The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 5 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month, 1 week ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months, 1 week ago
Ethiopian Music: Nahome Mekuriya (Wude Liyu) ናሆም መኩርያ(ውዴ ልዩ)New Ethiopian Music 2021(Official Video)
#የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ያለው ግጭትና በክልሎችና ብሔሮች መካከል ያለው የውጥረት ግንኙነት ያሳስበኛል አሉ፡፡
ፕሬዝዳንቱ በዋይት ሀውስ ጽ/ቤታቸው በኩል ባወጡት መግለጫ በተለይም በትግራይ ክልል ያለው ፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ተቀባይነት የለውም ያሉ ሲሆን በክልሉ ያሉ ተፋላሚ ወገኖችም ተኩስ አቁም ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
የኤርትራ ጦር ከክልሉ ለቆ ሊወጣ እንደሚገባ በዚሁ መግለጫቸው ያመለከቱት የአሜሪካው መሪ ጆ ባይደን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ መሥሪያ ቤትን በመጥቀስ ኢትዮጵያ በዚሁ ጦርነት መራዘም ሳቢያ የረሀብ አደጋ እንዳንዣበበባት ተናግረዋል፡፡
በዚህም ሳቢያ ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦር የእርዳታ መተላለፊያዎችን በመክፈት ያንዣበበውን የረሀብ ስጋት ሊያስወግዱ ይገባል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
አሜሪካም እነዚህን ኢትዮጵያ የተደቀኑባትን ችግሮች በጋራ ለመፍታት ፍላጎት እንዳላት በመጥቀስ ከኢትዮጵያ ጎን ቆመን ረጅሙን የግንኙነት ታሪካችንን እንቀጥላለን ያሉ ሲሆን ተያያዥ የሆነውን የአፍሪካ ቀንድ ችግር ለመፍታት አሜሪካ የመደበቻቸው ልዩ ልዑክ ጄፍሪ ፌልትማን በቀጣዩ ሳምንት ወደ ቀጠናው ተመልሰው እንደሚመጡም ጠቁመዋል፡፡
〰〰〰〰〰〰〰
@EBS_TV1
@EBS_TV1
በኢትዮጵያ ተቀማጭ የሆኑ የውጭ ሀገር ዘጋቢዎች ዐለማቀፍ የግጭት አዘጋገብ መርሆዎችን እንዲያከብሩ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በፌስቡክ ገጹ ባወጣው ማሳሰቢያ መክሯል፡፡
ወታደራዊ ዘመቻ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ዘጋቢዎች ከመግባት እንደሚታገዱ የገለጸው ባለሥልጣኑ፣ የውጭ ዘጋቢዎች የሀገሪቱን ሕጎች፣ በሥራ ፍቃዳቸው የተጣለባቸውን ግዴታ እና ሙያቸውን አክብረው ከሰሩ ተባባሪነቱን እንደሚቀጥል አክሎ አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ በሱዳን ድንበር ወታደሮች ማስፈሯ ተገለፀ፡፡
የሱዳን የዜና ምንጭ ሱዳን ትሪቡን ወታደራዊ ምንጮቼ ነግረውኛል ብሎ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያ በጋዳሪፍ ግዛት በአል-ፋሽቃ ድንበር ውስጥ ወታደሯቿን አስፍራለች፡፡
ከሁለት ሳምንታት በፊት የሱዳን ጦር ሠራዊት በአል-ፋሽቃ ሻይ ባይት እየተባለ የሚጠራውን ስፍራ ከአማራ ክልል ሚሊሻዎች ማስለቀቁን ገልፆ ነበር፡፡
ከአንድ ሳምንት በፊት ይህን ስፍራ የጎበኙት የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል ሌፍትናንት ጄነራል ሸምስ ኤልድን ካባሺ የሱዳን ጦር ለም መሬቷን አል-ፋሽቃ 95 በመቶ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልፀዋል፡፡
ሱዳን ትሪቡን በውል ስማቸውን ያልገለፃቸው ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያ መነሻቸውን ከአማራ ክልል ባህርዳር እና ጎንደር ከተሞች ያደረጉ ወታደሮችንና ሚሊሻዎችን በቦታው አስፍራለች፡፡
የዜና ምንጩ ይህን ያስነብብ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል ሚሊሻዎች እየተደገፈ ቀደም ሲል በተጠቀሰው ቦታ ወታደሮችን አስፍሯል የሚለውን መረጃ ማጣጣሉን ዘግቧል፡፡
ይልቁንም አዲስ አበባ ከካርቱም ጋር ጦርነት ውስጥ እንደማትገባና አለመግባባቱን በድርድር መፍታት እንደምትፈልግ መጥቀሷን በዘገባው አስታውሷል፡፡
Via አሐዱ ራዲዮ 94.3
ኢትዮጵያ የአሜሪካ ዉሳኔ ከጉዞዋ ወደ ኋላ እንደማያስቀራት አስታወቀች
የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ እንደሚጥል ማስተላፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ሰቷል፡፡
ሚኒስቴሩ ባወጣዉ መግለጫ ኢትዮጵያና አሜሪካ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸዉ አገራት ሆነዉ ሳለ አሜሪካ በኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷ አሳዛኝና ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ሲል ወቅሷል፡፡
የአሜሪካ መንግስት ያስተላለፈዉ ዉሳኔ የኢትዮጵያን ጉዞ እንደማያሰናክል የገለፀዉ መግለጫዉ ይልቁንም ኢትዮጵያ ከአገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትመረምር ና አማራጮችን እንድታስብ ትገደዳለች ነዉ ያለዉ ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በዉሳኔዉ ሳይገደብ በዉስጥም ከዉጭም የሚሰነዘሩ ጫናዎችን መታገሉን እንደሚቀጥልም በመግለጫዉ አንስቷል፡፡
የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ አናዳጅ ብቻም ሳይሆን ዘመናትን ያስቆጠረዉን የሁለቱን አገራት ግንኙት የሚጎዳ ነዉ ሲል ክፉኛ ነቅፏል፡፡
ኢትዮጵያ የአገር ዉስጥ ችግሮቿን እንዴት መፍታት እንዳለባት ማንም ሊነግራት አይችልም ያለዉ መግለጫዉ የአሜሪካ መንግስት በኢትጵያ የዉስጥ ጉዳይ ለመግባት እያደረገ ያለዉ ሙከራ ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ብሏል፡፡
በትግራይ ያለዉ አለመረጋጋትና የሰብአዊ መብት ጥሰት ከማንም በላይ የኢትዮጵያን መንግስት ያሳስበዋል ያለዉ የዉጭ ጉዳይ መግለጫ ችግሩንም ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነዉ ብሏል፡፡
አሜሪካ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ባለስልጣነት ላይ የጉዞ እገዳ እንደምትጥል ማሳወቋ የሚታወስ ሲሆን አገሪቱ በትግራይ ክልል ያለዉ አለመረጋጋት እንደሚያሳስባት በመግለፅ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ እንደምታደርግ ገልፃች፡፡
የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በቲዉተር ሰሌዳቸዉ ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ በትግራይ ክልል ያለዉ የሰብኣዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ በተደጋጋሚ ድምጻችንን ብናሰማም ችግሩ ባለመቆሙ ከዛሬ ጀምሮ እገዳዉን እናስተላልፋለን ነዉ ያሉት፡፡
ዋሽንግተን እገዳዉ የሚጣልባቸዉን ግለሰቦች ስም ባይጠቅስም ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸዉ ባለስልጣናት እንደሚሆኑ ብሊንከን ይፋ አድርገዉ ነበር፡፡
አሜሪካ በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ፣ የኢኮኖሚና የፀጥታ ድጋፍ ማዕቀብ ጣለች!
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ቢሊንከን ለመገናኛ ብዙሀን ባሰራጩት መግለጫ በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለስልጣናት፣ በወታደራዊና የደህንነት ሹማምንት፣ በአማራ ክልል አስተዳደርና የፀጥታ መዋቅር መሪዎች እንዲሁም በወንጀል የተሳተፉ የሕወሓት መሪዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጣለች።
እሁድ ማምሻውን ይፋ በተደረገው መግለጫ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረውን የኢኮኖሚ ማበረታቻና የፀጥታ ድጋፍ ታቋርጣለች። የስብዓዊ ዕርዳታ እንዲሁም ለትምህርት፣ ግብርናና ጤና ለመሳሰሉት የሚደረገው የልማት ዕርዳታ ግን ይቀጥላል።
አሜሪካ ማዕቀቡን ለመጣል የወሰነችው የትግራዩ ጦርነት እንዲቆምና የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል እንዲሁም ተፋላሚ ወገኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ ያቀረብኩት ሀሳብ ተቀባይነት አላገኘም በሚል ነው።
የጉዞ ማዕቀቡ የትኞቹን ባለስልጣናት እንደሚመለከት መግለጫው አልዘረዘረም።አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያም ሆነ በኤርትራ ባለስልጣናትና በሕወሓት አንዳንድ አባላት ላይ የተጣለው እገዳ የጠቀሰው ደንብ ቁጥር (Section 212a) ሲሆን በዚህ ደንብ መሰረት የማዕቀቡ ዒላማ የሆኑት ባለስልጣናትን ስም ለህዝብ ይፋ ማድረግን አይጠይቅም።
በተለምዶ ለከፋ የስብዓዊ መብት ረገጣና ሙስና ጉዳዮች ስራ ላይ የሚውለው የማዕቀብ አይነት ሲሆን (Section 7031c) ማዕቀቡ የሚመለከታቸው ባለስልጣናትና ግለሰቦች ስም ዝርዝር በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ ያዛል።
በሰብዓዊ መብት ጥሰት ግድያና መሰል ወንጀሎች የተሳተፉ ወገኖችን ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ ለፍርድ እንዲያቀርቡ የአሜሪካ መግለጫ ይጠይቃል።ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት በትግራይ ጦርነት የሚሳተፉ ወገኖች ላይ የጉዞና የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲደረግ የሚጠይቅ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።
የጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ ለመጣል ማቀዱን አስታወቀ!
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጲያና በኤርትራ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ ለመጣል ውጥን እንዳለው አስታውቋል።የቪዛው ክልከላው በኢትዮጲያ አሜሪካ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያስከትል የሚችል ሂደት ስለመሆኑ የፎሪን ፖሊሲ ዘገባ ያሳያል።
የጆ ባይደን አስተዳደር ለወራት የዘለቀ የዲፕሎማሲ ንግግር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ቢያካሂድም በትግራይ ቀውሱ እንዲያበቃ እና ወንጀል የፈፀሙ አካላት ለህግ በሚቀርቡበት ሁኔታ ላይ ልዩነት አላቸው።
የኢትዮጵያ መንግስት ቀውሱ እንዲያበቃ እየሰራ መሆኑን እንዲሁን ጥፋተኛ የሆኑ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ መስራቱን የሚቀርበውን ክስ ትክክለኛ እንዳልሆነ አሳውቋል።ህወኣት በትግራይ ክልል የሚገኘውን የሰሜን እዝን መውጋቱ የግጭቱ መነሻ እንደነበር አይዘነጋም።
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 5 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month, 1 week ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months, 1 week ago