The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 2 days, 16 hours ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 3 weeks, 2 days ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 8 months, 3 weeks ago
ጥሩ አመት አልነበረም ለኔ…
ድሮ “በጣም የምትፈራው?” ነገር ተብዬ ስጠየቅ “እናቴን ማጣት” የሚል ነበር መልሴ! የፈራሁት ነገር ደረሰብኝ!…እናቴን አጣሁ!
“አቢዬ በቅርብ እመጣለሁ አብረን እንኖረለን” ብላኝ ነበር እናቴ! እንደ እሷ ሀሳብ ቢሆን ኖሮ 2017ትን አብረን ነበርን! ግን አልሆነም!…2016 ላይ ቀረች! እግዚአብሔር የፈቀደው ሆነ!
ህይወትን ያለ እናቴ ተጋፍጫት አላውቅም!…አሁን ግን ልጋፈጣት ነው!…እንደማትመለስ ቁርጤን አውቅያለሁ!…ለበዓል “እንኳን አደረሰህ አቢዬ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ!…”ፀጉርህን ስትስተካከል በጣም አስገብቶ ቅርፅ እንዳያወጣብህ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ!…ለልደቴ “እንኳን ተወለድክ የኔ ልጅ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ!”አንተ ብቻ ጠንክረህ ተማር እንጂ እኔ እናትህ እያለሁ ስለምንም ነገር እንዳትጨነቅ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ ”ወድሀለሁ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ! ካሁን በኋላ ምንም እንደማትለኝ አውቅያለሁ!
“ Nothing in life is promised except death” ይላል ካንዬ ዌስት! ትክክል ነው! እዚህ ምድር ላይ ከሞት በስተቀር ቃል የተገባልን ነገር የለም! ሞት ደግሞ መች እንደሚመጣ አይታወቅም!…በህይወት ሳላችሁ ተዋደዱ! በህይወት ሳላችሁ ተፋቀሩ! እናታችሁን እንደ ምትወዷት በየደቂቃው ንገሯት! ምንም ከምታደርጉላቸው በላይ ደስታቸው ለነሱ ይሄ ነው!
ሰማይ ቤት ባለሽበት መልካም አዲስ አመት እናቴ! ለራሴ ነው እንጂ ማዝነው ከዚህ ክፉ አለም ላንቺ የእመብርሀን እቅፍ እንደሚሻልሽ ጠፍቶኝ አይደለም!
ልቤ ውስጥ አይደል የቀበርኩሽ? መቸም አትበሰብሽም!!!
ወድሻለሁ!
ላማርር ፈልጌ አይደለም! እንዲሁ ልቤ ውስጥ ያለውን ላውጣው ብዬ ነው!
ነገር ሁሉ ለበጎ ነው!…ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን!!
መልካም አዲስ አመት🌼
©[Eyob Z Mariam]
[በስቅለት ቀን ያጋጠመኝ አስገራሚ ክስተት]
:
መስገጃ ቦታ እንዳላጣ ብዬ በግዜ ብሄድም አልተሳካልኝም ነበር! የቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ በሰው ተሞልቶ ጠበቀኝ! ምንጣፌን ይዤ በአይኔ ክፍት ቦታ ስቃኝ ያየኝ አንድ አስተባባሪ "ና ቦታ ልስጥህ" ብሎ ወደ አንድ ቦታ መራኝና "እዚህ ጋ ተቀመጥ" ብሎ በእጁ ጠቆመኝ! ልጁን አመስግኜ ምንጣፌን አንጠፍሁና የአቅሜን ከሰገድሁ በኋላ ትንሽ ረፍት ለመውሰድ ተቀመጥሁ!
ድንገት አንዲት ሴት አጠገቤ መጥታ ቆመች!ዕድሜዋ በሀያዎቹ አጋማሽ ላይ ነው!...በእጇ መስገጃ የሚሆናት ምንጣፍም ሆነ ምንም ነገር አልያዘችም!..ያደረገችውን ክፍት ጫማ አወለቀችና ጠጠሩ ላይ መስገድ ጀመረች!...የያዝኩት ምንጣፍ ሰፊ በመሆኑ ምንጣፉ ላይ ሆና እንድትሰግድ ነገርኳት!.."እሺ" ብላ አመስግናኝ ወደ ምንጣፉ ተጠጋች!...ፊቷን አየሁት!...ጉንጮቿ ደም መስለዋል..ሁለቱም አይኖቿ በዕንባ ብዛት በሚመስል መልኩ ቀልተዋል!...ደነገጥኩ!..."ምን ሆነሽ ነው?" ብዬ ልጠይቃት አልኩና "እኔ ማነኝ?" ብዬ መልሼ ተውኩት!...ተነሳሁና መስገድ ጀመርኩ!...ጎን ለጎን ሆነን መስገድ ጀመርን!...ብዙ ከሰገድኩ በኋላ ደከመኝና ተቀመጥሁ!...ልጅቷ ከገባች ጀምሮ አላረፈችም!...እየሰገደች ነው!...ድንገት ጎንበስ ስትል ዕንባዋ ምንጣፉ ላይ ጠብ ሲል ተመለከትሁ!...ድጋሚ ዝም ማለት አልቻልኩም!...እጇን ያዝ አደረኳትና "እህቴ እስቲ ትንሽ አረፍ በይ" አልኳት ዕንባዋን በነጠላዋ ጫፍ ጠራረገችና ተቀመጠች!..."ምን ሆነሽ ነው የኔ እህት...ምን ሆነሽ ነው ምታለቅሺው?" አልኳት!...ስጠይቃት ይበልጥ አለቀሰች!..."ማንም ምን ሆነሽ ነው ብሎ ጠይቆኝ አያውቅም እኮ" አለችኝ!..."እንዴት"? አልኳት...ረጅም አመት የምታውቀኝ ያህል አወራችልኝ!...ከእናቷ በቀር ምድር ላይ ማንም ዘመድ እንደ ሌላት አወራችልኝ!...እናቷ በጣም ሀብታም እንደ ነበረች አወራችልኝ!...እናቷ ከ 5 ወር በፊት እንደ ሞተች አወራችልኝ!...እናቷ ስትሞት የመኖር ትርጉም እንደ ጠፋትና ሱስ ውስጥ እንደ ተዘፈቀች አወራችልኝ!...በዕንባ ብዙ ብዙ ነገር አወራችልኝ!...ላቋርጣት አልፈለግሁም!...ዝም ብዬ ሰማኋት!...መጨረሻ ላይ ዕንባዋን ጠራረገችና ፈገግ ብላ..."ታውቃለህ" አለችኝ..."ታውቃለህ እናቴ ከሞተች በኋላ መጀመሪያ ግዜዬ ነው ቤተክርስቲያን ስመጣ!...በእርግጥ የመጨረሻዬም ነው!...የመጨረሻዬ ስግደትም ስለሆነ ነው ያለማቋረጥ ስሰግድ የነበረው ምን አልባት ቢምረኝ ብዬ!"...ብላ ትንሽ ዝም አለችና!..."ይቅርታ በማያገባህ ብዙ ጨቀጨኩህ!...አመሰግናለሁ ቻው በቃ" ብላኝ ተነስታ ሄደች!...ከሄደች በኋላ ስታወራቸው የነበረችው ነገሮች አይምሮዬ ላይ ማቃጨል ጀመሩ...
"ታውቃለህ እናቴ ከሞተች በኋላ መጀመሪያ ግዜዬ ነው ቤተክርስቲያን ስመጣ!...በእርግጥ የመጨረሻዬም ነው"
"የመጨረሻዬ ስግደትም ስለሆነ ነው ያለማቋረጥ ስሰግድ የነበረው.... ምን አልባት ቢምረኝ ብዬ!"
በድንጋጤ ከተቀመጥሁበት ተነሳሁ!...ከህዝብ መሀል በአይኔ ፈለኳት...በሩ አከባቢ ስትወጣ ተመለከትኩ...ጫማዬን እንኳ ሳላደርግ በፍጥነት ሄድኩ!
:
:
የመኪናዋን በር ከፍታ ልትገባ ስትል ደረስኩባት!...እጇን ይዤ አስቆምኳት...ወደ ኋላ ዞራ አየችኝ...
"እራስሽን ልታጠፊ ነው አይደል?" አልኳት!
ምንም ሳትናገር እጇን አስለቀቀችና መኪናዋ ውስጥ ገባች...ምንም ብናገር...ምንም ባወራ በዚህ ስሜት ሆና ማድረግ ከፈለገችው ነገር እንደማትመለስ አውቃለሁ...ብቻ ግን እግዚአብሔር አንደበቴ ላይ ቃላቶችን አስቀመጠ..
"እግዚአብሔር ከ እናትም ከ አባትም በላይ እንደ ሆነ አታውቂም?...ተስፋን የሰጠን የታመነ እንደሆነ አታውቂም?....ክርስቶስ ተሰቅሎ አለምን ባዳነበት ዕለት አንቺ ትሞቻለሽ?"...አልኳት!....ተንሰቅስቃ አለቀሰች!
:
:
መርሀ ግብሩ ካለቀ በኋላ ከማውቃቸው ደግ እማሆይ ጋ አገናኘኋት!...ፀለዩላት!...አረጋጓት!...እንደ እናት አቀፏት!...አባበሏት!..አይዞሽ አሏት!...
ዲያቢሎስ አስቦባት የነበረውን የሞትን ደብዳቤ ክርስቶስ ኢየሱስ በስቅለቱ ዕለት ሰቀለው!....ስሟን ጠየኳት!...ሩት አለችኝ....
:
ሩት!....በእግዚአብሔር ምህረት ከሞት እና ከዘላለማዊ እሳት ያመለጠች ነፍስ!
[እዮብ ዘ ማርያም]
አይመስለኝም ነበር የምንረሳሳ
አይመስለኝም ነበር...
ልብሽና ልቤ በወረት ሚበሳ
ሁሉም ከንቱ ቀረ ተረሳሳን በቃ
የዘመናት ፍቅር ጠፋ በደቂቃ
እኔም ዘነጋሁሽ አንቺም ዘነጋሺኝ
በሌላ ተካሁሽ በሌላ ተካሺኝ
ያ ሁሉ መገዘት ያ ሁሉ መሀላ
ያ ሁሉ ቃል ማብዛት ሁሉ ሽንገላ
በቃ ለዚሁ ነበር?
ልብሽ ሊኮበልል እኔም ላቅፍ ሌላ?
የሚያስቀናው ፍቅር...
ሲታይ የሚመስለው ማይገኝለት አቻ
እዚህ ጋ ተቋጨ ሳይደርስ ዳርቻ
የኔና አንቺ ነገር ያሳዝናል ብቻ!
[Eyob Z Mariam]
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 2 days, 16 hours ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 3 weeks, 2 days ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 8 months, 3 weeks ago