ላትሪያ

Description
የተለያዩ ሀሳቦችን በግጥም ወግ እና የተለያዩ ፅሁፎች ልብ የምንልበት በ game የምንጨዋወትበት😁ቤት ነው ጎብኙን
ላትሪያ:-https://t.me/amlko000
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week, 4 days ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months, 1 week ago

1 month, 2 weeks ago
Highschool እያለን የfellowship leaderአችን "ሰሞኑን ልዩ …

Highschool እያለን የfellowship leaderአችን "ሰሞኑን ልዩ ፕሮግራም ሊኖረን ይችላል አንተ ብቻ ብዕርህን አነቅ አነቅ አድርጋት..." ያለኝ አባባል ትዝ ሲለኝ...😅 ብዕር ማነቅ ግን ምንድነው🤭...ከዓመታት በኋላ ዛሬ ወግ ነገር ልፃፍ ብዬ ብዕሬ ፊት አንድ ወረቀት ዘረጋሁኝ...አነቅኳት ጨበጥኳት...ሚፃፍ ነገር ከየት ይምጣ...የለም ወፍ😒እንዲሁ ስንታገል ብቻ ዋልን::ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ አንደኛ ቀን!🤭 እንዴ ወገን ተመለስ...ዘፍጥረት 1 ድረስ በሐሳብ ሄዳችሁኮ😅 እሺ በቃ መሄዱ እስካልቀረ አብረን እንሂድ🚶‍♂‍➡️
ማታም ሲሆን ቀንም ሲሆን... በነዚህ 6 ቀናት ውስጥ ብቻ ምድርና ሞላዋ ተፈጸሙ:: የትጋት ሁሉ ምሳሌ የሆነው የሰማዩ አባታችን ማድረግ በነበረበት ጊዜ ሁሉን አድርጎ ማረፍ በነበረበት ጊዜ ደግሞ አረፈ:: ልጆቹ የሆንን እኛስ ከአባታችን ትጋትን መማር÷... ለተፈጠርንበትም ዓላማ በተፈቀደልን ልክ መትጋት የለብንም እንዴ😔 ከዚህ ግባ ሚባል አንድ ነገር ሳንሰራ ሳንቃ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር እንዲሁ በአልጋችን ላይ ስንገላበጥ ማታም ሲሆን ቀንም ሲሆን...እልፍ ቀን😒
ጌታ ስንፍናችንን አስወግዶ ትጋትን ይጨምርልን🙏🙏
ደህና እደሩ😊😍

ላትሪያ
https://t.me/amlko000
https://t.me/amlko000

1 month, 3 weeks ago
1 month, 4 weeks ago

በድጋሚ...
---------የአልባስጥሮሴ----------------
...ከአይኔ ብሌን ታች÷ ከውስጥ ከደም-ስሩ
እንባ ይውረድልኝ÷ እንዲሆን ለእግሩ
እግሩን እንዳርሰው÷ በእንባዬ ዘለላ
ብዙ ላንባ እንጂ÷ አይኔ እስኪቀላ
እግሮቹን እየሳምኩ÷ የመምህሬን
ለእግሮቹ ማበሻ÷ ላርግለት ፀጉሬን...

ሰናይ ምሽት 😴
ላትሪያ
https://t.me/amlko000
https://t.me/amlko000

1 month, 4 weeks ago

የጎደለው ቁጥር 3 ነው
አሸናፊ @Dynamiittee ነው
ስለ ተሳተፋችሁ ከልብ እናመሰግናለን ቤተሰብ🥰🥰

1 month, 4 weeks ago

“ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።”
ይህንን ክፍል ከያዕቆብ መልዕክት ካጠናን በኋላ ነበር እኔና ጓደኞቼ ስድስት ሆነን ዘጠኝ ዘጠኝ የተቸገሩ ልጆችን ልንረዳ እና ልንጠይቅ ተዘጋጅተን የተነሳነው🚶‍♂🚶‍♂። የሆነ ያህል እንደሄድን ጥቂት የማይባሉ ልጆችን መንገድ ላይ ተኝተው አገኘናቸው፤ ሰላም አልን፤ ካናገርናቸውም በኋላ በቡድን በቡድን አደረግናቸው። በቂ ባይሆንም ለተገኙት ለሁሉም ሶስት ልብስ መስጠት ቀዳሚ ሀስባችን ነበር። ነገር ግን የኛን ቁጥር (ቅድም ስድስት እንደሆንን ነግሬአችሁ ነበር) ከልጆቹ ብዛት ጋር ስናስተያይ ተጨማሪ ሰው እንደሚያስፈልገን ነበር የተረዳነው። ስለዚህም በእኛ ላይ ስድስት ሰዎችን ልንጨምር ወሰንን። በቡድን በቡድን ላደረግናቸው ዘጠኝ ልጆች ልብስ ከመስጠት በተለየ ሌላ ልናደርግ ያሰብነው ነገር ነበር፥ ምሳ መጋበዝ😋😋። ሰዓቱም ወደ ሰባት ተኩል ነበር፥ ጥሩ ሰአት ይመስላል። ግን ቅድም በየቡድኑ የነበሩ ልጆች ቁጥር ለምግብ ሲሆን በዛ ስለሚል እንደገና ሌላ ቡድን😩... በመጨረሻም ምሳችንን ልንበላ ተቀመጥን። በየቡድኑ ለነበሩ ሰባት ልጆች ሶስት ምግብ አደረገን። ያው እንደአቅማችን🤷‍♂። ጸለይን፥ ከቃሉ ተካፈልን፥ ተጫወትን...በጣም ደስ የሚል ጊዜ አሳለፈን። ቀን ሰባት ሰአት የጀመርን እስኪመሽ ድረስ አብረን ነበርን። ጌታም እንዲህ ያለውን አምልኮ እንደሚቀበለው ምንም ጥርጥር የለውም።

ጌታ ይወደናል❤️
ላትሪያ
https://t.me/amlko000
https://t.me/amlko000

1 month, 4 weeks ago

ሰላም ቤተሰብ🤗 ልክ አሁን ከምሽቱ 1:00 ሲሆን በሚለቀቀው አጠር ባለ ፅሁፍ ውስጥ ያሉ ቁጥሮችን ሰብስባችሁ ታሞላላችሁ የሞባይል ካርድ ነው(ethiotelecom)
📌በመጨረሻ የጎደለ አንድ ቁጥር አለ እናም በግምት የሆነ ቁጥር በመጨረሻ አስገቡ
📌ያሞላ ሰው እንዳሞላና የመጨረሻው ቁጥር ስንት እንደሆነ comment ላይ ቢያስቀምጥልን🙏
📌ውድ የቻናላችን admins መሳተፍ እንደማትችሉ በጌታ ፍቅር አሳስባለሁ😁

https://t.me/amlko000

2 months ago
ከእግዜር እቅፍ ባዝና፥ ጠኔ ያስለቀሳት

ከእግዜር እቅፍ ባዝና፥ ጠኔ ያስለቀሳት
ረግጦ የገዛት፥ የኀጢአት ቀንበር፥ ሸክም ያጎበጣት
ይህቺ ቅብዝብዝ ነፍስ...
ዕንቁ ዕድል ደረሳት፥ እረኛዋን አውቃ
ለሞት ከመነዳት፥ ጉያው ተደብቃ
ዘላለሟ አምሯል፥ ኀጥእ ብርሃን አየች
ህይወት አሸተተች፥ ህይወትን ቀመሰች።

አሜን🙌

“እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥25

ጌታ ይወደናል❤️❤️
ላትሪያ
https://t.me/amlko000
https://t.me/amlko000

2 months ago
በሀሳብ...ብዕሬን ብድግ አደርግና የስንፍናን ስሌት አሰላለሁ …

በሀሳብ...ብዕሬን ብድግ አደርግና የስንፍናን ስሌት አሰላለሁ "ዛሬ church miss ባደርግ...አንብቤ አጥንቼ አጥቤ አስጥቼ😏...ብዙ ሰዓት አተረፍኩኝ ማለት ነዋ🤷 ደግሞ ሰሞኑን ፈተና ሊኖረን ይችላል::" የአስቆሮቱ ይሁዳዊ ሒሳብ💀....የትም ያባከንኩት ጊዜ ዱላው የሚያርፈው ከጌታ ጋር በማሳልፈው ጊዜ ላይ ነው:: አንዳንዴ ደግሞ ጊዜዬን ልጠቀም እልና እቤቴ አጠር ያለች መንፈሳዊ ጊዜ ለማሳለፍ እሞክራለሁ:: እሱም ቢሆን ብቻውን ከቅዱሳን ጋር የማደርገውን ሕብረት ሊተካው እንደማይችል ይገባኛል:: "ይህ የሽቱ ጥፋት ለምንድር ነው?" ካለው ከይሁዳ በተሻለ መንገድ ሒሳብ የገባኝ አይመስለኝም😒 ያቺ ሴት ለርሷ የከበረ የተባለውን ሽቱ ጌታ ላይ እንዳፈሰሰች...እንደሰዋችለት እኔም በጣም value ማደርገውን ጊዜዬን እንደአስፈላጊነቱ መሰዋት እንዳለብኝ ነው ሚገባኝ:: ጌታም በስራዋ ተደሰተ እንጂ "ለምን ታባክኛለሽ?" አላላትም:: እናም ከእርሱ ጋር ጊዜን ማሳለፍ...ጊዜን ማባከን ሳይሆን ማትረፍ እንደሆነ ገባኝ😊

ላትርፍ በሚል ቀመር ሒሳብ አላጎድፍም
የጊዜ አላዋቂ በመሆን አልሰንፍም
ደስ ከተሰኘህ በጊዜ መስዋዕቴ
እሰዋልሀለው ከነፍላጎቴ
ደግሞ...
ሽቱ ይሁን ገንዘብ
ጊዜ ይሁን ጉልበት
በገዛ ፈቃዴ ያቀረብኩ እንደሆነም
አተረፍኩኝ እንጂ አንዱም አልባከነም::

ጊዜያችንም ይገባዋል😊 በሉ ደህና እደሩ😴

ላትሪያ
https://t.me/amlko000
https://t.me/amlko000

2 months ago

Mezmur challenge...😁

የአባትነት ፍቅር ምክሩ
ሳይለየኝ ማስተማሩ
ልክ እንደ ዓይን ብሌን
ተንከባክቧት ሕይወቴን....
........................................
........................................
........................................
........................................

ቀድሞ አንጓውን(ቁጥሩን) የጨረሰ....card ይሸለማል😁😊በcomment. የማን መዝሙር እንደሆነም...

2 months, 1 week ago
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week, 4 days ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months, 1 week ago