The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 5 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month, 1 week ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months, 1 week ago
ካይሮን ያንቀጠቀጠው ኢትዮጵያዊ ሹመት
የኢትዮጵያችን ልጅ = የጆ ባይደን የምርጫ ማናጀር
Sudden Rise of Abraham Shocked Historical Enemy
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ አብራሀም በጆ ባይደን የተሠጠው ሀላፊነት በዚህ በኢትዮጵያ ከቁብ አልተቆጠረም። በግብፅ ግን ድንጋጤና ሽብር ሆኗል። ዮሐንስ የድህረ ምርጫው የሽግግሩን ሂደት እንዲመራ በባይደን ተመርጧል፡፡
ይህን ተከትሎ በአህራም ጋዜጣና አህራም ኦንላይን ዋና አዘጋጅ የነበረው ግብፃዊ ጋዜጠኛ ኢዛት ኢብራሂም በ "Egyptian Center for Strategic Studies" በኩል በአረብኛ የጻፈው አርቲክል ጭብጥ የአብራሃም ጉዳይ ለግብፅ ዱብ ዕዳ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
ዮሃንስ የተሠጠው ሀላፊነት ለግብፅ ከፍተኛ ዋጋ አንንድምታ ያለውን የዕለት ተዕለት ሥራው እንዲቆጣጠር የሚያደርግ ነው ብሏል፡፡ ባለስልጣናትን መምረጥ የሽግግር ቡድኑን መምራት መቻሉ አዲሱ ፕሬዝዳንት ማንም ይሁን ለግብፅ ራስ ምታት መሆኑን ኢዛት ጠቁሟል፡፡
ትውልደ ኢትዮጵያዊው አብራሃም ከታዋቂው ያሌ የዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድምኒስትሬሽን ማስተርስ ድግሪ የያዘ መሆኑን የጠቆመው ፀሀፊው ከዚህ ቀደም በኦባማ አስተዳደር ውስጥ በህዝባዊ ተሳትፎ እና በይነ-መንግስታዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ ሆኖ ማገልገሉንም አስፍሯል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦባማ ቅርብ ሰው መሆኑንም እንዲሁ...፡፡
ዮሐንስ ከሎስአንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ጋር አድርጎት በነበረው ቃለ-ምልልስ እራሱን የገለፀው “እኛ ፖለቲከኞች አይደለንም፣ የኦባማ ሰዎች እንጂ” ማለቱን በማውሳት ከኦባማ ጋር ያለውን ረዥም ወዳጅነት ለመግለፅ ሞክሯል።
"The rise of Abraham in American politics" ሲል የቀጠለው ግብፃዊው ፀሀፊ፣ "በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ የአብርሃም በዚህ ደረጃ መገኘት በአሜሪካ ያለው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የሚፈልገበውን የፖለቲካ መሪዎች ወደ ስልጣን ለማምጣት የፈጠሩትን አቅምና ዝንባሌ ያንፀባርቃል ነው ያለው። ከወራት በፊት በኮንግረሱ የጥቁር ካውከስ ፋውንዴሽን የፖሊሲ ትንታኔና ምርምር ምክትል ፕሬዝዳንትና የአሜሪካ የፖለቲካ ሳይንስ ማህበር (APSA) አባል መና ለገሠ በአባይ ወንዝ ላይ “የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት” በማለት ያደረጉትን ዘመቻ በመጥቀስም ጉዳዩን አጠናክሯል።
መና ደምሴ በታዋቂ ኢትዮጵያውያን "ስደተኞች" ይላል ፀሀፊው ዲያስፖራ ላለማለት መሆኑ ነው፤ መና ደምሴ በታዋቂ ኢትዮጵያውያን "ስደተኞች" የተቋቋመውን ማህበር በከፍተኛ የኮሚቴ አባልነት እየሠሩ ናቸውም ብሏል። ኮሚቴው ዓለም አቀፉን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያራምዳልም ብሏል፡፡
ፀሀፊው ያሳቀኝ ደግሞ በዋሽንግተን ያለውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በ 50 ሺህ ይገመታል ሲል ነበር። የሚገርመው በዋሽንግተን ከ 250,000 በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ በርካታ መረጃዎች በድረገፆች ይገኛል። 460 ሺህ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ እንደሚገኙም መረጃዎች ይናገራሉ።
የዓባይ_ልጅ_እስሌማን__ዓባይ_____________
@yona1278
https:/ @yona1278 /www.egypttoday.com/Article/1/89169/Who%E2%80%99s-the-Ethiopian-in-Biden%E2%80%99s-potential-administration
@alekage @alekage @alekage @alekage
ፍቅር የያዘኝ ሰሞን"
ፍቅር የያዘኝ ሰሞን እንዲህ ያደርገኛል፥
የቆምኩበት መሬት ያጠራጥረኛል፥
አካሌ ደንዝዞ ልቤን ይነዝረኛል፥
የማላውቀው ነገር ደርሶ ይወረኛል፥
ቃል አልባ ዝምታ ጬኸት ይሰማኛል፥
ፍቅር የያዘኝ ሰሞን እንዲህ አድርጎኛል፥
የጬኸቱ ሚስጥር ሳላውቀው ገብቶኛል።
......ያኔ.......
እኔ ነኝ የምትል ስሜን አስረስታ፥
በስም ልትጠራኝ ስሟን ለኔ ሰታ፥
እራስዋን በራሷ እኔ ላይ ተክታ፥
ነፍሴን አስጨነቀች አንዳች ነፍስ ገብታ፥
ውስጤ ሰው ልትፈጥር፥
በፍቅሯ ቅርፅ አውጥታ።
....... ያኔ.......
ፍቅር የያዘኝ ሰሞን እንዲህ ያደርገኛል፥
እራሴ ራሱ ጠፍቶበት፥
እራሴን ራሱ ይመኛል፥
ሳላስብ ሰው መውደድ አርግዤ፥
በድንገት ሰው መሆን ያምረኛል፥
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን፥
አንቺ እዚህ የለሽም፥
ስሜቱ አይገባሽም፥
በቃ ምን ልበልሽ፥
በምን ቃል ላስረዳሽ?
ከሞት በፊት ሄደሽ፥
የገነትን ኑሮ ስሜቱን ታውቂያለሽ?
ከልብሽ በማመን በእንቅልፍ ዓለም ገብተሽ፥
በፍቅር አልጋ ላይ በማፍቀር ተኝተሽ፥
በህልም ያለምሽውን፥
በእውን ምድር አይተሽ፥
በሰመመን ገላ የነፍስ እውነት ቃዥተሽ፥
ባነሽ ታውቂያለሽ ወይ?
ሰው ልብ ላይ ነቅተሽ።
........ውዴ........
በቃ ምን ልበልሽ፥
ከዚያ በባሰ ነው መግለፅ እስኪያቅተኝ፥
ያፈቀርኩሽ ሰሞን እንደዚህ ያረገኝ፥
.......በቃ.......
ከዚህ በባሰ ሁኔታ ዕሩሔ በስቃይ ተውጣ፥
ከሲዖል በክፉ ማዕበል፥
ከብቸኝነቱ መሃል ሰምጣ፥
ቆይታ.......ቆይታ
ድንገት ዛሬ ወጣች ነፍሴ አንቺን አይታ፥
ፈገግ ስትል አየው ነፍሰሽ ስትመጣ፥
ባዶው ገላዬ ልታድን ከሰው ሁሉ መርጣ፥
ልቤ ፍቅር ገዛች፥
ሃዘን የበዛበት ማንነቴን ሸጣ።
........ታዲያ.......
ከዚያች ቀን ጀምሮ ታሪክ ተቀየረ፥
ሁሉም አበቃለት ዓለም ፊቷ ዞረ።
በቃ ምን ልበልሽ፥
ደስታዬ ልክ አጣ መላቅጡ ጠፋኝ፥
የሰፋው ግዜዬ ዛሬ ላይ ጠበበኝ፥
ቀድሞ የሰለቸኝ ዕድሜዬ አጓጓኝ፥
ከፅንስነቱ ወጣሁ ማፍቀርም ወለደኝ፥
ምን ልበልሽ በቃ፥
ከዚያች ቀን አንስቶ፥
አንቺን እያሰብኩኝ ማሳለፌ በዝቶ፥
ባሳብ ብቻ ሳይሆን በቅኝት ተቀኝቶ፥
እንዳዜሙት ዜማ ቅላፄው ተዋዝቶ፥
ይሰማኝ ጀምሯል ከሙዚቃ ጎልቶ።
ደግሞም እኮ ውዴ፥
እጄ በነካው ነገር ሁሉ ከኣሻራዬ በላይ፥
በቀለማት ህብር በጥበብ ሸራ ላይ፥
እንደሳሏት ስዕል ምስልሽ ነው የሚታይ፥
ታዲያ እንዴት ቢሆን ነው፥
እኔ አንቺን አፍቅሬ የሆንኩትን ነገር፥
እንዴትስ አድርጌ እንዴትስ ልዘርዝር?
እእእ...ን....ዴ....ትትት??
.......ያኔ.......
ፍቅር የያዘኝ ሰሞን እንዲ ያደርገኛል፥
እንዴት እንደነበር መግለፅ ይሳነኛል፥
የኖርኩትን ህይወት ማመን ይከብደኛል፥
የኔ ያልኩት በሙሉ ያንቺ ይመስለኛል።
.......ውዴ.......
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አንቺ እዚህ የለሽም፥
ከዚያ ሰሞን ውጪ ደግመሽ አልታየሽም፥
ቢሆንም ግን ውዴ፥
እኔ እንዳለሁ አለሁ፥
የፍቅር ትርጉሙን ባንቺ አውቄያለሁ።
የሚወዱትን ሰው ከራስ ላይ ቀንሰው፥
ለሰው መኖር እንጂ በመንፈስ ተጋምሰው፥
መተኛት አይደለም አካል ተንተርሰው፥
ይህንን አውቃለሁ ባንቺ ተምሬያለው።
ስለዚህ ነው ወዴ፥
ባንቺ ቅርፅ ፈልፍዬ ስጋዬን በደሜ፥
ላንቺ መታሰቢያ ፍቅርን ተሸክሜ፥
ዛሬም ድረስ አለው እንደሐውልት ቆሜ።
እ...ወ...ድ...ሻ...ለ...ሁ!!! @alekage @alekage @alekage @alekage
ተመስገን 50 ሺ አለፍነ !!
~★★~
• https://t.me/yetenantun_lenege ተቀላቀል !!
• እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺእናት ዓለም ቅድስት ተዋሕዶ ሆይ “ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ #ንስር ያድሳል።” መዝ 103፥5
• ታሪክ እየተሠራ ነው። አከተመ።
#ETHIOPIA | ~ ወዳጄ አንድ ሚልዮን ልንሞላ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሺ የተዋሕዶ ልጆች ይፈለጋሉ። እኔ እንዲህ ነው የማስበው። ሁል ጊዜ በትልቁ ነው የምመኘው። በቁጥቁጥ አላምንም። እንጀራ ከነመሶቡ፣ ወጥ ከነ ድስቱ ሲቀርብ ነው ደስ የሚለው።
• ተነሥ ። አትቆዝም። በሌሎች አታሳብ፣ አታመኻኝ። ተነሥ አንተ ራስህ ተነሥ። ወደ ቤተ ክርስቲያን ቅረብ። ውብ እናትህን በሙያህ፣ በገንዘብህ፣ በጉልበትህ፣ በዕውቀትህ አግዛት። ተሰባሰብ። የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር ተዘጋጅ። አትፍራ፣ አትሳቀቅ። አታጎንብስ። ቀና በል። አትሸማቀቅ። አየህ እንዲህ ስንሰባሰብ እንዴት እንደሚያብርብን? አየህ የቀደመ ፍቅራችንን ስንመልስ እንዴት እንደምናምር? ተነሥ ነግሬሃለሁ። ጫትህን ትፋ። ሲጋራህን ርገጥ። ሃሺሽ ሺሻህን አሽቀንጥረህ ጣል። ካቲካላ አምቡላህን ድፋው። በዝሙት አትርመጥመጥ። የቀደመውን የከበረ ኢትዮጵያዊ ማንነት ተላበስ።
የማኅበራችን ዋና ዓላማውም ፦
• ነፃነት ከነክብሩ፥
• ሙሉ ትምህርት፥
• ሕግን ከነ ሥርዓቱ፥
• አንድነት ከነጀግንነቱ፥
• ኪነ ጥበብ በየዓይነቱ፥
• ሥነ ጥበብ በየመልኩ፥
• ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርስ፥
• ሰንደቅ ዓላማን ከነ ክብሩ፥
• ስም ከነምልክቱ ከነ ትርጉሙ፥
• አገር ከነ ዳርድንበሩ፣ ከነፍቅሩ፥
• ዜማን ከነመሳሪያው ከነምልክቱ፥
• ሥነ ጽሑፍ ከነጠባዩ፣ ከነሙያው፥
• እምነት/ ሃይማኖትን ከነፍልስፍናው፥
• ፍጹም ቋንቋን ከነፊደሉ፥ ከነቁጥሩ ከነትውፊቱ፦
… ፈጥረው አዘጋጅተውና አሳድገው ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ያበረከተቱን አበው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በሁለንተናዊ መልኩ መደገፍና ከነ ህመማቸው፣ ከነ ስቃያቸው እንዳዘኑብን እንዳያልፉ ማገዝ ነው።
፩ኛ ☞ • የአብነት ትምህርት ቤት መመህራንና የአብነቱ ተማሪዎች ያለ አብነቱ እንዳይጠፋ፣ እንዳይፈታም በያሉበት በጎደላቸው ሞልተነወ ሚያስፈልጋቸውም መደገፍ ምንጩ እንዳይደርቅ ማድረግ።
፪ኛ ☞ • በእርጅናና በጤና መጓደል ምክንያት እድሜ ዘመናቸውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው በስተመጨረሻ እንደ ሸንኮራ ተመጠው በህይወት ዘመናቸው ፍጻሜ ላይ ደግሞ በእኛው ቸልተኝነት፣ በእኛው ስህተት በቅማል፣ በቁንጫና በትኋን ደማቸው እንዲመጠጥ አሳልፈን የተሰጠናቸውንና በየስርቻው፣ በየመቃብር ቤቱ ያለጠያቂ እንዲሁ እንደዋዛ የወደቁትን አበው ሊቃውንት አባቶቻችንንና እናቶቻችንን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ነገር አለንላችሁ በማለት እነሱ ደስስ እንዳላቸው እኛም ተመርቀን በረከትን ለሀገርም ለትውልድም ጥለን ለማለፍ ነው እየተሰባሰብን ያለነው።
• ይኸው ነው። ምንም ዓይነት ሌላ ረጅም ኮተት የለውም። ተቀላቀል። አከተመ።
•••
" እኔ ግን እላለሁ ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት።+49 1521 5070996 ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው።
¶ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ግንቦት 6/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
"በግንቦት ሀያ ላይ ፣ ግንቦት ስላሴ ተቆጣ
ደርግ ጥሎን ሲሔድ ፣
ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ፣ሌላ ደርግ መጣ
ገዢ መንግስት ወርዶ ፣ ገዢ መንግስት ወጣ
ከተገዛች አይቀር
ድርሻዬ ይሰጠኝ ፣ ሀገሬ ተሽጣ"
ብዬ ነበር ያኔ
ዝም በል እያለ ሲገርፈኝ ወያኔ
ዝም አልልም ብዬ ፣ በሀገር ፍቅር ወኔ
በእልህ ሳለቅስ ፣
ለመብረር ሳነክስ
ደርግ ይግደለኝ እያልኩ ፣ ህወሀትን ስወቅስ
"ኢትዮጵያዊነት ሱስ"
ከሚል መፈክር ጋር
ድንገት ስትመጡ ፣ ይህ ልቤ ተፅናና
የነፃ አውጪው ሁሉ
ነፃ አውጪ ነህ ፣ ብዬ ሾምኩህ በልቦና
በቀነሱን መሐል
እንደመር ስትል ፣ ሰማሁ በፅሞና
ግና
ግና
ግና
ነገር የገባው ህዝብ ፣ ካአምናና ካቻምና
ነገር ሳይጠመጥም ፣ አካሔዱን አቅና
ሀገር አይመራም!!!
"ዝምታ መልስ ነው ፣ በሚል ፍልስፍና !!
━━━━━━━━━━━━
ሰሚ ባይኖረንም አሁንም እንጮሀለን ‼️
?━?━?
ፍትህ ለታገቱ ሴት ተማሪዎች ።
ፍርድ ደብተር የያዙ ሴት ተማሪዎችን በጠብመንጃ አግተው ጀግና ነን ለሚሉ ማፈሪያዎች!!! @alekage @alekage
"...ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደ ተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ...".
እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን!!!
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 5 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month, 1 week ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months, 1 week ago