Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Minber TV

Description
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ!

#ሚንበር_ቲቪን ለማግኘት

📡 በኢትዮሳት ይከታተሉ:– 👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 30000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

4 days, 21 hours ago

በኢትዮጵያ “የቤተሰብ ቀን” ለሁለተኛ ጊዜ ተከብሮ ዋለ

ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 7 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 7 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

በኢትዮጵያ የቤተሰብ ቀን በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ተከብሮ ዋለ። ቀኑ ለሁለተኛ ጊዜ ሲከበር “መተሳሰብ እንደ ቤተሰብ፣ ለሀገርና ለማኅበረሰብ” በሚል መሪ ቃል ነው።

በዓሉ በተከበረበት መድረክ ላይ የቤተሰብን ሁለገብ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ ለማሳደግ፣ ዕውቅና ለመስጠት እና ሁሉም ቤተሰብ፤ ለቤተሰብ አባላት ምሥጋና እና ክብር የሚሰጥበትን ዕድል ለመፍጠር በማለም መሆኑ ተገልጿል።

ቤተሰብ ትውልድን የመተካት፣ የልጆችን ሰብዕና የመቅረፅ፣ የሀገር ኢኮኖሚን የማሳደግ፣ ለቤተሰብ አባላት ዋስትና የመሆን ትልቅ ሚና ስላለው፣ ቤተሰብ ደኅንነቱ ሊጠበቅ እና ተገቢውን ክብር እንዲሁም ጥበቃ ሊያገኝ እንደሚገባም ክብረ በዓሉ በተሰናዳበት መድረክ አፅንኦት ተሰጥቶበታል።

በዛሬው መድረክ ላይ የተናገሩት በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ሕፃናት ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ ዓለሚቱ ዑመድ፣  ቤተሰብ የራሱን እና የአባላቱን ደኅንነት በመጠበቅ ለጤናማ ሀገር እና ማኅበረሰብ ምሥረታ መተኪያ የሌለው መሆኑን አብራርተዋል።

ሚኒስትር ዲኤታዋ በመልካም ሥነ ልቡና፣ በአካላዊ ጤንነት እና በኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይረጋገጣል ላሉት የቤተሰብ አባላት ደኅንነት መጠበቅ፣ ቤተሰብ እንደ ተቋም ቀዳሚ ድርሻ እንደሚወስድ አስታውሰዋል።

የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የዛሬውን በዓል ባከበረበት ወቅት ሁሉንም ቤተሰብ አባላት ተጠቃሚ ያደርጋል ያለውን ለአንድ ዓመት የሚቆይ ዕቅድ ይፋ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የተከበረው የቤተሰብ ቀን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ ተከብሮ አልፏል።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

4 days, 21 hours ago
Minber TV
5 days, 4 hours ago

ልዩ “ኸበር” - 76 ዓመታት ያስቆጠረው መቅሰፍት

ጣሪቅ አቡ አዙም ከሚገኝበት ጋዛ ለዓለም ይድረስ ብሎ ዛሬ ማለዳ ባሠራጨው ዘገባ፣ እስራኤል በፍልስጤም ንጹሐን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት በአየር እና በመሬት መቀጠሏን ይገልጻል፡፡ ጋዜጠኛው የአልጀዚራ ባልደረባ ነው፡፡ ጣሪቅ በተለይ ባለፉት ሰባት ወራት እስራኤል በንጹሐን ላይ ቦምብ ስታዘንብ እግር በእግር እየተከተለ ሲዘግብ ቆይቷል፡፡ ሕፃናት እና እናቶችን ጨምሮ ንጹሐን ሲረግፉ ዐይቷል፡፡ ውሎ አዳራቸውን፣ ሕልማቸውንም ጭምር የሚያጋሩት ወዳጆቹም በሞት ሲወሰዱ በአቅመ ቢስነት ሸኝቷል፡፡ የእስራኤል ቦምብ የሞያ ባልንጀሮቹንም ነጥቆታል፡፡

ጣሪቅ አቡ አዙም የዕለት ተዕለት ውሏቸውን የሚዘግብላቸው ፍልስጤማዊያን ሰቆቃ የጀመረው እ.አ.አ ከ76 ዓመት በፊት በዛሬው ቀን ሜይ 15/1948 ነበር፡፡ በእስራኤል መሬታቸው በወረራ ተይዞ ጥቃት የሚፈራረቅባቸው ፍልስጤማዊያን፣ ይህን ቀን መቅሰፍት (“ነክበህ”) ብለው ይጠሩታል፡፡ በየዓመቱም ይታሰባል፡፡

በዚህ ወቅት አይሁዳዊያን በፍልስጤማዊያን ላይ ጦርነት ከፍተው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ቀያቸውን ጥለው እንዲሸሹ አድርገዋል፡፡ የቀጠለው ጥቃት የፍልስጤማዊያንን የሰባት ዐስርት ዓመታት ኑሮ ተቆጣጥሮት ሕይወታቸውን በሰቆቃ ሞልቶታል፡፡

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ፍልስጤማዊያን በመሬታቸው ላይ ለመንቀሳቀስ ጭምር ፍቃድ ሰጪው ሌላ ሆኗል፡፡ እስራኤል በተለይ ከ1995 ወዲህ በወረራ የያዘችውን ዌስት ባንክን በሦስት ሸንሽና በ700 ሺሕ ሠፋሪዎች ሞልታ ፍልስጤማዊያን በአንድ አካባቢ እንዲወሰኑ አድርጋለች፡፡ በዌስት ባንክ እስራኤል የራሷን ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ስታሠፍር ከዐስር ሺሕ በላይ የፍልስጤማዊያን ግንባታዎችን አውድማ ነው፡፡

መሬታቸው ባዕድ የተወረረባቸው ፍልስጤማዊያን፣ ወደ ሥራ ሊሄዱ ሲሉ የይለፍ ፍቃድ ለማግኘት በማለዳ መሰለፋቸውም የዕለት ውሏቸው አካል ከሆነ ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ እስራኤል የፍልስጤማዊያኑ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ጥላ ሥማቸው በሥራ ፈትነት ከዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ ሆኗል፡፡

እስራኤል የፍልስጤማዊያኑን ሰቆቃ የምታበረታው የንግድ እንቅስቃሴንም በማፈን ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ፍልስጤም ከአጎራባች ዐረብ ሀገራት ጋር የንግድ ግንኙነቷ ተቆርጧል፡፡ የወጪ እና ገቢ ንግዷም በእስራኤል በኩል እንዲያልፍ ጉልበተኛ ተሹሞበታል፡፡

እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ የጣለችው ገደብ ወደ ቴክኖሎጂም የሚሻገር ነው፡፡ እስራኤል ለራሷ 5ጂ ኔትወርክ ስትጠቀም፣ ፍልስጤማዊኑ በ3ጂ ኔትወርክ እንዲወሰኑ ተደርገዋል፡፡ እስራኤል በገደብ የምትለቀውን ኔትወርክ ፍልስጤማዊያኑን ለመሰለል ጥቅም ላይ የምታውለው ነው፡፡ ፍልስጤማዊን የኔትወርክ ብቻ ሳይሆን የውሃ እና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ላይ ገደብ ተጥሎባቸዋል፡፡

ለ76 ዓመታት በወረራ በያዘችው መሬት ላይ የተሾመችው እስራኤል፣ ከጥቅምት 2024 ወዲህ በንጹሐን ላይ የምትሰነዝረውን ሰብዓዊነት የጎደለው ጥቃት በመጠን አስፋፍታ ቢያንስ 35 ሺሕ ሰዎችን ገድላለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺሕ የሚሆኑት ሕፃናት ናቸው፡፡ ፍልስጤማዊያኑ መቅሰፍት ሲሉ የሚጠሩትን የዛሬውን ቀን ሲያስቡ፣ በዓመታት ሰቆቃ ውስጥ ከአጠገባቸው የተለዩዋቸውን እያስታወሱ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
(ይህ ጥንቅር በዋነኝነት የተወሰደው ከአልጀዚራ ነው፡፡)

2 months ago
إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ …

إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُونَ 
እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡
(አል-ፉሲለት፤ 30)

#መወሰኛይቱ
ኑን የቁርኣን መድረክ 10
እሁድ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ል
በሚሊኒየም አዳራሸ

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

2 months ago
Minber TV
2 months ago
Minber TV
2 months, 1 week ago
እንኳን ለተከበረውና ለተወደደው የ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ …

እንኳን ለተከበረውና ለተወደደው የ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ ረመዳን ነገ ሰኞ መጋቢት 2/2016 መሆኑ አሁን ማምሻውን ተረጋግጧል።
ረመዷን ሙባረክ!!

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

2 months, 1 week ago
እንኳን ለተከበረውና ለተወደደው የ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ …

እንኳን ለተከበረውና ለተወደደው የ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ ረመዳን ነገ ሰኞ መጋቢት 2/2016 መሆኑ አሁን ማምሻውን ተረጋግጧል።
ረመዷን ሙባረክ!!

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

2 months, 1 week ago

"አንድ ደቂቃን ለባቡል ኸይር " የሚል ጥሪ ቀረበ

የካቲት 30/2016
ሻዕባን 28/1445
ሚንበር ቲቪ

አንድ ደቂቃን ለባቡል ኸይር በሚል መርኃ ግብር ኢትዮ ቴሌኮም ልዩ የረመዳን ስጦታ ማዘጋጀቱ ተገለጸ።
ትናንት በባቡልኸይር  ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆኑ በሰጡት የሁለትዮሽ መግለጫ ከመጋቢት 1 እስከ 30  "መጋቢትን ለባቡል ኸይር" በሚል መርኅ ኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊነቱን የመወጣት ዘመቻ እንደሚያከናውን ገልጸዋል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል።

ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ፍቃድ ካገኘበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት አምስት ዓመታት በተለያየ ዘርፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል ። በሴቶች ብቻ የተመሰረተው ይህ ድርጅት በተለይም ዜጎች ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ጤናማ የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ለማስቻል ከ126 ቤተሰቦች በመነሳት በአሁኑ ሰዓት በቀን ሁለት ጊዜ ከ4000 በላይ ለሚሆኑ ቤተሰቦች የምግብ ዋስትና እና የጤና መድህን አረጋግጧል።

ኢትዮ ቴሌኮም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጡ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሰው ተኮር ተግባር ላይ ለተሰማሩ ተቋማትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ በማድረግ ከህዳር 1 ጀምሮ ለ8 ማህበራት አንድ አንድ ወር በመስጠት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ሲገኝ በዚህም ለረመዳን ልዩ ስጦታ ለባቡል ኸይር ለግሷል።
መጋቢት ወርን ለባቡል ኸይር " በማለት የሰየመ ሲሆን በዚህም መሠረት ከመጋቢት 1 ቀን እስከ መጋቢት 30/2016 የኢትዮ ቴሌኮም የሶሻል ሚዲያ አማራጮችን ማለትም ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም ፣ ቲክ ቶክ ፡ ዩቱብ ፣ ዋትሳፕ ፣ ሊንክዲን ፣ እና ቴሌ ብር እንዲሁም ቴሌግራም ገጾቻቸውን ከመጋቢት 1 ቀን እስከ መጋቢት 30 ቀን የኢትዮ ቴሌኮም ሁሉንም ገጾች ጆይን፣ ሰብስክራይብ ሲያደርጉ በአንድ አዲስ ተከታይ በእያንዳንዱ አንድ ሰው 30 ብር  ኢትዮ ቴሌኮም ለባቡል ኸይር የሚለግስ ይሆናል።

በተመሳሳይ አንድ ሼር፣ ኮፒ ሊንክ ሲያደርጉም በተጨማሪም 10 ብር ለባቡል ኸይር ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል ።  እንደሚታወቀው ባቡል ኸይር ዓለም ባንክ ቤተል አካባቢ ያለውን 5000ካሬ ሜትር ቦታ ሙሉ በሙሉ ግንባታውን እውን ለማድረግ  ያስችለን ዘንድ
ከኢትዮ ቴሌኮም ታላቅ የሆነን እድል ተበርክቷልና፣ የኢትዮ ቴሌኮም ገፅችን ይወዳጁ ባቡል ኸይርን ይደግፉ በማለት የባቡል ኸይር ስራ አስኪያጅ ሀናን መህሙድ በባቡል ኸይር ስም መልእክት አስተላልፈዋል።

እርስዎም አንድ ደቂቃን ለባቡል ኸይር በመለገስ ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉንም የ ኢትዮ ቴሌኮም ገጾች እንዲወዳጁ እና ባቡል ኸይርን እንዲያግዙ በአረጋዊያን እናቶችና አባቶች ስም ጥሪ ቀርቧል።

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

2 months, 2 weeks ago
ዓለም አቀፍ እውቅና ያተረፉት ተወዳጁ ሱዳናዊ …

ዓለም አቀፍ እውቅና ያተረፉት ተወዳጁ ሱዳናዊ ቃሪዕ ሸይኽ አል-ዘይን ሙሐመድን ጨምሮ ሀገራችን ያፈራቻቸው መሻይኽ፣ ዱዓት፣ ቃሪኦች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ሌሎችም በሚገኙበት፤ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ል በግዙፉ ሚሊኒየም አዳራሽ ተወዳጁና ተናፋቂው ኑን የቁርኣን መድረክ 10ኛ መሠናዶውን በድምቀት ያከናውናል።
.
በኑን የቁርኣን ጥናትና ምርምር ማዕከል እና በ3ኢ ኤቨንትስ ትብብር የተዘጋጀ!
የሚዲያ አጋር፤ ሚንበር ቲቪ
.
ኑን የቁርኣን መድረክ
ልቅና በቁርኣን!

★★★★★
ሚንበር ቲቪን በኢትዮሳት በተሻለ የምስል
ጥራት ለመከታተል👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 45000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago