Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

The Jubair || The ጁበይር

Description
ሀሳብ አስተያየታቹን በ @thejubair ያድርሱኝ

ይህ የ The Jubair official የቴሌግራም ገፅ ነው

በቻናላችን አጫጫር ዳዕዋዎችን | ፈጣን መረጃዎችን |
አጫጭር የቁረዐን አያቶችን| እንዲሁም ሌሎች እጅግ
አስተማሪ ነገሮችን በአላህ ፍቃድ ያገኛሉ .
ይህን ሁሉ ቻናላችንን Join በማድረግ ብቻ ሀያ ቢስሚላህ 😊

ሹክረን ;)
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 month, 1 week ago

እንኳን ለ1445ኛው ዓ.ሒ የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ !

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

1 month, 1 week ago
ሰበር ዜና

ሰበር ዜና
አላሁ አክበር አካሁ አክበር
አንድ ቀን አለን
ኢድ አል-ፊጥር ረቡዕ እንደሆነ ተረጋግጧል!

እንኳን አደረሰን !
እንኳን አደረሳቹ

1445/2024 የኢድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ፣ ኤፕሪል 10 ቀን 2024 ነው።

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

1 month, 1 week ago

እንኳን 1445 ዓ.ሂ.የዒደ-ል-ፊጥር በአል እርሶንም ቤተሰቦንም በሰለም አደረሶ …

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

የምንባባልበት ቀን ሩቅ አይደለም ኢንሻአላህ !

ግን አጥብቄ ላስታውሳቹ ምወደው ነገር ቢኖር አሁንም ረመዳን ነውና መጨረሻውን እናሳምር ! ስራ በመጨረሻው ነው ሚወሰደውና ! ስለዚህ በኢስቲግፋር በሰለዋት ቁርዐን በመቅራት እንበራታ አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን.

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

1 month, 1 week ago
የሸዋልን ጨረቃ ለመመልከት በዝግጅት ላይ !

የሸዋልን ጨረቃ ለመመልከት በዝግጅት ላይ !

ሆኖም እንደ አብዛኛው የዘርፉ ባለሙያዎች ቅድመ ግምት መሰረት የዘንድሮ ወርሃ ረመዳን 30 እንደሚሞላና ዒድ እሮብ ላይ እንሚውል ያሳያል. አላህ በሰላም ያድርሰን.

ምንጭ : Haramain Info

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

1 month, 1 week ago

አህባቢ ዛሬ ከመቼውም በላይ በዱዐ እንተዋወስ ! ለፍልስጤማዉያን ወንድሞቻችን በይበልጥ በደምብ እናድርግ.

ያው እኔ ወንድማቹንም በዱዐቹ አትርሱኝ ባረከላሁ ፊኩም !

1 month, 1 week ago

አጭር ማስታወሻ ስለ ዱዓእ
~
ዱዓእ ተቀባይነት ያገኛሉ ተብለው በሚታሰቡ በላጭ ሰዓቶች ላይ ከፍ ላሉ ጉዳዮች ትኩረት እንስጥ።
አላህ ቀልባችንን እንዲያስተካክልልንና ዲን ላይ እንዲያፀናን። የነብዩ ﷺ ዱዓእ በብዛት እንዲህ የሚል ነበር፦
يا مُقلِّبَ القلوبِ ثبِّت قلبي على دينِكَ
በየትኛውም ዲናዊ ጉዳይ ለተሻለው እንዲመራን። ነብዩ ﷺ የሌሊት ሶላታቸውን በዚህ ዱዓእ ነበር የሚከፍቱት
اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ، وَمِيكَائِيلَ، وإسْرَافِيلَ، فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالأرْضِ، عَالِمَ الغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، أَنْتَ تَحْكُمُ بيْنَ عِبَادِكَ فِيما كَانُوا فيه يَخْتَلِفُونَ، اهْدِنِي لِما اخْتُلِفَ فيه مِنَ الحَقِّ بإذْنِكَ؛ إنَّكَ تَهْدِي مَن تَشَاءُ إلى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ.
ወንጀላችንን ምሮ ከእሳት እንዲጠብቀን፣ ጀነትን እንዲያድለን:- የሙስሊም ትልቁ ሃሳብ ጭንቀቱ ይሄ ነው መሆን ያለበት።
اللَّهمَّ إنِّي أسألُك الجنَّةَ وأعوذُ بِك منَ النَّارِ 
የአላህን ይቅርታ ለማግኘት መትጋት። እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ለነብዩ ﷺ ለይለተል ቀድር መሆኑን ካሰብኩ ምን ልበል ስትላቸው የጠቆሟት ዱዓእ ይሄ ነበር፦
اللَّهمَّ إنَّكَ عفوٌّ، تُحِبُّ العفوَ فاعفُ عنِّي.
ለዚክር፣ ለምስጋና፣ ላማረ የዒባዳ አፈፃፀም እንዲወፍቀን
اللهمَّ أعني على ذكرِك وشكرِكَ وحسنِ عبادتِكَ
ለወገኖቻችንም እንዲሁ የጠመሙትን እንዲያቀናልን፣ የሞቱትን እንዲምርልን፣ ለወላጆቻችን እንዲያዝንላቸው፣ በሃገራችን፣ በፊለስጢን፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በሌሎችም ቦታዎች መከራ ላይ ያሉትን ከፈተና እንዲያወጣልን፣ ሰላም እንዲሰጠን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።
* ባጠቃላይ በዱንያም በኣኺራም መልካሙን እንዲያድለን ጠቅላይ ጠቅላይ ዱዓኦችን መምረጥ መልካም ነው። ነብዩ ﷺ ያዘወትሯቸው ከነበሩ ዱዓኦች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር፦
اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا في الدُّنْيَا حَسَنَةً، وفي الآخِرَةِ حَسَنَةً، وقِنَا عَذَابَ النَّارِ.

©️ IbnuMunewor

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

1 month, 3 weeks ago

نورٌ ما بين الجُمعتين
اسم السورة :الكهف

🔴   ጁምዐችንን ሱረቱል ከህፍ በመቅራት
        እና ሰለዋት በማብዛት እናድምቀው🤍

وَأَمَّا الْجِدَارُ فَكَانَ لِغُلَامَيْنِ يَتِيمَيْنِ فِي الْمَدِينَةِ وَكَانَ تَحْتَهُ كَنزٌ لَّهُمَا وَكَانَ أَبُوهُمَا صَالِحًا فَأَرَادَ رَبُّكَ أَن يَبْلُغَا أَشُدَّهُمَا وَيَسْتَخْرِجَا كَنزَهُمَا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۚ وَمَا فَعَلْتُهُ عَنْ أَمْرِي ۚ ذَٰلِكَ تَأْوِيلُ مَا لَمْ تَسْطِع عَّلَيْهِ صَبْرًا

«ግድግዳውማ በከተማይቱ ውስጥ የነበሩ የሁለት የቲሞች ወጣቶች ነበር፡፡ በሥሩም ለእነርሱ የኾነ (የተቀበረ) ድልብ ነበረ፡፡ አባታቸውም መልካም ሰው ነበር፡፡ ጌታህም ለአካለ መጠን እንዲደርሱና ከጌታህ ችሮታ ድልባቸውን እንዲያወጡ ፈቀደ፡፡ በፈቃዴም አልሠራሁትም፡፡ ይህ በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻልከው ነገር ፍች ነው» (አለው)፡፡

[ሱረቱል ከህፍ : 82]

•●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_254

•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ጁምዐ 🤍

🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

1 month, 3 weeks ago

🔖 ‏إذا دبَّ إليك الكسل في هذا الشهر الفضيل فالزم: (لا حول ولا قوة الا بالله ).

• قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله-:

ولتكن هجيراه: (لا حول ولا قوة إلا بالله)، فإنه بها يحمل الأثقال، ويكابد الأهوال، وينال بها رفيع الأحوال.

• وقال ابن القيم -رحمه الله-:

هذه الكلمة (لا حول ولا قوة إلا بالله)  لها تأثير عجيب في معالجة الأشغال الصعبة، وتحمُّل المشاق، والدخول على الملوك، ومن يُخاف، وركوب الأهوال، ولها أيضا تأثير في دفع الفقر.

1 month, 3 weeks ago

'ሙስቴ አወወ እንዴት ነህ ? ሰይድ እባላለሁ። ሙስቴ ዓሊሞች'ና መሻይኮቹ ስለጎዳና ኢፍጥር የተናገሩት ነገር በሙሉ ልክ ነው ... አንተም ከእነሱ ጎን ሆነህ ሙስሊሙ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው የምትጥረውን ነገር ወድጄዋለሁ። ለዛ ነው ላወራህ የመጣሁት...

ሙስቴ ሃቂቃ የጎዳና ኢፍጥሩ በሙስሊሙ ላይ የመጣ ፈተና ነው። .... ዛሬ ባፍርበትም የዛሬ 3 ዓመት እኔና 5 ጓደኞቼ ሊያውም በረመዳኑ 'እስኪ አሪፍ አሪፍ ቺኮች ካሉ ዕድላችንን እንሞክር..' ብለን ነበር የጎዳና ኢፍጥሩ ወደ ተዘጋጀበት መስቀል አደባባይ የሄድነው። .... የዛኔ ከሄድነው 6 ሰዎች ሁሉቱ ጓደኞቻችን ደግሞ የሌላ እምነት ተከታዮች ነበሩ።
አሁን ሳስበው እፀፀታለሁ። የዛኔ አላህ ስላልፈቀደው ምንም ሳይፈጠር እኛም ሆን ክርስቲያን ጓደኞቻችን ከሴቶቹ ስልክ ብቻ ተቀባብለን ወደ ሰፈራችን ተመለስን .... አስበነው የሄድነው ቢፈፀም ግን አስበህዋል ? ... በሰዓቱ እስከ ምሽቱ 4 እና 5 ሰዓት የቆዩ ሴቶች ሁላ ነበሩ። በኋላ በሰካራሞች ምናምን እየተለከፉ'ና እየተጎነተሉ ነበር። አሁን እኔ አግብቻለሁ። እነዛ ስልካቸውን የተቀበልናቸው ሴቶች ግን ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር ምን ውስጥ ይግቡ ... ምን ያድርጉ የማውቀው ነገር የለም ?
አሁን ድረስ ያስጨንቀኛል....

ብቻ ይሄ ነገር ሌላ በላዓ ሳያመጣብን ቢቆም ጥሩ ነው ... እናንተንም አላህ ያግዛችሁ....'

ከላይ ያለው አንድ ወንድሜ በውስጥ የላከልኝ መልዕክት ነው። የዚህ የጎዳና ኢፍጥር አዘጋጆች ምናልባት ምን እያመጣችሁብን እንደሆነ ከተረዳችሁት በሚል ልጁን አስፈቅጄው አምጥቼው ነው የለጠፍኩት 🥲🥲

ምንጭ : ከፌስቡክ መንደር

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

1 month, 3 weeks ago

ፆምና ህመም
~
ህመምተኞች ከፆም አንፃር ለ4 ይከፈላሉ።

1ኛ፦ በህመሙ ምክንያት በቋሚነት መፆም የማይችል ሰው
ህመሙ ይድናል ተብሎ ተስፋ የማይጣልበት ቋሚ ህመም ያለበት ሰው ልክ መፆም እንደማይችል ትልክ ሽማግሌ ሲሆን በኢጅማዕ ማፍጠር ይችላል። የፆም ግዴታ የለበትም። አላህ እንዲህ ብሏል
(لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَاَ)
"አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡" [አልበቀረህ፡ 286]

ሚስኪን የማብላት ግዴታም የለበትም። ግዴታ እንደሆነ የሚያሳይ የቁርኣንም፣ የሐዲሥም፣ የኢጅማዕም አስገዳጅ ማስረጃ የለምና። ኢብኑ ሐዝምና ኢብኑ ዐብዲልበር ይህንን አበክረው ይናገራሉ።
ባይሆን ለእያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን ቢያበላ የተወደደ ነው። ከተለያዩ ሶሐቦች ተገኝቷልና። በዚያ ላይ ከሶሐቦች ጀምሮ የብዙ ዑለማኦች ምርጫ ነው። ይሄ ለሚችል ሰው ነው። ያልቻለ ምንም የለበትም።
* የምግቡ አይነት እቤቱ ከሚመገበው መካከለኛ ደረጃ ያለው ነው።

2ኛ፦ ህመም ቢኖርበትም መፆም የሚችል ነገር ግን በመፆሙ ህመሙ የሚባባስበት የሆነ ሰው
ለዚህ አይነቱ ማፍጠር ግዴታው ነው። አላህ እንዲህ ብሏል:-
(وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةَِ)
"በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡" [አልበቀራ: 195]

★ ባይሆን ሲሻለው ቀዷእ ያወጣል (በምትኩ ይፆማል።) አላህ እንዲህ ብሏል:-
{فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِیضًا أَوۡ عَلَىٰ سَفَرࣲ فَعِدَّةࣱ مِّنۡ أَیَّامٍ أُخَرَۚ}
"ከእናንተም ውሰጥ ህመምተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መፆም አለበት።" [አልበቀረህ: 184]

3ኛ፦ መፆም የሚችል፣ መፆሙ የሚያስከትልበት ጉዳት ባይኖርም ነገር ግን በህመሙ ምክንያት ፆም የሚከብደው ሰው
እንዲህ አይነቱ ማፍጠር ለሱ ግዴታም ባይሆን በላጭ ነው። ኋላ ግን ቀዷእ ያወጣል።

4ኛ:- ቀላል ህመም ያለበት ወይም ፆም ልዩነት የማይፈጥርበት ህመም ያለበት ሰው
ህመሙ በፆም የሚባባስ አይነት ካልሆነ (ለምሳሌ የጥርስ፣ የአይን፣ … ህመም አይነት) ወይም መፆም ምንም ተፅእኖ የማያሳድርበት ቀላል የህመም አይነት ከሆነ ሊያፈጥር አይፈቅድለትም። ለማፍጠር በቂ ምክንያት መኖር አለበት።

ማሳሰቢያ: –
* ህመምተኛ ህመሙን ችሎ ቢፆም ፆሙ በኢጅማዕ ይቆጠርለታል።
والله أعلم

©️ IbnuMunewor

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago