የፍቅር ጊዜ❤️

Description
ያፈቀረን ማፅናናት ለኛ ኖርማል ነው አያሳስብም?

#Join ያድርጉና


ፈታ እያሉ በውብ የፍቅር ቃላቶች ይደመሙ?

ዘፈን , ግጥም , ጠቃሚ ምክሮች...

ከቻልክ❤ ፍቅርን ተናገር፣ አስተምር፣ ኑር!
.
.
.
??ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን ☞ ? @kenity
.
.
.
.

.

.
.
Before you #leave plz tell us z problem?
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week, 4 days ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months, 1 week ago

4 years, 3 months ago

​​[.​​​​​ ​​
የፍቅር ጊዜ?
:¨·....................:¨·.

ከፈላስፋያን
ስለ ፍቅር ጥቅሶች!?
-----------](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)
1. "ፍቅር ሲኖር ስራ ሁሉ ቀላል ይሆናል.
......
"ካህሊን ጂብራን"

  1. "ሁሉንም ማፍቀር እንደማትችል ካላወቅህ ማንንም አታፈቅርም"
    .......
    ሪል ላይፍ ፕሪቸር

  2. "ምንም አይነት ስሜት የሌለህን ሰው ለማፍቀር አትሞክር :ፍቅርን ከውስጥህ እንጂ በጥረትህ ልታመጣው አትችልም"
    ......
    አለን ዋት

  3. "በጥበብ ማፍቀርን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ ምንም ካለማፍቀር ግን በሞኝነትም ቢሆን ማፍቀሩ ይመረጣል"
    ......
    ዊልያም ኤልቪስ

  4. " እርጅና ሁሉ በአንድ ውስጥ ቢታወር ከማፍቀር አያስጥልህም ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ ፍቅር ከእርጅና ያስጥልሀል"
    .....
    ጂያን ሞሬታ

  5. " እውነተኛ ፍቅር ሁሉንም ያሳያል በእውነት ስታፈቅር መስተዋት ፊት በየዕለቱ እንደመቆም ይቆጠራል"
    .....
    ጀኒፈር አኒስተን

  6. "ለፍቅር የበለጠ ከማፍቀር ውጭ ሌላ ፈውስ የለውም"
    ......
    [ሔነሪ ዴቪድ ሰሮው

━━━━━✦?✦━━━━━
••●◉Join us share @lovertimee
የፍቅር ጊዜ ┄┄┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉┄┄](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)

[​​](https://telegra.ph/file/6f13f35bdd5c4edad90ce.jpg)[.​​​​​ ​​
4 years, 3 months ago

​​[​​​​.
የሰው ፍቅር ?
:¨""""""""""""""¨:

♥️ ክፍል 7

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ?
◈ የመጨረሻው ክፍል](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)

ለኔ ስድቡ ምንም አይደል ብቻ ሌላ ነገር አታምጡ ብዬ ዝም ብዬ መኖር ቀጠልኩኝ የአንድነት እናት እና እህት የበለጠ እየከፉ መጡ..... ከእኔ ቀድሞ ቤቱን ለቆ የወጣው አንድነት ነበረ፣ ለካ እሱንም ያስቸግሩት ነበረ ማለት ነው? ከዛም ሁለታችንም ቤት ተከራይተን መኖር ቀጠልን..... በጣም ጥሩ የሚባል ጊዜ ማሰለፍ ጀመርኩኝ፣ አሁን በህይወቴ ደስተኛ ነኝ በሳሚ ቦታ ፈጣሪ አንድነትን ሰጠኝ የእናቴ ሞት ሁሌም የሚጎዳኝ ነገር ቢሆንም መርሳት ባልችልም የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው ብዬ አንድነትን እናትም ቤተሰብም አድርጌ እየኖርኩ ነው: የኔ ደስታ እኮ ለጥቂት ጊዜ እንኳን መቆየት አይችልም.... አንድነት ትንሽ አምሽቶ ሲመጣ ምን ተፈጠረ እያልኩ እጨነቃለሁ፣ አንድነት ትቶ የነበረውን ሱስ በድጋሚ ጀምረዋል? ቤት ውስጥ ሠላም የለም! ደግሞ ምን ሊፈጠር ይሁን እያልኩ ስጋት ውስጥ ነኝ የአንድነት ፀባይ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ መጣ.... ውሸቱ እና ድብብቆሹ እየባሰ መጣ፣ አምሽቼ መምጣቴ በሥራ ምክንያት ነው ብሎ ውጭ አድሮ መምጣት ሁለ ጀመረ.... ፍርሃቴ የእውነት ነበረ በድብቅ መከታተል ጀመርኩኝ በመጨረሻም አንድነት ሌላ ህይወት እንዳለው ደረስኩበት? ህይወት በድጋሚ አስጠላኝ፣ ለካ ለምን እርጉዝ የሆንሽ ቀን ግኑኝነታችን ያበቃል ይለኝ እንደነበረ አሁን ገና ገባኝ እኔ'ኮ እሱን ከማጣ ብዬ ልጄን የገደልኩ ክፉ ሴት ነኝ?? እራሴን ለማጥፈት ብዙ ሞክሬ ነበረ ግን አልሆነም: ከብዙ ወራቶች በኋላ ሳሚ ስልክ ደወለልኝ ትዳር መያዙ እርግጥ እንደሆነ ስለማውቅ መቼም ለኔ ብሎ የአንዲትን እህት ህይወት ሊያጠፋ ይሆናል ብዬ ሲም ካርድ ቀየርኩኝ አሁን ብቻዬን እየኖርኩኝ ነው፣ እንክብካቤ የሚያደርግ ሁሉ አፍቃሪ አይደለም እወድሻለሁ የሚል ሁሉ አፍቃሪ አይደለም እህቶቼ እንዴ'ኔ ከልክ በላይ የዋሀ አትሁኑ ዘመኑ ከፍቷል በፍቅር ምክንያት ቤተሰብ እና ውድ ህይወታችሁን አትጡ ታሪኩ ልቦለድ ሳይሆን በውስጥ መስመር የተላከልኝ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ ነው አጭር የሆነው በዛ ምክንያት ነው"

