጃ የሆነውን ዝንባሌ መከተል የሚመጣው ዕውቀት እና ከአላህም የኾነ መመሪያ ሳይኖር ሲቀር ነው፦
2:168 እናንተ ሰዎች ሆይ! በምድር ካለው ነገር የተፈቀደ ጣፋጭ ሲኾን ብሉ፡፡ የሰይጣንንም “እርምጃዎች አትከታተሉ”፡፡ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና፡፡
47:14 ከጌታው በኾነች አስረጅ ላይ የኾነ ምእመን ክፉ ስራቸው ለእነርሱ እንደ ተሸለመላቸው እና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉት ነውን?
30:29 ይልቁንም እነዚያ የበደሉ ስዎች ያለ ዕውቀት ዝንባሌዎቻቸውን ተከተሉ፤
28:50 እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ፡፡ ከአላህም የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ አላህ በደለኞች ሕዝቦችን አይመራምና፡፡

ዝንባሌን ማስወገድ ያላሰለሰ ጥረት ይጠይቃል፤ በደል ማለትም አድልዎና መድልዎ ሆነ ፍትህ አልባልነት የሚመጣው ከዝንባሌ ነው፦
4፥35 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! በፍትህ ቋሚዎች፣ በራሳችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢሆንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ሁኑ። ሀብታም ወይም ደኻ ቢሆን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው። እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ። ብታጣምሙም ወይም መመስከርን ብትተዉ አላህ በምትሠሩት ነገር ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።
5:8 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች፣ በትክክል መስካሪዎች ሁኑ። ሕዝቦችንም መጥላት፣ ባለመስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፤ አስተካክሉ፤ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። አላህንም ፍሩ። አላህ በምትሠሩት ሥራ ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።

2 months, 2 weeks ago

"የአላህ መልእክተኛን እና አይሁዳዊቷ ሴትዮ"

◍ ወንድም ሳላህ
◍ ወንድም ዒምራን
🆅🆂
◍ ወገናችን አቡሽ

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago