የብዕር ቀለሞች

Description
በዚህ ቻናል
👉 ግጥሞች
👉 አጭር ልቦለዶች
👉 አስቂኝና አስገራሚ ወጎች
👉 ድርሰቶች
👉 join በሉት ይደሰቱበታል

@amharic_poet join በሉት ይደሰቱበታል more connection
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 month ago

[ ማህሙድ ጋ ጠብቂኝ ]

ወጣት ሆኜ ሳለሁ
ችዬ ባላስነሳ የለውጡን አብዮት
ራሴን ላጠፋ ስትመረኝ ህይወት
እያሰብኩ እያለ
ስብሀት ከፃፈው
ትኩሳት መፅሀፍ ያ ምክር ትዝ አለኝ
ከውሳኔህ በፊት ፒያሳ ሂድ ያለኝ ።

ያኮረፍኳት ፍቅሬን አራዳ ቀጠርኳት
ገና ሳንገናኝ
ማህሙድ ጋ ስትመጣ በሀሳቤ ሳልኳት
ኖቬት የተገዛ ነጭ ቀሚስ ለብሳ
የካራቢያኑን
ጥቁር ጫማ አድርጋ  ትመጣለች እሷ
እኔማ ቀጥሬያት አትቀርም ፒያሳ

በሀኪም ቦራ አሳንሰር እየተንሸራተትኩ
ጴጥሮስን ጠምዝዤ ቁልቁል እንደወረድኩ
በፓስታ ቤት በኩል
ሀሳቦቼን ፅፌ ሳልክልሽ ብቀር
የትም አትጠብቂኝ
የትም አልቀጥርሽም ከማህሙድ ጋ በቀር

እስክትመጪ ድረስ ከቸርቸል ጎዳና ዱካሽን ስቆጥረው
ከማህሙድ ፊት ለፊት ወደ ወርቅ ቤቱ አካሌን ወሰደው
በሀሳብ ፈዝዤ
አይኖቼን አንስቼ ከወርቅ ቤቶቹ ጀርባ ብጥላቸው
ከዶሮ ማነቂያ ቅያስ ገብተዋሉ ከስጋው ላይ ናቸው

ስጋና ስጋትን
ሀዘንና ሀሴትን
በአንድ ላይ የየያዘች
በፍቅር ደግነት ሰዎችን ያነቀች
የፒያሳ እምብርት ተዐምረኛ መንደር ትጠብቀናለች

ሸግዬ ቶሎ ነይ
ከፒያሳ እግር ስር
ማኪያቶ እየጠጣን ተቀምጠን ቼንትሮ
አንቺን ደስ ካለሽ
የሆድ እያወጋን ጁሱን በ'ስትሮ
መጠን ስንጨርስ በኢንተር ላንጋኖ
ከንፈሬ ከንፈርሽ በአንድ ላይ ሆኖ
ሰዓት ስለሚሄድ
ገብተን መኮንን ባር
ከሰፈሩ ካበው ከሰፈሩ አድባር
ትንሽ አመሻሽተን
ከሰንሻይን ሻምፓኝ ካንቺ ባልራጭም
ጣይቱ ሆቴል ብናድር ዘበት አልቆጭም

ባ'ዲስባ መሐል ባ'ዲስባ ሰማይ
አልተቃጠርንም ወይ ፒያሳ አደባባይ

ትንሽ ብታረፍጂ ከአራት ኪሎ በኩል ከመጣች ኮበሌ
ወዝ ወዝ......  ወዝ ወዝ  ከሚል ሽንጥና ባት ዳሌ
ተመለከትኩ እንጂ አልዘሞተም አይኔ
ይህን የታዘብኩት
አንቺን ማህሙድ ጋ ስጠብቅ ነው እኔ

የህፃኑ ብዛት 'ሚጫወተው በአፈር
እንቅልፍ አይተኙም ወይ ሠራተኛ ሰፈር
እንዳትገረሚ ንግግሬ በዝቶ ፈላስፋ ብመስል
ብታረፍጂ ጊዜ ገብቼ ይሆናል ብሪትሽ ካውንስል

ፈዘዝ ያለን ሁሉ
ኑሮ አድክሞት ጫንቃው
ዲሞክራሲ አይደለም
የኔና አንቺን አካል ቡና ነው ሚያነቃው
ከቡናም ቡና አለ
የደስታ ጠረፉን ጣራ የሚለካ
ነይ እንሂድ ማንኪራ አትቅሪ ቶሞካ
እንድታስታውሺው እንዳትረሺው ሁሌ
ማህሙድ ወረድ ብለን
ኩርት ያለ ምሳ ልጋብዝሽ ካስቴሌ

ውዴ
አትደርሺም እንዴ ፍቅር ቆየሽ እኮ
ጣፋጭ ኬክ እንብላ ገብተን ኤንሪኮ
አንድ እንጨምርለት ወሬ ለሚያበዛ
ወይ ፒዛ ኮርነር ከናፈቀሽ ፒዛ
ይሻላል እንደዛ

ለካ አንቺ ቫቅላባ ትወጃለሽ በጣም
ወረፋ ልጠብቅ
ናፍቀው የጠበቁት ሁሌም ቶሎ አይመጣም

ማህሙድ ጋ ብትቆዪ ወዲያ ተሻግሬ
አይኔን ከስክሪኑ ጆሮዬን ከዳላስ ሰቅዤ ሰካሁት
አንቺሆዬ ባቲ አምባሰል ትዝታ ቅኝቱን ሰማሁት
በመጠብቅ ብዛት አልቀልጥም እንደ ሰም
ጊዜውም ለጋ ነው
አምፒር ለሲኒማው ሰዓቱ አልደረሰም

ግድየለም አርፍጂ

በእርግጥ ስትመጪ
ማህሙድን ከቦታው ፈልገሽ ብታጪው
ከእርምጃሽ ቆመሽ መንገድሽን አትቋጪው
ምናልባት ስትመጪ
አራዳ ብቻውን ቆሞ ብታገኚው
ፊት ለፊቱ አልቅሰሽ ቅር እንዳታሰኚው

ፒያሳ እንደ ተረት አይቀርም ደብዝዞ
ከመሬት ቢፈርስም
ልባችን ውስጥ አለ እልፍ ቦታ ይዞ

ብቻ ግን የኔ ዓለም
ማህሙድ ጋ ቀጠሮ     እንዳለን እንዳትረሺ
በልባችን ጉያ ፒያሳ አለች ዛሬም
ትዝታችን አለ ቀዬው ፈርሷል ብለሽ እንዳትመለሺ

[ በረከት_#ውዱ ]

@amharic_poet
@amharic_poet
@amharic_poet

1 month ago
የብዕር ቀለሞች
1 month, 3 weeks ago

መዳን ትፈልጋለህ
"""""""" """"""""""""""

ለብዙ ዘመናት አይኖቼ ተጋርደው ስኖር በጭለማ
የዓለም መድሀኒት በአጠገቤ በኩል ማለፉን ብሰማ
የናዝሪቱ እየሱስ ብዬ ተጣራሁኝ
ከበውኝ የቆሙት አይሰማም እያሉኝ

የናዝሪቱ እየሱስ
ደግሜ ጠራሁት አይኖቼ ባያዩ
ጆሮዎቼ ሰሙት መምጣቱንም ለዩ
የከበበውን ሰው መንገድ አስከፍቶ
ወደ እኔ ተጠጋ ተማፅኖዬን ሰምቶ

አይሰማህም ብለው
የናቁኝን ሁሉ መጥቶ አሳፈራቸው
አልጠሩትም እና እያየም አይናቸው
ወደ እኔ ተጠጋ
የጠራሁት ጌታ ዘመናት ጠብቄው
ሳይፈውሰኝ በፊት
" መዳን ትሻለህ ወይ ? " ነበረ ጥያቄው

ስለ ምን ጠራሁት መዳንን ብጠማ
ብርሀን እንዲሆን የዋጠኝ ጨለማ
አዎ አልኩት ጌታዬን መዳን ነው ምኞቴ
ብርሀን እንዲሆን ጨለማው ህይወቴ

ስለ ምን ጠየቀኝ

የጠሩት በሙሉ
የጮሁ በሙሉ ወደ አምላካቸው
ለመዳን አይደለም
አለሁ ለማለት ነው ሚሰማው ድምፃቸው
በአንደበት ብቻ ልብን ሳይፈተሹ
መዳንን ያይደለ መታየት የሚሹ
አለሁ ባዮች ሆነን ጠርተን የምንለግም
ፍላጎታችንን ሳይጠይቀን በፊት ታ'ምር አያደርግም

እሺታዬን ሰምቶ
ፍላጎቴን አይቶ በእጆቹ ዳበሰኝ
ድነሀል እይ አለኝ ማየት ቻልኩ ፈወሰኝ
ከሚሰሙት ሁሉ
ከከቡት ሁሉ ፍላጎት ያለውን ለመዳን ከልቡ
ያድናል ፈጣሪ ልጆቹን መጠበቅ ነውና ሀሳቡ ።

በረከት_#ውዱ

@amharic_poet
@amharic_poet
@amharic_poet

2 months, 1 week ago

ጠብቄሽ ነበረ!

መንፈሴን አንጽቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ፤

ብትቀሪ ጊዜ፣
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ

ብትቀሪ ጊዜ፣
የጣልኩብሽ ተሥፋ
እኔን ይዞ ጠፋ።

ደበበ ሰይፉ

@amharic_poet
@amharic_poet
@amharic_poet

2 months, 1 week ago

ሴት ሆይ
"""""""""""

ገና ዓለም ሳይፈጠር የዓዳም መኖር ሳይታሰብ
አሁን ያለው ሳይኖር በፊት ፍጡር ሳይሰበሰብ
አምላክ በህሊናው አስቦ ያኖረሽ
የአዳም ግራ ጎን ሄዋን እንደምን ነሽ

ባዶነቱን አይቶ
ሰው ብቻውን ቢሆን መልካም ስላልሆነ
ከአዳም ጋ አብረሽ........ተፈጥረሽ ነበረ
ስጋሽም ከስጋው
አጥንትሽ ከአጥንቱ.......አንድ በመሆኑ
ሴት ብሎ ሰየመሽ.........አዳም በልሳኑ

ሴት ሆይ እንደምን ነሽ
አዳም ሁሉ ሞልቶት      ምድርን ቢገዛ
መጉደልሽ አጉድሎት       ሀዘኑ ቢበዛ
ከባድ እንቅልፍ ወስዶት ብትኖሪ ሲነቃ
ደስታው እጥፍ ሆነ     ለሙሉነት በቃ

" ሄዋን " አላት አምላክ     የህያዋን እናት
" እንስት " አለ አዳም ከውስጡ ሲያገኛት
የአምላክ ጥበቡ
ሚስትና እናትን አርጎ ባንድ ስጋ
ባንድ አካል መፍጠሩ
ተዐምር ነው ሲመሽ   ድንቅ ነው ሲነጋ

ሄዋን ሆይ እንዴት ነሽ
አዳም በለስ በልቶ  መቼ ሞትን ጠራ
እንደውም እንደውም
ሰላሳ እና ስልሳ መቶ ፍሬ   አፈራ
እንዳሸዋ በዛ  ምድርን ሁሉ ሞላ
የብቸኝነቱ ሀዘን ተሽቀንጥሮ ተተካ በተድላ

ሄዋን ሆይ እንዴት ነሽ
የባለቤቷ ዘውድ የንግስናው ሚዛን
ውብ እናትነትሽ
ንፁህ ሚስትነትሽ ልባችንን ገዛን
ሴት ሆይ እንደምነሽ
ለአዳም መኖሩ ምክንያት አንቺ ነሽ ።

በረከት_#ውዱ

#መልካም የሴቶች ቀን

@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet

2 months, 2 weeks ago

ዋ! አድዋ
(አድዋ በሎሬት ጸጋዬ)

«አድዋ ሩቋ፣ የአድማስ ምሰሶ አለት ጥጓ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳሷ:
አድዋ! በአንቺ ብቻ ህልውና፣
በትዝታሽ ብጽእና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ! አድዋ!
የዘር አጽመ ርስቷ:
የደም ትበያ መቀነቷ
የኩሩ ትውልድ ቅርሷ
የኢትዮጵያዊነት ምስክሯ
አድዋ!
ከሞት የባርነት ስርዓት
በደም ለነጻነት ስለት
አበው የተሰውልሽ ዕለት
አድዋ !
የኩሩ ድል በአንቺ ጽዋ
ታድላ በመዘንበሏ
አጽምሽ በትንሳኤ ነፋስ
ደምሽ በነጻነት ህዋስ ሲቀሰቀስ
ትንሳኤዋ ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ ብርu፣ትር ሲል ጥሪዋ
ድው እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ ዋ!
አድዋ!…»

@amharic_poet
@amharic_poet
@amharic_poet

3 months ago

ይህ ግጥም ማስታወሻነቱ
አፍቅረው ለሚንገላቱ
በኩራዝ ባልነጋ ለሊት በጭለማ ውስጥ እያለሁ
የፍቅርን ትርጉም ሳላውቀው ከልቤ አፍቅሬሻለሁ
ከጀምበር እኩል ወጥቼ ደጅሽን ተሳልምያለሁ

ሰላም ለኪ
በእይታ አንበርካኪ
በጥላዋ ሰው የምትጥል
በጥርሷ እድሜ ምትቀጥል

አንቺን አየሁኝ

አስተፍረላ
ተውበት ያሰጠኝ ይሆን ማየቴ ያንቺን ውብ ገላ
ግን እኮ አልተመኘሁሽ ከማፍቀር ውጪ በሌላ
.......ያረቢ..........ጀሊሉ ድንቅ ጠቢቡ
ከምድር አፈር አንስቶ እንደ እንቁ አንቺን ማስዋቡ

አጃኢብ

እኔማ ውሉን ሳላቀው ስሜቱ ሳይገባኝ በልክ
አይኖቼን ወደ አይንሽ ብልክ
ዓለምን ጠባ አየኋት
ቱ...........ታዘብኳት

ላንድ አንቺ አንሳ
ተማሪ ልቤ ያየው አበሳ

አዲስ ሆኖበት ፍቅር የሚሉት ቅኔ ሲፈታ
ከናፍቆት ጋራ  ታግዬ ስዝል ጅስሜ ሲረታ
ከደረስሽበት አይኔ ሲቃርም መውጫ መግቢያሽን
ሳትታገይኝ ምርኮ ይዘሽኝ ፈተሽ ትጥቅሽን

ይህ ሁሉ ሲሆን
ምንም ሳትውቂ ብትሸልምሽ ድል
እንዴት አትጠበኝ እንዴት አትጎድል

ይህ ግጥም ማስታወሻነቱ
አፍቅረው ለሚንገላቱ

ላንድ ቀን መልኬን ሳታይው ልክ እንደ ጥላሽ አልፌ
ማፍቅሬን ተቀበይ የሚል ላኩልሽ ደብዳቤ ፅፌ
ሊያውም በሶስተኛ ሰው   እራሴ መቅረብ ፈርቼ
አንድ ቀን ቆረጥኩኝና   ለራሴ ብዬ    እስከመቼ
ደፍሬ ልነግርሽ መጣሁ ከልቤ አንቺን ማፍቀሬን
አካሌ ተርበተበተ   ምላሴ ያዘልሽ   ፍሬን

ከዛማ ምንም ሳልነግርሽ የበጋው ወራት አለቀ
ክረምቱ መጣ ሊለየን የፍቅር ጀምበር ጠለቀ
ግን ደሞ ተስፋ አልቆረጥኩም
ቤትሽን አፈላልጌ መንደርሽ መዋል ጀመርኩኝ
ከናፍቆት ቅጣት ወጥቼ 'ያይኔን ጥያቄ መለስኩኝ

አሁንም አልነገርኩሽም
ሰመመን ውሉ በረታ ከልቤ ጠለቀ ፍቅርሽ
መንፈሴ ሲያስጨንቀኝ ከቤቴ ወጣሁ ልነግርሽ
በርታልኝ እያልኩት ልቤን ብነግርሽ የልቤን ማፍቀር
በተናገርሽኝ አንድ ቃል ያ ፍቅር ከመሬት ቢቀር

አልከፋኝ
መልስሽ ምን ቢገፋኝ
ሳልነግርሽ ብቀደም አፈቀርኩሽ ብዬ
ባይገጥም ነው እያልኩ እጣሽ ከእጣዬ
እድሌን ስረግም ልረሳሽ ስሞክር ቢከብደኝም ያኔ
አሁን ግን እንዳልስት ሳፈቅር እንድናገር ሆኖልኛል ወኔ

እናም

ይህ ግጥም  

ማስታወሻነቱ
አፍቅረው ለሚንገላቱ
ፍቅረኛ ላልያዙ እስካሁን
መፈቀር ላላደላቸው እንደኔ ለሆኑት ይሁን ።

በረከት_#ውዱ

@amharic_poet
@amharic_poet
@amharic_poet

3 months, 1 week ago

ረብ ያጣንላቸው እንዲው የተረሱ
የኛ ቀን ያልነውን ዛሬን የሚከሱ
ትናንቶች አሉብን
ዛሬ ያሉ ቀደምት እሉፋን ትዝታ
የባለፉት ሀሴተ ጩኸት የአሁን ዝምታ
ሄዱ ብለን ከዛሬ ጋር ስንግባባ
ህልሞች አሉን ትዝታዎች ያዘልናቸው በአንቀልባ

ትናንት የሚያስቁን
ዛሬ ያስለቀሱን
ቀኖች አ ሉ ን...
ze.....fasi13

3 months, 2 weeks ago

'ለምን አልፈጠርክም.. ?'

(ኤፍሬም ስዩም)

ሳይደምን ሳይዘንብ ሳይጨልም ሳይነጋ ፤
ምድርና አርያምን ቀድሞ ሳትዘረጋ ፤
ፊተኛው ኋለኛው አልፋና ኦሜጋ ፤
እንዴት ነበር ኑሮህ ስፍራህስ ምኑጋ ?
ምንት ሳይኖር በፊት ኢምንት እያለ ፤
ያሁኑ ዙፋንህ ኪሩቤል ከሌለ ፤
ያኔ ያንተ ሀገር ከየት ነበር ያለ ?
ሀገርህ እንዳልል ያኔ ሀገር የለም ፤
ምንም ሳይኖር በፊት ስትኖር በምንም ፤
በእግዚአብሔርነትህ እግዜር ከሌለብህ ፤
ሁሉንም አዋቂ አንተ ብቻ ከሆንህ ፤
ስንት ዘመን ሆነህ ሆነህ ከተገኘህ ?
ፍጥረትስ ነበረ ከመፍጠርህ በፊት ?
ቀድመው የተሰሩ ከሰው ከመላዕክት ?
ካልነበረም ፍጥረት ፤
የዘመናት አምላክ የዘመናት ንጉስ ጥያቄዬን መልስ ፤
ለምን አልፈጠርክም እስክትፈጥር ድረስ ?
.

( ፍልስፍና እዚጋ ጋር አበቃ !)

@rasnflega

5 months, 1 week ago

https://t.me/beki_book

Telegram

beki_book

የስነ ፅሁፍ ስራዎች ውድ አንባብያን ! > ልቦለድ > ወግ > መጣጥፍ #በረከት\_ዘውዱ @Beki\_book

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago