የገጣሚያን ማኅበር

Description
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
?መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን?መነባነብ
?ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel? @Ye_Getamian_Mahiber
Group? @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 Monate, 1 Woche her

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 11 Monate her

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 2 Wochen, 6 Tage her

2 months, 1 week ago
2 months, 1 week ago

**የሚጠፋውና የማይጠፋው!

ጊዜያዊውና ዘላለማዊው!**

በቤተሰብ ዙሪያ ባለው ተጽእኖ አሳዳሪ አገልግሎቱ የሚታወቀው ጄምስ (James Dobson) አንድ ጊዜ እንዲህ ሲል ተናገረ፡-

“አንድ ጊዜ ድሮ high school የተማርኩበትን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት ስሄድ ቴኒስ ስጫወት አሸንፈ የተሸለምኳቸውን ዋንጫዎች በቆሻሻ ማጠራቀሚያ እቃዎች ውስጥ ተጥለው አየኋቸው፡፡

ይህንን ያደረጉት ሌሎች ተማሪዎች ለሚሸለሟቸው አዳዲስ ዋንጫዎች ስፍራ ለማዘጋጀት ሲባል ነበር፡፡ 

በዚህ ምድር ላይ የሰው ልጆች አከናወንኳቸው የሚሏቸው ነገሮች ሁሉ የጊዜን ፈተና ማለፍ የማይችሉና የኋላ ኋላ ቦታ እንደሚያጣብብ ቆሻሻ የሚቆጠሩ እንደሆነ እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡

ዛሬ ተጨብጭቦለት ነገ የሚጣለው ምድራዊ ስኬት ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ የሰዎችን ሕይወት በመለወጥ ላይ ማተኮር ምን ያህል ዋጋ ያለውና ዘላቂ እንደሆነ እንዳስብም አደረገኝ፡፡

ከምድራዊው የስኬት ሩጫ መለስ እያልን የሰዎች ሕይወት የሚለወጥበትን ስራም ለመስራት መመረጥ እጅግ መታደል ነው፡፡

እንቀጥልበት!

ይህንን ታሪክ ሳነብ ወደ ልቤ የመጣውና ከፍቼ ያነበብኩት ክፍል ይህ ነው፡- “ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ” - ዮሐ. 6፡27

እናንተስ ይህንን ታሪክ ስታነቡ የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ትዝ አላችሁ ?

Dr. Eyob

@worlds_light
@worlds_light

2 months, 1 week ago

????????????
በቀላሉ በስልካችን የተለያዩ አገልግሎቶችን በማንኛውም ሰዓት የሚያደርሱን
??‍♀የቴሌግራም ቻናሎችን ልጦቁማቹ

የምትፈልጉትን አገልግሎት መርጣቹ ተቀላቀሉ
?????????

2 months, 2 weeks ago

?አዳዲስ መዝሙሮች እና አልበሞች እየተለቀቁ ስለሆነ የምትፈልጉት ዘማሪ ስም በመንካት መሉ አልበም እና አዳዲስ ዝማሬዎችን ያገኙበታል ???????????

2 months, 2 weeks ago

እኔ እሱን የማውቀው #በመልካምነቱ❤️
እኔ እሱን የማውቀው #በአባትነቱ❤️
እኔ እሱን የማውቀው #በሰፊው #ትዕግስቱ❤️
እኔ እሱን የማውቀው #በመሐርነቱ

Join
@Ye_Getamian_Mahiber
@Ye_Getamian_Mahiber

2 months, 2 weeks ago

ሠላም ይብዛላችሁ እንዴት አመሻችሁ???

እስቲ ዛሬ ወደ ቤተክርስቲያን የሄዳችሁ ምን እንደተማራችሁ COMMENT Box ላይ አስቀምጡ እንባረክበት❤️?

2 months, 3 weeks ago

*እግዚአብሔር ባሪያህ ይሰማልና ተናገር እስክትሉ እየጠበቀ ነው

ንቃትህ ለሌላ ካደረግ እግዚአብሔር ጆሮ ላይ መጥቶ ቢጮህ አትሰማውም።

ሳሙኤል እግዚአብሔር ቢናገረውም፣ እርሱ ግን ለኤሊ ውጪ የሚናገረኝ የለም ብሎ ደምድሞ ስለነበር፣ ለሰማው የእግዚአብሔር ድምፅ ምላሽ ይሰጥ የነበረው ለኤሊ ነበር።

እግዚአብሔርም እርሱ እንደሚናገረው እስኪያውቅ እና እነሆ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር እስኪል ድረስ ሌላ ድምፅን አላከለትም ነበር።

ብዙዎች የእግዚአብሔርን ድምፅ የማይሰሙት እግዚአብሔር ሊናገራቸው እንደማችል ደምድመው ስለተቀመጡ እና እርሱ በተናገረ ጊዜ፣ ሐሳባቸው እንዲሁም ከአካባቢያቸው ያለ ሌላ ድምፅ ስለሚመስላቸው ነው።

?*@sela3mjoin & share ??

2 months, 3 weeks ago

መውደዴን እወደዋለሁ

ብዙ ቢሆን በአለም : ብትናወጥ ምድር
ምንም አይቀንስም : ላንተ ያለኝ ፍቅር
ዘመናት ቢያልፉ : መንግስታት ቢለዋወጡ
ትንሽ እንኳን አይቀንስ : የፍቅሬ ብዛቱ

ከሁሉም ደሞ : የምወደው ነገር
አንተን መውደዴን ነው : እንደ አዲስ ፍቅር
እራስ ወዳድነት : ቢነግስ ገዝፎ
የእርስ በርስ ፍቅር : ቢመለስም አፍሮ
እኔ ያንተ ወዳጅ : እኔ ያንተ አፍቃሪ
መውደዴን እወደዋለሁ : ሆኜ ስምህን አክባሪ
በዛም አያበቃም : ላንተ ያለኝ ፍቅር
ቃላቶች እስካይችሉ : መግለፅ ያንተን ክብር
በቃ : መውደዴን እወደዋለሁ
መምጣትህን : እናፍቃለሁ
ህህህ
ቀና ስል : ስላንተ ላወራ
ስመርጥ ሳለ : ከቃላት ተርታ
ልቤ እንዲ ተናገረ : በራሱ አንደበት
መውደዴን : እወደዋለሁ...

✍️ Zion

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

2 months, 3 weeks ago

ሠላም ወዳጆቼ?❤️
ከሰር ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉ አጅግ የሚጠቅም መንፈሳዊ ህብረት ነው ተባረኩልኝ❤️ https://t.me/Rapture_tube

3 months ago

የማይሰለች ዜና
ወርዶ ከዙፋኑ፤ ብውል፤ ንጉስ ተራ ስፍራ
በተናቁት መንደር፤ ከድሀ አደጎች ጋራ
እህላቸውን በልቶ፤ ቀምሶ መጠጣቸውን፤ ብያድር ከአልጋቸው
ምንኛ ውርደት ነው? ድሪቶውን ልብሶ፤ ካባ ብያለብሳቸው
        ታድያ እንዴት ይሆናል??
በአንድት ነጠላ ቃል፤ ምድርን መስርቶ
ያለ አንዳች ምሶሶ፤ ጠፈርን አጽንቶ
መላ ፍጥረታትን፤ በውስጧ ያኖረ፤ በ"ሁን" አበጅቶ
ፈጥሮ ሚያስተዳድር፤ ግሩም የሰውን ልጅ
ከሸክላ ከአፈር፤ ጠፍጥፎ በእጅ።
መንግስቱ ያለገደብ፤ ስልጣኑ ማይሻር
አልፋና ኦመጋ፤ ከዘላለም እስከ፤ ዘላለም ነዋር
ከ..እስከ የማይባል፤ ሹመት ተጎናጽፎ፤ ስኖር በክብር
አምላክ የነበረ፤ ከኃጥ ብቆጠር፤ ከአመጸኛው ዘር
      እኮ  እንዴት ይሆናል
ፈጣሪ ብመስል፤ ራሱን ዝቅ አድርጎ፤ ከእጁ ፈጠራ
ከመንበሩ ጎድሎ፤ ከሰው ልክ ልካፈል፤ የዓለምን መከራ
በአንድት እንስት ማህጸን፤ እራሱን ገድቦ
አጥንት ደም ልሸከም፤ የባሪያን መልክ ልይዝ፤ ውርደቱን አንግቦ
ሰው ሆኖ ብገለጥ፤ አምላክ ለብሶ ስጋ
ልራብ ልጠማ፤ በውርጭ በሀሩሩ፤ ክፍሎ ልኖር ዋጋ
  እኮ! እንዴት ይሆናል..?....... ሆነ ግን ለጌታ!!
የሞት ጣሪ ብከበን፤ ስኦል አፉን ከፍቶ
የበደላችን ልክ፤ ጽዋ፤ ከጫፍ ሞልቶ
ተስፋችን ተወስዶ፤ ተቅበዝባዦች ሆነን፤ ስንዋትት በመና
በኃጥአት ቀንበር ስር፤ ተቃኝተን ስንዝል፤ ለሞት ስንቃና
እጅግ ተጎሳቁለን፤ ብያየን ከሰማይ
ፍቅር አስገደደው፤ ማቃችንን ልወስድ፤ እንድወርድ ከላይ
      እሱስ ወድያ ይሁን
እርጉም አፈር መርገጥ፤ ከዙፋን ላይ አንሶ
በሰው መልክ መወለድ፤ ነውር ስጋ ለብሶ
ከቶ ሳያንስበት፤ እንድያው ለውርደቱ
ደግሞ ያስደመመኝ፤ ለላኛው ድርግቱ
      ነገሩ ወድህ ነው
ናፍቆት ሆኖ ሳለ፤ የመስህ ውልደት
አልጋ ተነጥፎለት፤ በክብር ስጠበቅ፤ ከቤተመንግሥት
እንደ በግ በበረት፤ በተናቀ ቦታ
መወለድ ማደሩ፤ እንደ መጻተኛ፤ የፍጥረታት ጌታ
   ለምን...???
ለምን?...ግን ለምን እያልኩኝ፤ ስማከር ከልቤ
ከአርያም..በረት፤ የውርደቱን ስፋት፤ ጥልቀቱን አስበ
ለካ የኔም ድንኳን፤ የተጠለልኩበት፤ መኖርያ ጎጆዬ
እዛው ሰፈር ሆኖ፤ ወትሮ መገኛዬ
ቁልቁል አዘቅት፤ ሸለቆን መውረዱ፤ ለክብሩ ሳይሳሳ
ገባኝ ተረዳሁኝ፤ ከልኩ ማነሱ፤ ነው እኔን ልያነሳ።
ስመጥሩ ስሆን፤ የልዑል አምላክ ልጅ፤ እንደ ነውረኛ
ያልተገባው ሆኖ፤ በበረት ስወለድ፤ መስሎ መጻተኛ
ከወርቅ ብያገጡለት፤ አልጋቸውን ትቶ፤ በግርግም ስተኛ
ለካ ልያከብረን ነው፤ ራሱን ዝቅ አድርጎ፤ ተዋርዶ ስለ እኛ
   የምስራች አለኝ......
የምስራች አለኝ፤ ምን ዘመን ብቆጠር፤ የማይሰለች ዜና
በፍቅር መሰረት፤ በግብር ታንጾ፤ ላይሻር የፀና
በጉ ብርሃናችን፤ የዓለም ሁሉ ንጉስ፤ የፍጥረታት ደስታ
በዛችን ክርስቶስ፤ ኢየሱስ ተወልዷል፤ የዘላለም ጌታ!!!
        ክርስስቶስ ተወልዷል

Written by Erkata S.
Like share react❤️??
Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 Monate, 1 Woche her

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 11 Monate her

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 2 Wochen, 6 Tage her