ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️
Last updated 4 months, 3 weeks ago
Last updated 1 month ago
Last updated 6 months ago
አንቀፅ 21(15) መሰረት ስለሆነ በህግ አግባብ ነው በማለት የመልስ ሰጭን ውሳኔ አፅንቶ መዝገቡን ዘግቷል ፡፡
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147/3/ሀ-ሐ/ እና አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 21/16 አንጻር አመልካች ተሽከርካሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የጦር ማሳሪያ ጭኖ የተገኘው በመኪናው ላይ በተገጠመ ባእድ/ሻግ/ ውስጥ ተደብቆ ባለመሆኑ እና የተሽከርካሪው ባለቤት ስለተጫነው ህገወጥ መሳሪያ ባላወቀበት ሁኔታ ወይም በድርጊቱ ተሳታፊ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ለመንግስት ውርስ ሊሆን ይገባል በማለት የተሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ጉዳዮች አጣሪ አካል እና የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የሰጡትን ውሳኔን በአብላጫ ድምጽ ሽሮታል፡፡ በልዩነት የባለንብረቱ እውቀት መኖር አለመኖር እና ድርጊቱን ሊያስቆም ይችል የነበረ ስለመሆን አለመሆኑ በቅድሚያ ተጣርቶ ንብረቱ ሊወረስ የሚገባ ስለመሆን አለመሆኑ ሊወሰን ይገባ ነበር በሚል የልዩነት ውሳኔ ተሰጥቷል ፡፡
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ህግ አዋጅ ቁጥር 1177/2012 እንጂ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አይደለም፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያጓጉዝ የተገኘው ተሽከርካሪ የደረቅ ጭነት እንጂ የህዝብ ማመላለሻ ባለመሆኑ የአዋጅ አንቀጽ 21/16/ መሰረት የሚታይበት አግባብ የለም፣ በአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 22/12/ ስር የወንጀል ቁጥር 481 የተመለከተው በወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል የተከለከለ ድርጊት ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ለማገናዘብና ለመመልከት እንጂ የግድ የተሽከርካሪው ባለቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ካልተሰጠ ወይም ጥፋተኛ ካልተባለ የአዋጅ 1177/2012 አንቀጽ 22/12/፣21/15 ተፈጻሚነት የለውም ወደሚል ድምዳሜ ላይ ስለማያደርስ የባለንብረቱ ማወቅ እንደ መስፈርት የተደነገገ አይደለም በማለት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔን በመሻር የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል ፡፡
አመልካች የካቲት 02 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ መነሻነት የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል በማለት መዝገቡን መርምሮ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነ ተሽከርካሪ የተከለከለ የጦር መሳሪያ የሆኑትን 05 ክላሽ፣ 01 ብሬል፣ 05 ክላሽ ካርታ፣ 1107 የብሬል ጥይት እና 5444 የክላሽ ጥይት ሲያጓጉዝ በተጠሪ የተያዘ እና የውርስ ውሳኔ የተላለፈ ቢሆንም አመልካች የድርጊቱን መፈጸም አላውቅም፣ የወንጀል ድርጊቱም ተሳታፊ አይደለሁም በአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23/3/ ላይ የተመለከተውን የሚያሟላ በመሆኑ ሊወረስ አይገባም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን በመግለፅ የጦር መሣሪያውን ያጓጓዘው ተሽከርካሪ እንዲወረስ ለመወሰን በአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 21(15) እና (16) ድንጋጌ መነሻነት በተሽከርካሪ ላይ የጦር መሳሪያ የመጫን ድርጊት ሲፈፀም የባለንብረት ዕውቅና የሚጠየቀው ተሽከርካሪው ህዝብ የተሳፈረበት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሆኖ በአንቀፅ 21(16) ላይ ሲያርፍ ብቻ በመሆኑ እና የአመልካች ተሽከርካሪ በዚህ ሁኔታ ላይ የማይወድቅ ስለሆነ የውርስ ውሳኔው መተላለፉ በአግባቡ ነው በማለት በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 226018 በቀን 30/03/2015 ዓ.ም እና በፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በቀን 04/06/2014ዓ.ም በመ/ቁ B-1334/13 የተሰጠውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል ፡፡
ማስታወሻ
ከላይ በፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ተጀምሮ እስከ ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመጨረሻውን ውሳኔ ያገኘው ይህ ክርክር የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የሚወስናቸው ውሳኔዎች ህግና መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ ፍትህን ፍለጋ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በመሆኑም ኮሚሽኑ የሚወስናቸው ውሳኔዎች ነፃና ገለልተኛ መሆናቸውን ከሚያመላክቱ መዛግብቶች መካከል ይህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
#Federal Tax Appeall Commission
የችሎት ውሎ
ለፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በመዝገብ ቁጥር B-1334 ፣ ለፌዴራል ከ/ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 280598 ፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 226018 እና ለፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 241787 በአቶ ሙሉሰው ተስፋሁን እና በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት መካከል የተደረገውን ክርክርና የተሰጠውን ውሳኔ የጦር መሳርያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 ዓ.ም ላይ የባለቤት ዕውቅናን በሚመለከት የሚሰጠውን የህግ ትርጉም አንባቢያን ትምህርት እንዲያገኙበት እንደሚከተለው አቅርበናል ፡፡
መልካም ንባብ !
ማስታወሻ
ለደህንነት ሲባል የይግባኝ ባይን ስም አቶ ሙሉሰው ተስፋሁን በማለት እና የምስክሮችን ስም በሌላ ስሞች የቀየርናቸው መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
በኮሚሽኑ መዝገብ ቁጥር- B-1334 በቀረበው ክርክር ይ/ባይ ሙሉሰው ተስፋሁን የጉምሩክ ጉዳዮች አቤቱታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት በሰጠው የተሽከርካሪ ውርስ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ያቀረበው ይግባኝ ሲሆን ለዚህ ውሳኔ መነሻ የሆነው ንብረትነቱ የይ/ባይ የሆነው የታርጋ ቁጥር ኮድ 3-A17255 አ.አ የሆነው ተሽከርካሪ በህግ የተከለከለ የጦር መሳሪያ 05 ክላሽ፣01 ብሬል፣05 ክላሽ ካርታ፣107 የብሬል ጥይት እና 5444 የክላሽ ጥይት ሲያጓጉዝ ተገኝቷል በሚል የአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 21(15) መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ይ/ባይ ስለ ወንጀል ድርጊቱ መፈፀም አላውቅም፣ በወንጀሉ ድርጊትም ተሳታፊ አይደለሁም፡፡ ይሁንና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአመልካች ተሽከርካሪ ሊወረስ ይገባል የተባለው በአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 22 ንዑስ አንቀፅ 3 ላይ የተጠቀሰው ሳይሟላ በመሆኑ የይ/ባይን ተሽከርካሪ ለመውረስ የአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 12 ተፈፃሚነት የሌለው ስለሆነ ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የይ/ባይ ተሽከርካሪ ይወረስ በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት የለውም፡፡ አቤቱታ አጣሪ የይ/ባይ ተሽከርካሪ የተወረሰው በአዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 21/15 መሰረት ስለሆነ የተሽከርካሪው መወረስ በህግ አግባብ ነው ብሎ የይ/ባይን አቤቱታ ውድቅ ያድርግ እንጂ በተሽከርካሪው ላይ ህገ-ወጥ መሳሪያዎች ተጭኖ የተገኘ መሆኑ ይ/ባይ ባይክድም ስለመሳሪያዎቹ መጫን ይ/ባይ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ከአዋጁ አንቀፅ 22(12) ንባብ መረዳት የሚቻለው አንድ ተሽከርካሪ የሚወረሰው በወንጀል ህጉ አንቀፅ 481 ላይ የተመለከተው እና በዚህ አዋጅ አንቀፅ 22 ንዑስ አንቀፅ 3 የተመለከተ ተግባር በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ነው፡፡ ሆኖም አሁን በተያዘው ጉዳይ የአዋጁ አንቀፅ 22(3) አልተሟላም፡፡ እንዲሁም ቅርንጫፉ የወረሰው አንቀፅ 22 በመጥቀስ ሲሆን ይህም ያለአግባብ ነው፡፡ የይ/ባይ ተሽከርካሪ ሊወረስ ይገባል ወይስ አይገባም በሚለው ላይ ውሳኔ መስጠት ሲገባው ይ/ባይ ቅሬታ ያቀረብኩበትን የህግ ድንጋጌ ተገቢነት ላይ በዝምታ በማለፍ ተሽከርካሪው የተወረሰው በአዋጅ ቁጥር 1177/12 አንቀፅ 21/15 ድንጋጌ መሰረት ነው ማለቱ የይ/ባይን ቅሬታ ከግምት ያላስገባና የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓትን የተከተለ አይደለም፡፡ አንቀፅ 21 ስለተቆጣጣሪ ተቋም ስልጣንና ተግባር እንጂ ስለወንጀል ተጠያቂነት ባለመሆኑ በተሽከርካሪው ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በአንቀፅ 22 ነው እንጂ በአንቀፅ 21 አይደለም፡፡ በመሆኑም የይ/ባይ ተሽከርካሪ ውርስ የሆነው ከህግ አግባብ ውጪ ነው በማለት ተከራክሯል ፡፡
በሌላ በኩል መ/ሰጭ በሰጠው ምላሽ የይ/ባይ ተሽከርካሪ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘቱ ያልተካደ ጉዳይ ሲሆን የፌዴራል የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/12 አንቀፅ 22 ንዑስ አንቀፅ 2 እና 3 የፀና ፈቃድ ሳይኖር ብዛት ያለውን የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ማስገባትን፣ ከሀገር ማስወጣት ማጓጓዝ ድርጊቱ የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል የተከለከለ ድርጊት ስለመሆኑ የሚደነግግ የህግ አንቀጽ ሲሆን የዚሁ አንቀፅ 481 ላይ የተመለከተው ተግባር የተፈፀመው ተሽከርካሪ በመጠቀም ከሆነ ለዚሁ ተግባር መፈፀሚያነት የዋለው ተሽከርካሪ ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን በማያሻማ ሁኔታ ግልፅ አድርጎ ስላስቀመጠ፤ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ጭነት ማጓጓዣ አማካኝነት ክልከላውን ፈፅሞ ስለተገኘ በዚሁ ህግ መሰረት ውርስ መደረጉ ተገቢ ነው፡፡ እንዲሁም የአዋጅ አንቀፅ 22/12 ሆነ 21/15 ህገወጥ ተግባሩ መፈፀሙን በቅድመ ሁኔታነት ከማስቀመጥ ውጪ የባለቤቱን ዕውቅና በተመለከተ ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ የለም ፡፡
ስለሆነም ብዛት ያላቸውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ በተሽከርካሪው አማካኝነት የተጓጓዘ መሆኑን ተረጋግጦና ይ/ባይም አምነው ተከራክረው እያለ የአዋጅ አንቀፅ 22/3 አልተሟላም ማለታቸው የድንጋጌውን ይዞታ ካለማወቅ የቀረበ ክርክር ስለሆነ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም በማለት የፅሁፍ ምላሽ ሰጥቶ ግራ ቀኙን ሐምሌ 16/2013 በችሎት ተገኝተው የቃል ክርክር ያደረጉ ሲሆን በፅሁፍ ላይ ያቀረቡትን ክርክር አጠናክረው አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ይ/ባይ ጉዳዩን የሚያስረዱ ሁለት ምስክሮች አለኝ በማለት ሁለቱም ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል የመጀመሪያው ምስክር አቶ ማስረሻ ሲሆን ይ/ባይ ተሽከርካሪውን የሚያሰራው ሹፌር ቀጥሮ መሆኑን እና ለሹፌሩ ጥር 20/2013 ቁልፍ ሲሰጥ እንዳየ መስክሯል፡፡ ሁለተኛው ምስክርም አቶ ይርገጤ ሲሆን አውጋቸው ለሚባል ሹፌር ቁልፍ ሲሰጥ እንዳየ እና ህገወጥ ስራ እንዳይሰራበት ሲነግረው ስለመስማቱ ለችሎት አስረድቷል ፡፡
ኮሚሽኑም ሁለቱ ወገኖች ያቀረቡትን የፅሁፍ እና የቃል ክርክር እንዲሁም ማስረጃ መርምሮ “የይ/ባይ ተሽከርካሪ ላይ የውርስ ውሳኔ መተላለፉ በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም” የሚለውን ጭብጥ በመለየት አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡
የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/12 አንቀፅ 21/15 በግልፅ እንደሚያስቀምጠው ተሽከርካሪው ህገወጥ የጦር መሳሪያ ጭኖ የተገኘ እንደሆነ ተሽከርካሪው ውርስ እንደሚደረግ በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ ይህ አንቀፅ ከአንቀፅ 21/16 በተለየ መልኩ ተሽከርካሪው ላይ ሻግ ኖረ አልኖረ፤ ባለቤቱ ያውቃል/አያውቅም የሚለውን ቅድመ ሁኔታ መሟላቱን እንዲረጋገጥ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡ በመሆኑም ይ/ባይ ተሽከርካሪው ላይ ህገወጥ የጦር መሳሪያ የተጫነው በእሳቸው ቁጥጥር ውጪ እና በማያውቁበት ሁኔታ ስለመሆኑ ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ምስክሮች ህጉ በቅድመ ሁኔታነት ያላስቀመጠው ስለሆነ ኮሚሽኑ አልተቀበለውም፡፡ እንዲሁም የጉምሩክ ጉዳዮች አቤቱታ አጣሪ ዳይሬክቶሬት ውሳኔ የሰጠበት አንቀፅ 21/15 ሲሆን ይህም ተሽከርካሪን ለመውረስ አግባብነት ያለው ድንጋጌ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ድንጋጌ መሰረት ዋናው ቅድመ ሁኔታ የሆነው ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ በማዘዋወር ድርጊት በተሽከርካሪው አማካኝነት የተፈፀመ በመሆኑ ይግባኝ ባይ የአዋጁ አንቀፅ 22(3) አልተሟላም በማለት የሚያቀርበውን ክርክር ኮሚሽኑ አልተቀበለውም ፡፡ ስለሆነም የይ/ባይ ተሽከርካሪ ኮድ 3-A17255 አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ህገወጥ የጦር መሳሪያ የተገኘ ስለሆነ የውርስ ውሳኔ መተላለፉ በጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/12
በአይነቱ ልዩ የሆነው ይህ የህግ ሶፍትዌር ይዞት ከመጣቸው መፍትሔዎች አንዱ በኢትዮጵያውያንም በጎርጎሮሳዊያን የዘመን አቆጣጠር የተዘጋጀ ዲጂታል ካሌንደር መያዙ ነው ይህም ተጠቃሚዎች በቀላሉ በስልካቸው አሊያም በኮምፒውተራቸው ቀጠሮአቸውን መመዝገብና መከታተል ያስችላቸዋል
ፈር ቀዳጅ የሁነውን ይህን ዲጅታል የሕግ ላይብራሪና ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ለሁሉም የሕግ ባለሙያዎች ፣ ለሕግ ተማሪዎች ፣ ለነጋዴዎችና ለቢዝነስ ተቋማት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
www.ethiopianlegaltech.com በሚለው አዲሱ አድራሻ መግባትና መመዝገብ ትችላላችሁ
#share #lawyer #legalsupport #legaladvice
#ethiopianlaw #legalcounsel #legalhelp
#ህግ #የህግምክር #የኢትዮጵያ
553-2016 የአንድነት ፓርኮች ኮርፖሬሽንን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️
Last updated 4 months, 3 weeks ago
Last updated 1 month ago
Last updated 6 months ago