The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 3 days, 16 hours ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 3 weeks, 3 days ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 8 months, 3 weeks ago
Vacancy Announcements
Addis Ababa University College of Health Sciences, Tiqur Anbessa Specialized Hospital
1 BSc in #Psychiatry professional
3 BSc in #Midwifery
50 BSc in #Nursing
3 BSc in Medical #Laboratory Technology
1 BSc in Medical #Radiology Technology
3 BSc In #pharmacy
3 BSc in #Anesthesiology
1 BSc in #Biomedical Engineering
1 BSc in #Dental Medicine
1 BSc in #Physiotherapy
Minimum Experience: Vary ( #0_year – 7 years)
Deadline: October 25, 2024
✅Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry
ከሰሞኑ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት አካዳሚክ ጉዳዮች
ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በሰርኩላር ደብዳቤ የአእምሮ ህክምና የሙያ ስያሜ በተመለከተ የውሳኔ ደብዳቤ መላኩ ይታወቃል።
በደብዳቤው ለማተት እንደተሞከረው
ሁሉም ጤና የሚያስተምሩ ተቋሟት
BSC IN PSYCHIATRY NURSING
ወይም የባችለር ሳይንስ ዲግሪ በአእምሮ ህክምና ነርሲንግ እንዲጠቀሙ ገልጿል።
ለዚህ ወሳኔ ዋቢ ያደረገው ደግሞ የሚመለከታቸውን አካላት ማወያየት እና ከ2012_2015 ዓም የተመረቁ ባለሙያዎችን ግራጁየት ፕሮፋይል ነው።
ነገር ግን ጥያቄው የሙያ ስያሜ መነሻው ምንድን ነው? ዝም ብሎ በአቦ ሰጥ መሰየም ይቻላል ወይ?
በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይህንን ሙያ በዲግሪ ደረጃ ቀላል ለማይባሉ አመታት እያስተማሩ እነደነበረና አሁንም እያሰለጠኑ ይገኛሉ።
በስልጠናው የሚመረቁ ባለሙያዎችም
ተመርቀው ሲወጡ የሰለጠኑበትን አግባብ (Scope of practice) መሠረት ያደረገ የሙያ ስያሜ እንዲሰጣቸውና በተማሩበት ልክ ወደ ስራ መስክ ሲሰማሩ እንዲጠቀሙ የተለያዩ ሰነዶችን እንደሰነዱ ይታወቃል።
ለአብነት ያክል june,2019 ድራፍት ተደረጎ በ Aprile 2021 የጸደቀውን ካሪኩለም መመልከት ይቻላል። በዚህ ካሪካለም ነደፋ ላይ ጤና ጥበቃ፣ወደ ዘጠኝ የሚደርሱ ዩኒቨርስቶች እና Jhpiego ተሳትፈዋል።ሲጸድቅም ወደ 7 ዩኒቨርሲቶች ተሳትፈውበታል።ይህ ካሪኩለም ታዲያ የተመራቂዎች የሙያ ስያሜ ያደረገው "BSC IN PSYCHIATRY PROFESION" ወይም ደግሞ የባችለር ሳይንስ ዲግሪ በአእምሮ ህክምና ሙያ " ነው።
ይህን የሙያ ስያሜ ሲጠቀም በዋናነት ታሳቢ ያደረገው የሙያው የቀድሞ ተመራቂዎችን ሚና፣የአእምሮ ህመም ጫና እና ሀገሪቷ ባለሙያዎች በምን መልክ ቢሰማሩ አዋጭነት እንዳለው ከግንዛቤ በማስገባት ነው።
በዚህም የተነሳ እስከአሁን በትንሹ ወደ 3000ገደማ የሚገመቱ ባለሙያዎች ተመርቀው አያሌ አገልገሎቶችን እየፈጸሙ ይገኛሉ።
እነዚህን ያህል ቀላል የማይባሉባለሙያዎች ዩኒቨርሲቲዎች ሲያበቁ ወይም ሲያስተምሩ ባለሙያዎች ህመምን ለይተው ተገቢውን ማዳኒት እንዲያዙ የሚያደርግ ክህሎት ኮርሶችን ሲማሩ እንደነበረ ካሪኩለሞቹና ባለሞያዎች የተግባር እማኞች ናቸው (80% diagnosis and treatment role) ።
ለዚህም ሀገሪቷ አያሌ ሀብት አፍስሳለች። አያሌ ባለሙያዎች ራሳቸውን በክህሎቱ ለማብቃት ደክመዋል።ከዚህ የዘለለ ሚና (role) ደፍረው ለመሰማራት የሚያስችል ስልጠና እንደለሌላቸው ግልጽ ነው።
ሲጀመር ይህ የሙያ ዘርፍ በድግሪ እንዲሰጥ ገፊ ምክነያቶች ውስጥ ዋናው ምክነያት በዘርፉ የሚመረቅ የሰው ሃይል እጅጉን አናሳ መሆኑና የአእምሮ ህመም ጫና አሳሳቢ በመሆኑ ነው።
በዚህ የተነሳ ሀገሪቷ 1987 ዓም 12/11 ነርሶችን ከተለያዩ ዲስትሪክት ሆስፒታሎች መልምላ የአንድ ዓመት ስለጥና በመስጠት ወደ ነበሩበት ተመልሰው እንዲያገለግሉ በማድረግ ጀምራላች።
ይህም በቂ ሆኖ አልገኝ ሲል በሁለተኛ ዲግሪ ደግም የተለያየ የሙያ ዘርፍ ያላቸውን
ማለትምHO: Comprhensive nursing: Midwifery: Anesthesia ሙያ ያላቸውን በክሊኒካልም በማህበረሰብ የአእምሮ ጤና ስፔሻሊቲ እንዲኖራቸው በማሰልጠን ሙያው እንዲያድግ ጥረት እየተደረገ እንደነበር ይታወቃለ።
ከዚህ ባሻገር የዲግሪው መርሓ ግብር ዘርፈ ብዙ ችግር የሚፈቱ ባለሙያዎችን አፍርቷል እፎይታም እንደሰጠ ግልጽ ነው።
ጥያቄ ሁለት
ታዲያ ይህን ሁሉ ባለሙያ የበለጸገበትን ክህሎቱን እንዳይሰማራ ወደሚያደርግ ወደማያቀው ብቃት እንዲሰማራ የሚያስመስል ስያሜ መስጠቱ ያዋጣል ወይ?
Bsc in psychiatry Nursing
የሚለው ስያሜ የትኛው ካሪኩለም እንደወለደው እና ይህን የሙያ ስያሜ የሚመጥን ካሪኩለም (scope of practice) ዩኒቨርስቲዎች ነበራቸውወይ? የትምህርት ጥራት ማለት ምን ማለት ነው?
ሲጀመር ጤና ጥበቃ እስካሁን ያለው program አይጠቅምም ብሎ የሚያሳምንበት ሳይንሳዊ መንገድ ካለው በግልጽ ማሳመኛ መንገዶቹን ማስረዳትና ውሳኔ ላይ መድረስ ይቻላል።
አይ ሀገሪቷ የምትፈልገው surgical nursing care for psy pt:፣advanced nursing care for psy pt፣pediatric nursing care for psy pt:adult nursing care for psy pt Or comprensive psychiatric nursing ከሆነ የምትፈልገው ካሪኩለም አስቀርጻ ተገቢውን ስልጠና አግኝተው እንዲፈሩ ማድረግ ይቻላል።
ማንም የሙያ ጥላቻ የለበትም ።
ካልሆነ ግን በ8ክሬዲት medical surgical የተማረ አንድ ሳይካትሪን፣በ5 Chr obs /Gyn የተማረን አንድ ሳይካትሪን፣በ2chr nursing art የተማረን አንድ ሳይካትሪ፥5 chr pharmacology ስላጠና፣3chr psychotherapy የተማረን አንድ ሳይካትሪ ወዘተ: ግባና __ ሁን፣ ሁን፣ መሆን ትችላለህ ይባላል ወይ?
በዲግሪው መርሓ ግብር የpsychiatryዉን science 100% diagnosis and treatment ነው የሚያውቁት በተማሩበት ይሰማሩ ማለት ነውር ነወይ።
ካልሆነ
1.ይህ አካሂድ የባለሙያዎችን ሞራል ይጎዳል
2.ለሀገሪቷ ኪሳራ ነው
3.የሙያው ዘርፍ ያቀጭጫል
4.ከሁሉም በላይ ሰው የተማረበትን ሙያ መንጠቅ ነው።ለማንኛው በህግ መታየት አለበት።
በሌላም የጤና ዘርፍም ብንሄድና Nomenclature ብናይ፦
ANSTHESIA: Bachelor of science (BSC) in Anesthesia ነው።
Opthamology:optometry ነው
midwifery: midwife ነዉ።
physiotherapy እንደዛው ሁሉንም ማየት ይቻላል። እና ነርሲን የሚባል የተከበረ ሙያ ራሱን ችሎ የሚሄድ ትልቅ የጤና ዘርፍ ነው። ነርሲንግ ሙያ በአብዛኛ ዓለም በዲግሪው ጠቅላላ ዕውቀትን የሚፈልግ እና በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ ወደ አንድ ስፔሻሊቲ እያደላ የሚሄድ ነው።
ባለሙያዎች
በተማሩበት የስራ ክህሎት ይሰማሩ።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)
ጥቅምት/ 4 /2017
✅Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry
ሰበር ዜና እንዲሁም ተሰባሪ ዜና😂 እጅግ በዝቷል። ዜና ከሰማችሁ በኋላ እስቲ የውጥረት (Stress) መጠናችሁን አስተውሉ። ደስ የሚል ዜና መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ የሰማችሁት?🤔
ዜናን ተከትሎ የሚመጣ የውጥረት ሁኔታ Headline Stress Disorder ይባላል። 'ሰበር' ም ይሁን አል 'ሰበር' 😂 ዜናዎች ሁለት ወሳኝ አሉታዊ ነገሮች ያስከትላሉ።
1) አቅመቢስነት(Powerlessness)- አብዛኞቹ ዜናዎች ተስፋ ያስቆርጣሉ። ሴራ፣ ደባ፣ አሻጥር፣ ተንኮል፣ ጦርነት፣ ክፋት.....ወዘተ ናቸው። ከዛ ደግሞ በግለሰብ አቅም ምንም ማድረግ አንችልም። ሆኖም ስራችን ላይ ጠንክረን እንዳንሰራ ተነሳሽነታችንን ይሰልቡታል።
2) ህይወት ትርጉም የለሽ (Meaningless) እንዲመስለን ያደርጉናል። የሚሰማው ዜና ሁሉ መጥፎ ሲሆን ህይወት ትርጉም የለሽ ይመስለናል። "ሰራሁ አልሰራሁ ምን ለውጥ አለው?" እንድል ያደርገናል። ከራሳችን አቅምና ፍላጎት ይልቅ ትርጉም የለሽ ነገሮችን እንድንመለከት ያደርጉናል። ሰበር ዜናዎችን ስንመለከት ነገሮች ከመጥራት ይልቅ ይወሳሰቡብናል። ይሄኛው ያኛውን እወቀሰ ዜና ይሰራል። ያኛው ይሄኛውን እየከሰሰ ይተነትናል።እኛ በመሀል ተቃ.......ጠልን!
ጥሩ ነገሮች ለምን ዜና እንደማይሆኑ ግራ ይገባኛል።
ለምሳሌ፦
-ስዊዘርላድ ጦርነት ከተደረገ በጣም ቆይቷል።
-60 ሰዎችን ይዞ ሲሄድ የነበረው የህዝብ ማመላሻ አውቶብስ ለተሳፋሪዎቹ ቆሎ በነፃ እያደለ ነበር።
-አንዳንድ ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደነገሩኝ ከሆነ 'ውስጥ አዋቂ ምንጮች' የሚባለው ዜና እነሱን እንደማይወክልና ስም ተጠቅሶ በመረጃ ተደግፎ እንዲቀርብ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።😂
ለማንኛውም ዜና መቀነስ ለአእምሮ ጤና ጥሩ ነው።
በአንድ ሰበር ዜና እንለያይ "ቀላሉን ነገር አታካብድ" 6ኛ እትም ገበያ ላይ ነው!!!
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
✅Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry
Prescribing psychotropics from drug interactions to pharmacogenetics
✅Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry
"ፍቺ ሲያጋጥም ልጆች እራሳቸውን ይወቅሳሉ። ወላጆቻቸው በእነሱ ምክኒያት የተለያዩ ስለሚመስላቸው ከፍተኛ ፀፀት (Guilt) ውስጣቸው ይፈጠርና ወደፊት የስነ ልቦና ተፅእኖ ያመጣል።"
ይህን ያለው ፓስተር ቸሬ በሰይፋ ሾው በነበረው ቃለምልልስ ነበር::
በነገራችን ላይ
በተለይም ከ 11 አመት እድሜያቸው በፊት ወላጆቻቸውን በፍቺም ይሁን በሞት ያጡ ልጆች የኋላ የኋላ ለድብርት ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ እንደሆነ በተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ::
እንደ ማጣቀሻ ይህን ጽሁፍ ይመልከቱ:-
Roy A. Early Parental Separation and Adult Depression. Arch Gen Psychiatry. 1985;42(10):987–991. doi:10.1001/archpsyc.1985.01790330067008
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)
✅Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry
Movie recommendations for sunday!
Enjoy ?
?American sniper —- Post traumatic stress disorder
?Split , and ?The three faces of eve —- Dissociative identity disorder
?Touched with fire —- Bipolar disorder
?Rain man —— Autism spectrum disorder
?Prozac nation ? Little miss sunshine ? Ordinary people —— Depression
?A star is born ? Flight —— Substance related disorders
Ethio Psychiatry
✅Join Us
@ethiopsychiatry@ethiopsychiatry
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 3 days, 16 hours ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 3 weeks, 3 days ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 8 months, 3 weeks ago