Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

የሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኀነት ሰንበት ት/ት ቤት መንፈሳዊ ቴሌግራም ገጽ

Description
የሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኀነት ሰንበት ት/ት ቤት አባላት መማሪያና መልእክት መጋሪያ ብቻ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ አውታር ነው። ለማንኛዉም አስተያየት እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለመጠየቅ ይህን ቡት በመጠቀም ማድረስ ትችላላችሁ፡፡ 👉🏽 @SaintGebrielSundaySchoolbot
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

5 days, 1 hour ago

https://www.youtube.com/watch?v=CByFrDWYvwQ&t=199s የሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት (መራሒ ሚዲያ)

የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com/profile.php?id=100069444095761

የቴሌግራም አድራሻ: https://t.me/SaintGebrielSundaySchool

የዩቲዩብ ገፅ: https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared

YouTube

ትንሳኤ | መምህር ገመቹ ታረቀኝ | የኤማሆስ መንገደኞች

1 week ago
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይድረሰውና መድኃኒታችን ኢየሱስ …

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይድረሰውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ትንሳኤው በሁዋላ ለደቀ መዛሙርቱ በጉባኤ 3 ጊዜ ተገልጦላቸዋል:-

1.በዕለተ ትንሳኤ ምሽት በፍርሃትሳሉ
2.ያላመነ ቶማስን ለማሳመን በተነሳ በ8ኛው ቀን (ማለትም ዛሬ)
3.ከተነሳ ከ23 ቀናት በሁዋላ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ላይ ነው::

+ጌታ ፵ውን ቀን ለአንዱም: ለሁለቱም በግል ይገለጥላቸው ነበር:: እመቤታችንን ግን ፈጽሞ አይለያትም ነበር::

+ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለሳምንት ተለይቷቸው ስለ ነበር በቤተ ክርስቲያን ውዳሴ ማርያም እንጂ መልክዐ ኢየሱስ በማሕበር አይደገምም::

+በዚሕች ዕለት ደቀ መዛሙርቱ በጽርሐ ጽዮን ሳሉ ጌታችን "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሏቸዋል:: ቶማስንም "ና ዳስሰኝ" ብሎታል:: ሐዋርያው እጁን ከተወጋ ጐኑ ላይ ቢያሳርፍ በመቃጠሉ "ጌታየ አምላኬም" ሲል ጮሆ ምስጢረ ተዋሕዶውን መስክሯል::

+ጌታም ቶማስን "እስመ ርኢከኒሁ አመንከኒ" (ማለትም ስላየኸኝ አመንከኝ)! "ብጹዐንሰ እለ እንዘ ኢይሬእዩኒ የአምኑኒ" (ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብጹዐን (ማለትም ንዑዳን ክቡራን) ናቸው ብሎታል:: (ዮሐ. 20:24)

=>ከጌታችን ከትንሳኤው: ከቅዱሱም ሐዋርያ በረከት አይለየን::

© ዝክረ ቅዱሳን

+ ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር +

የሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት (መራሒ ሚዲያ)

የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com/profile.php?id=100069444095761

የቴሌግራም አድራሻ: https://t.me/SaintGebrielSundaySchool

የዩቲዩብ ገፅ: https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared

1 week, 1 day ago

ውድ የሰንበት ት/ት ቤቱ አባላት በሙሉ ነገ ቅዳሜ በ03/09/2016 ዓ.ም ሊደረግ የነበረው የህይወተ ወራዙት መ/ግብራችን በመ/ግብራት መደራረብ ምክንያት ለቀጣይ የተዛወረ መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን!!!!

2 months ago
የሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም …
2 months ago
2 months ago
"…ብልህ ሰው ከእግዚአብሔር በረከት ይጠግባል…" መ.ሲራክ …

"…ብልህ ሰው ከእግዚአብሔር በረከት ይጠግባል…" መ.ሲራክ 37፥6

ለ ሰ/ት/ቤታችን 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ ልዩ መርሐግብር!

በዓለማዊ ትምህርት ቤቶች " Day"  በሚል መጠርያ የሚከበሩ አጉል ልምዶችን አስቀርተን መንፈሳዊ በረከትን በምናገኝባቸው ቀናት ቀይረን በረከትን እናግኝ በሚል መነሻ  የፊታችን እሁድ የዐብይ ጾምን 2ኛ ሳምንት ("ቅድስት")  ምክንያት በማድረግ

#የአባቶችጥየቃ እና #የምክረካህን ቀን በሚል በረከት የምናገኝበት ልዩ መርሐግብር ተዘጋጅቷል።

👉12ኛ ክፍሎች ሁላችሁም በዚህ መርሐግብር እንድትገኙ እናሳስባለን።

👉ቀን እና ሰዓት:- እሁድ ከቀኑ 10:00 ሰዓት

"…በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋል…"1ጴጥ 3፥9

መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት

የሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት መገናኛ ብዙኃን ( መራሒ ሚዲያ )

የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com/profile.php?id=100069444095761

የቴሌግራም አድራሻ: https://t.me/SaintGebrielSundaySchool

የዩቲዩብ ገፅ: https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared

2 months, 1 week ago
የሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም …
2 months, 1 week ago

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
እንኳን ለ2016 ዓ.ም ዐቢይ ጾም በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ‹‹ ቀድሱ ጸመ፣ ወስብኩ ምሕላ፣ አስተጋብዑ ሊቃውንተ፣ ወኵሎ ዘይነብር ውስተ ምድር ውስተ ቤተ አምላክነ፤ ወጽርሑ ኀበ እግዚአብሔር ኅቡረ፡፡›› ‹‹ጾምን ቀድሱ፤ ጉባኤውንም አውጁ፤ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ፡፡›› ኢዩኤል 1፣14

ጾም ለነፍሳችን አስፈላጊ የሆነ መንፈሳዊ ተግባር ነው፡፡ መንፈሳዊ ተግባርነቱም እግዚአብሔርን የሚያስደስት መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ በዚሁ መሰረት ነቢዩ ኢዩኤልም በትንቢቱ ጾምን እንጹም ብላችሁ ለዩ፤ ምሕላ እንያዝ ብላችሁ አዋጅ ንገሩ፤ በኢየሩሳሌም የሚኖረውን ሰው ሁሉ በፈጣሪያችን ማደሪያ ሰብስቡ፤ አንድ ሁናችሁም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለምኑ በማለት የጾምና የምሕላን አዋጅ አውጇል፡፡ ምክንያቱም እስራኤላውያን ከገጠማቸው መከራ የሚወጡበት መንገድ ይህ ነውና፡፡

ጾም ቍስለ ነፍስን የምታክም የአጋንንትን ፈተና የምታሻግር መንፈሳዊ መሣሪያ ናት፡፡ እኛም ዛሬ ሰላም በማጣት ታመናል፡፡ አንድነታችንን የሚሸረሽር በሕዝባችን መካከል ልዩነትን የሚያውጅ እርስ በእርስም የሚያጠፋፋ መንገድ ሁሉ የነፍሳችንን መታመም ማሳያ ናቸው፡፡ ስለዚህ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት ሆነን ይህንን የነፍሳችንን ቁስል በተገቢው ለማከም ጾምን እንጹም ብለን የምናውጅበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየፈሰሰ የሚገኘው የመከራ ጎርፍ ሁሉ ሊገታ የሚችለው በጾምና በጸሎት ብቻ ነው፡፡ የመፍትሔው ባለቤት የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት መጠየቅ መፍትሔ የምናገኝበት ብቸኛና ዋነኛ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህም እንደ ነቢዩ ኢዩኤል ዛሬም ኑ ስለ ሀገራችንና ስለ ሕዝባችን ምሕላ እንያዝ ብለን አዋጅን እናውጃለን፡፡ ይህ ሲሆን ለገጠመን ችግር መፍትሔ ማግኘት እንችላለን፡፡ ይህ ታላቁ ጾማችን (ዓቢይ ጾም) እግዚአብሔርን የምንማጸንበት የተለየ ወቅት ነው፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ካህናትና ምእመናን ሁላችን እግዚአብሔር በረድኤት በሚገለጽበት በቤተ እግዚአብሔር በመሰብሰብ ከገጠመን ሁለንተናዊ ችግር እንሻገር ዘንድ በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን መማጸን በአንድነትና በሕብረት ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ እግዚአብሔር መጮህ ከምንም ጊዜ በላይ ዛሬ ያስፈልገናል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ፡- ጾማችን ፍቅርን መሠረት ባደረገ ንስሐ እግዚአብሔርን በመጠየቅ፤ የተቸገሩ ወገኖቻችንን የችግራቸው ተካፋይ በመሆን፤ ስለ ሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚጠበቅብንን እንድንወጣ ከአደራ ጭምር እናሳስባችኋለን፡፡ በመዋዕለ ጾሙ ቃለ እግዚአብሔርን በማስተማርና በመማር ስለ ሀገራችን ሁለንተናዊ ሰላም እንዲሁም ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በጾምና በጸሎት በመትጋት እንድትበረቱ በድጋሚ ከአደራ ጭምር መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር መዋዕለ ጾሙን በሰላምና በአንድነት በፍጹም ፍቅር አስጀምሮ ያስፈጽመን፡፡ አስፈጽሞም ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በጤና ያድርሰን፡፡ አሜን

መልእክተ ሕይወት ኢየሱስ ክርስቶስ ሀገራችንንና ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ  የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ

ማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ይቀላቀሉ👇

የሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት መገናኛ ብዙኃን ( መራሒ ሚዲያ )

👉 የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com /profile.php?id=100069444095761

👉 የቴሌግራም አድራሻ: https://t.me/SaintGebrielSundaySchool

👉 የዩቲዩብ ገፅ: https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared

2 months, 1 week ago

**"በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየፈሰሰ የሚገኘው የመከራ ጎርፍ ሁሉ ሊገታ የሚችለው በጾምና በጸሎት ብቻ ነው፡፡"

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ

የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም**

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ የ 2016 ዓ.ም ዐቢይ ጾምን አስመልክቶ ያስተላለፉት  መልእክት

2 months, 2 weeks ago

**††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሆሴዕ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ †††**

††† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር): መጻዕያትን (ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: (ሐዋ. 11:27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: (ቅዳሴ ማርያም)

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: (ዮሐ. 4:36)

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: (ማቴ. 13:16, 1ዼጥ. 1:10)
ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት
¤15ቱ አበው ነቢያት:
¤4ቱ ዐበይት ነቢያት:
¤12ቱ ደቂቀ ነቢያትና
¤ካልአን ነቢያት ተብለው በ4 ይከፈላሉ::

"15ቱ አበው ነቢያት" ማለት:-
ቅዱስ አዳም አባታችን
ሴት
ሔኖስ
ቃይናን
መላልኤል
ያሬድ
ኄኖክ
ማቱሳላ
ላሜሕ
ኖኅ
አብርሃም
ይስሐቅ
ያዕቆብ
ሙሴና
*ሳሙኤል ናቸው::

"4ቱ ዐበይት ነቢያት"
ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
ቅዱስ ኤርምያስ
ቅዱስ ሕዝቅኤልና
ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

"12ቱ ደቂቀ ነቢያት"
ቅዱስ ሆሴዕ
አሞጽ
ሚክያስ
ዮናስ
ናሆም
አብድዩ
ሶፎንያስ
ሐጌ
ኢዩኤል
ዕንባቆም
ዘካርያስና
ሚልክያስ ናቸው::

"ካልአን ነቢያት" ደግሞ:-
እነ ኢያሱ
ሶምሶን
ዮፍታሔ
ጌዴዎን
ዳዊት
ሰሎሞን
ኤልያስና
ኤልሳዕ . . . ሌሎችም ናቸው::

ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
የይሁዳ (ኢየሩሳሌም):
የሰማርያ (እሥራኤል)ና
*የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ::

በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
ከአዳም እስከ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት):
ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)
ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት)
ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ::

ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::
ቅዱስ ሆሴዕ ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ/ል/ክርስቶስ በ800 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ 14 ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::

ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ሆሴዕ 'ዖዝያ' በመባልም ይታወቃል:: ቅዱሱ ነቢይ የቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ-ቃል ባልንጀራ የነበረ ሲሆን በ4 ነገሥታት ዘመን (ዖዝያን : ኢዮአታም : አካዝና ደጉ ሕዝቅያስ) ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናግሯል:: የትንቢት ዘመኑም ከ70 ዓመት በላይ ነው::

ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሆሴዕ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራም በስፋት ተንብዩዋል:: 14 ምዕራፎች ያሉት የትንቢቱ ጥራዝ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል:: ሆሴዕ ማለት መድኃኒት ማለት ነው:: የመዳን ትምሕርትንና ትንቢትን ሊናገር ተመርጧልና::

††† ቸር አምላከ ነቢያት የነቢያቱን መከራ አስቦ ከመከራ: በእንባቸውም ከእንባ ይሰውረን:: ከተረፈ በረከታቸውም አያጉድለን::

††† የካቲት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ (ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት)
2.ቅዱስ ሳዶቅ ሰማዕት
3."808" ሰማዕታት (ከቅዱስ ሳዶቅ ጋር የተሰየፉ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

††† "ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንመለስ:: እርሱ ሰብሮናልና: እርሱም ይፈውሰናል:: እርሱ መትቶናል: እርሱም ይጠግነናል:: ከሁለት ቀን በሁዋላ ያድነናል:: በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል:: በፊቱም በሕይወት እንኖራለን:: እንወቅ:: እናውቀውም ዘንድ እንከተል . . . " †††
(ሆሴዕ 6:1-3)

@ዝክረ ቅዱሳን

††† ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር †††

ማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ይቀላቀሉ👇

የሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት መገናኛ ብዙኃን ( መራሒ ሚዲያ )

👉 የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com /profile.php?id=100069444095761

👉 የቴሌግራም አድራሻ: https://t.me/SaintGebrielSundaySchool

👉 የዩቲዩብ ገፅ: https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago