Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ፊቅህን ለመረዳት

Description
📚 አል ፊቅሁ አል ሙየሰር

📚 ፊቅህን በቀላል አቀራረብ ማቅረብ ይማሩ

📚 ቁርዓን እና ሱነን መሰረት ባደረገ መልኩ ከኡለማዎች አቋሞች ለመረጃ የቀረበዉን መለየት የሚችሉበትን ክህሎት ያዳብርልዎታል
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago

2 years, 1 month ago
**ታላቅ የዳዕዋ ኮንፈረንስ በጉብሬ ከተማ ነሲሓ …

**ታላቅ የዳዕዋ ኮንፈረንስ በጉብሬ ከተማ ነሲሓ መስጂድ

ቅዳሜ መጋቢት 17 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ

የረመዳንን መቃረብ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ታላቅ ፕሮግራም

ተጋባዥ እንግዶች
1,ሸይኽ ኢሊያስ አሕመድ
2,ኡስታዝ ሰልሰቢል ሀጅ ዙመካን
3,ኡስታዝ ዐብዱልካፊ ሙሐመድ

በተጨማሪም በጉራጌ ዞን የዳእዋ እንቅስቃሴ ተሳትፎ ያላቸው ኡስታዞች፣ ዱዓቶችና ጀመዓዎች የሚታደሙበት የማይቀርበት ፕሮግራም ነው

___
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር**@merkezuna

2 years, 3 months ago

ርዕስ ፦ ላኢላሀ ኢለላህ

🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ

ርዝመት፦ 57:17 ደቂቃ

💾 መጠን፦ ጥራት ያለው 26.55 MB

@nesihastudio

2 years, 4 months ago

Coming Soon...

#_ነሲሓ_ቲቪ_1000

2 years, 5 months ago

ውዱዕ አደራረግዎን ይገምግሙ

____
ፊቅህን ለመረዳት
@easyfiqh

2 years, 6 months ago
**የተሸጠ እቃ አይመለስም አይለወጥም!**

የተሸጠ እቃ አይመለስም አይለወጥም!

አንዳንድ ሱቆች ላይ ተለጥፎ የምናገኘው ማስጠንቀቂያ እንደሸሪዓ ተቀባይነት የሌለው መስፈርት ነው። ገዥ የገዛው ነገር ላይ እንከን ካገኘ እቃውን መልሶ በሌላ የመቀየር ወይም ገንዘቡን የማስመለስ መብቱ የተጠበቀ ነው። ሻጭ የዚህ አይነት ማስጠንቀቂያ ስለለጠፈ ብቻ የገዥን መብት ማሳጣት አይችልም።

የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ቅፅ 13 ገፅ 197

t.me/abujunaidposts

2 years, 10 months ago

*🗞 ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት*

ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦

عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رَضِيَ الله عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ". صحيح الجامع ، رقم 1133

ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ ቀናት ናቸው። ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናት» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚዕ 1133 ላይ አስፍረውታል

عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر. قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء" أخرجه البخاري

ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:‐
«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች በበለጠ ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል

በነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል:‐

1. ጾም፦ ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም)

2. ዚክሮችን ማብዛት፦ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል።

عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : "ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد" أخرجه احمد 7/224 وصحّح إسناده أحمد شاكر

ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፤
«ከነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል አህመድ ሻኪርም ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል።

ከተክቢር አደራረግ መካከል፤
الله أكبر ، الله أكبر لا إله إلا الله ، والله أكبر ولله الحمد
አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ” የሚለው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ይዘቶች አሉት።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሊደረግ የሚገባው ይህ ተክቢር ብዙ ሰዎች ስለማይፈጽሙት እየተረሱ ካሉ ሱናዎች መካከል ነው። ሰዎችን ለማስታወስ እና ሱናን ህያው ለማድረግ ድምጽን ከፍ አድርጎ ተክቢር ማድረግ ያስፈልጋል። ዓብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቡሁረይራህ በነዚህ አስር ቀናት ገበያ ወጥተው ተክቢራ ሲያደርጉ ሰዎችም እያስታወሱ ተክቢራ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ይህም፤ ሁሉም ሰው የራሱን ዚክር ያደርጋል ማለት ነው እንጂ ሰዎች እየተሰባሰቡ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ያድርጉ ማለት አይደለም። ይህ መረጃ ያልተገኘለት የተሳሳተ አፈፃፀም ነው።

3. ሐጅና ዑምራ፦ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعته يقول: "الحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة" متفق عليه.
ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡»
ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል

4. ኡድሂያ፦ በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች አጠር ያለ ግንዘቤን ይሰጣሉ፤

- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ሱናዎች መካከል ነው። የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረጉ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ (ተቅዋ) ነው።

- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

- ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል
ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

- የአላህ መልዕክተኛ እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ፣ የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋርትም ይቻላል።

- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ለቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

- ኡድሂያውን ለራሱ፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።

- በዒድ ቀን ኡድሂያን ለማረድ አስቦ የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም። ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህ በሀጅ ላይ ያሉ ሰዎችን የሚመሳሰልበት ነብያዊ ትዕዛዝ ነው። ሆኖም ይህ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው። እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም።

የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸውና የቻልነዉን ሁሉ በመፈጸም ወደ አላህ መቃረብ ይገባል፤ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ሰደቃ ማብዛት፣ ሱና ሰላቶችን ማብዛት፣ ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማብዛት፣ ዱዓን ማብዛት…ወዘተ ያስፈልጋል።

አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ የአላህ ባሮች ያድርገን።

አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
ህዳር 23/ 2004 ዓ.ል

----------------
📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts

2 years, 10 months ago

ሰው መሆንህ ክብር መሆኑን ካመንክ ሌሎችም ሰው መሆናቸውን አስታውስ!
7122 SMS | ከፍታ
_
ወደ 7122 በ SMS ok ብለው ቢልኩ መሰል ማስታወሻዎችን ያገኛሉ
https://t.me/sms7122

Telegram

7122 SMS nesiha መልዕክቶች

ወደ 7122 ok ብለው የላኩ ሁሉ የህይወት ክህሎታቸውን እያሳደጉ ነው እርስዎም አሁኑኑ ወደ 7122 ok ብለው በመላክ ይመዝገቡ፤ ከመልእክቶቹ ይማራሉ! ነሲሓ ቲቪንም ይደግፋሉ።

**ሰው መሆንህ ክብር መሆኑን ካመንክ ሌሎችም ሰው መሆናቸውን አስታውስ!**
3 years, 1 month ago

አስ-ሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ!
ውድ የነሲሓ የበጎ አድራጎት ቤተሰቦች:

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ከፊታችን እየመጣ ላለው ታላቁ እንግዳችን ለረመዳን ወር አላህ በሰላም ያድርሳችሁ እያልን፣
"ረመዳንን ይዤ በምን አፈጥራለሁ?" እያሉ በማሰብ ለሚጨነቁ ወገኖቻችን የማስፈጠር ፕሮግራም ቀርጸን ለናንተው ውድ ቤተሰቦቻችን አቅርበናል።

ለአንድ ቤተሰብ ለማስፈጠሪያ ያዘጋጀነው ዝርዝር የሚከተሉትን ያካትታል።
- ተምር 3 ኪሎ፣
- የሾርባ እህል 10 ኪሎ፣
- ሩዝ 5 ኪሎ፣
- ዘይት 3 ሊትር፣
- መኮረኒ 3 ኪሎ፣
- ፓስታ 3 ኪሎ፣
- ዱቄት 10 ኪሎ!

ይህን ለአንድ ቤተሰብ የተዘጋጀ ፓኬጅ በጥሬ ገንዘብ 2, 100 ብር በመክፈል ወይም በአይነት በማበርከት እነዚህን ቤተሰቦች "ረመዷንን እናስፈጥር!" በማለት ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ጥሪውን ያስተላልፋል።

🏦 በዚህ የማስፈጠር መርሀግብር ለመሳተፍ የሚከተሉትን የባንክ አካውንቶች ይጠቀሙ፦

1) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000328070778
2) ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ
1357377300001
3) አዋሽ ባንክ
01410797317600
4) ዳሽን ባንክ
7913417861611
5) ንብ ባንክ
7000016912412

🤳 ለበለጠ መረጃ በ 0972747474 ላይ ይደውሉ!

በዚህ የከፍተኛ ምንዳ መሰብሰቢያ ወር የሚያፈጥሩበት አጥተው በጭንቀት ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን በማገዝ ታላቅ ምንዳን ከአላህ እናግኝ!

ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ለመቀላቀል
t.me/NesihaCharityMain

3 years, 1 month ago

«ዝክረ ረመዳን App»

ለረመዳን በእውቀት እንዘጋጅ

ከማስታወቂያ ነፃ የሆነ ድንቅ የፆም ህግጋት መማሪያ አፕ ይጫኑና ለረመዳን ይዘጋጁ!

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nesiha_org.HTML

ከጎግል ፕለይ ማውረድ ላልቻላችሁ Apk ፋይል አታች አድርገናል
www.nesiha.com

@nesihastudio

3 years, 1 month ago
**ባለቤትህን አዝናና...**

ባለቤትህን አዝናና...
(የአላህ መልችክተኛ በምሽት ከአኢሻ ጋር እያወሩ ይራመዱ ነበር) ቡኻሪ ዘግበውታል

@tenbihat

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago