Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Ethio Psychiatry

Description
No Health Without Mental Health!

☎️ +251949114685
📩 ethiopsychiatry@gmail.com
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago

3 weeks, 4 days ago

ለአንድም ሰው ከጠቀመ እነሆ🙏

ስነ-አዕምሮ ህክምና የት ይገኛል?

➜ለድምፅ አልባዎች ድምፅ እንሁን!

➜መገለል መድሎን ፈርተው መታከም ለፈሩቱ እንድረስ!*የአዕምሮ ህመምተኛን ማግለልም መድሎም ያብቃ!!

➜ያለ አዕምሮ ጤና  ጤና የለም👌

◆ የአዕምሮ ህመምተኛ በቤታችሁ በአከባቢያችሁ እንዲሁም በርቀት ታማሚ ሰው እንዳለ ተደውሎ የተነገራችሁ ነገር ግን መሄጃ ላጡቱ

◆ለወራት: ለአመታት ታስሮም ሆነ በቤት ውስጥ ተከርችሞበት ተገልሎ የተቀመጠ

◆በሱስ ስራው ጤንነቱና ማህበራዊ ህይወቱ ለተረበሸ

◆በየእምነት ቦታዎች ለረጅም ጊዜ ሆነ በቅርቡ የተወሰዱ ወዳጅ ዘመድ የአዕምሮ ህመምተኞች እንዲሁም እዛው ለተተዉቱ

◆ህፃናትና አዋቂዎች ብሎም አዛውንት የዓዕምሮ ህመም ያለባቸውን የሚከተለውን አድራሻ በመጠቀም የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እርዷቸው!!
👇

የቤተ-እምነት እርዳታው እንዳለ ሆኖ! ህክምናው ከቤተእምነት እርዳታ ጋር አይጋጭምና👌

የሆስፒታሎች ዝርዝርና የሚሰጡት ግልጋሎት

  1. ቅዱስ አማኑኤል የአዕምሮ ልዩ ህክምና ሆስፒታል (ተመላላሽ+የተኝቶ ህክምና አለ) + የሱስ ህክምና (ተኝቶና ተመላላሽ)

  2. ጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
    ተመላላሽ ህክምና

  3. ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል (ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ) የአዋቂ + የህፃናት የአዕምሮ ህክምና

  4. የካቲት 12 ሪፈራል ሆስፒታል የአዋቂ +የህፃናት የዓዕምሮ

  5. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  6. ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  7. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል
    ተመላላሽ ህክምና ብቻ

  8. ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል
    (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  9. ወላይታ ሶዶ ሪፈራል ሆስፒታል (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  10. ጂማ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  11. ሻሸመኔ ሪፈራል ሆስፒታል

  12. ይርጋለም ሪፈራል ሆስፒታል
    ተመላላሽ ህክምና ብቻ?🤔

  13. መቀሌ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል (ተመላላሽ+ተኝቶ ህክምና)-መቀለ
    +የአልኮልና ዕፅ ሱስ ማገገሚያ ማዕከል

  14. ሀረር ሪፈራል ሆስፒታል (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  15. ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል

  16. ሆሳዕና (ንግስት ኢሌኒ ሆስፒታል)
    ተመላላሽ ህክምና

  17. ጦር ሃይሎች ሆስፒታል
    (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  18. አዲስአበባ ፓሊስ ሆስፒታል
    ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና

  19. ቅዱስ ጴጥሮስ እስፔሻላይዝድ  ሆስፒታል (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  20. ገፈርሳ የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከል
    (ተኝቶ ህክምና)

  21. ፈለገህይወት ሪፈራል ሆስፒታል-ባህር ዳር
    (ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና)

  22. አሰላ ሆስፒታል
    ተመላላሽ ህክምና ብቻ

  23. አዳማ ሆስፒታል

  24. ዘዉዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል (የሱስ ህክምና)

  25. ደብረታቦር ሆስፒታል
    (የሱስ ማገገሚያ ማዕከል+የስነአዕምሮ ህክምና)

  26. ጋምቢ ሆስፒታል (የግል ባህርዳር)

27.ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል
(ተመላላሽ ህክምና)

  1. ራስ ደስታ ሆስፒታል

29.ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል
(ተመላላሽ+ተኝቶ+"የሱስ ህክምና)

  1. ድሬዳዋ
    30.1 ድሬዳዋ ድልጮራ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመላላሽ ህክምና
          30.2 ድሬዳዋ ሳቢያን አጠቃላይ ሆስፒታል
  2. አዲግራት አጠቃላይ ሆስፒታል (ተመላላሽ ህክምና)

  3. ኣክሱም አጠቃላይ ሆስፒታል

  4. ወራቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ተኝቶና ተመላላሽ ህክምና

  5. ዱራሜ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመላላሽ ህክምና

  6. ሃላባ
    ተመላላሽ ህክምና

  7. ቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመላላሽ ህክምና

  8. መቱ ሆስፒታል ተመላላሽ ህክምና

  9. ደሴ ቦሩ ሜዳ ሆስፒታል (ተመላላሽ፣ ተኝቶ፣ የሱስ ህክምና)

እናም
የተለያዩ ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች።

ቃልኪዳን ዮሐንስ (የስነ-አዕምሮ ባለሙያ)

**""ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!!" 

Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

3 weeks, 5 days ago

የአእምሮ ጤና ልክ እንደ አካላዊ ጤና!!!

በፈጣን እና ብዙ ጊዜ በሚፈለግ አለም ውስጥ፣ የአካል ጤንነታችንን እንደምንሰራ ሁሉ ለአእምሮ ደህንነታችን ቅድሚያ መስጠቱ ወሳኝ ነው። ስለዚህ በዚህ አስፈላጊ ጉዳይ ላይ ትንሽ ብርሃን በማብራት ቀኑን እንጀምር።

የአእምሮ ጤና እያንዳንዳችንን ይነካል። የምናፍርበት ወይም ችላ የምንል ሳይሆን በግልጽ ልንወያይበት እና ልንደግፈው የሚገባ ጉዳይ ነው።

ብዙ ሰዎች እንደ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ወይም የተለያዩ የአእምሮ ጤና ተግዳሮቶች ጋር ይታገላሉ። እነዚህን ትግሎች በመረዳት እና በመረዳዳት የበለጠ ሩህሩህ እና ሁሉን አቀፍ ማህበረሰብ መፍጠር የተሻለ ነው።

**""ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!!" 

Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

4 weeks ago

WHAT YOU NEED TO KNOW ABOUT 'AUTISM'
Autism, or autism spectrum disorder (ASD), is a complex neurological and developmental condition that affects how a person communicates, interacts with others, and experiences the world. It is a spectrum disorder, meaning that it manifests differently in each individual. Here is an overview of signs and symptoms, as well as treatment options for autism:

Signs and Symptoms of Autism:
1. Social Challenges: Difficulty with social interactions, such as making eye contact, understanding social cues, or developing relationships.
2. Communication Difficulties: Challenges with verbal and nonverbal communication, including delayed speech development, repetitive language, or difficulty initiating or sustaining conversations.
3. Repetitive Behaviors: Engaging in repetitive behaviors or routines, such as hand-flapping, rocking back and forth, or fixating on specific interests.
4. Sensory Sensitivities: Heightened sensitivity to sensory stimuli, such as loud noises, bright lights, or certain textures.
5. Difficulty with Change: Resistance to change, inflexibility with routines, or difficulty adapting to new situations.

It's essential to remember that each individual with autism is unique, and treatment should be tailored to their specific needs and strengths. A multidisciplinary approach involving healthcare professionals, educators, and family members can provide comprehensive support and resources for individuals with autism.

If you suspect that you or someone you know may have autism, seek guidance from qualified professionals for a comprehensive evaluation and personalized treatment plan.

Remember, individuals with autism have diverse abilities and contributions to make to society. With understanding, acceptance, and support, individuals with autism can thrive and lead fulfilling lives.

Ethio Psychiatry

#AutismAcceptanceMonth #AutismAwarenessMonth #Autism #AutismAwareness #AutismAcceptance #CelebrateDifferences #AutismSupport

Join Us
@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

1 month ago

Fayyaa sammuu

Namni-tokko "sammuun dhibame" jechuuf dirqama qullaa buusuu qabaa?  Hin qabu.

Dhibee sammuu wayita jedhamu huccuu ofirraa gatanii qullaa daandii irra fiiguu qofa kan itti fakkaatu ni jiraam!  Namoota qullaa buusaanii daandii irra jiraatan kanaaf iyyuu namoonni gaaffii waliif dhiyeessan ni jiru.

Fakkeenyaaf namni dhibee sammuu qabu tokko daandii irratti lubbuu isaa oolfachuuf konkolaataa jalaa yoo baqate, namni kun “Sobeetu malee utuu dhibameera ta’ee jalaa hin dheessu ture”, jedhuun.
Namoota muraasaan immoo yoo doorsifamee sodaate “Elaa, lubbuu isaa beekaam!” jedhuun itti ga’isuun kanuma jirtu.

Qullaa buusuun qalbii darbuu utuu hin taane mallattoo dhukkuba sammuu keessaa isa tokkodha. Yeroo baay’ee namoota yeroo dheeraaf dhukkubsataniifi battala dhibaman irrattis darbee darbee mul’achuu danda’a. Namoonni fayyaa ta’anii wayita akka malee aaran (danfan) uffata ofii isaanii ofirratti ciranii gatan, yookiin qullaa buusanis jiraachuu malu.
Haa ta’u malee qorannooleen garaagaraa akka ibsanitti, dhibee sammuu jechuun namni tokko dandeettii waan tokko hubatee raawwachuu, fedhii yookiin amala isaa duraa irratti jijjiiramni haaraan ifa ta’e yoo jiraatedha. Kana jechuun miiraafi dandeettii kanaan dura qabu yoo dhabe yookin yoo gad bu’e jechuudha. Jijjiiramni kunis hojii guyyaa guyyaa, jireenya hawaasummaafi walitti dhufeenya namoota waliin qabnu irratti rakkoo fidaa jira yoo ta’e sammuun miidhamaa jiraachuu agarsiisa.

Namni tokko dhukkuba sammuu qaba jechuuf waan huccuu ofirraa baaseef qofa osoo hin taanee, ulaagaafi mallatoolee agarsiiftuu dhukkuba murtaa’ee tokkoo qabaachuuf dhiisuun adda baha.

Fakkeenyaaf giinga’uu, sireerratti fincaa’uun, araadaan qabamuu, miiraa saal-qunnamtii dhabuu yookiin humna ol qabaachuun, waanuma salphaaf dhiphachuunii fi wantoota biroo akka hawaasa keessatti akka fayyummaatti ilaalaman garuu mallattoo dhukkuba sammuu ta’an kaasuun ni danda’ama.

Kanaaf namoonni keenya ykn maatiin keenya yeroo jijjiiramni amalaafi of to’achuu dadhabuu kana malees rakkoo sammuu isaan muudatu gara ogeessa yaala sammuutti fudhachuun ogeessa mariisisuun barbaachisaadha. Hanga qullaa buusanitti eeguun gaarummaa hin qabu. Namni hundiyyuu yoo yeroon yaalame fayyuu ni danda’a. Kana hundaaf hubannaa uumuun fayyaalessummaa dhuunfaa keenyaati.

Kana qofaa osoo hin taanee, namoonni dhibee sammuu qaban akka nama miidhaniifi hamoo ta’aniitti yaaduun ni jira. Garuu kan miidhaa geessisan namoota dhibee sammuu qaban muraasa.

Tolasaa Burqaa (Oggessa Fayyaa Sammuu)

“FAYYAA SAMMUU MALEE FAYYAAN HIN JIRU”!!
**Ethio Psychiatry

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

1 month ago

ማህበራዊ ጭንቀት እክል-Social Anxiety Disorder

በሌሎች እንዳይፈረድብህ በጣም ትፈራለህ?
አዳዲስ ሰዎችን ከመገናኘት ትቆጠባለህ?

እንደዚህ አይነት ስሜት ቢያንስ ለ6 ወራት ከተሰማዎት እና እነዚህ ስሜቶች የእለት ተእለት ተግባሮችን ለምሳሌ በስራ ቦታ ወይም በትምህርት ቤት ከሰዎች ጋር መነጋገርን ከባድ ያደርጉዎታል?

የማህበራዊ ጭንቀት መታወክ አብዛኛው ሰው ላይ የሚታይ አንዱ የአእምሮ ህመም ሲሆን በሌሎች ሰዎች የመታየት እና የመፈረድ ከባድ፣ የማያቋርጥ ፍርሃት ነው።
ይህ ፍርሃት በስራ፣ በትምህርት ቤት እና በሌሎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎችዎ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።

ጓደኛ ማፍራት እና ማቆየት  እንዲሁም አቅማችንን እንዳንገልጥ ያደርገናል።

በእነዝህ ቦታዎች በሌሎች እንዳይፈረድብህ በጣም ትፈራለህ?

👉በተለያየ ቦታ ሃሳብ መስጠት፣
👉አዳዲስ ሰዎችን መገናኘት/ማዎራት፣
👉በሰዎች ፊት መሥራት፣
👉ክፍል ውስጥ Presentation ማቅረብ፣
👉ምግብ ቤት፣ ሱቅ፣ አምልኮ ቦታ ወይም ሌላ የህዝብ ቦታ ላይ እርዳታ መጠየቅ፣
👉የፍቅር ጓደኛ ማግኘት/መተዋወቅ ፣
👉በሰዎች ፊት ለጥያቄ መልስ መስጠት፣
👉በሰዎች ፊት መብላት፣
👉በቃለ መጠይቅ ውስጥ መሳተፍ፣ እና ወዘተ...

ማህበራዊ ጭንቀት እክል ውጤታማ ሕክምና አለው።

የንግግር ሕክምና-የስነ ልቦና ድጋፍ እንዲሁም የመደኃኒት ሕክምና አለው

ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
**Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

1 month ago

ልጄ አልተኛም ይለኛል ምን ይሻላል?

አቢቲ 4 አመቱ ነው። ሲመሽ እናቱ አጥባ እራት አብልታ "ደህና እደር" ብላ ስማው ወደ መኝታ ክፍሏ ከመግባቷ "እማዬ ውሀ" የሚል ድምፅ ትሰማለች። ውሀ ይዛለት ለትንሽ ጊዜ አብራው ከሆነች በኋላ "ደህና እደር" ብላ ወደ ክፍሏ ትሄዳለች። ገና አልጋ ላይ ሳትወጣ "እማዬ እንቅልፍ እንቢ አለኝ" የሚል ድምፅ ትሰማለች። እየተናደደች መምጣቷ አይቀርም። ምን ይሻላል?

በመጀመሪያ መጠኑ ይለያይ እንጂ አብዛኞቹ ልጆች ላለመተኛት የተለያየ ሰበብ እንደሚፈጥሩ ማወቅ ያስፈልጋል። መንስኤው እንደ እድሜያቸው ይለያያል። 2 እና 3 አመት የሆናቸው ህፃናት ከወላጆቻቸው መለየት በራሱ ያስፈራቸዋል። ከ4 እስከ 6 አመት የሆኑ ህፃናት ለብቻቸው ሲሆኑ እና ጨለማ ሲሆን "ሴጣን/ጭራቅ ቢመጣስ? ወይም ሌባ ቢገባስ?" የሚል ፍርሀት አላቸው። እና ወላጆች ምን ማድረግ ይችላሉ?

የእንቅልፍ ሰአት መወሰን፦ እድሜያቸውን ባገናዘበ መልኩ ወጥ የሆነ ሰአት መወሰን እና ለእነሱም ማሳወቅ። የእንቅልፍ ሰአታቸው ከመድረሱ በፊት አንድ 10/15 ደቂቃ ቀደም ብሎ ማስታወስ።

ከእንቅልፍ ሰአታቸው በፊት አብሮ ጊዜ ማሳለፍ፦ ቀጥታ ከቲቪ ወደ አልጋ ከሚሄዱ ይልቅ አልጋቸው ላይ ሆነው ወላጆቻቸው ተረት አውርተውላቸው/አንብበውላቸው ሲሆን የተሻለ የመተኛት እድል አላቸው።

አሻንጉሊት እና ብርሀን፦ አንዳንድ ልጆች አሻንጉሊት አጠገባቸው መኖሩ መረጋጋት ይፈጥርላቸዋል። ጨለማ የሚያስፈራቸው ከሆነ ሊተኙ ሲሉ ደብዘዝ ያለ ብርሀን እንዲኖር ማድረግም ክፍሉ ውስጥ ጭራቅ እንደሌለ አይተው አረጋግጠው እንዲረጋጉ ያደርጋቸዋል።

አልጋቸው ላይ መልሶ ማስተኛት፦ አንዳንድ ልጆች እንቅልፍ አልወስድ ሲላቸው የወላጆቻቸው አልጋ ላይ ሄደው ይተኛሉ። እንደዚህ ሲያጋጥም አረጋግቶ ወደ አልጋቸው መልሶ ማስተኛት ይመረጣል።

መሆን ያለበት "ሳትወልድ ብላ ሳይሆን ሳትወልድ ተኛ" ነው!

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!

ዶ/ር ዮናስ ላቀው
**Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

1 month, 1 week ago

Mental Health Issues?

When talking about Mental health people always take a step behind (It is also seen in Ethiopian Health Professionals and Ministry of Health, Ethiopia)
Due to this, a maximum number of people don’t talk about their mental health issues or take the proper treatment.

The topic ‘Mental health’ should be normalized to reduce mental health stigma!!

Starting from the ground level, mental health should be discussed within the family (Talk and spend time with your family members or relatives who understand your situation if you suffer from mental health issues). This will reduce Mental health stigma and also make feel good, and feel a sense of support.

Schools are the second most crucial place to spread awareness and discuss mental health. Schools are the place that shapes our values and beliefs. Suppose the school curriculum and the teachers talk about mental health. This will reduce Mental health stigma..

Similarly, Mental health stigma can be reduced in the workplace by discussing the employees’ mental health issues and giving them the required assistance.

👉🏿Workplace burnout can cause various mental health issues for employees and employers. This can cause a decrease in productivity and motivation to work. This will help encourage the employees to help others undergoing mental health issues and support them.

#BreakTheStigma

Yordanos Yihun (Psychiatry Professional)
**Ethio Psychiatry

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

1 month, 1 week ago

Deprescribing Guidelines
**Ethio Psychiatry

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

1 month, 1 week ago

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ በታች ለተመለከተው ክፍት የስራ መደብ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ተፈላጊ መደቦች
1.  Senior Psychiatry Nurse
2.  Senior Biomedical Engineer
3.  Neurologist
4.  Radiologist
5.  Gynecologist
6.  Specialist Physician (Internist)
7.  General Practitioner
8.  Junior Pharmacy Service Officer
9.  Junior Psychiatry Nurse
**Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

1 month, 2 weeks ago

ስለ ኦቲዝም የተሳሳቱ አመለካከቶች

#ChildsMentalHealthAwarenes
#የልጆች_የአእምሮ_ጤና_ግንዛቤ.

ኦቲዝም ማለት ቋሚ የሆነ የማህበራዊ ተግባቦትና ግንኙነት ችግር ሲሆን፤ አዕምሮ በሚፈለገው ደረጃ በተለያዩ ለመኖር በሚያስፈልጉ ክህሎቶች ማሳደግ እና መበልፀግ ሳይችል ሲቀር ማለት ነው፡፡

👉ኦቲዝም ባብዛኛው ከ3 ዓመት የሚጀምር ወይም የሚታይ (አንዳንዶች አንድ ልጅ በጣም ትልቅ እስኪሆን ድረስ አይታወቅም)  ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በብዛት ይስተዋላል፡፡

        ስለ ኦቲዝም ዋናዎቹ አምስት የተሳሳቱ አመለካከቶች

👉🏻ኦቲዝም የሚከሰተው በክትባት ምክንያት ነው.

👉🏻ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ጓደኛ ማፍራት አይፈልጉም.

👉🏻ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች መማር አይችሉም.

👉🏻ኦቲዝም የሚከሰተው በመጥፎ ወላጅነት ነው.

👉🏻ኦቲዝም ያለባቸው ሰዎች ጥሩ ችሎታ አላቸው.

🔺ስለዚህ የግንዛቤ ማነስ በኦቲዝም ስፔክትረም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁኔታቸው እንዲታወቅ እና የሚፈልጉትን ድጋፍ ለማግኘት አስቸጋሪ ያደርገዋል.

🔺የተሳሳቱ አመለካከቶች አንዳንድ የኦቲዝም ሰዎች የብቸኝነት ስሜት እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል.

🔺ኦቲዝምን በህክምና ለማዳን ይሄ ነው የሚባል የህክምና መፍትሄ ባይኖረውም ሆኖም ግን ልጆችን ምልክቶቹ በታዩባቸው ቀድም ያሉ ጊዜያቶች ባህሪያዊ፣ ስነ-ልቡናዊ እና ተግባቦታዊ ምክክሮችና እና ፕሮግራሞች የልጆቹ የማህበራዊ ግንኙነትን ክህሎት በጥቂቱ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል፡፡

🔺ሌላው በኦቲስቲክ ልጆች ላይ ብቻ ያተኮረ ትምህርት ቤት ውስጥ ልጆቹን ማስተማር የዐዕምሮ ብቃታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምረዋል በዚህም የወላጆች ከፍተኛ እና ንቁ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው፡፡

🔺በእርግጥ ነው ኦቲዝም በአንድ ልጅ ብቻ ላይ ቢያጋጥም እንኳን መላው ቤተሰብ ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር ችግር ነው ስለዚህ ልጅዎ የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆኑ/ኗ በህክምና ከተረጋገጠ በኋላ በቅድሚ ማድረግ የሚኖርብን ችግሩን መቀበል ነው.

🔺በዚህም ልጆችን ጓዳ ውስጥ ደብቆ ከማስቀረት ይልቅ እርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት የልጆቹን ሁለንተናዊ የሆነ አእምሮኣዊና አካላዊ እድገትን ያፋጥናል.

🔺ቤት ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን ሁኔታዎችን ማሙዋላት ይኖርብናል ለምሳሌ መጫወቻዎች፣ ቤትን ለልጆች ምቹ ማድረግን እና የመሳሰሉትን ሌላው ትምህርት ቤት በሚገቡበት ጊዜ ከመምህራኖቻቸው ጋር የቅርብ ግንኙነት በመመስረት የየዕለት ልዩነታቸውን እና እድገታቸውን መከታተል ያስፈልጋል.
ዮርዳኖስ ይሁን (የስነ-አእምሮ ባለሙያ )

**""ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!!" 

Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)

Join Us**@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago