The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 2 Monate, 1 Woche her
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 11 Monate her
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 Wochen, 6 Tage her
"ምትክ"
.
.
ሁሌ ከማዘወትርበት መድሀኔአለም ቤተክርስቲያን ጥግ ስር ፀሎቴን
አቋርጦ የሚመጣው ድምጽ ተከትዬ አመራሁ። ብቻዋን ሁሌ በነጠላ
ክንብንብ ውስጥ ራሷን ደብቃ እምባዋን የምታፈስ እንስት አያለሁ ዛሬ
ላናግራት ወሰንኩ ሶፍት አቀብያት ምን እንደሆነች ጠየኳት እንዲህ
ነበር ታሪኳን የጀመረችልኝ ……
.
.
…… "በውበትሽ ማሰብ ስትጀምሪ ማንነትሽን ታጫለሽ ነበር ያለኝ !! "
……… እንቅልፍ ህልም ቅዠት እየተደራረቡ ይጫወቱብኝ ጀመር እሱን
ከእቅፌ ሳስወጣው ሁሉም ወደ እኔ መጡ ድባቴ…ትካዜ…ብስጭት…
ንጭንጭ በሙሉ ተሰበሰቡ እንዲህ ራሴን ጥዬ ስታይኝ አትፍረጂብኝ ?
ሴት ልጅ ንጽህናዋን ስትጠብቅ ነው አትበይኝ? ካለሱ ንጹህነት የለም
፡፡ካለሱም ክብር የለም ፡፡
…………… ቀጥ ብሎ የቆመውን ረጅሙን አፍንጫዋን በሹራቧ ጠርዝ
ጭምድዳ አበሰችው፡፡ በዚያው በነካ የሹራቧ ጫፍ የአይኖቿን ክፈፍ
ሞዠቀቻቸው ፡፡
………በእርግጥም ውበቴ ሲበዛ በራስ መተማመኔ ጨመረ መሰለኝ
ወንዶች ዙሪያየን የሞሉት ይመስለኛል "እዩዋት አታምርም?" የሚሉኝ
መሰለኝ ሁሉም በስስት የሚያዩኝ ፡፡
.
.
………… " እንዲህ እንደ ክዋክብት አትበተኝ እንደ ጨረቃ ሰብሰብ በይ
ያ ሲሆን ብርሀንሽ ጨለማን ይሰነጥቃል !! " አለኝ
……… ቃላቶቹ ያፈራርሳሉ ይበታትናሉ ከአቅሜ በላይ ናቸው ብዙ
ቀጥሮኝ የቀረሁ ቀን ፡፡ እሽ "ነገ" ሲለኝ ከተመቸኝ አልኩት አሁንም
ስቀር "ነገ" አለኝ ከጓደኞቸ ጋር እንደሆንኩ ነገርኩት፡፡
"ግዜ ሲራራቅ ናፍቆትን ሳይሆን መለያየትን ያቀርባል እንደምትናፍቂኝ
ታውቂ የለ ? አብረሽኝ ሁነሽ እንኳን ትናፍቂኛለሽ አትራቂኝ፡፡" ሲለኝ
አልገባኝም ነበር ፡፡
.
.
…… እጁ ላይ ያደረገውን አብረቅራቂ ተለጣጭ ጌጥ አውጥቶ "ይሄ
ቀኝ እጄን እንደ ጓደኞችሽ እና ቤተሰቦችሽ አስቢ ፡፡ ይህ ግራ እጄ ደሞ
እኔ ነኝ፡፡ አንች ይሄ ጌጥ ነሽ ፡፡ " ሁለት እጆቹ መሀል ላይ ጌጡን
አስገብቶ ለጠጠው፡፡ "ይህን ጌጥ አየሽው? በሁለት እጆች መሀል
ሲለጠጥ? አንችም በአንድ ጎን በቤተሰብ እና ጓደኞችሽ እየተሳብሽ
ነው ፡፡ እኔም ደሞ በዚህኛው ጎን እየሳብኩሽ ነው ፡፡ ከአቅም በላይ
ተለጥጠሻል በግዜ ወደ አንዱ ካልሆንሽ ትበጠሻለሽ፡፡"
ጌጡን ወደ ግራ እጁ አስገብቶ ለበሰው፡፡ "አየሽ ? እንዲህ ሲሆን ልክ
ነው አይጠብም አይሰፋም ፡፡"
እኔም ወይ ከሱ ወይ ከቤተሰብ እና ጓደኞቸ አንዱን እንድመርጥ
ጠየቀኝ ማለት ነው ? ጨዋታ እያጫወተኝ ነበር የመሰለኝ ፡፡
.
.
………… " ዙሪያሽን አትይ በራስሽ አለም ኑሪ፡፡ ከበታችሽ ያሉትን ካየሽ
አንች የበላይ የሆንሽ ስለሚመስልሽ ከአለም ትጋጫለሽ ፡፡ ከበላይሽ
ያሉትን ካየሽ ደሞ አንች እንዳነስሽ ስለሚሰማሽ ከራስሽ ጋር ትጣያለሽ
፡፡ "
…………አይገርምም? ምን ለማለት እንደፈለገ ሁሉ እንዳይገባኝ
በቃላት ልቤን አረሰው እስከዛሬ ለምን አልነገረኝም ነበር ሳላጠፋው
በፊት እንድማርበት ማድረግ ይችል አልነበር? ሳየው ማወቁን
እንዳውቅበት አይፈልግ ሲመስለኝ እንኳን እንዳልጠይቀው አፌን
አሸገው፡፡ ሁሌ ቅዳሜ ምሽት እምንቀመጥበት ቦታ ላይ ሁነን ቦታው
እንግዳ መሰለኝ ሳሮቹ የደረቁ መቀመጫችን የራሰ፡፡ የሞቀው
ሰውነቱን ስነካው ደስ የሚለኝን ልነካው ፈራሁት ሳየው ደስ የሚለኝን
ሳቁን ደበቀብኝ አይኖቹ ሽፋሽፍት የሞላቸው እንዳላየው የሚከልሉት
ክንፎች መሰሉኝ ፡፡
.
.
…………… " ፍቅር መስዋእትነትን ይጠይቃል ለፍቅር ሁሉን ነገርሽን
እጭ፡፡ ፍቅር በሚያጡት እጥፍ ማግኘት ነው ፡፡ በሚያጡት እጥፍ
መቀበል ወይም በማንኪያ ትሰጭ እና በአካፋ ትቀበያለሽ ፡፡ አንች ለዛ
አልተዘጋጀሽም የምታጭው ትልቅ ይመስልሻል የምታገኝው ከዛ
እንደሚበልጥ ልብ አላልሽም፡፡ በቃ መሄዴ ነው ብሎኝ ተነሳ ፡፡
……… ከመቀመጫው ተነስቶ ሲሄድ ቆይ አላልኩትም፡፡ ለምን?
ትተኸኝ አትሂድ ብዬ አልተጋፈጥኩትም ሲሄድ አየሁት ጨለማው
ውስጥ ገብቶ ተደበቀ ከአይኔ ማየት ውጭ ሆነ፡፡ በተቀመጥኩበት
ብዙ ቆየሁ የረጠቡትን አይኖቸን ንፋስ አራገባቸው ቅዝቃዜው ፊቴን
መታኝ አፍንጫዬ ቅጥልጥል ንፍጦችን አመረተ፡፡ ንጹህ ነኝ ብዬ አስቤ
ነበር፡፡ ግን አይደለሁም ነኝ ያልኩትን እንዳልሆንኩ ሲነግረኝ አፈርኩ ፡፡
.
.
……ያጣሁትን ማስመለስ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ ህይወትን ግን
ካለሱ ልኖራት ትከብደኛለች ልሸከማት ጫንቃዬ ይዝላል ጉልበቴ
ቄጤማ ይሆናል እጆቸ ይሰልላሉ ሊኖር ቃል ሲገባልኝ በአንድ ጀምበር
ያውም በጨረቃ አጣዋለሁ ብዬ ተጨንቄ አላውቅም፡፡ ሁሌ ፍቅሩ
ከእግሮቸ ማደግደግ ያስተውታል ብዬ አልነበረም ጨካኝ ነው ለማን
ትቶኝ ሄደ? ትቶኝ ሲሄድ ማን አብሯት አለ ብሎ አያስብም? ካለሱ
መኖር ለካ ከባድ ነው፡፡
.
.
…… ምናልባት ርህራሄው ጸበል ሁኖ ሰውነቴን ቢያረጥብ ፈውስ ባገኝ
ብዬ ብደውልለት ላገኘው አልቻልኩም ስልኩን ዘግቶት እንደሆነ
በማመኔ ወደ ቤቱ ሄድኩ በዛ አካባቢ ሰፈሩ ግርግር ሲበዛው
ባውቅም በአካባቢው ከወፍ ዝማሬ ውጭ ሌላ ምንም አልነበረም፡፡
ይሞታል ብዬ ገምቻለሁ? ላሳምነው ነበር የሄድኩት እቅፍ ላደርገው
ግን እሱ አይናገርም የሚያቅፉኝ እጆቹ በክር ታስረዋል አይኖቹን
የማንቀሳቀስ አቅም አልነበረውም ዳግም ላይስቁኝ ጥርሶቹ
ተከድነዋል ይሄን ሁሉ እንዴት ይነጥቀኛል?፡፡ ሰው ብቻውን
አይሞትም? ሰው እንዴት ሁለት ሰው ይዞ ይሞታል፡፡
.
.
……የዛኔ ተነጥሎኝ ሲሄድ እምባዬ እስኪደርቅ አልቅሼ ወደ ቤቴ ስሄድ
የተከሰተውን ሰምቻለሁ የኔ መሆኑን መች አወኩ እንዲህ ሀዘን
ከሚያኮራምተኝ ምናለ ተቃቅፈን ሁለታችንንም ገጭቶን በነበር እስኪ
ጎን ለጎን ብንቀበር ምን ነበረበት ግን ያንን ሁሉ አልችልም ቃል
ይሞታል? ቃሉን ግን ይሄው ቀን ገድሎታል፡፡ አሁን ማርገዜን ቢሰማ
አፈር ልሶ ይነሳል? ልጅ ሲወድ መጠን አልነበረውም ግን የእሱ አይነት
ሲወለድ የእሱ አለመኖር ምን ይባላል? ፡፡ መሞት አያስፈራም
አሟሟት ግን ያስፈራል፡፡ አራስ ልጄን ትቼው እዚ አለቅሳለሁ ፍቅር
ሲደቅቅ ሀዘን ከልብ አይወጣም እንደምወደው በእንባዬ ልጽፈው ነው
እዚ መገኘቴ ፡፡
.
.
…… ሁሌም የአንድ ነገር መምጣት የአንድ ነገር ማጣት ምልክት
ይሆን? በነገረችኝ ታሪክ ልቤ እንዲህ አዘነ ማልቀስ መፍትሄ
አይደለም ወይም ሰው እንደሚለው ማንም ከሞት አይቀርም ብዬ
ላጽናናት አልደፈርኩም እምባም ፍትህ ነው ታልቅስ አልቅሰውም
የማይወጣለት ስንት ሀዘን አለ በሱ መሞት ረፍት እሷ ሀዘኗን
ልትቋቋም ነበር? ፡፡ ወደምሄድበት ሳልወስን ቻው ሳልላት ብቻዬን
እያልጎመጎምኩ በፍጥነት ከአካባቢው ተሰወርኩ፡፡
@BetsinaD
አልፈልግም ስትለኝ እምባዬ እንዳይመጣ ታግዬ ፈገግ አልኩኝ ።
.... ለእምባዬ ፊት መስጠት አልፈለኩም ።
...የሄደን ሰው እምባ አይመልሰውም ብዬ ነው መሰለኝ !
ግን ከፋኝ....
...ተደግፌባት ነበር ።
...አደጋገፌ በጥርጣሬ አልነበረም ።
ከኔ እሷን አምናት ነበር.... እንዳልጎዳት ስጣጣር ነበር ።
... እንዳላሳዝናት ሁኔታዬን ሁሌ ዓየው ነበር...!
አልፈልግህም ስትለኝ ....
ጭር አለብኝ...
...በግርግር ውስጥ ጭርታ ስሜት እንዴት ይወለዳል...?
ጭርታው አስፈራኝ ጭርታው ድብርት ወለደ...
እሷ ስታብራራ እኔ መልስ መስጠት አልፈለኩም...
...እንዲ ስለው እንዲ ይላል ብላ ምላሽ ተሸክማ እንደመጣች ገብቶኛል ።
...ምላሽ ካጠና ሰው ጋር ውይይት ትርፍ የለውም ።
...ማን ለማን ብሎ ከማን ጋ ይሆናል...? ይሄ መስቀል ሳላጉረመርም የምሸከመው ነው...!!
ግን ይሄን ሁሉ ሲሰማኝ ፈገግ ብዬ ነበር።
..እሷም አልፈልግህም ስለው "ፈገግ ብሎ".. ነበር ትል ይሆናል ።
አድሃኖም
ርዕስም ትርጉምም የለዉም........
አንዳንዴ ነገሮችን ለማብራራት ከየት እንደምንጀምር ግራ ይገባናል....አለ አይደል አሳቢ እና ታዛዥ ከመሆን ......ምን አገባህ... ምን አገባሽ... አይመለከትህም አይመለከትሽም... ወደማለት እንዴት እንደተሻገርን እኛም አናዉቀዉም ...እናዉቀዋለን ግን እንዴት ነዉ የምናስረዳዉ? ...በቤተሰብና ጓደኛ መከበብን ጨዋታና ወከባ ከመዉደድ .....ለብቻ መቀመጥን እና ወከባ መጥላትን እንዴት ልምድ እንዳደረግን አናዉቅም...ብቻ አንዳንድ ሁኔታዎች ቅርፅ ይሰጡናል ...አንዳንድ ሰዎች ሰብረዉ ራስን መዉደድ ያስተምሩናል....አንዳንድ ጨለማ ምሽቶች ፅልመት ጋር ያወዳጁናል ...አንዳንድ ቀዝቃዛ ጊዜያት ዉስጣችን የተቀጣለዉን ፍቅር እና የሰዉ ተስፋ አጥፍተዉ አቀዝቅዘዉት ይሄዳሉ ....እናም ደና ነን ...ደና ነኝ
@BetsinaD
እና እሱ ጨረቃዬ ነበር። ቆንጅዬው ብርሃኔ፣እውነተኛው ፈገግታዬ።
ጨረቃዬ ስለው ለካ አንድ እውነታ ዘንግቻለሁ...ጨረቃ ሁሌም አታደምቀንም ለወረት ታይታን ስንላመዳት ትጠፋለች ....እሱም ..እሱም እንደ ጨረቃ ነበር ...ባልተረዳሁት ማንነቱ ያልተረዳሁትን ቃል በትክክለኛው ቦታ ስጠቀመው ነበር....
:--
.....አንዳንዴ የፈራነው ሁሉ ሳይሆን የጠበቅነውም ቀርቶ ያልጠበቅነው ይሆናል አይደል......
....አንዳንዴ ከአሸናፊዎች ወገን ለመሆን ስንሻ ከተሸናፊዎች ተርታ እንሰነፋለን አይደል......
ግን ሀቅ ነው እኛ ከዛም በላይ ነን
አንዳንዴ እየወደድን የምንርቀዉ አንዳንዴ ደግሞ እየጠላን የምንቀርበዉ ብዙ ጊዜ ግን ዝም ብለን አብረን የምንኖረዉ ሰዉ አለ..
አንዳንዴ ፍቅሩን ሳይገልጽልን የሚወደን አንዳንዴ ደግሞ እወዳችዋለዉ እያለን የሚጠላን ብዙ ጊዜ ግን ስሜቱን የማናውቀው ሰዉ አለ...
አንዳንዴ እየራበን የማንበላዉ አንዳንዴ ደግሞ ጠግበንም የምንመገበዉ ብዙ ጊዜ ግን ዝም ብለን የምንዉጠዉ ነገር አለ...
አንዳንዴ ሳንኖር የምንሞትብት አንዳንዴ ደግሞ ሞተንም የምንኖርበት ብዙ ጊዜ ግን ዝም ብለን የምንጏዝበት ህይወት አለ...
**አንዳንዴ አስደስቶን የምናለቅስበት አንዳንዴ ደግሞ አሳዝኖን የምናለቅስበት ብዙ ጊዜ ግን ዝም ብለን የምናነባበት ጉዳይ አለ...
አንድ አንዴዎች........
ሰዉ ስያሜ ቢያጣ ማእረግ ባይጨምር
ስሞችን ቀጣጥሎ ክብርን ባይከምር
እድሜን መቁጠር ቢያቆም ታናሽ ታላቅ ቢቀር
ቤት በሰም ባይዋብ ወርቅ ያንገት ጌጥ ባይሆን
ልብሱን አወላልቆ ሰዉ ጫማዉን ቢጥል
ሰዉ'እነት እርቃን ነዉ
ሰዉ እርቃኑን ነበር
የቴሌብር ሱፐር አፕን በማውረድ በመመዝገብ እና በመገበያየት ተሸላሚ እዲሆኑ ጋብዤዎታለሁ. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1635518748044544&inviterId=1006605396172801&language=am&time=Sept-03-2024-Dec-02-2024
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 2 Monate, 1 Woche her
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 11 Monate her
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 Wochen, 6 Tage her