✎ ውድ የፍቅር ጊዜ? ቤተሰቦች ታሪኩን እንዴት አገኛችሁት መቼም የማይረሳ ጣፋጭ የፍቅር ታሪክ እንደሰነቃቹ አልጠራጠርም በሌላ ድርሰት እስከምንገኛኝ ድረስ ባላችሁለት ሰላማችሁ ይብዛልን አስተያየታችሁን አድርሱኝ መልካም ጊዜ።?♥️


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @lovertimee
የፍቅር ጊዜ
┄┄┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉┄

[​​](https://telegra.ph/file/933e868201075de6295c8.jpg)[​​​​.
4 years, 3 months ago

​​[​​​​.
የሰው ፍቅር ?
:¨""""""""""""""¨:

♥️ ክፍል 6

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ?](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)

በሁለተኛው ቀን ጠዋት ላይ እዛው መጠጥ ቤት አንድ ክፍል ውስጥ በአንድነት ደረት ላይ ተለጥፌ እራሴን አገኘውት?? ሰውነቴ በብረት እንደተቀጠቀጠ ድንጋይ ደቋል ሞራል እና ጉልበቴ ከእኔ ተለይቶ ሄድዋል፣ ትልቅ ስህተት እንደሠራው አሁን ገና ገባኝ አንድነት ተነስቶ ፍፁም ሁሉም ነገር የተፈጠረው በስህተት ነው በጣም ይቅርታ የሆነው ነገር አንዴ ሆኗል አታልቅሽ አለኝ እኮ እንደዛ እወደው ለነበረ ሳሚ እንኳን ለመስጠት ሰስቼ ያሰቀመጥኩትን ክብሬን ድንግልናዬን በአንድ ቀን ትውውቅ ብቻ አሳልፌ ልስጥ!? ማነው ባለጌው? እሱ ወይስ እኔ? እኔ ግን እሱን ለመውቀስ አልሄድኩም እራሴን ነው የወቀስኩት፣ እንደዚህ ሆኜ ተመልሼ ቤት ከምሄድ ብዬ እዛው ተመልሼ እንቅልፌን ለጥ አልኩኝ አንድነት አይኑን በጨው አጥቦ ቀኑን ሙሉ ምግብና Soft drink እያመጣ እንክብካቤ እያደረገልኝ ዋለ እኔ ግን ምንም ደስ አላልኝም የዚያን ቀን እንደዛው ዋልኩኝ የአንድነት እንክብካቤ በሁለተኛው ቀንም እንደዛው ቀጠለ በልቤ የእውነትም በስህተት ነው እንዴ ብዬ ዝም አልኩኝ ከዚህ በኋላ ምንም የማጣው ክብር ሆነ ነገር የለም አልኩና እዛው ቤት ሥራዬን ቀጠልኩኝ የአንድነት እንክብካቤ ግን አሁንም እንደበፊቱ ቀጠለ፣ አንድነት የዋሀ ሰው ይመስላል እዛ ቤት ብዙ ይዘውኝ ለመውጣት የሚፈልጉ ሌላ ወንዶች ስለነበሩ ከማንም ጋር ከምወጣ ለምን እንዴ በስህተት የተፈጠረውን ነገር ለመልካም ነው የሆነው ብዬ በፀጋ ተቀብዬ ከአንድነት ጋር አልሆንም የሱ ጓደኛ ከሆንኩ እሱ ሁሌም እዚህ ቤት ስለሚኖር ማንም አያስቸግረኝም ብዬ ወስኜ ከአንድነት ጋር የፍቅር ይሁን የsex ብቻ አላውቅም ምርጥ ጓደኛሞች ሆነን ቀጠልን እንደዚህ እየሆነን ለብዙ ወራቶች አብረን መስራት ቀጠልን በዚህ አጋጣሚ ሳሚ በእኔ ቦታ የሚሰራ ሌላ ወንድ ልጅ አምጥቶ ቤት ውስጥ አስገባ እኔ ቤት ውስጥ እንደ ቤተሰብ ዝም ብዬ መኖር ጀመርኩኝ በዚህ ጊዜ ሁሉ የአንድነት ፊት ለአንድም ቀን ተለውጦ አያውቅም በቃ ሁሌም ያከብረኛል ሁሌም እንክብካቤ ያደርግልኛል አሁን እንደበፊቱ አይደለም ብዙ ሰዎች ግኙኝታችንን አውቀው ለእኔ አንድነት ላንቺ አይሆንም ከእሱ በቶሎ ብትሸሽ ይሻላል ይሉኛል ብዙዎች አይጠቅምሽም ተይው ይሉኛል ለእኔ ግን ክፋቱ ምንም አይተየኝም የሚታየኝ መልካምነቱ ብቻ ነው ለእኔ ችግር የሆነብኝ እሱ ሳይሆን የእሱ እናት እና እህቱ ናቸው: ምክንያቱ ምን እንደሆነ አላውቅም ብቻ ቤት ውስጥ አይኔን ማየት አይፈልጉም፣ እሱ ቤት ሲኖር ሁሉም ነገር ሠላም ነው እሱ ከቤት ሲወጣ ግን ውይ የስድብ መአት? ስድቡ ለኔ ምንም አይደል ብቻ ሌላ ነገር አታምጡ ብዬ በትእግስት መኖር ቀጠልኩኝ የአንድነት እህት ግን.....

꧁༺༒༻꧂

?ክፍል ሰባት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @lovertimee
የፍቅር ጊዜ
┄┄┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉┄

[​​](https://telegra.ph/file/ee307e3144d4567a7624b.jpg)[​​​​.
4 years, 3 months ago

​​[​​​​.
የሰው ፍቅር ?
:¨""""""""""""""¨:

♥️ ክፍል 5

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ?](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)

በዚህ አጋጣሚ ነበረ ሌላ ሰው ወደ ህይወቴ የመጣው ሥራ ቦታ ሄጄ ሁሉንም ነገር ተነጋግሬ ጨርሼ ወደ ቤት መጣሁኝ በሁለተኛ ቀን ተመልሼ ወደ ሥራ ቦታ ሄድኩኝ ከማንም ቀድሞ የተቀበለኝ የዛ ቤት ልጅ ነበረ፣ ትንሽ አፍጥጦ ሠላም አለኝ እኔ ሠላም አልኩት አንድነት እበላለሁ ሲለኝ እኔም ፍፁም አልኩት ሥራ የሚያሳይሽ ሰው አሁን የለም እስኪመጣ ነይ ከእኛ ጋር ቁጭ በይ ብሎ እዛው ጊቢ ውስጥ አንድ ክፍል ይዞኝ ገባ፣ ቤት ውስጥ ስገባ ጫት እና ሽሻ ሞልቷል ለካ ሥራ አለ የተባልኩት ካፌ ውስጥ ሳይሆን መጠጥ ቤት ውስጥ ነው ወዲያውኑ ፈጥኖ ቁጭ አለና ነይ ጫት እንቃም አለኝ ምን አይነቱ ደፋር ነው ብዬ እኔ ጫት ቅሜ አላውቅም አልኩት እሺ ከሽሻው ከእህቴ ጋር ሞክሪ አለኝ ሽሻ አንድ በከፋኝ ቀን ሞክሬ ስለነበረ እሱ ይሻላል ብዬ ቁጭ አልኩኝ ቀስ በቀስ ወደ ሙዳቸው ገብቼ እኔም የጉድ ማጬስ ቀጠልኩኝ አንድነት ቀስ እያለ ወደ ጨዋታ አስገባኝ የተጎዳሽ ሰው ትመስያለሽ ምን ሆነሽ ነው አለኝ አይ ምንም አልሆንኩም አልኩት ውሸት አያምርብሽም! ሰው ጎድቶሽ ነው አይደል? እኔም በሰው ተጎድቼ ነው ይኼን የጀመርኩት ደግሞኮ ጭንቀትን ለሰው ሲናገሩ ቀለል ይላል አለኝ እውነት መስሎኝ እምባ በእምባ ሆኜ የእናቴን ሞት የሳሚን በደል ሁሉንም ነገር ነገርኩት አይዞሽ በቃ ይኼ እኮ ያለ ነገር ነው እኔ አለውልሽ ከእንግዲህ ወዲህ ብቻሽን አይደለሽም አለኝ እኔም አመሰግናለሁ ብዬ ዝም አልኩኝ የኔ የሥራ ሰአት ከቀኑ 11 እስከ ሌሊቱ 8 ሰአት ነው ወደ ሥራ ገብቼ ሥራ ቀጠልኩኝ ከምሽቱ አራት ሰአት አከባቢ አንድነት መጥቶ ቁጭ ብሎ መጠጣት ጀመረ በአጠገቡ ሳልፍ ፍፁም ብሎ ጠራኝ አቤት ብዬ ሄድኩ ነይ ቁጭ በይ አለኝ ሥራውስ አልኩት ችግር የለም እህቴ ያንቺን ቦታ ተክታ ትሠራለች የመጀመሪያ ቀን በጣም እኮ ነው የሚያደክመው አለኝ አመሰግናለሁ ብዬ አጠገቡ ሄጄ ቁጭ አልኩኝ ስለ ክህደት አንስቶ ማውራት ጀመረ ሳሚን እያሰብኩ በፍጥነት መጠጣት ቀጠልኩኝ እሱ ቢራ ጨምሮ ጨምሮ ያመጣል እኔም ጨምሬ ጨምሬ በመጠጣት ላይ ነኝ በዚህ ቅስፈት አይዞሽ እሺ ብሎኝ ከንፈሬን በድንገት ሳመው? ሞቅ ብዬ ስለነበረ በጣም ደስ አለኝ ድፍረት ከየት እንደመጣ አላውቅም እኔም ሳምኩት ከዛ በኋላ የሆነውን ነገር አላውቅም ብቻ በሁለተኛ ቀን ጠዋት ላይ እዛው መጠጥ ቤት አንድ ክፍል ውስጥ በአንድነት ደረት ላይ ተለጥፌ እራሴን አገኘሁት

꧁༺༒༻꧂

?ክፍል ስድስት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @lovertimee
የፍቅር ጊዜ
┄┄┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉┄

[​​](https://telegra.ph/file/3eb9897463ab020c69fb3.jpg)[​​​​.
4 years, 3 months ago

​​[​​​​.
የሰው ፍቅር ?
:¨""""""""""""""¨:

♥️ ክፍል 4

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ?](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)

ይህ ሁሉ ግን እናቴን ከመሞት ማዳን አልቻለም እናቴ ሞተች? የቀብር ቀን አይኔ ሳሚን ፍለጋ ላይ ነው ሳሚ የት አለ? በእናት ቀብር ላይ የሚወዱትን ሰው ከአጠገብ ማጣት ምነኛ የሚጎዳ ነገር ነው? ከእናት ሞት በላይ የሚጎዳ ነገር ምናለ ልትሉኝ ትችላላችሁ ትክክል ናችሁ ምንም የሚጎዳ ነገር የለም! ከዚህም ይልቅ በእናት ቀብር ላይ ተስፋ ላይ ደስታ ላይ ህልም ላይ ቆመሽ አፈር ስትለብሽ አጠገብሽ ቆሞ አይዞሽ እኔ ተስፋ እሆናለሁ የሚል ሰው ማጣት ይበልጥ ሞቱን ሲኦል አያደርገውም!? ብጠብቅ ብጠብቅ ሳሚ የለም የእናቴን ሥጋ እና አጥንቶች ቻው ብዬ ተሰናብቼ በልቤ ህልሟን ሳቋን ቁም ነገሯን ይዤ ወደ ጨለማው ቤት ተመለስኩኝ። ስለ እናት ማጣት ጉዳት ብዙም ማውራት አልፈልግም ምክንያቱም ይኼ ለማንም ግልጽ የሆነ ነገር ነው፤ እኔ እኮ ግርም የሚለኝ ስትሞት ይኼ ሁሉ ትርጉም ላላት እናት በህይወት ስትኖር በአፍ ከማውራት የዘለለ በተግባር እናትናቷን መግለጽ የሚችል ምንም ፍቅር መስጠት አላመቻላችን ነው? ወይኔ ፀፀቱ ወይኔ ጉዳቱ አሁንም እንግዲህ ሁሉም አልፏል... ለእኔ ግን ህይወት ሞት ሆኖብኛል፣ ኑሮ በጣም ከብዶኛል፣ በዚህ መሃል ሳሚ ስልክ ደወለልኝ እውነት ለመናገር ልቤ በደስታ ዘሎ ነበረ ነገር ግን አእምሮዬ የሚወድሽ ሰው ቢሆን በሃዘንሽ ቀን ይመጣ ነበረ ሌላው ሁሉ ይቅር ሳሚ መልካም ሰው ቢሆን ለጓደኝነት ብቻ ብሎ እንኳን ይመጣ ነበረ የሱ ፍቅር ግን ከዛም የወረደ ነው ዝም ብትይ ይሻላል አለኝ ትክክል ነህ ብዬ ዝም አልኩኝ አአ ውስጥ ኑሮ ከበደኝ፣ በቀጥታ ተመልሼ ወደ ድሬ ሄድኩኝ.... ድሬ ውስጥ የእናቴ ጓደኛ ጉዳቴን አይታ እሷ ቤት ውስጥ እንድኖር ፈቀደች። በአእምሮዬ ሳሚ ላይ ቂም ብይዝበት እሱን ከመጠየቅ ግን ዝም ማለት አልቻልኩም..... ሳሚ ሰፈር ውስጥ የለም: ለሱ የቅርብ የነበሩ ልጆችን ስጠይቅ ሳሚ እኮ አአ ሄደ ምን መሄድ ብቻ ሠርጉ ራሱ በቅርቡ ነው ያለፈው አሉኝ አልቅሶ ከልብ ማውጣት ለማይችሉት ነገር የምን ማልቀስ ነው መሳቅ ነው እንጂ! እኔ አልቅሼ የማይወጡልኝ ሁለት ቁስሎች ልቤ ውስጥ ስለገቡ ለቅሶን በራሴ ምርጫ በሳቅ ለውጬ በሳቅ ለመኖር ወሰንኩኝ። እችል ይሁን? ለእናቴ ጓደኛ የትኛውንም አይነት ሥራ መስራት እፈልጋለሁ ሥራ ፈልጊልኝ አልኳት እሷም አንድ የማውቀው ካፌ ውስጥ አስተናጋጅ እየፈለጉ ነበር እዛ መስራት ትችያለሽ ወይ ብላ ጠየቀችኝ የትኛውንም አይነት ሥራ መስራት እፈልጋለሁ አልኩሽ አይደል ብዬ የሃዘን ልብሴን አውልቄ ሥራ ቀጠልኩኝ.... እምባዬን በውሸት ሳቅ ለመግታት ጥረት እያደረኩ ሥራዬን ቀጠልኩኝ በዚህ አጋጣሚ ነበረ ሌላ ሰው ዳግም ወደ ህይወቴ የመጣው..... . . . . . .

꧁༺༒༻꧂

?ክፍል አምስት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @lovertimee
የፍቅር ጊዜ
┄┄┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉┄

[​​](https://telegra.ph/file/b4052ca3aed38562bd075.jpg)[​​​​.
4 years, 3 months ago

​​[​​​​.
የሰው ፍቅር ?
:¨""""""""""""""¨:

♥️ ክፍል 3

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ?](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)

በፊት ቤት ውስጥ ከእኔ በላይ እንቅልፋም ሰው አልነበረም ዛሬ ምነው እምቢ አለኝ? ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? ለጊዜው መልሱ ምን እንደሆነ ባለውቅም ዝም ብዬ አደርኩኝ ሳሚ በጣም ምርጥ ልጅ ነው፣ ለኔ በቃ ሁሉ ነገሩ ተመችቶኛል በቀላሉ ነበረ መግባባት የቻልነው፤ እንግዲህ መግባባት ሲመጣ አብረው የሚመጡ አስፈላጊ እና አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮች አሉ፣ እኔን ከመጀመሪያው የጀመረኝ ናፍቆት ጭንቀት ፍርሃት ነበረ፣ ሳሚ የሆነ ቦታ ሄዶ ለጥቂት ሲቆይ ምቾት አይሰማኝም በቃ እጨነቃለሁ እፈራለሁ ብቻ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ቀልዱ ቁም ነገሩ ኧረ እኔ'ጃ ብቻ ፊቱ ራሱ ይናፍቀኛል፡ አንድ ሁለት እያልን ይበልጥ መቀራረብ ጀመረን..... እኔም ከት/ቤት እሱም ከሥራ ተመልሰን ማታ አከባቢ ለቤታችን ቅርብ ወደሆነው ቤተክርስቲያን ሁሉ አብረን መሄድ ቀጠልን... በዚህ ጊዜያት ሁሉ ሳሚ ስለፍቅር ምንም ነገር ጠይቆኝ አያውቅም፣ እኔ ግን ከእሱ ሙሉ በሙሉ ፍቅር እንደያዘኝ አውቃለሁ፤ ሳሚን የወደድኩት ገና በመጀመሪያው እይታ ነው፣ አሁን አሁንማ መልካምነቱን አስተዋይነቱን አይቼ ህይወቴ ከእሱ ውጪ ከማንም ጋር መኖር አትችልም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ። እሱ ግን ይወደኝ ይሁን? ከእለታት አንድ ቀን ዘወትር እንደምናደርገው ሁሉ አብረን ቤተክርስቲያን ሄደን.... ፀሎት አድርገን አብረን ቁጭ አልን፣ ፍፄ ዛሬ አንድ ነገር ልነግርሽ ነው አለኝ ልቤ ምን ይሁን እያለ ጭንቅ ብሏል፣ እሺ ምንድነው በፍጥነት ተናገር አልኩት ፍፄ ምን መሰለሽ አንቺ አሁን ገና ተማሪ ነሽ እኔ ግን አልቻልኩም ይኼን ስሜት ለመቆጣጠር ብዙ ሞክሬ ነበረ ግን አልቻልኩም፣ ፍፄ ወድጀሻለሁ ትምህርት እስክትጨርሺ በትዕግስት እጠብቃለሁ ቃል እገባለሁ መቼም ቢሆን አልጎዳሽም አለኝ የደስታ እምባ ከአይኔ በራሱ ጊዜ መውረድ ጀመረ.. ሳሚ እኔም እኮ በጣም እውድሃለሁ አልኩት አቅፎ ጉንጬን ሳም አደርገው፤ ህይወቴ ሀ ብሎ አዲስ ምዕራፍ ቀጠለ....በህይወቴ ይበልጥ ደስተኛ ሆንኩኝ፣ ግን ምን ያደርጋል የዚህ አለም ሀብት እና ደስታ ልክ እንደ አየር ንብረት ዛሬ ሞቅ ብሎ ነገ ተመልሶ ቀዝቀዝ ይላል ደስታዬ ብዙ መቀጠል አልቻለም? በድንገት እናቴ ላይ ትልቅ ህመም መጥቶ ደስታዬን ቀማው ድሬ ውስጥ ብዙ ህክምና ብታገኝም የእናቴ ህመም ግን እየባሰ መጣ.... በመጨረሻም እናቴ ለህክምና ወደ አአ ተወሰደች በእናቴ ህመም ምክንያት ቤት ውስጥ የነበረው ሁሉ ንብረት እቃ ራሱ አለቀ። በመጨረሻም ሁላችንንም አአ ሄደን ቤት ተከራይተን መኖር ቀጠልን...... ይህ ሁሉ ግን እናቴን ከመሞት ማዳን አልቻለም?እናቴ ሞተች? የቀብር ቀን አይኔ ሳሚን ፍለጋ ላይ ነው ሳሚ የት አለ?

꧁༺༒༻꧂

?ክፍል አራት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @lovertimee
የፍቅር ጊዜ
┄┄┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉┄

[​​](https://telegra.ph/file/4db961bb34d4a75447b8a.jpg)[​​​​.
4 years, 3 months ago

​​[​​​​.
የሰው ፍቅር ?
:¨""""""""""""""¨:

♥️ ክፍል 2

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ?](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)

ለቤቱ ባለቤት የቀብድ ገንዘብ ሰጥቶ እኔንም አመስግኖ ስሜ ሳሚ ነው ብሎ እቃ ለማምጣት ጥሎኝ ሄደ። እኔ ግን እዛው ቆሜ ቀረሁኝ.... በርግጥ ስለ ሳሚ ምንም የማውቀው ነገር የለም በአንድ ቀን ትውውቅ ለዛውም ለእንደዚህ አይነቱ አጭር ትውውቅ ለአንድ ሰው እንደዚህ ቦታ መስጠት ትንሽ የሚገርም ነገር ሳይሆን አይቀርም፤ ለራሴም ግርም እስኪለኝ ድረስ የሳሚን መምጣት መጠባበቅ ጀመርኩኝ.... የእውነት እመጣለሁ ብሎ ትንሽ ሲቆይ ከአሁኑ ጭንቅንቅ እያልኩኝ ነው ለስሙ ቤት ውስጥ ነኝ አይኔ ግን መንገድ መንገድ ብቻ አሻቅቦ በማየት ላይ ተጠምዷል፤ ይመጣ ይሁን እያልኩ ስጠብቅ ስጨነቅ በድንገት መጣ... ከዛም እቃውን ተጋግዘን ቤት አስገባን፣ እቃው በጣም ብዙ ነው ኧረ እንደውም አይደለም ወንዳላጤ ቤት በአንዳንድ ባለትዳሮች ቤት ራሱ የማይኖር እቃ ነው: ታላቅ ወንድሜ እና የሱ ጓደኞች ለቤቱ ምርቃት ጫት ይዘው መጡ?? እኔም ቡና ለማፈላት በሚል ሰበብ የሳሚን ጓዳ ገና ከአሁኑ መቆጣጠር ቀጠልኩኝ ድሬዎች በቃ እንዲህ ነን እኛ ሰፈር መጥቶ ማንም ብቸኝነት አይሳማውም፤ ቡና ተፈልቶ ወንድሜ እና ጓደኞቹ ጫት እየቃሙ እየተጫወቱ ብቻ በጣም ደስ የሚል ቀን ነበረ፣ ሳሚ ራሱ በጣም ተጫዋች ልጅ ነው፣ እንግዳ ሳይሆን ልክ ከእኛ ሰፈር የመጣ ሰው ነው የሚመስለው:: ብዙ አብረን ከተጫወትን በኋላ ደክሞካል ትንሽ አረፍ በል ብለን እኛም ወደ ቤት መጣን.... በነገራችን ላይ ሳሚ የተከራየው ቤት እኛው ቤት አጠገብ ነው ቤቱ የኛ አይደለም እንጂ ግቢው አንድ ነው ማለት ይቻላል አጥር ራሱ የለውም፣ ማታ ላይ ቤት ውስጥ እራት ቀረበ... እናቴ ፍፁም አዲሱን ልጅ ጥሪው ዛሬ እራት ከእኛ ጋር አብሮ ይብላ ለቦታው አዲስ ስለሆነ ምግብ ምናምን መስራት ደስ አይለውም አለችኝ እናቴ ለዚህ እኮ ነው የምወድሽ አልኳት?? ለምኑ ስትለኝ ደንግጬ አይ ደግነት እኮ ብዬ ዝም አልኩኝ? ቆይ እኔ ምን ቤት ነኝ? እኔ'ኮ መጀመርያውኑ በምን ሰበብ ልጥራው እያልኩ ፈርቼ ነበረ ዝም ያልኩት ቢሆንም ግን ሳሚ እዚህ እንዲመጣ አልፈልግም፣ ለእናቴ እሺ ብዬ ከቤት ወጥቼ ውጪ ትንሽ ቆይቼ ተመልሼ መጥቼ እማ ትንሽ አሞኛል ብሎ ተኝተዋል አልኳት??? እራት ለመውሰድ በሚል ሰበብ ቤቱ መሄድ ፈልጌ እኮ ነው? ውይ ምን ሆነ? በቃ እራቱን እዛው ወስደሽ ስጪው ካልሆነም አብራቹ ብሉ ብላ እራት ሰጠችኝ በልቤ ዬስስስስ ብዬ እራቱን ይዤ ስሄድ ሳሚ አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ነበረ፣ ከዛም አብረን እራቱን መብላት ጀመረን... ሳሚ የአ.አ ልጅ እንደሆነ እና ድሬ የመጣው ለሥራ እንደሆነ ነገረኝ እራት በልተን ከቤት ልወጣ ስል ፍፄ ብሎ ጠራኝ፣ በጣም ደነገጥኩኝ ምክንያቱም ከእዚህ በፊት ማንም ሰው እንደዚህ አቆላምጦ ጠርቶኝ አያውቅም፤ አቤት ብዬ ዞር ስል ስለ ሁሉም ነገር በጣም አመሰግናለሁ አለኝ ምንም አይደል! ደህና እደር ብዬ ከቤት ወጣሁኝ እግሬ ከቤቱ ወጥቶ መጣ እንጂ ልቤ እዛው ቤት ቀረ... በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ እንቅልፍ እምቢ አለኝ በፊት ቤት ውስጥ ከእኔ በላይ እንቅልፋም ሰው አልነበረም ዛሬ ግን እምቢ ብሎኛል፣ ምን አዲስ ነገር ተፈጥሮ ይሁን?

꧁༺༒༻꧂

?ክፍል ሶስት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @lovertimee
የፍቅር ጊዜ
┄┄┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉┄

[​​](https://telegra.ph/file/bb6ff3200eeb85e98186c.jpg)[​​​​.
4 years, 3 months ago

​​[​​​​.
የሰው ፍቅር ?
:¨""""""""""""""¨:

♥️ ክፍል 1

◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ?](https://t.me/joinchat/AAAAAFBnI6SIia54sidCnw)

ፍፁም እበላለሁ ትውልድ ቦታዬ አአ ውስጥ ሲሆን እድገቴ ደግሞ ድሬ ውስጥ ነው: አአ ውስጥ ብዙም የመቆየት እድል አላገኘውም ምክንያቱም በዛ ጊዜ ትክክለኛ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባለውቅም ቤተሰቦቼ የአአ ህይወትን ትቶ ወደ ድሬ እኔንም ይዘውኝ መጡ... ህይወት ከዛ በኋላ በጣም ጥሩ ሆነ፣ ለትምህርት ጎበዝ ስለነበርኩ ቤት ውስጥ ቤተሰቦቼ ጥሩ እንክብካቤ ያደርጉልኛል፤ የቤተሰቦቼ እንክብካቤ በትምህርት ላይ ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጥ ይበልጥ ጠንካራ እንዲሆን ረድቶኛል ብዬ አስባለሁ:: ሰፈር ውስጥ ጓደኛ ምናምን ያዝኩኝ በእድሜም ቢሆን ልጅ ከሚባል የእድሜ ደረጃ ወደ ወጣት የሚባልበት የእድሜ እርከን ውስጥ እየገሰገስኩ ነው ታዲያ በዚህ የእድሜ እርከን ውስጥ ልጆች በፊት የሚያውቁትን ብዙ ነገሮች ይጀምራሉ.... ይህ እድሜ ለብዙዎች የጥፋት እድሜ ሳይሆን አይቀርም! ብዙ ወጣቶች በዚህ የእድሜ እርከን ውስጥ ብዙ አዳዲስ ፀባዮችን ያመጣሉ.... ምን ፀባይ የብዙዎች መልክ ራሱ የሚቀየርበት የእድሜ እርከን ውስጥ ነኝ፣ በዚህ የእድሜ እርከን ውስጥ እያለሁ አንድ ቀን በእኛ ሰፈር ውስጥ አይቼ ከማላውቀው ልጅ ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝን... መገናኘቱ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም ማለቴ መንገድ ላይ ከማያውቁት ሰው ጋር መገናኘት ኖርማል እና ያለ ነገር ነው የኔን አጋጣሚ ትንሽ ለየት የሚያደርገው ልጁ ጠርቶ ስሠላም ማለቱ ነው፤ እኔ ሠላም አልኩት በትህትና ይቅርታ አንድ ነገር ላስቸግርሽ ስለኝ ታድያ ይቅርታ ለምን አሰፈለገ ምነው እዚህ ሰፈር ቤት ጠፍቶብህ ነው ወይ አልኩት አይ ሰው ቤት አይደለም የማጣውት የሚከራይ ቤት ፈልጌ ነበረ የዚህ ሰፈር ልጅ ትመስላለሽ የሚታውቅ ቤት የሚያከራዩ ጊቢ አለ ወይ ብሎ ጠየቀኝ አዎ አለ ና እንደውም ለሳይህ ብዬ አንድ ቤት ወስጄ አሳየሁት እሱም ለቤቱ ባለቤት የቀብድ ገንዘብ ሰጥቶ እኔንም አመስግኖ ሥሜ ሳሚ ነው ብሎ ጥሎኝ ሄደ። እኔ ግን እዛው ቆሜ ቀረሁኝ።

꧁༺༒༻꧂

?ክፍል ሁለት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @lovertimee
የፍቅር ጊዜ
┄┄┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉┄

[​​](https://telegra.ph/file/10c3678ea86f27b4dc93f.jpg)[​​​​.
4 years, 4 months ago

​​​​​​...ሰላም ውድ የፍቅር ጊዜ ቻናል ተከታታዮች እናንተን ሚያስተምር እና አሪፍ ታሪክ በማዘጋጀት ተጠምጄ ነበረ ይሄው አሁን አሪፍ እና እናንተን ያስተምራል ያልኩትን አሪፍ ታሪክ ይዤ መጥቻለው የታሪኩ ርዕስ የሰው ፍቅር❤️ ይሰኛል
ማነው እስቲ ይጀመር የሚል ️VOTE♥️ በማረግ አሳዩኝ!!

[​​](https://telegra.ph/file/b64621e23659099223b66.jpg)​​​​...ሰላም ውድ [የፍቅር ጊዜ](https://t.me/joinchat/AAAAAFQIykjSNPfEUjjYHA) ቻናል ተከታታዮች እናንተን ሚያስተምር እና አሪፍ ታሪክ በማዘጋጀት ተጠምጄ ነበረ ይሄው አሁን አሪፍ እና እናንተን ያስተምራል …
4 years, 4 months ago

​​[.

​​የፍቅር ወግ

┉┉✽̶»̶̥??»̶̥✽̶┉┉](https://t.me/joinchat/AAAAAFQIykjSNPfEUjjYHA)

2 በእድሜ ገድሜ ያሉ ባለትዳሮች ናቸው
በጣም ድብር ሲላቸው ባልየው እንዲህ አላት
"የወጣትነታችንን ጊዜ የጋብቻችንን ጊዜ ወደ ኃላ
ብንመልሰው ምን ይመስልሻል"
.
ሚስት:- በጣም ደስ ብሏት እሺ አለቺው!
ባል እኔ ታች ሱቁ ጋር ልውረድና ቁጭ ባልኩበት አንቺ
ትመጪና በድንገት እንገናኛለን አላት
እሺ ተባባሉና ሄደ ወረደ ታች ሊጠብቃት ቢጠብቃት
ቢጠብቃት አትመጣም 4 ሰአት ሙሉ ጠበቃት
አሁንም ወፍ የለም የሆነ ነገር አጋጠማት እንዴ ብሎ
በፍርሃት ቶሎ ወደ ቤት ተመለሰ ሊያያት
እሷ ቁጭ ብላ ስቅስቅ እያለች ታለቅሳለች
ባል ደንግጦ ምን ሆንሽ ውዴ?? አላት
.
ሚስት:- እናቴ ከቤት መውጣት ከልክላኝ ነው ብላ እርፍ?

ሼር ማንንም አይጎዳም ሼር አድርጉ ይህ የፍቅር ጊዜ entertainment ነው?

[​​](https://telegra.ph/file/b9f11d5f21d102fbdf2f7.jpg)[.
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week, 4 days ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months, 1 week ago