Mulugeta Anberber

Description
ፈጣን መረጃ እንዲሁም ለዕለታዊ ክንውኖች ወዳጅ ይሁኑ❗️

ዜናው ጥሩም ይሁን፤ መጥፎ እነግራችኋለሁ፡፡


መረጃ ለመላክ @Mulugetaanberberrrr
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

2 weeks ago
እንኳን ለፋሲካ/ትንሳኤ በዓል በጽናት አደረሰን፤ አደረሳችሁ!

እንኳን ለፋሲካ/ትንሳኤ በዓል በጽናት አደረሰን፤ አደረሳችሁ!

https://t.me/MulugetaAnberberEthio251

2 weeks, 1 day ago

ከአማራ ፋኖ ወሎ እዝ
ከአማራ ፋኖ በጎጃም
ከአማራ ፋኖ በጎንደር
ከአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ

ለመላው የአማራ ህዝብ እና የትግሉ አባላት የቀረበ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት:-

የአማራ ፋኖ ለመላው የአማራ ህዝብና በህልውና ትግሉ ማዕቀፍ በፅናት እየተሳተፈ ለሚገኘው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ማለት ይወዳል።

የአማራ ፋኖ ህዝብ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ ብሎ፣በአማራ ህዝብ ላይ የሚሰራውን መንግስት አቀፍ የፖለቲካ አሻጥር እና የታወጀበትን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመመከት፣እሱ ተሰውቶ የአማራን ህዝብ ትንሳኤ ለማብሰር ከሞቀ ቤቱ ወጥቶ ፣ከቤተሰቦቹ ተለይቶ በዱር በገደል በዓልን ሲያሳልፍ የነገውን ትንሳኤ በማሰብ የዛሬውን ስቃይና መከራ በብቃት ይወጣል።

ለሰላሳ ዲናር ብሎ ፈጣሪውን እንደሸጠው ይሁዳ ለሚጣልላቸው የዳቦ ምንዳ እና ለዙፋናቸው ሲሉ የአማራን ህዝብ አሲዘው ቁማር የሚጫወቱት የአማራ ተወካይ ነን የሚሉ ባለስልጣናት ለወንበር ያበቃቸውን ህዝብ ለሞትና ስደት፣ለእንግልትና ውርደት ሲዳርጉት ስናይ እኛ የአማራ ፋኖዎች የምንከፍለውን ሁሉን አቀፍ መስዋዕትነት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቡን ለማዳን ሲል የተቀበለውን መከራ እና ሲቃይ እንደዘላለማዊ ስንቅ እንጠቀመዋለን።

በርግጥ ሊነጋ ሲል ይጨልማልና አሁን ላይ የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለው መከራና ሲቃይ፣ስደት እና እንግልት ፣ርሀብና ጥም የአማራ እናት አምጣ የወለደችው ጀግናው የአማራ ፋኖ ከብልፅግና መራሹ ከአገዛዙ መንጋ ጋር የሚያደርገው ህዝባዊ ተጋድሎ ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳው አምላክ ይቆጥረዋል፤ የትግል ድሉንም በቅርቡ ይጎናፀፋል።

ውድ የአማራ ህዝብና የአማራን የህልውና ትግል ባንድም በሌላም እየደገፋችሁ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጽያውያን በዓሉ የሰላም፣ የጤና እንዲሆንላችሁ እየተመኘን በዓሉን ስታከብሩ ርሀብና ጥም፣ሀሩር እና ብርዱ፣ ድካምና እንግልቱ ሳይበግረው፤ የበዓሉ ድምቀት ሳያማልለው ለህዝብ ሲል ነፍጥ አንስቶ እየተዋደቀ ያለውን የአማራ ፋኖ ቤተሰቦችን በመደገፍና በመንከባከብ ፣ አቅመ ደካሞችን በማገዝ እንዲሁም አማራዊ ማንነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያው የሚገኙ አዛውንቶችን ወንድምና እህቶቻችንን በመደገፍና በመጠየቅ ይሆን ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የወገንህ ግፍ እና መከራ አንገሽግሾህ የአገዛዙን ስርዓት በቃህ ብለህ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈልክ የምትገኘው የአማራ ፋኖ:- የምናደርገው ተጋድሎ መነሻ ብቻ ሳይሆን መደራሻም ያለው ታላቁን የአማራ ህዝብ ስንቅና ትጥቅ ያደረገ ስለሆነ እንደ አለት ፀንተን የህዝባችንን የድል ችቦ በአጭር ጊዜ ማንፀባረቅ ይኖርብናል።

ህዝባዊ ትግሉን በተለያየ መንገድ እያገዛችሁ ሲደክመን እያበረታታችሁ፣ ስንሳሳት እያረማችሁ ያላችሁ መላው የአማራ ህዝብና የትግሉን እውነተኛነት በዉል የተረዳችሁ በየትኛውም አካባቢ የምትገኙ ማህበረሰባችን ትግላችን ተገፍተን፣ ተበድለን፣ ችለን፣ ታግሰን፣ ተናግረን፣ ጮኸን ሰሚ አጥተን የጀመርነው ትግል እንጂ የፀብ አጫሪነት ትግል አለመሆኑን በመረዳት የጀመራችሁትን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ የግፍ ሞት በታወጀበት የአማራ ህዝብ ስም መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

በድጋሜ መልካም የፋሲካ በዓል።
"ድላችን በክንዳችን"

ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓ/ም
ከአማራ ትግል ሜዳ!

2 weeks, 1 day ago

የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ በጎንደር የተሰጠ መግለጫ!

የተከበርከው የአማራ ህዝብ፣ የመላው አማራ ፋኖ አባላትና፣ የተከበራችሁ የአማራ ሕዝብ ወዳጆች፤ በተለይም ዐብይ ጾምን ለምትፈቱ ወገኖቻችን፤ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሳኤ አደረሳችሁ።

ይህንን በአል ስናከብር ቀጣዩን ፈታኝ የትግል ምእራፍ በድል እንደምንወጣውና ለህዝባችን የድል ብስራትን በፈጣሪ እርዳታና በክንዳችን እንደምናመጣ የፀሐይን መውጣት ያህል እርግጠኛ በመሆን ነው፡፡ ይህ የትግል ቃልኪዳናችን የሕዝባችን ትንሳኤ መባቻ እንደሚሆን የጸና እምነታችን መሆኑን በመግለጽ፤ ሕዝባችንን ለውርደት፣ ለጭፍጨፋና ለከፍተኛ ውድመት በመዳረግ እንዲሁም እራሳችንን እንዳንከላከል ለዘመናት እጅ እግራችንን አስሮ የኖረውን የብአዴን(ብልጽግና ምስለኔ) አገዛዝ በጣጥሰን እየጣልን ወደማይቀረው ነጻነት መቃረባችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

በብአዴን (ብልጽግና) መቃብር ላይ የሕዝባዊ አስተዳደር መዋቅሮችን ለመዘርጋት በሚደረገው ጥረት በንቃት ትሳተፉ ዘንድ ሁለንተናዊ ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን የሚከተለውን የጥንቃቄና የትግል ጥሪ መልዕክት እናስተላልፋለን። 

1) የአካባቢ ሰላምና ደህንነት አጠባበቅን በተመለከተ፤

• በቤተ እምነት፣ በድግስና በገበያ አካባቢዎች ተሰባስቦ ማክበር ለድሮን ጥቃት ኢላማነት ስለሚያጋልጥ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይህንን ባለማድረግ የራሱን ደህንነት መጠበቅ እንዲችል፤

• በገበያና በእምነት ቦታዎች ዙሪያ የማህበረሰቡን ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ጸጉረ ልውጦችን በአትኩሮት በመከታተል በተለይ ወጣቶች ይህንን በማድረግ የማህበረሰቡንና የአካባቢውን ደህንነት ለማስጠበቅ ሀላፊነት እንድትወስዱ ጥሪ እናቀርባለን።

• በድግስ፣ የደስታ ወይም የሀዘን መግለጫ ቦታዎች ላይ ወይንም ማንኛውም ሰላማዊ ሰዎች በተሰበሰቡበት አካባቢ ምንም አይነት ተኩስ እንዳይኖር፤ ይህንን ተላልፎ ህገወጥ ድርጊት የሚያደርግ አካል ካለ በአካባቢው ላሉ የፋኖ አባላት በአስቸኳይ ሪፖርት እንዲደረግ ስንል እናሳስባለን፡፡ 

• በአልን ተገን በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች በሀሰት የፋኖ አባላት በመምሰል የዝርፊያ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦችን በመለየት ለማህበረሰቡ ብሎም በአካባቢው ላሉ ለትክክለኛ የፋኖ አባላት አጋልጦ በመስጠት እንድትተባበሩን ስንል እናሳስባለን።

