❤❤የኪያ ደብዳቤዎች❤❤

Description
🌃 🌇


.
We recommend to visit

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Last updated 6 months, 1 week ago

🌃 🌇


.

Last updated 3 weeks, 4 days ago

3 weeks, 4 days ago

`አንዱ አባወራ ከሥራው በጊዜ ወደ ቤቱ ሲመለስ መኝታ ቤቱ ውስጥ ያልተለመደ ድምፅ ሰማ። መኝታ ቤት ሲገባ ሚስቱ ራቁቷን ላብ በላብ ሆና ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል።

"ምን ሆነሽ ነው ውዴ?"

"የልብ ድካሜ ተነስቶብኝ ነው" ብላ ማልቀስ ጀመረች።

ባልየው ደንግጦ አምቡላንስ ለመጥራት ስልኩን ሲያነሳ ትንሹ ልጁ እየሮጠ መጣና "አባዬ! ቁምሳጥን ውስጥ አጎቴ ተደብቋል። ደሞ'ኮ ልብሱን አውልቆ ራቁቱን ነው" ብሎ ተናገረ።

አባትዬው ቁም ሳጥኑን ሲከፍተው እውነትም ወንድሙን ራቁቱን ቁጭ ብሎ ሲያገኘው በንዴት እየተንቀጠቀጠ እንዲህ አለው "አንተ ዕድሜ ልክህን የማትረባ አህያ ነህ! ሚስቴ የልብ ድካሟ ተነስቶባት ልትሞት ደርሳለች አንተ ግን ራቁትሀን ቤት ውስጥ እየተሯሯጥክ ልጄን ያጫወትክ መስሎህ ታስደነግጥብኛለህ?"

ባሻዬ! እኔም አውነት እውነት እልሃለሁ! እኛም እንደዚህ ሰውዬ የዋህ ካልሆንን የእግዚአብሔርን መንግሥት አንወርስም`።

3 weeks, 5 days ago

`"ተረት ተረት..."

"የላም በረት..."

"አንዲት አይናማ ነበረች..."

"እሺ ..."

"ስታየኝ ስታየኝ ስታየኝ ስታ...የኝ የኖረች..."

"እሺ..."

"አንድ ቀን እርሟን ባታየኝ ነፍሴ መለስ ያለች..."

"እሺ ..."

"አይኗን የመለሰች ቀን .. ያስለመደችኝን ብትተወው
እኔ ታውሬ ቀረሁ... ማየትን ተቀማሁ...
"

"እግዚኦ ተዓምር አጀብ የሱ ስራ ...እ...ሺ "

"አማልዱኝ

ትየኝ የጨፈነችውን ትግለጥ .. ጨለማዬን ታብራ

ማን የሷ ብቻ አደረገው የግዜሩን እጅ ስራ

ተረት የለም ቀርቷል የምን አብሱ ነው አፌን
ባይኗ ገድላው የለም ወይ ልቤን !

መልሺ በሏት

ግለጪ በሏት

በአይኗ በኩል ነው ገነቴን 'ማያት!

መልሺ በሏት
ግለጪ በሏት` ...

3 weeks, 5 days ago

ሚስት ባሏ መታጠቢያ ቤት ሲገባ ጠብቃ የባሏን ሞባይል መበርበር ስትጀምር እነዚህን ስሞች አገኘች፣

  1. Super Woman

  2. My Love

  3. Woman of my Dream

  4. princess

  5. Second Mom

በጣም ተናደደችና የመጀመሪያውን ስትደውል የባሏ እናት አነሱ፣ ሁለተኛውን ስትደውል የባሏ ታላቅ እህት አነሳች፣ ሶስተኛውን ስትደውል የተይዟል ምልክት አሳያትና ቀጥሩን ስታጣራ የራሷ መሆኑን አረጋገጠች፣ አራተኛውን ስትደውል የሴት ልጇ ቁጥር ሆነ፣ አምስተኛውን ስትደውል የራሷ እናት ቁጥር ሆነ።

ባሏ ከመታጠቢያ ቤት ሲወጣ ሞባይሉን ስትጎረጉር በመድረሱ "ምን ፈልገሽ ነው?" ሲላት "ስለተጠራጠርኩህ ይቅርታ አድርግልኝ። 5 ስልኮች ላይ ደውዬ ታማኝነትህን አረጋግጫለሁ" ብላ የደስ ደስ 5000ብር ሰጠችው።

ባልየው ብሩን ተቀብሎ "Abebe Mechanic" በሚል ስም ለተመዘገበችው ውሽማው ሥጦታ ገዝቶላት ሄደ።

ባሻዬ! ወንድ እኮ ሁሌም ወንድ ነው!!

3 months, 1 week ago

**በስተመጨረሻ ጅምላ ጭምደዳው የተረፈው ወረቀት ጋር ተፋጠጥኩ ..ብእሬን አቀባበልኩ መፃፍ ጀመርኩ

"እንደውም ላይሽ አልፈልግም አጠገቤ ድርሽ እንዳትይ እስካሁን የታገሽኝ ይበቃል.."

ይሄን እንደፃፍኩ ናፈቀቸኝ ወድያው ወረቀቱን ቀደድኩት ከራሴ ጋር ግብ ግብ ገጠምኩ ቆይ አለመውደድ አለማፍቀር መብት አደለም እንዴ?

?121**

3 months, 1 week ago

ነገን ማለም ቀርቶ ዛሬን መኖር አቃተን፤አረጀን መሰል ትላንትና ላይ ቀረን አይደል? የህልም አለም ሰዎች መሆን ሆነ እጣፈንታችን። ከህልማችን ስንባንን እውነታው አሳማሚ ሆነብን።ሁላችንም በማንም ሊሞላ የማይችል ባዶ ቦታ አለችን፤ ወይም በሆነ ሰው ተከፍቶ የቀረ ሽንቁር። ለምን ማንም ህይወታችን ውስጥ ቢገባ ያለ ምክንያት መከፋታችንን ይሁን በሰው መሀል ብቸኛ መሆናችንን ሊያስወግድልን አልቻለም?

ነፍሴ ከአዳኟ እንደምታመልጥ እርግብ ይህን አለም ሸሽታ ትበራለች። መብረር ሲታክታት የምታርፈው በሸሸችው አለም ነው፤ ባያሳርፋትም። ያኔ ቀድሞ በነበረው ፍርሀቷ ላይ ተስፋ መቁረጥ ይጨመራል። እንደገና የህልም አለም በረራ ትጀምራለች፤ ስትባንን አመለጥኩት ካለችው አስቀያሚ እውነት ጋር ትላተማለች። የመሸሽ ሩጫዋ አብቅቶ እንዳልኖረች ትሞታለች። አይ ነፍሴ!

ብረሪ አምልጪ ከፍ ወደ ሰማይ
አዳኝ ነው እንጂ አዳኝ የለም ከላይ
ፈራሁልሽ ነፍሴ የህልም በራሪ
መፅደቅ የተመኘሽ በሀጥያት ዘውታሪ።

  ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

3 months, 1 week ago

`አንድ ቀን አዳም በኤደን ገነት ውስጥ ከቆየ በኋላ “ጌታ ሆይ ችግር አለብኝ” ብሎ ተጠራ።

“አዳም ሆይ ችግሩ ምንድን ነው?” ጌታ ይመልሳል።

"ጌታ ሆይ እንደፈጠርከኝና እንዳዘጋጀኸኝ አውቃለሁ እናም በዚህ ውብ የአትክልት ስፍራ እና በእነዚህ አስደናቂ እንስሳት  አጥረኸኛል ግን ደስተኛ አይደለሁም።"

“አዳም ሆይ ይህ ስለምንድነው?” የሚል መልስ ከሰማይ መጣ።

"ጌታ ሆይ ይህን ስፍራ ከዚህ ሁሉ የተወደደ ምግብና ውብ እንስሳት ጋር እንደፈጠርክልኝ አውቃለሁ። እኔ ግን ብቸኛ ነኝ።"

“እንግዲህ አዳም እንደዚያ ከሆነ ፍፁም መፍትሄ አለኝ 'ሴት'ን እፈጥርልሃለሁ።”

አዳም "ጌታ ሆይ 'ሴት' ምንድን ናት?"

ፈጣሪም “ይህች 'ሴት' ከፈጠርኳቸው ሁሉ የበለጠ አስተዋይ፣ ስሜታዊ፣ አሳቢ እና ቆንጆ ፍጡር ትሆናለች። እሷ በጣም አዋቂ ከመሆኗ የተነሳ ከመፈለግህ በፊት የምትፈልገውን ነገር ማወቅ ትችላለች። ስሜትህትን እንዴት ማስደሰት እንዳለባት የተካነች ነች”

"በጣም ጥሩ ትመስላለች" አዳም በጉጉት ተናገረ።

ፈጣሪ “ትሆናለች ይህ ግን ዋጋ ያስከፍልሃል አዳም!!”

"ይህች 'ሴት' ምን ያህል ዋጋ ታስከፍለኛለች?" ሲል አዳም ጠየቀ።

“ጆሮውህን፣ ልብህን፣ ዓይን እና በዋነኝነት አዕምሮን ያስከፍልሃል። እነዚህን ካንተ ወስጄ ከሰራዋት ከጆሮህ አዳማጭነት፣ ከአይንህ አስተዋይነትን፣ ከልብህ ታጋሽነትን፣ እናም ከአዕምሮ ደግሞ ታላቅ አሳቢ የሆነች ሴት ትወጣለች”

አዳም ፊቱ ላይ ጥልቅ ሀሳብ እና ጭንቀት ይታያል። እና ለጥቂት ጊዜ ካሰበ በኋላ "ጌታ ሆይ ይህ ሁሉ ዋጋ ከፍዬ የማገኘውን ነግረኸኛል። እኔ ምለው ከጎድን አጥንቴ ብቻ ብትሰራት ምን አገኛለሁ?"`?

6 months ago

?በአዲስ አመት ዋዜማ ሚገርም ቻሌንጅ ነው የገጠመኝ ማሽኔ ተበላሸ ለቀጣይ አመት አንዲስ እንድገዛ ነው መሰለኝ አይመስላችሁም? ህይወት እንዲ ናት በአስደናቂ ፈተናዋች የተሞላች

?121

6 months ago

❗️*❗️ warning ይሄ ፁሁፍ ያፈቀራቹ ሰዋችን ብቻ ነው ሚመለከተው ....ይሄን ያልኩት ያለአፍቃሪ ባንዳዋችን መረን የለቀቀ ኘሮፓጋዳዋችን ላለመስማት ነው ..ፍቅር እውር ነው ነው ወይስ አደለም?*

?121

6 months, 1 week ago

ዛሬ ያሰብነውን እንዳሳካን አምናለሁ በአጠቃላይ ደስ የሚል ውሎ ነበረን አደል? እስኪ በemoji ግለፁት

የኔ ? ነበር የናተስ? ሰናይ ምሽት ይሁንላቹ

121

9 months, 4 weeks ago

?°•ደሀ ሆነክ ከተወለድክ የአንተ ስህተት አይደለም፣ደሃ ሆነክ ከሞትክ ግን ያንተ ስህተት ነው።°

°መልካም ምሽት

We recommend to visit

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Last updated 6 months, 1 week ago

🌃 🌇


.

Last updated 3 weeks, 4 days ago