The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 3 days, 16 hours ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 3 weeks, 3 days ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 8 months, 3 weeks ago
እወዳለሁ ብትይ
እወዳለሁ ብትይ
ወንዳወንድ ጀግና
አንበሳን ከጫካ ልፋለም ሄድኩና
ፈልጌ አጣሁት
እወዳለሁ ብትይ ሞትን የማይፈራ
ከረዥሙ ፎቅ ላይ ቆምኩና ከጣራ
እያሰብኩ እያለ ዘልዬ ልወርድ
ብርክ ብርክ ቢለኝ መላ አካሌ ቢርድ
ተመልሼ ተውኩት
እወዳለሁ ብትይ ጎበዝ ዋናተኛ
በህንድ ውቅያኖስ ላይ ጀርባዬ ሲተኛ
ላሳይሽ ነበረ መንገዱ ባይርቀኝ
አንቺ የምትወጂው
እኔ የምችለው ምን ይሆን ጨነቀኝ
እወዳለሁ ብትይ ኮሜዲ ቀልደኛ
የማስታውሰውን ቀልድ ተናግሬ
መርዶ እንደሰማ ሰው አልቅሰሻል ፍቅሬ
እወዳለሁ ብትይ
ድምፁ በጣም ሚያምር የሚያንጎራጉር ሰው
ልዘፍንልሽ ብዬ
መረን አልባው ድምፄ ታምቡርሽን ቢቀደው
ዘፈን እርሜን ብለሽ አቁመሻል አሉ
ልቤስ ምን አጠፋ
አንቺ ምትወጂውን መሆን ነው አመሉ
እወዳለሁ ብትይ ጎበዝ ኳስ ተጫዋች
ኳሷ ስታመልጠኝ ከአንግሉ ጋር ስጋጭ
ኳስም አስጠልቶሽ መደገፍ ትተሻል
ግን አሁንም ቢሆን
ምትወጂውን ሳልሆን ለኔ መች ይመሻል ።
እንባ ይታገለኛል
አልቅስ ይለኛል ልቤ
ግን ደሞ አላልቅስም አልኩ
ጠንካራ እንደሆንኩ አስቤ
አይነካውም ጉንጬን የእንባዬ ዘለላ
በል ናልኝ ደስታዬ ሀዘን ወዲያ ክላ
ብዬ እየገፋሁት ስታገል ስታገል
ችግሬን በመሸሽ መስሎኝ ምገላገል
ስሜቴን ሳደምጥ እውነታውን ትቼ
ልክ ነው በምለው
በስህተት ጎዳና ብዙ ተራምጄ
መሀል ላይ መቆሜን ሳስተውል ነቅቼ
አነባሁ
ባደመጥኩት ልቤን
ስሜት በጎዳናው ሊመራኝ ሲታትር
ትምክህቴን ብከፍለው በእንባዬ በትር
ተመኘው
ለካስ ከእንባ ነው እውን ሳቅ ሚገኘው
ለምን
ልብ ያወቀዋልና የስሜትን ጣጣ
ቀድሞ ከዛስ ይላል ውጤቱ ሳይመጣ
አሁንም አነባሁ ሳገኘው መንገዴን
ማልቀስ አላቆምኩም በጄ ይዤው ገዴን
አዎን ልብ እንዲህ ነው
በእንባ ይናገራል የመጪውን ነገር
እውነትና ጊዜ ስለገፉት ብቻ ስለማይበገር
አይነጋም
""""""""'""
ይነጋል እንዳትይ ተስፋ ልታሳጪኝ
አይነጋም ብያለሁ ተይ አታበሳጭኝ
አይነጋም በፀሀይ አይነጋም በብርሀን
ምንም እንዳይገባ በእኔና አንቺ መሀል
አኩኩሉም ቢሆን
የመሸም ቀን ቢሆን
መንጋት የለበትም ከልቤ አይነጋም ስል
ከዕቅፍሽ ርቄ ብርሀን የለውም የሚታየኝ ምስል
`ገል እና አበባ
"""""""""
[ በረከት_ዘውዱ ]
ለዘመናት ያህል ሳይኖረው ሰባራ
ብዙ ሰው ያበላ ብዙ ወጥ የሰራ
የገል ድስት ነበረ
በቆይታ ብዛት ድንገት ተሰበረ
ከስብራት ወዲያ
ማገልገል ቢሳነው ልክ እንደ በፊቱ
ከውጪ ተጣለ ደጃፍ ሆነ ቤቱ
ከዳጃፍ እንዳለ
ይተክዝ ነበረ አልጠቅምም እያለ
አላወቀምና
ከላዩ የሚኖር አበባ እንዳለ
የሰባራውን ገል ሀዘን ያስተዋለ
የሚያምረው አበባ እንዲህ ተናገረ
" እባክህ ሸክላ ሆይ
አበቃልኝ ብለህ አትዘን ለአፍታ
መኖሪያ ሳይኖረኝ የማርፍበት ቦታ
ካንተ ተጠግቼ
መኖር ጀምሬያለሁ ህይወትን ድጋሚ
አይደለሁም አትበል ለኔ'ስ ነህ ጠቃሚ "
እያለ ነገረው
ይህን እንደሰማ ገል እንባ አበሰ
ደስታው ተመለሰ
ከመሰበር ወዲያ መጥቀም በመቻሉ
የአንድ ውብ አበባ መኖሪያ መሆኑ
ዳግም ተስፋ ሰጠው ከሀዘኑ ተፅናና
በሰባራው በኩል
ድጋሚ ታየችው ዓለም ሙሉ ሆና
እንዲህ ነው አንዳንዴ
አበቃልን ብለን
ተሰበ'ርን ብለን ተስፋ ባጣን ጊዜ
ዙሪያችን ሲከበብ በሀዘን ትካዜ
የህይወትን ትርጉም ፈልገን ስናጣ
ተሰብረህም ቢሆን
አኑረኸኛል ሚል ምስክር ሲመጣ
ይገርማል ይደንቃል
ለካ'ስ
ለመኖር ያነሰ ለማኖር ይበቃል`@amharic_poet
@amharic_poet
@amharic_poet
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻2017🌻መልካም🌻አዲስ አመት🌻
🌻🌻🌻
መልካም🌻አዲስዓ መት
መልካም🌻 አ🌻ዲ🌻ስ
መልካም 🌻 ዓ🌻መ🌻ት
ለወዳጄ 🌻 ዓ🌻መ🌻ት
🌻🌻🌻🌻 አ🌻ዲ🌻ስ
ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ
አ🌻ዲ🌻ስ
ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ
ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ
ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ
ዓ🌻መ🌻ት 🌻🌻🌻🌻
🌻መ🌻ል 🌻ካ🌻ም🌻🌻🌻🌻
🌻አ🌻ዲ🌻ስ🌻ዓ🌻መ🌻ት 🌻
🌻 🌻 🌻
🌻መል🌻🌻🌻ካም🌻
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት
🌻መ🌻ል🌻ካ🌻ም🌻
🌻 🌻 🌻
🌻🌻አዲስ
🌻🌻🌻አመት
🌻🌻መ🌻ልካም
🌻🌻አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
አዲስ🌻ዓመት
🌻መልካም 🌻 አዲስዓመት
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
አዲስዓመት🌻ለወዳጄ🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌺 ይ🌻ህ🌻🌻አ🌻መ🌻ት🌻🌼
የ🌻ሰ🌻ላ🌻ም🌻🌻አመት🌻🌷
የ🌻ፍ🌻ቅ🌻ር 🌻🌻አመት🌻🌷
የ🌻ሞገስ 🌻
የ🌻ክብር 🌻
የ🌻ሹመት🌻
የ🌻ታላቅነት🌻
🌻ዓመት 🌼
🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻🌷🌹🥀
🌻ይ🥀ሁ🌹ን🌷ላ🌼ች🌹ሁ 🌾
🌻🥀 🌼 🥀🌹🌺 🌷
🌻የበረከት 🌻
🌻የሹመት 🌻
🌻የምርቃት 🌻
🌻የመግዛት 🌻
🌻የከፍታ 🌷🌻
🌻ዓመት 🌷🌻
🌻 ይሁን 🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌼🌼🌼
🇪🇹ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት 🙏 🕊🌻🌻
🌻🌻🌻 ያሰብነው የሚሳካበት 🌻🌻
🌻🌻🌻 🌻🌻
🌻የካሳ🌻የሰላም🌻የጤና🌻የበረከት🌻🌻
🌻🌹🌾ዓመት 💐🌷ይሁንልን።🌻🕊🌻🌻
እግረ መንገድ
`አንድ ሰውዬ በጣም ትልቅ አዋቂ ከሆኑ ሰው ምክር ፍለጋ ይሄዳል
እንዳገኛቸውም "ምክር ፈልጌ ነበረ አላቸው "
አዋቂውም ምክር መስጠት የዘወትር ስራቸው ነበርና
" ስለ ምን ? " ሲሉ ጠየቁት
ሰውየው በእሺታቸው እየተደሰተ
" በህይወቴ ምንም ነገር መያዝ አልቻልኩም ምንም የኔ የምለው ነገር የለም " አላቸው
አዋቂውም " ከምክሬ በፊት አንድ ማድረግ ያለብህ ነገር አለ ምታደርገውም ነገር ሁለት ህጎች አሉት ብለው " ነገሩት
ሰውየም የሚያዙትን በደስታ እንደሚፈፅም ነገራቸው
አዎቂውም " ትዕዛዙ ይኸው ነው ከዚህ ከሚታየው የበቆሎ ማሳ ውስጥ የፋፋውን ወይም ትልቁን በቆሎ ታመጣለህ ፣
ማሳው ሶስት ክፍሎች አሉት ከመጀመሪያው ክፍል አልፈህ ከሄድክ መመለስ አትችልም ሁለተኛው ደግሞ ባዶ እጅህን ከማሳው መውጣት አትችልም " አሉት
ሰውዬውም በመጀመሪያው ማሳ ትልልቅ በቆሎውችን አገኘ ነገር ግን ሌላኛው ማሳ ውስጥ ከዚህ የተሻለ ሊኖር ይችላል ብሎ በማሰብ የመጀመሪያውን የማሳ ቦታ አልፎ ሄደ ፣ በቀጣዩም ክፍል መካከለኛ በቆሎውችን አገኘ አሁንም ወደ ፊት የተሻለ ሊኖር ይችላል ብሎ በማሰብ ሁለተኛውንም ክፍል አልፎ ሄደ ፣ በሶስተኛው ክፍል ግን እንጭጭ ወይም ትንንሽ በቆሎዎችን ብቻ አገኘ
ወደ ኋላ እንዳይመለስ አንደኛው ህግ ወደ ኋላ እንዲመለስ አይፈቅድም ባዶ እጁን ከማሳው እንዳይወጣ ሁለተኛው ህግ ባዶ እጅ ከማሳው መውጣትን አይፈቅድም ስለዚህ እንጭጩን በቆሎ ይዞ ከማሳው ወጣ
አዋቂውም " ከመጀመሪያው ማሳ ትልልቅ በቆሎዎች ነበሩ ፣ ከሁለተኛውም ማሳ መሀከለኛ በቆሎዎች ነበሩ ለምን ከነሱ አላመጣህም ? " ብለው ጠየቁት
ሰውየውም " ከነሱ የበለጠ የተሻለ አገኝ ይሆናል ብዬ ነው ሁለቱንም ማሳዎች አልፌ የሄድኩት በህጉ መሠረት ባዶ እጅ መመለስ ስለማይቻል ነው ይህን እንጭጭ በቆሎ ይዤ የመጣሁት " አላቸው`
አዋቂውም " ልጄ በህይወትህ የተሻለ ነገር እስክታገኝ አሁን ያለህን ጠበቅ አድርገህ ያዝ ብልህ የያዘውን ይዞ ያለቅሳል " አሉት ።
ምንጭ ከበራሪ ታሪኮች
እኔ በቆሎ
"""""" """""""
ከውስጡ ጠጉር ከላዩ ልስልስ
በነኩት ቀጥር
ወደ ብዙነት የሚፈራርስ
ማንነት አለኝ እንደ በቆሎ
በአንድ አካሌ
ዕልፍ ማንነት በውስጤ በቅሎ
ተጫዋች ሲሉኝ የማልናገር
ጀግና ነው ሲሉኝ የምደናበር
አማኝ ነው ሲሉኝ የማውደለድል
ደካማ ሲሉኝ የምነሳ ድል
ጠጉር ገላዬን ሸፍኖት ጨርቄ
ከታች ነው ሲሉኝ መሬት ርቄ
ከላይ ነው ሲሉኝ ከስር ወድቄ
እየተምታታ ሀጥያት ከፅድቄ
አብሮ የሚወርድ እንባና ሳቄ
እኔ በቆሎ
ዕልፍ ማንነት በውስጤ በቅሎ
ለነፍሴ መብል ቢያለብሰኝ ስጋ
ነፍሴን በላሁት ምንም ሳልሰጋ ።
ብቻ ስትስቅ ልያት
""'''''''' """""""" """""""
የደስታዋ ምክንያት ለመሆን ስሞክር
ጭንቀቷ ላይ ቆሜ እምቢኝ ስል ልፎክር
ዱካኳን ገርፌ ልሰደው እርቃኑን
ሀዘኗን ደብድቤ ላሳጣው እርባኑን
ስፈልግ አመሹሁ የደስታዋን ዓለም
ሳቋን ለመመለስ ያልሞከርኩት የለም
ጥርሷን ባየው ብዬ የጉንጮቿን ስርጉድ
ከንጋት እስኪመሽ እያልኩኝ ሽር ጉድ
ኧረ ጉድ
ኧረ ጉድ
ምን ያልሆንኩት አለ ያልዋልኩበት ቦታ
የሷን ሳቅ ልሸምት ሸጥኩኝ የኔን ደስታ
ብቻ ትሳቅልኝ ሲከፋት እንዳላይ
የነጥብ ደመና እንደሌለው ሰማይ
ፍክትክት እንዳለች ይቆጠር ዘመኑ
ከአድማስ ይራቃት እንባና ሀዘኑ
እንባዎቿን ስጠኝ ሀዘኗን ልጋራት
መደሰቴ አይቀርም ፈገግ ብላ ሳያት
ለመላው እስልምና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እናት አባቶቻችን እንኳን ለ 1445ኛው የ ኢድ አል አድሃ ( አረፋ ) በአል በሰላም አደረሳችሁ !!!!
በዓሉን የፍቅር የደስታ የጤና የሰላም ያድርግልን
መልካም በዓል !!!!!
???Eid Mubarak ???
[ ማህሙድ ጋ ጠብቂኝ ]
ወጣት ሆኜ ሳለሁ
ችዬ ባላስነሳ የለውጡን አብዮት
ራሴን ላጠፋ ስትመረኝ ህይወት
እያሰብኩ እያለ
ስብሀት ከፃፈው
ትኩሳት መፅሀፍ ያ ምክር ትዝ አለኝ
ከውሳኔህ በፊት ፒያሳ ሂድ ያለኝ ።
ያኮረፍኳት ፍቅሬን አራዳ ቀጠርኳት
ገና ሳንገናኝ
ማህሙድ ጋ ስትመጣ በሀሳቤ ሳልኳት
ኖቬት የተገዛ ነጭ ቀሚስ ለብሳ
የካራቢያኑን
ጥቁር ጫማ አድርጋ ትመጣለች እሷ
እኔማ ቀጥሬያት አትቀርም ፒያሳ
በሀኪም ቦራ አሳንሰር እየተንሸራተትኩ
ጴጥሮስን ጠምዝዤ ቁልቁል እንደወረድኩ
በፓስታ ቤት በኩል
ሀሳቦቼን ፅፌ ሳልክልሽ ብቀር
የትም አትጠብቂኝ
የትም አልቀጥርሽም ከማህሙድ ጋ በቀር
እስክትመጪ ድረስ ከቸርቸል ጎዳና ዱካሽን ስቆጥረው
ከማህሙድ ፊት ለፊት ወደ ወርቅ ቤቱ አካሌን ወሰደው
በሀሳብ ፈዝዤ
አይኖቼን አንስቼ ከወርቅ ቤቶቹ ጀርባ ብጥላቸው
ከዶሮ ማነቂያ ቅያስ ገብተዋሉ ከስጋው ላይ ናቸው
ስጋና ስጋትን
ሀዘንና ሀሴትን
በአንድ ላይ የየያዘች
በፍቅር ደግነት ሰዎችን ያነቀች
የፒያሳ እምብርት ተዐምረኛ መንደር ትጠብቀናለች
ሸግዬ ቶሎ ነይ
ከፒያሳ እግር ስር
ማኪያቶ እየጠጣን ተቀምጠን ቼንትሮ
አንቺን ደስ ካለሽ
የሆድ እያወጋን ጁሱን በ'ስትሮ
መጠን ስንጨርስ በኢንተር ላንጋኖ
ከንፈሬ ከንፈርሽ በአንድ ላይ ሆኖ
ሰዓት ስለሚሄድ
ገብተን መኮንን ባር
ከሰፈሩ ካበው ከሰፈሩ አድባር
ትንሽ አመሻሽተን
ከሰንሻይን ሻምፓኝ ካንቺ ባልራጭም
ጣይቱ ሆቴል ብናድር ዘበት አልቆጭም
ባ'ዲስባ መሐል ባ'ዲስባ ሰማይ
አልተቃጠርንም ወይ ፒያሳ አደባባይ
ትንሽ ብታረፍጂ ከአራት ኪሎ በኩል ከመጣች ኮበሌ
ወዝ ወዝ...... ወዝ ወዝ ከሚል ሽንጥና ባት ዳሌ
ተመለከትኩ እንጂ አልዘሞተም አይኔ
ይህን የታዘብኩት
አንቺን ማህሙድ ጋ ስጠብቅ ነው እኔ
የህፃኑ ብዛት 'ሚጫወተው በአፈር
እንቅልፍ አይተኙም ወይ ሠራተኛ ሰፈር
እንዳትገረሚ ንግግሬ በዝቶ ፈላስፋ ብመስል
ብታረፍጂ ጊዜ ገብቼ ይሆናል ብሪትሽ ካውንስል
ፈዘዝ ያለን ሁሉ
ኑሮ አድክሞት ጫንቃው
ዲሞክራሲ አይደለም
የኔና አንቺን አካል ቡና ነው ሚያነቃው
ከቡናም ቡና አለ
የደስታ ጠረፉን ጣራ የሚለካ
ነይ እንሂድ ማንኪራ አትቅሪ ቶሞካ
እንድታስታውሺው እንዳትረሺው ሁሌ
ማህሙድ ወረድ ብለን
ኩርት ያለ ምሳ ልጋብዝሽ ካስቴሌ
ውዴ
አትደርሺም እንዴ ፍቅር ቆየሽ እኮ
ጣፋጭ ኬክ እንብላ ገብተን ኤንሪኮ
አንድ እንጨምርለት ወሬ ለሚያበዛ
ወይ ፒዛ ኮርነር ከናፈቀሽ ፒዛ
ይሻላል እንደዛ
ለካ አንቺ ቫቅላባ ትወጃለሽ በጣም
ወረፋ ልጠብቅ
ናፍቀው የጠበቁት ሁሌም ቶሎ አይመጣም
ማህሙድ ጋ ብትቆዪ ወዲያ ተሻግሬ
አይኔን ከስክሪኑ ጆሮዬን ከዳላስ ሰቅዤ ሰካሁት
አንቺሆዬ ባቲ አምባሰል ትዝታ ቅኝቱን ሰማሁት
በመጠብቅ ብዛት አልቀልጥም እንደ ሰም
ጊዜውም ለጋ ነው
አምፒር ለሲኒማው ሰዓቱ አልደረሰም
ግድየለም አርፍጂ
በእርግጥ ስትመጪ
ማህሙድን ከቦታው ፈልገሽ ብታጪው
ከእርምጃሽ ቆመሽ መንገድሽን አትቋጪው
ምናልባት ስትመጪ
አራዳ ብቻውን ቆሞ ብታገኚው
ፊት ለፊቱ አልቅሰሽ ቅር እንዳታሰኚው
ፒያሳ እንደ ተረት አይቀርም ደብዝዞ
ከመሬት ቢፈርስም
ልባችን ውስጥ አለ እልፍ ቦታ ይዞ
ብቻ ግን የኔ ዓለም
ማህሙድ ጋ ቀጠሮ እንዳለን እንዳትረሺ
በልባችን ጉያ ፒያሳ አለች ዛሬም
ትዝታችን አለ ቀዬው ፈርሷል ብለሽ እንዳትመለሺ
[ በረከት_#ውዱ ]
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 3 days, 16 hours ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 3 weeks, 3 days ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 8 months, 3 weeks ago