The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 2 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months ago
በነጻ አንብቡ 💚
ክላሽ የታጠቀን ወታደር ‘የመሸበት የእግዜር እንግዳ’ ብሎ ቤቱ ወስዶ እንደማሳደር ካለ ደግነት አንስቶ፣ ድንገት ‘ግልፍ’ ያደረገውን ፖሊስ በጥፊ እስከ መምታት የደረሰ ቁርጥ ኃይለኝነት... በእነዚህ ጠርዝ እና ጠርዞች መሀል ያሉ ትውስታዎች የተቋጠሩበት የአባት ማስታወሻ ነው።
አጽንኦት እንዲያገኝ ስለፈለግኹኝ ነው። በነገራችን ላይ ቤተሰቦቼ እንኳን ወዳጅነታችንን አሁን ከእናንተ ጋር ነው የሚያነቡት። ይኽንን አደረግኹኝ ብዬ ልታበይ ወይ ልደነቅበት አይደለም። ወዳጅ ነኝ የሚል ቀርቶ፣ ማንም ሰው ለክብሯ እና ለprivacyዋ ሲል ማድረግ የሚጠበቅበት የኅሊና ግዴታ መሆኑን ግልጽ ለማድረግ ነው።
እኔና ጥቂት ወዳጆቼ ከጎኗ ሳንርቅ፣ በሰው እና በገንዘብ አቅም በሚታለፍ ነገር ሁሉ ለማገዝ ያልሞከርነው ነገር፣ ያልፈነቀልነው ድንጋይ የለም። እኛ እንዲህ የሞከርን የቤተሰቦቿን መገመት ነው። ቢያንስ መኖሪያ አካባቢዋን ለመቀየር ብዙ ጊዜ ታስቦ እና ተሞክሮ በእሷ እምቢታ ነው የተፋረሰው። እንግዲህ ትልቅ ሰው ናት የአገሩም ህግ አይፈቅድምና፣ ካለእሷ ፍቃድ እና ፍላጎት ጣልቃ መግባት አይቻልም።
ሀኪሞችም ጥቂት እንኳን የጤናዋን ሁኔታ trigger የሚያደርግና የሚያባብስ ነገር እንዳይደረግ፣ ሁሉም ነገር በእሷ ፍቃድ እና ፍላጎት ላይ እንዲሆን አበክረው አሳስበዋል። ያንን ማክበር ነው። የሚባለውንም ሁሉ ብታይ እንዳዲስ የመቀስቀስ እና የመረበሽ አቅም አለውና፣ እስከ ጊዜው ድረስ ከዚህ በላይ ማለት አልችልም። ቢያንስ የሰለጠነ አገር እንደሚኖር ሰው ይኽን መረዳትና ራስን ከተጠያቂነት ማራቅ ይገባ ነበር። ግን አስገራሚ ፍጡሮች ነን።
እንግዲህ እንዲህ የቀረጸውን ቪዲዮ ይዞ ነው እለቀዋለሁ ብሎ ማስፈራሪያ አድርጎት ዛሬ የለቀቀው። ትክክለኛ ቀረጻ እንዳልሆነ ያውቀዋል። ያለችበትን ሁኔታ እና የምትፈልገውንም ከለላ ይረዳል። ለዚያም አይደል ማስፈራሪያ አድርጎት የነበረው? ባይሆንና በሰላም የተቀረጸ ቢሆን በወቅቱ ባሰቡት ቻናል ይለቁት ነበር። እኛም ተደስተን በናፍቆት እናየው ነበር። የቀረጿትም አሁን የታየው ያህል ብቻም አይደለም።
በወቅቱ እሷ ህክምናዋን በተሻለ ሁኔታ ላይ ለመከታተል በጣም ጥሩ ሂደቶች ስለነበሩ ላለማበላሸት ላይ ታች ተብሎ ለእርሷ ሰላም እና ደህንነት ሲባል፣ በመሀል በነበሩ በጎ ሰዎች እገዛና ትብብርም እንዳይለቁት ተሞክሮ ቀርቶ ነበር። ይኸው ነገሩን መልሰው ይዘውት መጥተዋል።
ነፍሱን ይማረውና የአድማስ ሬድዮው ቴዎድሮስ ከማርክስ ባለቤት ከማያ ኃይሌ ጋር ሄዶ ቀርጾ የነበረው ድምጽ ይታወቃል። ቴዲ ራሱ በወቅቱ ሚዲያ እንደማትፈልግና በድብቅ መቅረጹን እዚያው ሬድዮ ላይ ተናግሮ ነበር። ለምን የማትፈልገውን አደረገ? ለምን በድብቅ? ልክ እንዳልሆነ ለማወቅ ህሊናውን ምን ጋረደበት? ለእሱ የአንድ ቀን ቀረጻ ነበር። እሷ ግን ብዙ ተጎዳችበት። ቀርጾ ከተመለሰ በኋላ አንድም ቀን መልሶ ለመደወል አልሞከረም ነበር። እሷም በድብቅ ቀርጾ ማስተላለፉን ስትሰማ እና ስታውቅ በጣም ተረብሻ አዝናበት ነበር ያለፈው።
ሁኔታዋን እንዳየ ወዳጅ እኔም በጣም አዝኜበት ነበር። በወቅቱ እኔ ጋ ደውላ የተናገረችውን እና የተሰበረችውን እስክሞት አልረሳውም። "ጆንዬ እኔ እኮ እንደ አንተ ሰው ወንድም እየመሰሉኝ ነበር በሬን ሲመቱ ተደስቼ የምከፍተው። ምን አደረግኳቸው ይኽን ያህል? ለምን አይተዉኝም?" ብላ ነበር። ያንን መረበሿን ሳይ ቴዲ ጋ ደውዬ ላወራው ሞክሬ ነበር። እሱ እንኳን ሊጸጸት "እንደውም ብዙ ነገር ቆራርጬ ያወጣሁት። ብዙ የተውኩት ድምጽ አለ።" ብሎ ጭራሽ ምስጋና ፈልጎ ነበር። በሰላም ይረፍ።
ግን ለምን ይኽን ያህል አስፈለገ? ጂጂ ሙዚየም ወይ መደበሪያ አይደለችም። የትልቅ ልጅ እናት ትልቅ ሰው ናት። ያንን መገንዘብ ለምን አቃተን? ሚዲያው አስፈላጊ እና ጠቃሚ ቢሆንላትስ ከልጅነት እስከ እውቀት የማደንቃት እኔ አላደርገውም ነበር? ከዚህ ቀደም ክንፉ አሰፋ ያወራበትን ድፍረት ልክ በደፈናው አንስቼው ነበር። ለአንድ ቀን ለሃያ ደቂቃ አግኝቷት ስንት ስዓት ስንት ነገር አወራ? ብቻ በጣም አሳፋሪ ነው።
የሀኪም ትዕዛዝ ስናከብር፣ ለእሷ የሚያስፈልጋትን ብቻ ለማድረግ ስንሞክር እንጂ፣ እንዲህ አይነት ነገር ከእለት ርካሽ የሶሻል ሚዲያ ጩኸት በቀር፣ ለእሷ ጥቅም ቢኖረው፣ ይኽን ድሮ አናደርገውም ነበር? ጭራሽ እንዲህ ዓይነት ነገር ብዙ ወደ ኃላ ይመልሳታል። ሀኪሞችም በሕይወት ላይ ሁሉ ስለሚመጣ ጉዳትና ህመም ማባባስ ሊደርስ ይችላል ልዩ ጥንቃቄ ትፈልጋለች ብለዋል።
አሜሪካ ውስጥ የስነ ልቡና እና አእምሮ ህመም በጥንቃቄ ነው የሚያዘው። ሰው ካልፈቀደ መታከምም ከቦታ ቦታ መዘዋወርም አይችልም። ወዳጅ ነኝ ያለ ያንን ማክበር፣ ሊያደርግ ከሚችለው በጣም ትንሹ ነገር ነው። ትክክለኛ ምርመራዋንም እንኳን እኔ ወይ ሌላ ሰው፣ ሀኪሞች እንኳን እርስ በርስ እንዳያወሩ የHIPPA ህግ ያስገድዳቸዋል።
እንደ ተወዳጅ መዚቀኛ ይቅር፣ ብዙ እንደሰራ ሰው ይቅር፣ እንደ አንድ ሰው፣ እንደ የአገር ልጅ፣ እሷን ያያት እና ያለችበትን ሁኔታ ያየ ሰው ሊያደርግ የሚችለው አንድ ነገር እሷን መጠበቅ እና ከለላ መስጠት ነው። የሚፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልጋትን የሞራል ግዴታ መፈጸም ነው። እንጂ መረሳቱ ትዝ ባለው ቁጥር እንዲህ ዓይነት ግብታዊና ፍጹም ሊጎዳት የሚችል መረጃ ማሰራጫት ተገቢ አይደለም።
አሜሪካ ውስጥ በህግም ቢሆን ራሱን መከላከል የማይችልን ሰው፣ ለራሱ የህግ ከለላ ፍላጎት ወይ በቤተሰብ ፍቃድ (ወላጆች እና ልጅ) እሱንም ታካሚው ቀድሞ ይሁንታ ከሰጣቸው ለህክምና ሂደት ካልሆነ በቀር መቅረጽ ፎቶ ማንሳት በህግ ያስጠይቃል።
ቤተሰቦቿ ለምን ወጥተው አይነግሩንም? የconspiracው ቋሚ ማጀቢያ ነው። ለምን ይነግሩናል? እኛ እንደ አድናቂ ይኽንን ያህል የተጨነቅን እንደ ቤተሰብ እንቅልፍ አግኝተው ይኖራሉ? ሌላው ነገር ቢቀር ቢያንስ ከእኛ አፍ ሰላም ለማግኘትና እፎይ ለማለት ይኽንን ማድረግ ቢችሉ ለምን አይመርጡትም?
ወጥተው ሚዲያው ላይ እንዲህ ነው እንዲያ ብለው መስማት የምንፈልገውን ቢነግሩን፣ እሷ ስትሰማውስ ምን ይሰማታል? ጭራሽ ወደባሰ ሁኔታ እና ድብርት ውስጥ ለመክተት trigger ያደርጋል ተብሎ አይታሰብም?
እናንተ እህታችሁ ወይ ወንድማችሁ ላይ ተመሳሳይ ነገር ቢከሰት እንዲሁ ለወሬ ፍጆታ ታውሉታላችሁ? ብዙ ደስታ ለሰጠችን ሰው ለምን ሰላም እና ከለለ መስጠት ከበደን? የወሬ ፍቅራችን ይህን ያህል ለምን ህሊናችንን አሸነፈው?
አሁንም የተሻለ ህክምናዋን የመከታተል ሁኔታ እና ጥረት ላይ ናት። (ነበረች ባልል ደስ ይለኛል። ግን ይህን ቪዲዮ ካየችው በጣም ትረበሽና የከፋ ሁኔታ ውስጥ መግባቷ አይቀርም። :( ) ብዙ ጊዜ ነገሮች ሊቃኑ ሲሉ ፈተና የሆነው እንደ ቅቤ ሚዲያው ላይ ጠብ የሚደረገው እንዲህ ሆነች፣ በዚህ ገባች ነው። ዋና የምትፈልገው ሰላም እና ከለላ (protection) ነው። Privacyዋን እናክብርላት።
የምትወዷት ከሆነ የምትፈልገውን space እና ነጻነት ስጧት። ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን በዚያ እናሳያት። እንርዳት እናሳክማት የሚለው ሀሳብ ከጥሩ ልብ የሚነሳ ቢሆንም፣ ስትፈልግ እና ስትፈቅድ ነው። እስከዚያ የእኛን እርዳታ በግልጽ የጠየቁ ብዙ አርቲስቶች አሉ። እነሱን እናግዝ። በየእምነታችን እንጸልይላት።
ይኽ በእንዲህ እንዳለ በተለቀቀው ቪዲዮ የተነሳ በጤናዋም ሆነ በህይወቷ ላይ ሊደርስ ስለሚችለው ነገር የENT TV ሰዎች እና ጋዜጠኛ ወድንወሰን ከበደ ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ። ሌሎቻችን ፍቅራችንን እና አድናቆታችንን በመተው፣ ሰላሟን ባለመንሳት እናሳያት። አገር አለኝ ወገን አለኝ ትበል።
P.S. ይኽን ፎቶ የተነሳነው ከአንድ ዓመት በፊት ከእንጅባራ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት በተሰጣት ጊዜ፣ የሰማችሁትን የምስጋና ድምጽ በቀረጽኳት እና በወቅቱ ያያችሁትን ፎቶ ባነሳዃት ጊዜ፣ ለማስታወሻ እንነሳ አብረህ ላክላቸውና ይውጣ ብላኝ ያስቀረነው ነበር። በወቅቱም ከዚያም በኋላ በጭራሽ ፎቶውን የማጋራት ፍሎጎት አድሮብኝ አያውቅም ነበር። እንደ ቅርብ ወዳጇም ላደርግ ከምችላቸው ነገሮች መካከል በጣም ተራው ነው። አሁንም የማጋራው በእሷ ፍቃድ፣ በሀኪም ምክረ ሀሳብ መልእክቱ
??
ቃና ዘገሊላ መጽሐፍን የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ከቁጥር 1 እስከ 11 ድረስ ያለውን የቃና ዘገሊላ ሰርግ ታሪክ በመረጃና ዋቢ መጽሐፍት አዳብሮ፣ በሰርጉ ቤት እያመላለሰ፣ አንዴ ከእናቱ ጋር አንዴ ከአሳላፊዎቹ ጋር እያጋጠመን፣ አግዳሚ ወንበሮቹ ላይ አስቀምጦን ከመልካሙ ወይን እያስጎነጨን ቆይቶ፤ ወደ ሰማያዊው ዕለተ አርብ ሰርግ ሸኝቶን....
“ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደ ሙሽራ አጊጣ፣ ለበጉ ሰርግ ያለ እድፍና ያለ ነውር ውብ ሆና ተዘጋጅታ በምትቀርብበት በዚያ ሰማያዊ ሰርግ ለመገኘትና ወደ በጉ ሰርግ ራት ገብተን፣ ካጌጡ ቅዱሳን ጋር ለመቀመጥና ለመብላት የበቃን ያድርገን።” ብሎ ሲያበቃ “አሜን” ብለው ተደንቀው፣ ከቃና ዘገሊላው ሰርግ ቤት እንደወጡ ሰማያዊውን ሰርግ እታደም ይኾንን በሚል ተስፋ እና ጉጉት መቆዘም ቢቀር እንኳን፣ በአጻጻፉ ለዛ እና በመረጃ አደረጃጀቱ ተደንቀው አመስግነው የሚጨርሱት መጽሐፍ ነው።
የብርሃን እናት
ስለ “የብርሃን እናት” ለማውራት ቃላት የሉኝም። እያንዳንዱ ገጾች ሲገለጹ ነፍስ እንዳላቸው ሁሉ የሚንቀሳቀሱ፣ አረፍተ ነገሮቹ ሁሉ ልብን አፍነው የሚይዙና በስሜት የሚወዘውዙ ናቸው። እንደው በአጭሩ ተናገር ብባል፥ ለእኔ የብርሃን እናት የብዙ ነገር መጽሐፍ ሆኖብኛል፤ የትምህርት መጽሐፍ ነው። የምርምር መጽሐፍ ነው። የጸሎት መጽሐፍ ነው። የውዳሴ እና የመዝሙር መጽሐፍ ነው። የሕይወት መጽሐፍ ነው። የትህትህና እና የጥበብ መጽሐፍ ነው። የታላቅ እውቀት መጽሐፍ ነው። የንጽጽር መጽሐፍ ነው። የእቅበተ እምነት መጽሐፍ ነው። የቋንቋ፣ የስነጽሁፍ መጽሐፍ ነው። የመነቃቃት መጽሐፍ ነው። የጥበብ መጽሐፍ ነው።
የማርያም ጸሎትን ተንትኖ ሲጽፍ ሳይ፣ ተደንቄ ተደንቄ ልሞት። ምን ትዝ አለኝ? አርጋኖን ሚዲያ ላይ በ10 ይኹን በ11 ክፍል የተላለፈው “የአባታችን ሆይ” ትምህርቱ። ይኽንን ከቃና ዘገሊላ አንድ ምዕራፍ፣ 11 ቁጥር ጉዳይ ወደ 178 ገጽ የመለወጥ አቅም ጋር ሳያይዘው፣ እንደ ሄኖክ ብቻ የሚባል አጻጻፍ እና አቅም አለ ለማለት ድፍረት ይሰጠኛል። ምን ሲሆን እንደዚያ ዓይነት የስሜት ባህር ውስጥ ገብቶ እንደጻፈው ለመመራመር እድሉን ሳናገኝ፣ እኛም እዚያው ባህሩ ውስጥ ሰጥመን አብረን ስንቃትት፣ ስንወጣ ስንወርድ እናገኘዋለን።
አቅም ባገኝ የብርሃን እናትንም ለሦስተኛ ጊዜ አንብቤ የተሻለ ዳሰሳ ለመጻፍ እሞክራለሁ። ይኽንንም ከቃል አትቁጠሩብኝ። እስከዚያው ግን መጽሐፉ ላይ የተጠቀሰ ቅዱስ ባስልዮስ፣ አምፊሎኪዮስ ለተባለ ተማሪው በጻፈው ደብዳቤ ቅርጽ እኔም ይኽንን ልጻፍ፥
ዲያቆን ሄኖክ ለማስተማር ያለው ፍላጎት የሚያውቁትን ለማካፈል ዳተኞች የሆኑ ሰዎችን ሳይቀር የሚያነቃቃ ነው። “እናውቃለን” ብለው የሚታበዩትን፣ “አይ ይኽን ማወቅ አንፈልግም” ብለው የሸሹትን፣ “ይኽን ሳናውቀው አንቀርም” ብለው የሚመጻደቁትን ሁሉ የሚጠራ ነው። ቆይ እንዴት እንደምናውቅ እናሳያቸው ብለው የሚታበዩትንም የሚያራራ ነው። ከሄኖክ አብልጬ የማደንቀው ግን፣ ትምህርቶቹ በዚህ ዘመን እንደምናያቸው ብዙ ሰዎች ሰውን ግራ ለማጋባት ወይ አውቃለሁ ለማለት (ማወቅን ለማሳወቅ) የተዘጋጁ ሳይሆኑ፣ በቅንነት እውነትን ለማሳወቅ ከመጓጓት ብቻ የመነጩ መሆናቸው ነው።
እግዚአብሔርን፥ Henok Haile እነዚህን ድንቅ መጽሐፍት እንዲጽፍ ስላበረታው፣ አነሳስቶ ስላስጀመረው፣ አስጀምሮም ስላስጨረሰው በታላቅ አንክሮ አመሰግነዋለሁ። "አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች።" ~ መዝሙር ፻፬: ፳፬
እውነት አቅም ቢኖረኝ ሦስቱንም ገዝቼ ለማውቃቸው ሁሉ በሰጠሁ የምላቸው ናቸው። እንዳልኩትም የሌላ እምነት ተከታዮች ወይም እምነት የለንም የምትሉ ሰዎችም ብታነቧቸው አንዳች ቁም ነገር አታጡም። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ከሆናችሁ ደግሞ፥ they are must-reads!
ለሁላችሁም ብሰጥ ብዬ ፎክሬማ አልቀርም! ?
20 መፅሐፍት ለመስጠት ፈልጌያለሁ። 10 የብርሃን እናት ወይ ቃና ዘገሊላ (ቃና ዘገሊላ ገበያ ላይ ይኑር አይኑር ስላላወቅኹኝ ነው) እና 10 ሕማማት፥ በድምሩ 20 መጽሐፍት ለ20 ወዳጆች ለመስጠት ፈልጌያለሁ። መስፈርቱ ቀላል ነው፤ የልብን እውነት ማወቅና ሳይዋሹ ይገባኛል ማለት ነው። ከዚያ አንብባችሁ የተሰማችሁን ብትነግሩኝ ደግሞ ደስታዬ ልክ አይኖረውም።
▪︎ ሕማማትን “እግዚአብሔር አለ/የለም” በሚል ትኩስ ውዝግብ ውስጥ ላላችሁ 10 ወዳጆች።
▪︎ እንደዚሁ ደግሞ የብርሃን እናትን (ወይም ቃና ዘገሊላን ከሁለት አንዱን) ሀይማኖት ለመቀየር ውዝግብ ውስጥ ላላችሁ፣ ወይም በቅርቡ ቀይራችሁ ነፍሳችሁ ላላረፈች፣ ወይም ፕሮቴስታንት ውስጥ ሆናችሁ ውዝግብ ውስጥ ለሆናችሁ 10 ወዳጆች።
P.S.
አጠያየቃችሁን አሳምራችሁ ብትጽፉ ደግሞ ሰው ቢበዛ ለመለየት ያግዛል። ?
አማኝ ሆነው ለስጦታ መዋሽት ተገቢ አለመሆኑ የእኔ ወዳጆች አይጠፋችሁም መቼ ም። እንደውም ብትችሉ አብራችሁ መስጠት ነው። ?
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 2 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months ago