Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

❤❤የኪያ ደብዳቤዎች❤❤

Description
🌃 🌇


.
እንማር @Kiya000
Advertising
We recommend to visit

ለሚወዷቸው ሰዎች በራሳቸው ፎቶ የተሰሩ ልዩ ስጦታዎች (customized gift) ያበርክቱ እና ትዝታዎችን ይፍጠሩ።

Last updated 4 months, 2 weeks ago

Unmute The Channel You Dumb Hoe.


powered by እንጀራ በወጥ.💪🏽🇪🇹
ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ፡፡
For business inquiries @onlyf0rme

https://telega.io/c/injera_niggas

Last updated 3 months ago

4 weeks ago

😊የኔ እውነተኛ ታሪክ ነው

አkoብya:
የኔ የፍቅር ታሪክ ለመባል የሚበቃ ታሪክ ሆኖ አይደለም እና ትሁን ካልሽ ይህው ፍቅር የያዘኝ አንዴ ነው 8ተኛ ክፍል እያለው።ለመጀመሪያ ግዜ ልብ ያልኳት አማርኛ መምህራችን ልቦለድ አንብባችሁ አቅርቡ ሲሉን የእሷ ተራ ደርሶ ስታቀርብ በቃ የአንደበቷ ጥፍጥና የድምፃ አወራረድ ወፎች እራሱ በድምፃ ውበት ተማርከው እሷን ለማዳመጥ መዝፈን ሚያቆሙ ነው ሚመስለኝ ከዛማ ልቤም እንደ ኦኬስትራ ባድ በሃይል መምታት ጀመረ ግራ ገባኝ ከዛች ታሪካዊ ቀን በሀሏ  እሷ ስትመጣ የምፅአት ቀን የደረሰ ነው ሚመስለኝ ቃላቶቹ እራሱ የት እንደሚገቡ እንጃ ማወራው እየጠፋብኝ ለይምሰል መሳቅ።ጥሎብኝ መፅሐፍ ሳነብ ቦታ አልመርጥም እና ክላስ ውስጥ እያነበብኩ አጠገቤ መጥታ "ምን የሚል መፅሐፍ ነው ምታነበው አለችኝ''  አቤት ቃሉን ለማውጣት የማማጥ ያህል ነው የከበደኝ አፌ ላይ ነው በምን አቅሜ ብዬው ልገላገል በድን አርጋኝ ሁላ ግራ ሲገባኝ መፅሐፉን አሳየዋት "ውይ ዴርቶጋዳን ነው እንዴ ምታነበው ስወደው እኮ ደራሲውም ጎበዝ ነው " የዛኔማ ይስማከን ለመሆን እንዴት እንደ ተመኘው.....
ይቀጥላል

የዛንኔማ ይስማከን ለመሆን እንዴት እንደተመኘው።"ምነው ዝም አልክ እረበሽኩክ አኪ አለቺኝ" እንደምንም የሞት ሞቴን "አይ"የምትለውን ቃል አወጣው።"እሺ አኪ በቃ ስጨርስ ታውስኛለክ" በእሺታ አንገቴን ነቀነኩ "ቃል ገብተሃል ደሞ" እያለች እየሳቀች ወደ ወንበራ ተመለሰች።ድንጋጤዬ አለቀቀኝም ነበር ትንሽ ስረጋጋ ከሚጣፍጠው አንደበቷ የኔን የሚስኪኑን ልብ ይዛ እብስ ያለች መሰለኝ እንዴት አላውቅም ፍርሃቴ ጨመረ።በከዚች ልቤን ካስረከብኩበት እለት ጀምሮ አምሮዬ ስራ በዛበት ብል ማጋነን አይሆንብኝም በቃ ስለሳ ማሰብ አመማት እራት በላች ደበራት ምናምን አንዳዴማ እንደ ውዳሴ ማርያም ጥዎትና ማታ telegram ላይ ያወራነውን ደግማለው ከዛ እንደ እብድ ስቃለው።ፍቅር ማለት ወርቁ የተሰወረ እግዜሩ የፃፈልን ቅኔ ነው?
ምኗን አይቼ ወደድኩት አላውቅም ፍቅር እውር ነው ሲባል ሰምቼለው ሳስበው ግን እኔ የታወርኩ ነው ሚስለኝ ግንኙነታችን በዚህ መንገድ አመት ከመንፈቅ ሞላው እኔ ስለፍቅር ማውቀው ነገር የለም ከመፀሐፍና ከፊልም ከቃረምኩት ውጪ "ትንሽ እውቀት አደገኛ ናት"ማን ነበር ያለው በቃ ነኔም ነገር እደዛ ነው የሆነው በቃ ክላስ ስትመጣ ሰላም ብያት ትሔዳለች የሆነ ግዜ ላይ ጠበኩዋት አልመጣችም ለትመለስ ልቤን ይዛ በዛው ቀረች ቀረች።አርስቶትል "አፍቅር ከተሳካልህ ደስተኛ ትሆለህ ካልተሳካልህ ደሞ ፈላስፈ ትሆናህ " እኔም ልክ ይመስለኛል በምን ልብ ያፈቅራል ታድያ።

1 month ago

የቀጠለ **..

ሰአቱ ይፍጠን ይቀርዝዝ ግድ የማይሰጠኝ ልጅ ብዛት ሸረሪት ካደራባቸው የፍቅር መፅሐፍ አንዱን አንቼ መኮምኮም ጀመርኩ...ሰአቱን አየሁት 8:30 ይላል ቶሎ ብዬ ይኑፎርሜን ለብሼ ላይብረሪ ደሰረስኩ እንዴት እንደደረስኩ እራሱ ለኔም አልገባኝም ላይብረሪ ውስጥ እንደ ገባው ወንቦሮቹ ልክ እንደ ሀብታም ቤተሰብ ጠረጴዛ በትይዩ ተሰድረዋል ሉሊትን በአይኔ እፈልጋት እጀመርኩ ደሞም እሷን መፈለግ ይሔን ያህል ከባድ አይደለም እንዳየቺኝ ከዳር ሆኗ እጇን አውለበለበችልኝ ...የልቤን በር ዘልቃ ያንኳኳችው ነበር የመሰለኝ በዛ ላይ በእሷ ትይዩ እንደምቀመጥ ሳስበው ልቤ በሀል መምታት ጀመረ ድው..ድው...ቁና እየተነፈስኩ ከእሷ ትይዩ ካለው ወንበር ተሰየምኩ "እንዴ ሳሚዬ መጣህ" አለችን ሳቅ እያለች "አዋ" "እኔማ ስታረፍድ ግዜ ምትቀር መስሎኝ ነበር" አለቺኝ ደሞ ስታሾካሽኽ አቤት ደስ ስትል "መፅሐፍ እያነበብኩ ነው እኮ ሰአቱ የሔደብኝ" አልኳት ከአይኗ ለመሸሽ ጣራ ጣራው እያየው "ኸረ ባክህ እርግጠኛ ነኝ የትምህርት አይደለም አ" "አዋ" "የትምህርትም አንብብ እሺ 1ኛውን ጥያቄ ሞክረው" አለቺኝ ደሞ እኮ ባዬሎጂ ነው ባዬሎጂ ትምህርት በጣም ነው ምጠላው እንደአሸን ከተረደረደሩት አንዱን መፀሐፍ አንስቼ መልሱን አገኘሁት ወደ ወንበሬ ተመልሼ ለሉሊት አሳየዋት ከመቀስፈት "ብራቮ ሳሚ ብላ" ጮኸች "እንዴ ላይብረሪ መሆናችንን እረሳሽው" ብዬ መፃፌን እንደቀጠልኩ ትከሻዬ ላይ እጅ አረፈብኝ**

....
🖌አኮብያ

1 month ago
መፍራት ጥሩ ነው

መፍራት ጥሩ ነው

Game of Trone ጸዴ ፊልም ነው። ፊልሙ ላይ አንድ ዲያሎግ አለ። አባቱ ኔድ ስታርግ እንደታሰረ ሲሰማ ልጁ ሰራዊት ይዞ ለመዝመት አውርቶ ሲጨርስ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር። አብሮት የነበረው ጓደኛው ይህንን አይቶ

ፈርተሀል እንዴ

መሆን አለበት

ጥሩ

ለምን ይሄ ጥሩ ይሆናል

ምክንያቱም ከፈራህ ደደብ አይደለህምና

ድፍረት ጥሩ መፍራት ግን ጠንቃቃ ያደርጋል። መፍራት እንድንመረምር ያደርጋል። ጠርጣራዎች ናቸው የተደበቀን የሚያገኙት። የሚፈሩ ናቸው ከከባድ አደጋ የሚያመልጡት።

1 month ago
የጅንጀና ጥበብ ***🧠***

የጅንጀና ጥበብ 🧠

ምን እያረግሽ ነው?

"ጉንፋን አሞኝ ማር እየጠጣው"

ቱ የመጨረሻው ዘመን ደረሰ ማለት ነው 😭

"ምነው?"

በመጨረሻው ዘመን ማር በማር ላይ ይነሳል😁

1 month ago

*😊*የቀጠለ

"ሳሚ ቀና በል እንጂ" አለቺኝ ፈገግ ብላ እፍረቴ ገፄ ላይ እንደ ዘመኑ ሜካብ ጎልቶ ይታያል ቀና ማለት ፈራሁ ድጋሜ ስሜን ጠራችው አይኔ መሬት ላይ እንደተቸነከረ ቀና አልኩ "ሳሚ የአንደኛውን ጥያቄ ሞክረው ደሞ አትጨናነቅ መልሱን ባትመልሱም ችግር የለውም" አለችኝ ፈገግታዋ አሁንም አልተያትም አንዳንዴ ሳስበው ስትወለድ እራሱ እየሳቀች ነው ሚመስለኝ...የሰጠችኝን ጥያቄ ያለወትሮዬ መስራት ከበደኝ ፍዝዝ ድንዝዝ ብዬ ከባዶ ወረቀት ጋር መፋጠጥ ሆኗል ስራዬ "ቢኒ በቃ አትጨናነቅ ከሰአት library መጥተን እንሰራዋለን "አለችን "እሺ" ብዬአት ልክ እንደ ጥንት ካሜራ አየት አርግቼአት ጨፈንኩ..ሁኔታዬ ገርሟት ነው መሰል መሳቅ ጀመረች ሳቋ በፊት ከሰማዋቸው ሁሉ የተለየ አንዳች የምትሀታዊ ሀይል የተላብሷል የሆነ በልኩ የተቀመረ ነው ሚመስለው "ደሞ ቀርተህ ጉድ እንዳታረግኝ " ብላኝ ወደ ቦታ ተመለሰች ...ሰአቱ ይፍጠን ይቀርዝዝ ገድ የማይሰጠኝ ልጅ በምናቤ ሁሉ ሰአት መቁጠር አማረኝ....**

😊ይቀጥላል.....

🖌አኮብያ

1 month, 1 week ago

የቀጠለ

የቤተሰቤ "ና ግባ" ጩኸት የለማ ..ስድብ የለማ...ከዝምታዬ የራሴን አርምሞ እያደመጥኩ በግዜ ሒደት ጓደኞቼን ከነመፈጠራቸው እረሳዋቸው ብቸኝነቴን ተላመድኩት ቀስ በቀስ የህይወቴ አንድ አካል ሆነ ከትምህርትቤት ወደ ቤት ከቤት ትምህርትቤት የሚገርመው ነገር ደግሞ ከትምህርት ቤትም ጓደኛ አለመፈለጌ ነበር...ጓደኝነት ፍቅር ለኔ እንግዳ ነገር ናቸው ...ድንቡሿን ሉሊትን ሳያያት ደስ ይለኛል በተለይ ስትስቅ ነፍሴን ወደሌላ አፅናፍ ነው ምዘፍቀው ግን በጣም ነው ምፈራት ..መምህራችን አሳይመንት ስሩ ብለውን ከነ ሉሊት ጋር ደረሰን ደስታም ፍረሀትም ተሰማኝ.." ሳሚ ቃና በል እንጂ" አለችኝ ፈገግ ብላ እፍረቴ ገፄ ላይ በደማቁ ያሳብቃል ቀና ማለት ፈራሁ

😊ይቀጥላል ...

🖌አኮብያ

1 month, 1 week ago

"**ውዴ አንተ እኮ ፍቅር አይገባህም " ትለኛለች እንዴ ደሞኮ አኩሩፋለች እሺ እኔ ፍቅር አይግባኝ ..ማኩረፏ ምን የሚሉት ጉድ ነው ..አስተዳደጌን ብታውቅ ኖሮ እንዲ አትለኝም ነበር ሲጀምርም ሚትቀርበኝ አይመስለኝም ...

ስሜ እንኳን ለኔ ላወጣልኝ እራሱ ትርጉም ያለው ያለው አይመስለኝም ህይወቴም እንዲሁ ትርጉም አልባ እየሆነ መጥቷል ..ስምን መለአክ ያወጣዋል ሚባለው እውነት ነው እንዴ? ...ያደኩት "እንግዳ መጥቷል ሂድ ወደ ጓዳ ግባ " እየተባልኩ ነው በዛ ለጋ እድሜዬ በአምሮዬ የተቀረፅው እንግዳ ደሞ "የሚያስፈራ ፍጡር ነበር "እናቴም አባቴም ሚፈሩት ልክ እንደ ጭራቅ አይቼው አላቅማ...ይባስ ብሎ ነፍስ አውቄ እራሱ እንግዳ መቷል ና አናግራቸው ስባል ወደ ጓዳ መሔድ ይቃጣኛል..በጨቅላነቴ በአምሮዬ የታተመው ድብዝዙ የእንግዳ ምስል አሁም አልነፃም...ውጪ ከልጆች ጋር ለመጫወት ስሞክር ቤተሰቦቼ በአይነ ቁራኛ እየተከታተሉ ያስገቡኛል የሆነ ግዜ ላይ እኔም ውጪ የመውጣት ፍላጎቴ ኮሰመነ ከጓደኞቼ ጋር ተጫውቼ የማገኘው ደስታ በላይ እቤት ቁጭ ብዬ የማገኘው ሰላም ገዘፈብኝ ለምን ከተባለ የቤተሰቤ "ና ግባ" ጬኸት የለማ ..ስድብ የለማ..
😊**ይቀጥላል ..

🖌አኮብያ

1 month, 1 week ago
❤❤የኪያ ደብዳቤዎች❤❤
1 month, 1 week ago

**አቢሲኒያ ባንክ ግን እንደዚህ አየር ተይዟል ወይስ ሰራተኞቹ እየደበራቸው ነው... ይደውሉና

-ኤቲኤም ካርድህ ደርሷል
-ወስጃለው
-ኦ ኦኬይ... በተረፈ አማን ነው... ምን አዲስ ነገር አለ
-እ
-ሞባይል ባንኪንግ ተመዝገባ
-አለኝ እኮ
-ኦ ኦኬይ... ፒያሳን አፈራረሱት አ?!
-ምንድነው የምትይኝ?
-ለሴቶች ብቻ የተከፈተ ከወለድ እና ከወሊድ ነፃ የሆነውን ሀቢብቲ አል ሙሸበክ ላ ሙጢልጢል የተባለውን አካውንት ሚስትህን አስመዝግባታ
-ሴትዮ ሚስት የለኝም
-ሂዛ... ውሸታም... ማርያምን በል እስቲ... ውሸታሞች እኮ ናችሁ... በለጠ አናጢውም እንዲህ ብሎ ነው የተጫወተብኝ... ሲጀመር ሌላ ነገር አስበህ ከሆነ...
-ቻው!
-እሺ... ነገ እደውላለው... ቲንደር ባን... ማለቴ አቢሲኒያ ባንክ**...

1 month, 2 weeks ago
[#Repost](?q=%23Repost)

#Repost
የእኛ ቢሆን ብላቹ በምትመኙት በምትወዱት ከልባቹ በምትናፍቋቸው ሰዎች ግዴለሽነት ችልተኝነት አለመፈለግ ሲገጥማቹ ቀድሞ ወደ አዕምሯቹ የሚመጣው ምን ይሆን? ለነዛ ሰዎች እንደማትገቧቸው እንደማትመጥኗቸው ወይስ እነዛ ሰዎች እንደማይገቧቹ እንደማይመጥኗቹ

እራሳችሁን እንደ ሰዎች ፍላጎት ማሟያነት የምታስቡ ከሆነ ወደዳችሁም ጠላችሁም ሚዛናቹ በእነርሱ ተቀባይነት ማግኘት አለማግኘታቹ ነው

እራሳችሁን ለእነርሱ ብቁ ማድረግ ላይ ካተኮራቹ መለኪያቹ የእነርሱ ምላሽና ተቀባይነት ይሆናል
እነርሱ የሚያሰምሩላችሁን መስመር መቀበልና ማለፍ ሲሳናቹ የጀመራችሁትን የእራሳችሁን ትክክለኛ መንገድም ትስታላቹ የእነርሱን ምላሽ እንደ ማንነታቹ ልኬት መቀበል ትጀምራላቹ

በናተ ደረጃ በናተ ልኬት ያልሆነ አናተን የማይመጥን የትኛውም ነገር አናተ ጋር የሚሆንበት ምክንያት አይኖረውም ብዙ ጊዜ እናተ በቂ ሳላልሆናቹ ሳይሆን እናተ ከበቂ በላይ ስለሆናቹ መተው ያለባቹ ሁኔታዎች ወይም ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ

ከናተ አንሶ መገኘት ከናተ አለመቻል ከናተ ብቁና ዝግጁ አለመሆን ሳይሆን ከተቀባያቹ ከደረጃ ማነስና ብቁ አለመሆን ያሰባችሁት ነገር ላይሳካ ይችላል ለራሳቹ ትክክለኛ ታማኝ ወዳጅ ተንከባካቢና አሳቢ እንደሆናቹ ከተሰማቹ ወደ ህይወታቹ የሚገቡትም ሰዎች እንደዛው ይሆናሉ ብላቹ አትጠብቁ

አናተ ታታሪ ጠንካራ ለአላማቹ የምትታገሉ ከሆናቹ በጥቃቅን ጊዜያዊ ተግባር ላይ ጉልበትና ግዜያችሁን የምታጠፉ ከሆነ በእርግጥም የማይመጥናቹ ስፍራ ላይ ተገኝታችኋል ማለት ነው

በህይወታቹ ጥበቃን ተለማመዱ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቁ የሚመጥናችሁን ሰውም ሆነ ሁኔታ በትዕግስት ተጠባበቁ የናተ ለነገሮች ዝግጁ መሆን ብቻ ግንኙነታችሁን ወይም ስራችሁን ውጤታማና ስኬታማ አያደርግም በምትወዱት ሰው አለመወደድ የናተ ችግር አይደለም በምትወዱት ስራ ለውጤት አለመብቃት የናተ ክፍተት አይደለም የምትፈልጉት ቦታ ያልደረሳችሁት ስለማትችሉ አይደለም

አንድም ፍላጎታቹ ከናተ ልኬት በታች ነው ሌላም ጊዜው አሁን ስላልሆነ ነው የማይወዳችሁን ሰው እንዲወዳቹ የመታገል ግዴታ የለባችሁም የማይመለከታቹ ስፍራ መገኘት አይኖርባችሁም በተመጣጣኝ ሁኔታ ለናተ ስሜት ከሌለው ሰው ጋር ጊዜያችሁን የምታባክኑበት ምንም ምክንያት የለም ኧ

We recommend to visit

ለሚወዷቸው ሰዎች በራሳቸው ፎቶ የተሰሩ ልዩ ስጦታዎች (customized gift) ያበርክቱ እና ትዝታዎችን ይፍጠሩ።

Last updated 4 months, 2 weeks ago

Unmute The Channel You Dumb Hoe.


powered by እንጀራ በወጥ.💪🏽🇪🇹
ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ፡፡
For business inquiries @onlyf0rme

https://telega.io/c/injera_niggas

Last updated 3 months ago