????? ??ᶠᴼᴴᴬᴹሸቀ

Description
አንድም ሙስሊም ሰው ቁርአንን ሳያውቅ መሞት የለበትም!!!!!!!

ካልፈለጋችሁ Leave ብላችሁ መውጣት መብታችሁ ነው፤?‍♂?‍♂ ለAllah ሲባል እንጂ የምናገኘው ጥቅም የለም???

—͟͟͞͞?F̺͆O̺͆H̺͆A̺͆M̺͆▓࿐

??????????

islam is ????????
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 months, 2 weeks ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 3 days, 5 hours ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 7 months, 3 weeks ago

11 months, 1 week ago

?የቻናል ባለቤቶች ተመልሰናል*? *ወደኔ ⚡️*?*wave folder *?*መግባት የምትፈልጉ ሰዎች ሊሞላ 10 ሰው ብቻ ነው ምፈልገው አናግሩኝ *?*?****@kira_Wave

⚡️⚡️⚡️ @Kira_wave*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*⚡️*@Kira_wave⚡️*⚡️*⚡️***

11 months, 1 week ago

*?ዝቅ አድራጊዋና ከፍ አድራጊዋ እለት!

▪️*قال العلامة ابن عثيمين :

?ታላቁ ሸኽ ኢብኑ ዑሠይሚን እንዲህ ይላሉ:

«وكم من إنسان في الدنيا رفيع الجاه معظم عند الناس يكون يوم القيامة من أحقر عباد الله»

«ስንት ሰዎች አሉ በዱንያ ክብራቸው የላቀ በሰው ዘንድ ታላቅ የተባሉ የቂያማ እለት ግን ከሰው በታች የተዋረዱ የሚሆኑ!! »[አልዋቂዐህ 328]**

11 months, 1 week ago

Old telegram groups መሸጥ ለምትፈልጉ

Old telegram ግሩፖች ያላችሁ ke 2022 ena betach የ Group ሜምበር ብዛት አያስፈልግም የGroup ሜምበር 1 ሰው ቢሆንም በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን ነው።  ግን የተከፈተበት አመተ ምህረቱን ነው የምፈልገው  ቢያንስ አንድ አመት የቆየ መሆን አለበት

ቢያንስ አንድ አመት የቆየ እና ትንሽ ሜምበር ያለው ግሩፕ (ከ1 ሜምበር ጀምሮም ይቻላል) ያላችሁ ሰዎች እና መሸጥ የምትፈልጉ inbox ላይ አናግሩኝ በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን እንገኛለን።

@foham2
@foham2
@foham2 ??? bezi anagrun

11 months, 2 weeks ago

እያየችዉ ነዉ...
አይኖቿ ሙጭሙጭ ብለዉ ቀልተዋል..ስታለቅስ እንደነበር ገባዉ..ለመነሳት ሲሞክር ጭንቅላቱ ከበደዉ ህመም ተሰማዉ...እጆቹ ላይ የተሰካኩ መርፌዎች አሉ...አዎ አለምነህ ክሊኒክ ዉስጥ እንዳለ አወቀ...
"ተመለስክ አለምነህ..እንዴት ደስ ይላል" አለች ትእግስት አፏን በእጆቿ እየከደነች...
"አንተ ደነዝ አስጨንቀኸን ነበር" ፊቱን መታ መታ አደረጉት ጓደኞቹ...
"ምንድነዉ የሆንኩት ግን" አለምነህ ጠየቀ ግራ በመጋባት..
"ምን ያልሆንሽዉ አለ ልትሾልኪብን ነበር" አለ አንደኛዉ ጓደኛዉ በጫት እንጨት(ስትኪኒ) ጥርሱን እየጎረጎረ...
"ዘካሪያስ ከጀርባህ ጭንቅላትህን መጥቶህ ነዉ" ትእግስት መለሰች...
"ማናባቱ ነዉ ደሞ ዘከሪያስ...? መኮርኮም አለበት" አሉ ሁለቱ የአለምነህ ጓደኞች (ቢኒያም እና ሚኪያስ ይባላሉ...ቢኒ የሀረር ልጅ ሲሆን ሚኪያስ ከአዳማ ነዉ የመጣዉ..ጫት ዉስጣቸዉ ነዉ...የሰዉ ልጅ ካልቃመ ምንድነዉ ሲያደርግ የሚዉለዉ ብለዉ ለመፈላሰፍም ይቃጣቸዋል...በየቀኑ ይቅማሉ...መሸትሸት ሲል ደሞ "ጫማ ያለ ካልሲ..በርጫ ያለ ጨብሲ አይነፋም" ይሉና ቅምቀማ(መጠጥ) ይጀመራሉ...ምርቃናዉ ይሰበራል...ሞቅ ሲላቸዉ የጨብሲ ወሬ ይጀመራል...ከተመቻቸዉ በዛዉ ይቀጥሉና ጭፈራ ቤቶች ጎራ ይላሉ..ካልተመቻቸዉ ደሞ ሞቅ እንዳላቸዉ ከምሽቱ 4 ሰአት በፊት ወደ ግቢ ይገቡና ቺኮችን ሲላከፉ ከተመቻቸዉ ጋር ሲበሩ ለሊቱን ያጋምሱታል።...ይሄዉ ነዉ እንግዲህ የእነሱ ህይወት ዛሬን ግን ምንም አይነት መጠጥ አልቀመሱም..ምርቃናዉ አናታቸዉ ላይ ወጥቷል..አይናቸዉ ፈጧል..ሲያወሩ እንኳን ጥርሳቸዉን እያፋጩት ነዉ...በአንድ እጃቸዉ ፀጉራቸዉን አየጠቀለሉ በሌላኛዉ እጃቸዉ ጥርሳቸዉን በስትኪኒ እየጎረጎሩት ነዉ...እረ ነቀሉት..?

"እናንተ ደሞ ስትመረቅኑ የህንድ አክተር ምትሆኑት ነገር አለ.." ሰዉዬዉን እንኳን አታዉቁትምኮ" አለ እየሳቀ መጠጥ ብቻ የሚያዘወትረዉ ተመስገን..(ቶም እዚሁ የአዲስ አበባ ልጅ ነዉ)
"ምን ታካብዳለህ አንተ ጠጃም..አረቄ ጋን ዉስጥ ካልነከሩህ ነገር አይገባህማ..እሷ ታዉቀዋለች በዛ ላይ እሱን መፈለግ ለኛ ከባድ ነገር እንዳልሆነ ታዉቀዋለህ" አለ ሚኪያስ ምርቃናዉ እያንተባተበዉ...
"ለነገሩ በለጬዉ ነዉ የሚያወራዉ ዝም ብልስ" ቶም በድጋሜ የሹፈት ሳቅ ሳቀ
"አቦ ተወን በቃ አጦልበን በዳሁህ እሺ" አለ ቢኒ ስትኪኒዋን ከአፉ እያወጣ...
"ተረጋጉ ሰዎች...እኔም ምንሞ አይነት ግርግር አልፈልግም.." አላቸዉ አለምነህ በነገረ ስራቸዉ እየሳቀ..
"የተማረ ይግደለኝ ይልሃል ይሄ ነዉ አያችሁ እንደኔ ሰከን ብሎ ሲያስብ..በህግ አግባብ ነዉ ሊጠየቅ የሚገባዉ" ቶም ከአፉ ነጥቆ ተናገረና በመኮፈስ ሚኪያስን አየዉ..
"ድንቄም የተማረ" አለ ሚኪያስ እየሳቀ የመልስ ምቱን...
"አዎ ዘከሪያስ መከሰስ አለበት" ትእግስት የተመስገንን ሀሳብ ደገፈችዉ..
"አይ አይሆንም አልከሰዉም..መጠጡ ገፋፍቶት ነዉ እንጂ መጥፎ አስቦ አይመስለኝም...በዛ ላይ ቅድም እኔም ተናድጄ መትቼዉ ነበር...እኔም ልክ አልሰራሁም" አላቸዉ ሁሉንም በአይኑ ለማዳረስ እየሞከረ...
ትእግስት አልሞገተችዉም...ምንም አልመለሰችለትም...ማንነቱ ዉስጧን ማረከዉ...ለሰከንዶች እሷን አይደለችም..
ከመቀመጫዋ ብድግ አለችና ተንጠራርታ ጉንጩን ሳም አደረገችዉ...

የአለምነህ ጓደኞች እርስ በእርስ እየተያዩ ሳቁባቸዉ...የተተከለለት ግሉኮስ እንዳለቀ ሀኪሙ ፈቅዶላቸዉ አለምነህን ወደ ዶርሙ ደጋግፈዉ አስገቡት...

ከሁለት ቀናት በኋላ በተለመደዉ ቦታ በተለመደዉ ሰአት ተገናኙ...ምሽታቸዉን ለማሳመር ደፋ ቀና አሉ..አንዱ አንዱን ለማስደሰት ተራኮቱ...በስንኞቻቸዉ ተጠበቡ በግጥሞቻቸዉ ሩቅ መንገድ ተጓዙ...እልፍ አእላፍ ነጎዱ..ተሳክቶላቸዉም ፊቶቻቸዉ ላይ ፈገግታን በተኑ...ቀኑ ተገባዶ ብርሃን ለጨለማዉ እጅ ሰጠ...ድቅድቅ ጨለማ በቦታዉ ተተካ...አለምነህ እና ትእግስት በጨለማዉ ዉስጥ እየተራመዱ ነዉ..ጨረቃዋ ሙሉ ሁናለች ፈገግ እያለች ትከተላቸዋለች..እንቅፋት እንዳይመታቸዉ ከጀርባቸዉ ሁና ታበራላቸዋለች..
"ግን ስለ እኔ ምን ታስባለህ.." አለችዉ ትእግስት እጆቿን የሹራቧ ኪስ ዉስጥ እየከተተች..
"ምርጥ ጓደኛዬም እህቴም ሁነሽልኛል...እየደገፍሺኝ ነዉ ...ቲጂ አንቺን እንደ አህቴ ነዉ ማይሽ ለእህቴ የማደርግላትን ነገሮች ላንቺም ሳላመነታ አደርግልሻለሁ...መልካም ሴት ነሽ" አላት ፈገግ እያለ...
ትእግስት አልከፋትም እንደዉም ደስ ብሏታል...የጠበቀችዉም መልስ ነበር..."ግን ያ ዘከሪያስ ድጋሜ የሆነ ነገር ቢያደርግህስ..?"ፊቷን ቅጭም አድርጋ ፍርሃቷን ተነፈሰችዉ..
"አትጨነቂ ምንም አያደርገኝም አንድም ከእንደሱ አይነት ሰዎች ነዉ ምጠብቅሸ"
"እሺ መከታዬ ልበልህ ጋሻዬ...የኔ ጠባቂ መላእክ" ትእግስት እየዘለለች ከፊት ለፊቱ ሄዳ መንገድ ዘጋችበት..
"አንቺ እብድ" አላትና በድጋሜ ሳቅ አለ..
"ግን ዘከሪያስን እንዴት ነዉ ያወቅሽዉ...?" አለምነህ ጥያቄ ሰነዘረ..
"እዚህ እንቀመጥ..? አለችዉ እርምጃዋን ገታ አድርጋ..
የአሰፓልቱን ጠርዝ ይዘዉ ጎን ለጎን ተቀራርበዉ ተቀመጡ...
"እሱን ያወቅኩበት ቀን የተረገመ ይሁን...የሪጅስቴራል ምዝገባ ቀን ነዉ..የምዝገባ ሂደቱ ግራ ሲሆንብኝ አንተን ፈለግኩህ ግን አልነበርክም...በሚቀጥለዉ ቀን ሬጅስትራል ሄድኩ..እዛዉ በቆምኩበት ዘካሪያስ ተብዬዉ መጣ..ተዋወቀኝ ፍሬሽ እንደሆነም ነገረኝ...እንድመዘገብ ረዳኝም እኔም ከልቤ አመሰገንኩት...ግን የልጁ ፍላጎት እኔን ከመርዳት ያለፈ ነዉ...ወሬዉ ሁሉ ይቀፋል..ለሰአታት ቤተሰቡ ስላለዉ ሀብት እንደዶሰከረልኝ ነበር...እዚህ ሄድኩ..ይሄ አለን...እዚህ ተዝናናሁ...አቋርጬዉ መሄድ ብልግና ስለመሰለኝ ቋቅ እስኪለኝ ሰማሁት...ለእሱ ሌሎች ሰዎች ተራ ምናምንቴ ናቸዉ..ሁሉንም ነገር መግዛት የሚችል ይመስለዋል...ከዛን ቀን በኋላ ሰላሜን ነሳኝ...በሄድኩበት ሁሉ ይከተለኛል ይጨቀጭቀኛል.. ወድጄሻለሁ ይለኛል ግን ወዶኝ አይደለም እኔን በብሩ መሳብ ስላልቻለ ሊገዛኝ ስላልቻለ እልህ ይዞት ነዉ...በዚህች ጥቂት ቀናት ዉስጥ ህይወቴን ሲኦል አደረገዉ...እንዳየኸዉ ከሁለት ቀናት በፊት ገደቡን አለፈ...የእኔ ጦስ ላንተም ተረፈ..ይሄዉ ነዉ" አለችዉ.. በረዥሙ እየተነፈሰች....
"ቲጂ በህይወትሽ ብዙ አይነት ሰዎች ያጋጥሙሻል..ጠንካራ ሴት መሆን አለብሽ" አላት አለምነህ ወደ ሰማይ አንጋጦ የጨረቃዋን ዉበት በዉስጡ እያደነቀ...
"በጣም ታምራለቻ" አለችዉ እሷም ወደ ላይ እያንጋጠጠች...
"ሁለታችሁም ታምራላችሁ" አላት ቀና ካለበት መለስ ብሎ ትእግስትን እየተመለከተ...

11 months, 2 weeks ago

?ፍቅር ብቻ?

?የወጀቡ ጥግ?

?ክፍል 6

ደራሲ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ(ምትኩ)
.
.
.
ትእግስት ደንግጣ ፊቷን አዞረች...ዘከሪያስ ነዉ..አለምነህን ባጣችባቸዉ በነዛ ሶስት ቀናት ዉስጥ ያወቀችዉ ዘከሪያስ...በነዛ አስቀያሚ ቀናቶች ተሯሩጦ ያስመዘገባት ዘካሪያስ..
ዘከሪያስ ደርሶ የትእግስትን ክንድ ጠንከር አድርጎ ያዘዉ "ማነዉ ደሞ ይሄ አብሮሽ ያለዉ" አላት በቁጣ..መጠጥ የጠጣ ይመስል አፉ ተያይዟል..
"ላንተ ማስረዳት አለብኝ...? እእ እስኪ ቅድሚያ ስርአት ይኑርህ እጄን ልቀቀዉ" ድፍረቱ ገርሟታል..
"ቆንጆ ስለሆንሽ ሁሉም ሰዉ ሊመኝሽ ይችላል..እኔ እያለሁ ግን ሊነኩሽ አይችሉም..እኔ የፈለግሽዉን አደርግልሻለሁ..በአልማዝ አንቆጠቁጥሻለሁ..ከዚህ ሌላ ምን ትፈልጊያለሽ..የኔ ከሆንሽ ሁሉም ነገር ይኖርሻል እእ" ዘካሪያስ ክንዷን ይበልጥ ጠበቅ አድርጎ ያዛት...
"ከዚህ በላይ እራስህን አታዋርድ..ልትገዛኝ እየሞከርክ ነዉ..? እኔ እቃ እመስልሃለሁ እንዴ..አትረባም እሺ..ልቀቀኝ" ትእግስት እንዲለቃት ትታገለዉ ጀመር...
ነገሩ ሁሉ ያላማረዉ አለምነህ ቀረባቸዉ "ምን እየሆነ ነዉ ያለዉ..?" አለምነህ ጠየቀ..
"ምን አገባህ" አለዉ ዘካሪያስ አለምነህን በንቀት አይን ተመለከተዉ..
"ክንዷን ልትለቀዉ ትችላለህ.." አለምነህ በትህትና እያናገረዉ ነዉ..
"ማን ነኝ ነዉ ምትለዉ..መኖር ከፈለክ በማያገባህ አትግባ" ዘካሪያስ ሲናገር ደም ስሮቹ ተገታትረዉ በጉልህ ይታያሉ..
"ተረጋጋ አሁን ልክ አይደለህም..እረፍት አድርግ ሌላ ጊዜ እንደ ትልቅ ሰዉ እናዉራ..አሁን ቲጂን ልቀቃት እያሳመምካት ነዉ ትሂድበት" አለምነህ ዘካሪያስ እንደጠጣ ገብቶታል..
"እኔ ደግሞ ባለቃት ምን ታመጣለህ እያልኩህ ነዉ..ከፈለኩ እንደሷ አይነቱን ሺ መግዛት እችላለሁ..አንተንም ከጎኔ ማሰለፍ እችላለሁ" አለ ዘከሪያስ ቅንድቡን ከፍ ዝቅ እያደረገ...
"አሁን ትለቃታለህ ወይስ አትለቃትም..?" አለምነህ የትእግስቱ ጫፍ ላይ ደርሷል..ዘካሪያስ የተሰመረለትን መስመር አልፏል...
"አለቃትም አልኩህኮ ሰዉዬ..ምን..." አለምነህ አላስጨረሰዉም በአንድ ቦክስ አስፖልቱ ላይ ዘረረዉ...
"እረፉ.. አለምነህ ተዉ እባክህ ችግር ዉስጥ አትግባ...እረ ሰዎች ተጋዳሉ" ትእግስት እየጮኸች ማልቀስ ጀመረች...

ዘካርያስ ድጋሜ ተነሳ ነገር ግን ሌላ ቡጢ ተቀበለዉ...በአከባቢዉ ተቀምጠዉ እያወጉ የነበሩ ተማሪዎች..መሃል ገብተዉ ሊያገላግሏቸዉ ሞከሩ...የተማሪዎች ፕሬዝዳንቱ እና ሌሎችም እንዲሁም የጥበቃ ሰራተኞች ደረሱ።..
የተማሪዎች ፕሬዝዳንቱ አለምነህን በሚገባ ያውቀዋል..አለምነህ ግቢዉ ዉስጥ በጥሩ ስነምግባሩ እና በቀለሜነቱ ነዉ የሚታወቀዉ..ከሁሉም ከሁሉም በግቢዉ ዉስጥ የሚካሄዱ በጎ ስራዎች ላይ አለምነህ በቀዳሚነት የሚሳተፍ ተማሪ ነዉ...ለመልካም ነገሮች ነጭ ላቡን ይሰጣል...ላመነበት ነገር ሁሉ ነገሩን ይሰዋል ህይወቱንም ቢሆን..

አለምነህ ፣ ዘካሪያስ እና ትእግስት የተማሪዎች ፕሬዝዳንት ቢሮ ወንበር ይዘዉ ተቀምጠዋል...
"ምንድነዉ የተፈጠረዉ..ትልልቅ ሰዎች አይደላችሁ እንዴ..ለምን የግቢዉን ሰላም ትረብሹታላችሁ" አለ የተማሪ ፕሬዝዳንቱ በትኩረት እየተመለከታቸዉ...
"አጥፍቻለሁ በጣም ይቅርታ ታሜ" አለ አለምነህ ወደ መሬት እንዳቀረቀረ..(የተማሪዎቹ ፕሬዝዳንቱ ታምራት ይባላል።)
"እሺ ካንቺ ልጀምር እህት..ስምሽን ፣ ዲፓርትመንትሽን ፣ ስንተኛ አመት ነሽ..? የተፈጠረዉን በደንብ ንገሪኝ" አላት ብእሩን ከጠረንጴዛዉ በላይ እያነሳ...
ትእግስት ከመጀመሪያዉ ጀምሮ የሆነዉን ሁሉ በዝርዝር አስረዳችዉ...
"ዘካሪያስ ነዉ መሰለኝ ስምህ ትእግስት እንደነገረችኝ...እሺ የምትለዉ ነገር አለህ" አለዉ ፕሬዝዳንቱ እይታዉን ዘካሪያስ ላይ እያደረገ...
"እንደምታየዉ ተደብድቤያለሁ..ስለዚህ ይሄ ወንበዴ እንዲቀጣልኝ እፈልጋለሁ!!" አለ ዘካሪያስ ድምፁን ከፍ አድርጎ....
"አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንደሆናችሁ ተማሪ ትእግስት ነግራኛለች...እንኳን በሰላም መጣችሁ ልል እወዳለሁ..ግን ህጉ ለሁሉም ነዉ የሚሰራዉ..እዚህ ግቢ ስትኖር የግቢዉን ህጎች ልታከብር ይገባል..ማንንም ማስጨነቅ አትችልም...ትእግስትንም ሆነ የትኛዋንም ሴት ማስገደድ አትችልም..በዛ ላይ መጠጥ ጠጥተህ ነዉ እየረበሽክ ያለኸዉ ይሄ ከፍተኛ የድስፒሊን ቅጣት አለዉ ስለዚህ እባክህ ይቅርብህ ዘኪ...እኔ እዚህ ያለሁት በእናንተዉ ተመርጬ ነዉ...እናንተኑ ላገለግል ድምፅ ልሆናችሁ ነዉ የሾማችሁኝ..በእናንተ ላይ ክፉ ለመሆን አልሞክርም..እኔም ተማሪ ነኝ እናንተ ሚሰማችሁ ስሜት ይሰማኛል መስማማት አለባችሁ ነገሮችን በዉይይት ለመፍታት ሞክሩ።" ፕሬዝዳንቱ ረዘም ካለዉ ንግግሩ በኋላ ትንፋሽ ለመዉሰድ ሞከረና "በሉ እዚህች ጋር እየፈረማችሁ መሄድ ትችላላችሁ" አላቸዉ መዝገቡን ወደነሱ እያዞረ..
"እና ፊቴን እንዲህ አበላሽቶት ምንም አታደርጉትም..?" ሁላችሁም ለዚህ ነገር ትከፍላላችሁ" ዘካሪያስ እየተንዘረዘረ ፈርሞ ወጣ..
ትእግስትና አለምነህም ፊርማቸዉን አስቀምጠዉ ቢሮዉን ለቀዉ ሄዱ...
ትእግስት በዘካሪያስ ዛቻ በጣም ፈርታለች..ፍርሃቷን ግን ንዴቷ አሸንፎት እንደ እብድ እያደረጋት ነዉ...
"ተረጋጊ ቲጂ..አልፏል በቃ" አላት አለምነህ..
"እንዴት ልረጋጋ..በገንዘቡ ብቻ ነዉ የሚያስበዉ..እና እንደ እቃ ሊገዛኝ ፈለገ..ወይኔ ቲጂት ምን መሰልኩት ቆይ"...
"እራስሽን አታስከፊ አንዳንድ ሰዎች እንደዛ ናቸዉ  በቃ" አለምነህ እጇን ያዝ አደረጋት...
ትእግስት ንዴቷ ብን ብሎ ጠፋ..መዳፎቿን ሞቃቸዉ...በመሀላቸዉ ዝምታ ሰፈነ...ሳያስቡት አይኖቻቸዉ ተገጣጥመዋል...አይኖቻቸዉ ዉስጥ አንዳቸዉ አንዳቸዉን የሚፈልጉ ይመስላሉ...
"እእ በቃ ዶርም ልግባ" አለችዉ ትእግስት እየተቅበዘበዘች...አለምነህ እጇን ለቆ አይኖቹን ወደ ሌላ ቦታ በየአቅጣጫዉ ላካቸዉ..ተደነባበረ።
ትእግስት አለምነህን በቆመበት ጥላዉ ጥቂት እንደተራመደች "እህ..እህ" የሚሉ ቅፅበታዊ ድምፆች ተሰሟት...ደንግጣ በፍጥነት ዞረች..አለምነህ መሬት ላይ ወድቋል..ሰዉነቷ በፍርሃት ተንዘፈዘፈ...አንገቷን ጥቂት ቀና አድርጋ ስትመለከት ዘካሪያስ ድንጋይ በእጁ እንደያዘ ቁሟል..."አለምነህ"...አለችና ጮኸች...
"አንተ ማትረባ ምንድነዉ ያደረከዉ" ትእግስት ሩጣ አለምነህ ስር በርከክ አለች...ዘካሪያስ እግር አዉጪኝ ብሎ ከቦታዉ ተፈተለከ..ከአከባቢዉ ተሰወረ..
"አለምነህ ተነስ...ተነስ" እያለች ጭንቅላቱን ጭኖቿ ላይ አስደገፈችዉ...ጭንቅላቱን ስትዳብሰዉ እጆቿ በደም ጨቀዩ "እባካችሁ እርዱኝ..አለምነህ እየሞተ ነዉ" ትእግስት በጣም ጮኸች...
ወዲያዉ በሰዎች ተከበበች..አለሞነህን ተቀብለዋት ግቢዉ ዉስጥ ወደ ሚገኘዉ ክሊኒክ ወሰዱት....ትእግስት መተንፈስ እያቃታት ነዉ..አየር አጠራት..ቆም ብላ በረዥሙ ተነፈሰች..እራሷን ለማረጋጋት ሞከረች..ግን ከአይኖቿ የሚዘንቡትን የእንባ ዘለላዎች ልታስቆማቸዉ አልተቻላትም...ሳግ እየተናነቃት ሰዎቹን ተከተለቻቸዉ...ክሊኒኩ ዉስጥ ያሉት ሀኪሞች የተቀደደዉን ጭንቅላቱን ሰፍተዉ ደሙ ፈሶ ከማለቁ በፊት ታደጉት...ግልኮስ ተከሉለት...በደም ስሮቹ መድሀኒቶችንም ሰጡት።..አለምነህ ደህና ይመስላል..ከሰአታት በኋላ ከምሽቱ 4 : 30 አከባቢአለምነህ አይኑን ገለጠ..ደብዘዝ ብለዉ የሚታዩት ነገሮች ቀስ በቀስ እየጠሩ ነዉ።..የት እንዳለ ለማወቅ ቃኘት ቃኘት አደረገ...በጓደኞቹ ተከቧል ..ከጎኑ ደግሞ ቆንጂዬዋ ትእግስት ወንበር ላይ ተቀምጣ በፈገግታ

11 months, 2 weeks ago

"ተስማምተናል..እሺ አሁን ላዉንች እራት ልጋብዝህ..እንደማስበዉ ከሆነ አልበላህም..እኔም እርቦኛል" ትእግስት ዉስጧ እየቦረቀ ነዉ...
"አዎ አልበላሁም..
​​እሺ እንብላ ባይሆን እኔ ነኝ ጋባዡ ምክንያቱም ቤቴ መጥተሻል እንግዳዬን መንከባከብ አለብኝ" አላት ከተቀመጠበት እየተነሳ...
"እሺ ይሁንልህ" ...
ተያይዘዉ ወደ ተማሪዎች ላዉንች አመሩ...ወንበር አጥተዉ እዛ እዚህ የቆሙ ተማሪዎች...ግድግዳዉን ተደግፈዉ በቁማቸዉ ሻይ የሚጠጡ የቸኮሉ ተማሪዎች...በየቦታዉ ዉር ዉር የሚሉ አስተናጋጆች...ላዉንቹ ዉስጡም ዉጪዉም አፍ እስከ አፉ ጢም ብሎ ሞልቷል... በሰዎች ድብልቅልቁ ወጥቶ ገበያ መስሏል...የዚህን ሰሞን እንዲህ ነዉ...በብዛት ላዉንቹን የሚያጨናንቁት ፍሬሾች ናቸዉ..ፍሬሽ ስትሆን ገንዘብ አለህ...ፍሬሽ ስትሆን መርጠህ ነዉ ምትመገበዉ...ላዉንቹን የሚያዩት ነባር ተማሪዎች "እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አርጎን ነበር" የሚሉ ይመስለኛል...
ገና የዩንቨርስቲ መግቢያ ዉጤት እንደመጣልህ ነዉ በቤተሰብህ..በጎረቤትህ አለፍ ብሎም በሰፈርህ እንክብካቤ የምትጨናነቀዉ...የማይዘጋጅልህ ነገር አይኖርም..ላንተ ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ትባላለህ..ጉዞ የምትጀምርባት ቀን ስትመጣ ሁሉም ላንተ ያሸረግድልሃል..ETVን እያየ ፊቱ ተፈቶ ማያዉቀዉ አባትህ አስበኸዉ የማታዉቀዉን ገንዘብ በእጅህ ያስጨብጥህና "በርታ ልጄ አኩርተኸኛል ከዚህ በላይ አኩራኝ" ይልሃል ፈገግ እያለ...እንዴ ፋዘር ፈገግ አለ በሰርፕራይዙ ተገርመህ ሳታበቃ እናትህ ከአባትህ የደበቀችዉን ገንዘብ ሳያያት ሸጎጥ ታደርግልሃለች....ደስታ ትን ይልሃል....በአንድ ምሽት የቢሊየርነት ስሜት ይሰማህና "የቢልጌትን ልጅ ካላገባሁ ሞቼ እገኛለሁ ትላለህ...ያለዉ ይጨመርለታል አይደል አባባሉ አያቶችህ..አጎቶችህ.. ዘመድ አዝማዱ..ጎረቤቶችህ..ጓደኞችህ መላዉ የሰፈር ሰዉ እንዳለ ግልብጥ ይላል ቤትህ...ሁሉም እንኳን ደስ ያለህ እያለ እንዳቅማቸዉ ሸጎጥ ያረጉልሃል..ብር ታዲያ አንተ ላይ አይደል እየዘነበ ያለዉ..? ነፍስህ ከስጋህ ልትላቀቅ ትደርስና ይሄን ሁሉ ብር ሳላጠፋዉማ የትም አልሄዳትም ብላ ትመለሳለች...
ከመጡት ሰዎች መሃል የማታዉቃቸዉም ይኖራሉኮ ግን ብር እየሰጡህ አይደል ምናገባህ አቅፈህ ትስማቸዋለህ...አዝለኻቸዉ አደባባዮችን ዙር ሁላ ያሰኝሃል...ጉዞ ላይ ምትበላቸዉን ስፔሻል ምግቦች ስታስብ ጨጓራህ መሻፈድ ይጀምራል...ቃሚ ከሆንክ ደሞ ሙሉ ፌስታል ጫት ገዝተህ መኪናዉ ዉስጥ ፌስታሉን ሳይቀር ስትቅመዉ እያሰብክ ምንም የሌለዉ ባዶ አፍህን ታላምጣለህ... በሀሳብ መርቅነህ ሳትጨርስ 10ኛ ክፍል እያለህ ጠይቀሃት እምቢ ያለችህ የክፍላችሁ ቆንጂዬዋ ልጅ ስታሽቃብጥልህ ታያታለህ...ይሄ ነገር እንዴት ነዉ ነገሩ ወደ ሞት ነዉ እንዴ የምሄደዉ ብለህ እንድታስብ ያረጉሃል...የቤታችሁ ግቢ ዉስጥ ያሉት ዛፎች ሳይቀሩ ቅርንጫፎቻቸዉን እያማቱ በደስታ ያሰክሩሃል...ለሊት ጉዞ ልትጀምር ስትነሳ ቤተሰብህ ጓደኞችህ እንባ እየተራጩ ይሸኙሃል...በዚህ ወጣህ በዚህ ገባህ እያለ ያስመረረህን አባትህን እራሱ ጥሎ ለመሄድ አንጀትህ ይንሰፈሰፋል...እጥፍ እጥፍ ይልብሃል...ኩራት ይሰማሃል ...ምን ያህል አስፈላጊ ሰዉ እንደሆንኩ በተግባር አሳየኋቸዉ ትላለህ...ግቢ ስትገባ የካፌ ምግብ ከጉሮሮህ አልወርድ ይልሃል..."ይሄንን ነዉ እንዴ እየበሉ የሚማሩት" ብለህ ምግቡን ጥለህ ትወጣለህ...በገንዘብህ አማርጠህ ያሰኘህን ትመገባለህ..ይሄ ምቾት ግን ብዙ አይዘልቅም....ገንዘብህን በየቦታዉ ስትበትነዉ በሻንጣም ቢሆን ያልቃል። ቢሆንም ምቾትህ ያን ያህል አይቀንስም....አባትህ ወይም እናትህ የሚልኩልህ ገንዘብ የተጋነነ ነዉ...ወጪዎችህን ይሸፍኑልሃል...የመጀመሪያ አመትህን ጨርሰህ ወደ ቤትህ ትመለሳለህ...የእረፍት ጊዜህን ጨርሰህ ወደ ግቢ ልትመለስ ስትል አባትህ እንደመጀመሪያዉ አልቅሶ አይሸኝህም..ክፍሉ ሄደህ ዳድ ስትለዉ..ከአልጋዉ ሳይወርድ"ወገቤን ብርድ እንዳታስመታኝ በሩን ዝጋዉ..በል ሰላም ግባ" ይልሃል..
ያ ሁሉ አሽቃባጭ ሰዉ የለም...የፈረደባት እናትህ ብርዱ ሳይበግራት በለሊት ተነስታ ትሸኝሃለች...ከአይኗ እስክትርቅ ትከተልሃለች...ልቧ መኪናዉ ዉስጥ ከጎንህ ይቀመጣል የትም ሂድ አብሮህ ይጓዛል።...
ትምህርት ተጀምሮ የደመወዝህ ቀን ሲደርስ ገንዘብ ልታወጣ ወደ ባንክ ታመራለህ..የላኩልህ ገንዘብ ግን ተቆርሶ ተቆርሶ አጥሬራ ሆኗል...እንጥልህ መሬት ዱብ ሲል ይታወቅሃል..."ድሮምኮ ህይወት አጭር ናት" እያልክ እየዘፈንክ የግቢዉ ክክ ጋር መጠባጠብ ትጀምራለህ።...?

አለምነህ እና ትእግስት ወረፋዉ ረገብ ብሎላቸዉ ተቀምጠዉ እየተመገቡ ነዉ...አልፎ አልፎ ቢያወሩም ዝምታቸዉ ይረዝማል...ወሬ ከሚያወሩ ይልቅ እየተሰራረቁ መተያየትን መርጠዋል...እራት ተመግበዉ እንደጨረሱ ላዉንቹን ለቀዉ ወጡ...በዝግታ እየተራመዱ ነዉ..."ነገም እንገናኛለና" አለችዉ ትእግስት የቲሸርቷን እጅጌ ለጥጣ የእጆቿን መዳፎች እየሸፈነች...
"ለምን አንገናኝም..እንገናኛለን" አላት ፊቱን ዘወር አድርጎ እያያት..
"እኔንጃ የምጠፋብኝ እየመሰለኝ ነዉኮ"
"ጓደኛ የሆንን መሰለኝ...ስጠፋም አሳዉቅሻለሁ" አላት እየሳቀ..
የሚለያዩበት መንታ መንገድ ጋር ደረሱ..እንደባለፈዉ ጊዜ ዶርማ ሊያስገባት አይቻለዉም ..ወደ ሴቶች ዶርም መሄድ የተከለከለ ነዉ..ያስቀጣዋል።
"ምሽቴን ስላሳመርክልኝ አመሰግናለሁ...ሰላም አምሽ" አለችዉ እየተፍለቀለቀች...
"እኔም አመሰግናለሁ...ሰላም አምሺ" ብሏት ወደ ሌላኛዉ ቅያስ መንገድ ትንሽ እንደተራመደ "ቲጂ" የሚል ቁጡ የወንድ ድምፅ በጆሮዉ ጥልቅ አለ..
አለምነህ ድምፁን ተከትሎ ፊቱን ሲያዞር ከዚህ በፊት አይቶት የማያዉቀዉ ረዘም ያለ ልጅ ወደ ትእግስት በፍጥነት እየገሰገሰ ነዉ...

ይ..................
     ቀ....................
         ጥ....................
             ላ....................
                 ል........................

11 months, 3 weeks ago
"ወዳጅ" የታሪኩ ባባ የመጨረሻ ፊልም ተለቁዋል።

"ወዳጅ" የታሪኩ ባባ የመጨረሻ ፊልም ተለቁዋል።

በአማርኛ ፊልም ቻናላችንን ያገኙታል።

JoiN ?

11 months, 3 weeks ago
GOLD VIP TICKET***?***

GOLD VIP TICKET?
════════════════

⭗ - የዛሬ VIP ትኬት ከአሁን ሰአት ጀምሮ ዝግጁ ነው ?

⭗ 100%  የተረጋገጠ (FIXED) ነው ?
FREE NO PAY AFTER

⭗ ትኬት 100% SURE
⭗ free አገልግሎት ለማግኘት

?  ?? ?

11 months, 3 weeks ago

?
እዚህች ዱንያ ላይ ምኞቴ ልቤ ቀዝቀዝ ብላ ሳትታመምና ሳትጎዳ ለፈጠራት ፈጣሪ ብቻ እንድትመታ ነው ። .......

11 months, 3 weeks ago

በፈፀምከው ወንጀል በዱንያ እንድትቀጣ ከተወሰነብህ ቅጣቱ.......!!

<በጤና መጓደል
<በሀብት መቀነስ
<በቤተሰብ ማጣት
<በጭንቀትና አለመረጋጋት
<በፀብ
:
:
ሊሆን ይችላል።

«ከሁሉም ከባዱ ቅጣት ግን በቀልብ ድርቀትከተቀጣህ ነው።»

اللهم  انا نعوذبك من قلب قاسية

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 months, 2 weeks ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 3 days, 5 hours ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 7 months, 3 weeks ago