2) እንደወግ እንደባህላችን በታላላቅ በዓላት ወቅት በሰፊው ደግሶ ከወዳጅ ዘመድ ጋር ማክበር የተለመደ እሴታችን ነው፡፡ ይሁን እንጅ የዘር ማጥፋት ጦርነት የታወጀብን ሕዝብ እንደመሆናችን መጠን በተለያዩ አካባቢዎች በጦርነቱ ምክንያት በረሃብ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ጧሪ ያጡ አቅመ ደካሞችን፣ ቤት ንብረታቸው የወደመባቸውን፣ በብልጽግና ወንበር ጠባቂ ወታደሮች የተደፈሩ እህቶቻችንን፤ እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት የስነልቡና ጫና የደረሰባቸውን የማኅበረሰባችን አባላትን በመደገፍ በአብሮነት እና በመተሳሰብ፤ ያለንን በማካፈል ፍጹም በሆነ አማራዊ መተሳሰብ በዓሉን እንድናከብር ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 

3) በታወጀብን ጦርነት ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ የሰማዕታት ቤተሰቦችና የሰማእታት ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ድጋፍ በማድረግ እና በማጽናናትና በማበረታታት ማኅበረሰባችን የወገኑን ችግር በሚችለው ሁሉ እንዲጋራ ስንል አደራ እንላለን። 

4) በጦርነቱ መሃል የመቁሰል እና የአካል ጉዳት ያጋጠማቸውን የፋኖ አባላት ለማከም የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ወደ ጤናማ ሰውነት እንዲሸጋገሩ የተለመደውን ድጋፍ እንድታደርጉላቸው ስንል በሰማዕታት ስም አደራ እንላለን።  

5) የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት (ወያኔ) ላለፉት አምሳ አመታት በአማራ ህዝብ ላይ ያደረሰው ስፍር ቁጥር የሌለው በደል አልበቃው ብሎ ዛሬም የአማራ ደንበሮችን በመጣስ እየተተናኮሰ ይገኛል፡፡ ይህ የትም የማያደርስ ትንኮሳ በአማራና በትግራይ ህዝቦች መካከል ያለውን ስንጥቅ ከማስፋት የዘለለ ፋይዳ እንደማይኖረው ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ 

6) የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ የሚቀለበሰው በተባበረ የአማራ ክንድ በመሆኑ ሁሉም አቅም ያለው በጉልበቱና በሀብቱ፤ አቅም የሌለው በጸሎቱ ለዚህ አላማ እንዲረባረብ እና ይሄንን ዘር አጥፊ ስርአት ከስሩ ነቅሎ ለመጣል የሚደረገውን ትግል በተቻለው ሁሉ እንዲደግፍ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡ 

7) በመጨረሻም መላው ኢትዮጵያዊያን ግፈኛውን የብልጽግና አገዛዝ ከአማራ ፋኖ ጎን ሆነው እንዲታገሉ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 

ነፃነታችን በክንዳችን፤
ድል ለፋኖ፤ ድል ለአማራ ሕዝብ።

ሻለቃ ባዬ ቀናው፤
የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና አዛዥ

ሚያዚያ 26 ቀን 2016 ዓ.ም.

https://t.me/ethio251media

2 weeks, 6 days ago

190 ይቀረናል!

የዛሬ መግቢያ ነው። 1000 ሰብስክራይብ እንሙላት። በየግሩፑ ሼር ይደረግ።

https://www.youtube.com/@ethio251media22

2 weeks, 6 days ago

የፋኖ አንድነት!: ሊበረታታ የሚገባው ትልቅ ተግባር:

ስለ አሸናፊነት ሲታሰብ አንድነት በእጅጉ ቁልፍ ነገር ነው። የአንድነትን አስፈላጊነት የሚያጎሉ ብዙ ታሪካዊ ምሳሌዎች ተነግረው እናገኛለን። ለአብነት ያህል: አንድነት ኃይል ነው፣ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር፣ ያልተባበረ ተሰባበረ እያልን መቀጠል እንችላለን።

የፋኖ መተባበርና አንድ መሆን የብዙዎቻችን ጥያቄ እንደነበር የማይታበል ሐቅ ነው። የዛሬ ሁሉት ወር ገደማ የጎጃም ፋኖዎች ወደ አንድነት ሲመጡ ሌሎቹም የእነሱን ፈለግ እንደሚከተሉ ተስፋ ሰጭ ክስተት ነበር።

ከምድረገጽ እንዲጠፋ የተፈረደበትን የአማራ ሕዝብ ሕልውና ለማስጠበቅ ነፍጥ አንስተው ጫካ ዱር ቤቴ ያሉት አርበኞች ከብረት የጠነከረ አንድነት አስፈላጊ መሆኑን ዘንግተውት ሳይሆን፣ አንዳንድ የግል ፍላጎታቸውን በፋኖ ኃይል ለማስፈጸም የሚፈጉ የዳያስፖራ ቡድኖች በሚያስድሩት ጫና ምክንያት እንደነበር አሁን ገሐድ ሆኖ እየታየ ነው።

ከሳምንት በፊት የጎንደር ፋኖዎች፣ በትናንቱ እለት ደግሞ የወሎ ፋኖዎችን የአንድነት ዜና ስንሰማ ልባችን በሐሴት ተሞልቷል።
የሸዋ ፋኖዎችም በቅርቡ የመጨረሻውን የአንድነት ዜና እንደሚያሰሙን ተስፋ እናደርጋለን። ሒደቱን እንዲያፋጥኑ የአካባቢው ተወላጆች ከፍተኛ ግፊት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። እንደዚያ ካልሆነ ግን ሁለቱ ድኩላዎች እርስ በርስ ሲታገሉ የነብር ሲሳይ የሆኑትን እጣ ይደርሳቸዋል። ከፊትና ከኋላ አፉን ከፍቶ ለሚጠብቃቸው ዘንዶ ሰርግና ምላሽ እንዲሆንለት ራስን ማመቻቸት ነው የሚሆነው።

የአማራው ዳያስፖራ ሚና

የአማራው ዳያስፖራ ለትግሉ አጋዥ ኃይል እንጅ ከሕዝብ የተለመነን ገንዘብ አንዳንድ የፋኖ አደረጃጀቶችን እጅ መጠምዘዣ ከማድረግ መቆጠብ ይኖርበታል።
ፋኖዎችም የሕይወት ዋጋ የሚያስከፍልን የህልውና ትግል በገንዘባቸው ሊገዙ የሚሞክሩ አንዳድ ኢጎይስት ግለሰቦችን በአደባባይ የማጋለጥ ድፍረቱ ሊኖራቸው ይገባል። ትግልና ይሉይታም እንዲቀላቀሉ መፍቀድ የለባቸውም ።

የቅርብ ጊዜ ተስፋችን
===××××××××====
የአማራው ሕዝባችን የመኖር ተስፋ በፋኖ ልጆቻቸው ተንጠልጥሎ ይገኛል። ግባቻቸውም ትግሉን በአሸናፊነት መወጣት ብቻ ነው። አንዲት ትንሽ ስሕተት ብትሠራ የህልውና ትግሉ መታጠፊያ ሊሆንና የሕዝባችንን የመኖር ተስፋ ሊያሳጣ ይችላል።
ቀጣዩ ተስፋችንም የአራቱ ጠቅላይ ግዛት የፋኖ እዞች ወደ አንድ ማእከላዊ ኮማንድ መጥተው የትግሉን የድል ብስራት ማቅረብ መሆን አለበት።
ይህ ሁኔታ ሲስተካከል ደግሞ በየጎጡ የሚሰበሰበው የዳያስፖራው ድጋፍ ወደ አንድ ቋት እንዲገባ እድል ይፈጥራል። "ፋኖዎች ወደ አንድ ኮማንድ ካልመጡ ድጋፍ አናደርግም" ብለው ዳር የቆሙ ምክንያተኞችንም ትክክለኛ መልካቸውን ለመለየት ያስችላል።
ስለሆነም የፋኖ አንድ መሆን ለጠላቶቻችን መርዶ ለወዳጆቻችን ደግሞ ተስፋና ደስታ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

ድል ለተገፋው የአማራ ሕዝብ!!

2 weeks, 6 days ago
Mulugeta Anberber
2 weeks, 6 days ago

https://www.youtube.com/live/d6iWuLwgNfA?si=6k0UITccgwfxqpHU

YouTube

የምስራቅ አማራ አለም አቀፍ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት

PayPal / https://www.paypal.com/donate/?hosted\_button\_id=8CCLQPWQ3LN6N&source=qr Cash app:- +1267-835-7205 Zelle:- +1267-835-7205 #ሮሃ\_ቲቪ ለመደገፍ በዚ ሊንክ የበኩሎን አስተዋጽሆ ያድርጉ***👇*** #Roha\_tv support fund link ***👉*** https://gofund.me/230e0032 #የሮሃ\_ቲቪ የዩቱዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ…

Mulugeta Anberber
2 weeks, 6 days ago
ጀምሯል***‼***

https://us02web.zoom.us/j/87224383289?pwd=d3BWTFh2K1kvSXNNRkNpZmhPSGQwdz09

ጀምሯል
ማስፈንጠሪያውን በመጫን ገባ ገባ በሉ!👆👆

3 weeks ago

የአማራ ፋኖ ሳምንታዊ የድል ካባዎችና የአገዛዙ ስርዓት የሽንፈት ፅዋ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ የተቀዳጀውን ድል ከሳምንቱ የድል ቅምሻዎች ጀባ ልንላችሁ ወደድን ።

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ስር የሚገኘው በፋኖ አለሙ ሀብቱ የሚመራው የጋተው ብርጌድ ከስድስት ቀን በፊት በወሰደው የማጥቃት ኦፕሬሽን ደብረብርሀን ከተማ አፍንጫ ስር በሚገኘው በጫጫ ከተማ ወታደራዊ ካምፕ ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅሟል።በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ ጠባቂ ቡድን የንፁሀንን ተሽከርካሪዎች እና የአርሶአደሩን ሀብት መዝረፍ ላይ መጠመዱን ስንነግራችሁ በታላቅ አግርሞት ነው።

ሌላው በሳምንቱ መጠነ ሰፊ ዉጊያ ያደረገው የከሰም ክፍለጦር ሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ ለተከታታይ ሶስት ቀን ያህል በሞዬ፣መስኖ በር፣ጥጎር አፋፍ ፣ወለሌና ጭሳቤራ አካባቢዎች ባደረገው የደፈጣና የግንባር ውጊያዎ የፋኖን መብረቃዊ ምት መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ጀሌ ስንቁንም ትጥቁንም እያዝረከረከ፣ የተሰዋ ሀይሉን አፈር ሳያለብስ እግሬ አውጪኝ እያለ ሲፈረጥጥ ከመሰንበቱም በላይ ለሽንፈቱ የማረጋገጫ ማህተም ይሆን ዘንድ ሾላ ገበያ ከተማ አካባቢ በሚገኘው በፋኖ ወንደሰን ቤት ላይ የእሳት ቃጠሎ ፈፅሟል የአርሶአደሩን ሀብትና ንብረት ዘርፏል።

በተመሳሳይ ዜና የብልፅግናው ጥምር ጦር በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ስር በሚገኘው ከሰም ክፍለ ጦር አስማረ ዳኜ ብርጌድ ላይ ጥቃት ለመፈፀም የሚመካበትን ዙ23፣ሞርተርና ዲሽቃ በመያዝ ጥቃት ቢጀምርም ክንደ ብርቱው የአስማረ ዳኜ ፋኖ ብትንትኑን በማውጣት ጥምር ጦሩ የናፈቃትን የአሳግርት ከተማን አይኑን ሳያሳየው ሙትና ቁስለኛውን አሸክሞ ሸኝቶታል።ሽንፈትን የተከናነበው የብልፅግና ጀሌ አማራ ህዝብ ላይ ያለውን ግልፅ የማንነት ጥላቻ ለማሳየት ተመቶ ሲወጣ የአንድ ቤተሰብ አባል በሆኑ ሶስት ንፁሐን ግለሰቦች ላይ ግድያ ፈፅሟል።

ሌላኛውና ሳምንታዊው የድል ዜና:- ለብልፅግና ወታደሮች አገልግሎት ለመዋል በፒካፕ ተሽከርካሪ ሲንቀሳቀስ የነበረ 4 በርሜል ነዳጅበአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በከሰም ክፍለ ጦር ነበልባል ብርጌድ እጅ ገብቷል።

በደራሲና አርበኛ አሰግድ መኮንን የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በየአካባቢው በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ከማድረሱም በላይ በሳምንቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአገዛዙ ወታደሮች ተቋሙን ለቀዋል ።ብዙዎችም ከነትጥቃቸው የአማራን ህዝባዊ ትግል ተቀላቅለዋል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
ድል ለአማራ ፋኖ
ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም

3 weeks ago
ሰበር ዜና!

ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ዋና አዛዡን ዋርካው ምሬ ወዳጆን አድርጎ መረጠ።

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የወሎ ዕዝ ፋኖ ውህደት ፈጽሟል።

ውህደቱ ከተፈፀመ በኋላ የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ዋና አዛዡን ዋርካው ምሬ ወዳጆን፣ ምክትል አዛዡን ደግሞ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሃቤን አድርጎ መርጧል።

ከወራት በፊት የተጀመረውና ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ውህደቱን ለመፈፀም የተጀመረው ንግግር በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ውህደት በመፈፀም፤ ቀሪ የዕዙን መዋቅራዊ አደረጃጀት በቀጣይ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ተደርሷል። ጦሩም የደስታ ተኩስ በመተኮስ ውህደቱ ተፈጽሟል።

ዘገባው የኢትዮ 251 ሚዲያ ነው።

https://t.me/ethio251media

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago