መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

Description
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months ago

2 months, 1 week ago
2 months, 1 week ago
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr …
2 months, 1 week ago
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr …
2 months, 2 weeks ago

👉 የሕትመት ዋጋ በመጨመሩ አንባብያን በመጻሕፍት መሸጫ ዐጥተውት በጠየቁት መሠረት የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ "888" መጽሐፍ ለአራተኛ ጊዜ ታትሞ ለአንባብያን ቀርቧል።
👉 መጽሐፉ በሀሁ የመጻሕፍት ማከፋፈያ እና በተለያዩ መሸጫዎች ይገኛል።

💥 መጽሐፉ በ27 ምዕራፍ የተከፈለ ሲኾን በኢትዮጵያ የፊደል ቀመር ውስጥ የሚገኙ:-
👉 የፊደላት ጂኦሜትሪ፣ ድምፅ፣ ቁጥር
👉 በመቅረዙ ውስጥ የተቀመጠው የ7 የብርሃን ቀመር
👉የ አ ቡ ጊ ዳ ሙሉ ቀመር
👉 በመጽሐፈ ሔኖክ የሚገኘው የስመ አምላክ ቀመር
👉 በገነት ውስጥ የነበሩ የዕፀ ሕይወት እና ዕፀ ጥበብ ቀመር
👉 በግእዝ ፊደላት ያለው የ3.14 የፓይ ቀመር
👉 የ DNA እና RNA ቀመር
👉 የፔሪዮዲክ ሠንጠረዥ የንጥረ ነገራት ቀመር
👉 የፕሩቶንና የኤሌክትሮን ቀመር
👉 የልብ እና የአእምሮ ዐይኖች መክፈቻ የግእዝ ቀመር
👉 በ182 የግእዝ ፊደላት የተቀመረው የኢኪውኖክስ (Equinox) ቀመር
👉 በፊደላችን የሚገኝ የሥርዐተ ፀሐይ ቀመር
👉 ከአድማስ እስከ ናጌብ የምድር ልኬት ቀመር
👉 በፊደላችን የተገለጸ የጨረቃና የምድር ራዲየስ ልኬት
👉 በግእዝ ፊደላችን የተገለጸ በሜትር ፐር ሰከንድ የሚቀመር የድምፅ ፍጥነት
👉 በፊደላችን የተገለጸ በሚክሮሜትር የሚቀመር የቀይ የደም ሴል፣ በደም ቧንቧ ውስጥ ያለው ቀመር
👉 በግእዝ ፊደላት ውስጥ የሚገለጸው ቀመረ ምጽአትና የርኅወተ ሰማይ (የሰማይ ደጃፍ) Portals መክፈቻ ቀመር እና ሌሎች ብዙ ድንቅ ምስጢራት ተካተውበታል።
👉 በውጪ ሀገር የምትኖሩ በቀላሉ በአማዞን ላይ ማግኘት ይቻላል። ሊንኩም https://www.amazon.com/dp/B0BGZ14FBD/ref=cm_sw_em_r_mt_dp_X81QK1M112XS84KPYFSY

#የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር

አድራሻ  ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
               2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ
              ስ.ቁ  0911006705/0924408461

2 months, 3 weeks ago

[የመስከረም ሰማይ ጫና የተፈጥሮ አደጋ]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ቀንና ሌሊት እኩል በሚኾንበት Equinox በሚደረግበት በዚህ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር በመስከረም ለየት ባለ መልኩ ሰማይ በብዙ ምልክት የተመላበት ምድርም (የብሱም ባሕሩም) የተባበሩበትና በምድራችን ጫና የነበረበት ወር ነውና በሰማይ ላይ እየተከናወኑ ስላሉት ሰማያዊ አካላት ጥቂት ማለት ወደድኹ።

👉ረቡዕ መስከረም 8 (Sep. 18) የዐዲስ ዓመት ታላቋ ሙሉ ጨረቃና Super Harvest Moon እና ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ Partial Lunar Eclipse የተከሰተበት።

👉 ማግሰኞ መስከረም 14 (September 24) ሄለኔ ዐውሎ ነፋስ (Hurricane Helene) በፍሎሪዳ ግዛት ከፍተኛ ጉዳት በሰው ሕይወትና ንብረት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰበት

👉እሑድ መስከረም 19 (September 21) በመሬት ስበት አስትሮይድ 2024 PT5ን በመያዙ ላይ ሚኒ ጨረቃ (ሚጢጢ ጨረቃ) በመኾን እስከ ኅዳር በመቆየት የስበት ጫናቸውን በምድራችን አጠናክረዋል።

👉 ረቡዕ መስከረም 22 (October 2) ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ (annular solar eclipse) በደቡብ አሜሪካ፤ ጠፍ ጨረቃ (New Moon) በዕለቱ ሮሽ ሀሻናህ የእስራኤል ዐዲስ ዓመት ተባብሮበታል።

👉ኀሙስ መስከረም 23 (ኦክቶበር 3) - በሰባት ዓመታት ውስጥ ያልታየ በጣም ኃይለኛ ነበልባለ ፀሐይ X9.05 solar flare ከፀሐይ ነቁጥ sunspot የተነሣበት።

👉 በእኛ አንጻር ካየነው እሑድ መስከረም 26 በዐዲስ አበባ ርዕደ ምድር የተሰማበት።

👉 ሰኞ መስከረም 27 (October 7) ከፀሐይ ነቁጥ (Sunspot) AR 3842 እኩለ ቀን ላይ ከፍተኛ ሶላር ፍሌር (የፀሐይ ነበልባል) ተከሥቷል።

👉 ሰኞ መስከረም 27 (ኦክቶበር 7) የደራጎን ሕብረ ኮከብ ተብሎ ከሚጠራው ድሬኮ ሕብረ ኮከብ Draco constellation ውስጥ [Draconids Meteor Shower] (በሰዓት ወደ 10 ተወርዋሪ ከዋክብት) እየወጡ ይታያሉ። ሥነ ከዋክብታዊ ነገረ መለኮትን የሚያጠኑ ይኽንን የድሬኮ ሕብረ ኮከብ፦
✍️ “ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው”
— ራእይ 12፥4 ከሚለው ጋር አነጻጽረው ያዩታል (ስለዚኽ ለመረዳት ማዛሮት መጽሐፌን ያንብቡ)

👉 መስከረም 28 - 29 (October 8 - 9) በምድብ 5 ያለ ሚልተን የተባለ ከፍተኛ ዐውሎ ነፋስ ድጋሚ ወደ ፍሎሪዳ እየመጣ ያለበት።

👉 ቅዳሜ ጥቅምት 2 (ኦክቶበር 12) Tsuchinshan-ATLAS የተባለው ዥራታማ ኮከብ ምድርን የሚያልፍበት ነው።

👉 ኀሙስ ጥቅምት 7 (October 17) የጥቅምት ሙሉ ጨረቃ ሚጢጢ ጨረቃ የተባለው አስትሮይድ 2024 PT5ን ከመጣ በኋላ የመጀመሪያዋ ሙሉ ጨረቃ የምትወጣበት።

💥 እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እነዚኽ ሰማያዊ አካላት ለምልክትነት የተሾሙ ስለመኾናቸው ጌታ እንዲኽ ይላል፦

✍️ “በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና።” (ሉቃስ 21፥25-26)

5 months, 2 weeks ago

[ስለ ሕዋ ዐለቶች በምዕራብ ኢትዮጵያ ስለወደቀው ዐለት]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
? በቅርቡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ይልቁኑ በጅማ የቡ ከተማ ስለተሰማው ድምፅና ስለታየው የተሰባበረ ዐለት ጥቂት ለማለት ወደድኹ።
ከሰማይ ስለሚወድቁ የሕዋ ዐለቶች ለመረዳት፦
1. አስትሮይድ
2. ሜትዮራይድ
3. ሚትዮር
4. በሜትሮይት
መካከል ያለውን ልዩነት አንድነት መረዳት ያስፈልጋል፡-

  1. አስትሮይድ
    ? በዋነኛነት በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው የአስትሮይድ ቀበቶ ውስጥ የሚገኙት ዐለታማ ሥሪትነት ያላቸው አካላት ናቸው። መጠናቸውን ለመረዳት ለምሳሌ አስትሮይድ ቬስታ መጠኑ 329 ማይል (530 ኪሎ ሜትር) ዲያሜትር ያለው ሲኾን ከታናናሾቹ ውስጥ ከ33 ጫማ (10 ሜትር) በታች የኾኑም ይገኙበታል። የኹሉም አስትሮይድ አጠቃላይ ክብደት ግን ከምድር ጨረቃ ያነሰ ነው።

? በዚኹ አጋጣሚ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም ወይም እንደ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ኤፕሪል 13/ 2029 አፖፊስ የተባለው አስትሮይድ ከምድር በላይ 30,600 ኪሎ ሜትር (19,000 ማይል) ርቀት ላይ የሚያልፍ ሲኾን ቢሊዮኖች በዐይናቸው ያዩታል። መሬትን የመመታት ዕድሉ 2.7 ፐርሰንት ብቻ ነው። (አንድሮሜዳ ክፍል 2 ገጽ 388 - 394 )

  1. ሜትዮራይድ
    ? ሜትዮራይዶች በሕዋ ያሉ ትናንሽ ዐለቶች ሲኾኑ መጠናቸው ከከሸዋ ቅንጣት እስከ 1 ሜትር አካባቢ ይደርሳሉ። አንዳንድ ሜትዮራይድ ዐለቶች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ብረታ ብረት ወይም የድንጋይ እና የብረት ውሕዶች ናቸው። ሜትዮራይድ ብዙ ጊዜ ከአስትሮይድ ወይም ከኮሜት ወይም ከሌሎች ፕላኔቶች ጭምር የሚመጡ ናቸው። በአጠቃላይ ሜትዮራይድ ስንል ገና በሕዋ ላይ ያሉትን ነው።

  2. ሚትየር
    ? ከላይ እንዳየነው ሜትዮራይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ወይም ወደ ሌላ ፕላኔት በከፍተኛ ፍጥነት ሲገቡ እና ሲቃጠሉ ሚትዮር ይባላሉ። በሌላ አጠራር “ተወርዋሪ ኮከቦች” ብለን የምንጠራቸው ሲኾን አንዳንድ ጊዜ ሜትየሮች ከቬኑስ የበለጠ ብሩህ ኾነው ሊታዩ ይችላሉ። ያን ጊዜ “የእሳት ኳሶች” ተብለው ይጠራሉ። ብዙ ተወርዋሪ ከዋክብት በአንድ ላይ በሰዓታት ሲታዩ "ሜትየር ሻወር" በመባል ይታወቃሉ።

  3. ሜትሮይት
    ? ሳይቃጠል የምድርን ከባቢ አየር ዐልፎ በምድር ላይ የሚያርፍ የሜትሮይድ ቁራጭ መጠሪያ ነው። በሰዓት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ በኃይለኛ ግፊት ወድቆ ሲበታተን ብሩህ ነበልባል ይመስላል።
    ሜትሮይትስ በሦስት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላሉ፡-
    1) ድንጋያማ ሜትሮይትስ (በዋነኛነት ከሲልኬት) ማዕድናት የተውጣጡ ናቸው)፣
    2) የብረት ሜትሮዮትስ (በአብዛኛው ከብረት-ኒኬል ውሕዶች የተውጣጡ ናቸው)
    3) ድንጋያማ ብረት ሜትሮይትስ (በግምት እኩል መጠን ያላቸው የሲሊኬት ማዕድናት እና ብረት ኒኬል ይዘዋል)

? ሜትሮይቶች ሲታዩ የምድር ዐለቶችን ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚያብረቀርቅ ሊመስል የሚችል የተቃጠለ ውጫዊ ክፍል አላቸው። ይኸውም በከባቢ አየር ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ የሜትሮይት ውጫዊ ገጽታ ሲቀልጥ የሚፈጠር ነው።

?በምድር ላይ ከ 50,000 በላይ ሜትሮይትስ ተገኝተዋል.
ከእነዚህ ውስጥ 99.8% የሚሆኑት ከአስትሮይድ የሚመጡ ናቸው።
? በየቀኑ 48.5 ቶን የሜትሮይት ቁስ አካል ወደ ምድር ይወድቃል። ይህም በዓመት 17,000 ሚቴዮራይትስ እንደማለት ነው። አብዛኛው ግን በከባቢ አየር ውስጥ ተንኖ ተወርዋሪ ኮከብ ይኾናል።
? በቅርብ የተከሰቱ አደገኛ የሜትሮይትስ ክስተቶች ውስጥ ኹለቱን በማንሣት ጽሑፌን ልቋጭ፦
1ኛ) በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ሜትሮይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ የገባው እኤአ በ1908 ሲኾን የቱንጉስካ ክስተት በመባል ይታወቃል። ይህ ሜትዮር በሩሲያ በሳይቤሪያ ላይ የተከሰተ ሲኾን ምድሩን ሳይመታ በፊት በአየር ላይ ጥቂት ማይል ርቀት ላይ ፈነዳ።

? የፍንዳታው ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ስፋት ባለው ክልል ውስጥ ዛፎችን ለማውደም የሚያስችል ኃይለኛ ነበር። ሜትዮሩ 120 ጫማ (37 ሜትር) ስፋት ያለው እና 220 ሚሊዮን ፓውንድ (100 ሚሊዮን ኪሎ ግራም) ይመዝን ነበረ። በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ አጋዘኖች ሲሞቱ ነገር ግን ማንም ሰው በፍንዳታው መሞቱን የሚያሳይ ቀጥተኛ መረጃ የለም።

2ኛ) እ.ኤ.አ. በ 2013 በቼልያቢንስክ ሩሲያ ሰማይ ላይ ቤትን የሚያህል ሜትሮይድ በሰከንድ ከ11 ማይል (18 ኪሎ ሜትር) በላይ ወደ ከባቢ አየር በመግባት ከመሬት በላይ 14 ማይል (23 ኪሎ ሜትር) ላይ ፈነዳ። ፍንዳታው ወደ 440,000 ቶን የሚገመተውን የቲኤንቲ ኃይል በመልቀቁ ከ200 ስኩዌር ማይል (518 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) በላይ መስኮቶችን የሰባበረ እና ሕንፃዎችን ያበላሽ አስደንጋጭ ኹኔታን ፈጠረ። በፍንዳታው ይልቁኑ በመስታወት ስብርባሪ ከ1,600 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
(ስለ ሥነ ፈለክ ለመረዳት አንድሮሜዳ ክፍል 1፤ አንድሮሜዳ ክፍል 2፤ ማዛሮት መጽሐፍን ያንብቡ)
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

5 months, 3 weeks ago

የእግዚአብሔርን ልጅ ሰው መኾን ስለርሷ የተናገሩላት እመቤታችን ድንግል ማርያም አይደለችምን፤ ስለዚኽ እግዚአብሔር ስለ እመቤታችን ጥንታዊ የልደቷን አመጣጥ በየጊዜው ምልክት እንደሚሰጥ ልብ አድርገን ማስተዋል ይገባናል) በማለት አብራርተው ተርጒመዋል፡፡

?❖ ሊቁ አባ ሕርያስቆስም በቅዳሴው በቊ ፴፪ ላይ "ተናግዶቱ ለአብርሃም" (የአብርሃም እንግድነቱ አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን ጠቅልሎ የገለጠውን ይኽነን ድንቅ ምስጢር፤ ሊቁ በነገረ ማርያም ላይ በስፋትና በጥልቀት፡-

"ወዓዲ ኀይመት ዘአብርሃም ዘውስቴታ ተአንገደ እግዚአብሔር አኮ ከማሁ ዘኮነቶ ምጽላለ በእንተ ምዕር አላ ኮነቶ እመ ወተከድነ ሥጋሃ ወረሰዮ አሐደ ምስለ መለኮቱ" (ዳግመኛም እግዚአብሔር (በሦስትነት) በዕንግድነት ያረፈባት የአብርሃም ድንኳን አንቺ ነሽ፤ ለጥቂት ጊዜ ብቻ መጠለያን፣ መጠጊያን የኾነቺው አይደለም፤ እናትን ኾናው ሥጋዋን ተዋሕዶ ከመለኮቱ አንድ አደረገው እንጂ) በማለት በአብርሃም ድንኳን ብትመሰልም እንኳ ክብሯ ከፍ ያለ፤ ለዘላለም የአምላክ ማረፊያውና እናቱ መኾኗን አብራርቶ ገልጧል፡፡

?❖ ሊቅነትን ከንግሥና ጋር ያስተባበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ በመጽሐፈ ሥላሴ መጽሐፉ ላይ፦
? "ኦ ብእሲ ዘትትከሓድ አይኑ ዕለት ለአግዚአብሔር ሰገዱ ሎቱ ምስለ መላእክቲሁ በዕሪና እምነ ኩሉ ፍጡራኒሁ..." (ሥላሴን የማታምን አንተ ሰው ሆይ ከፍጡሮች ወገን በመላ እግዚአብሔርን ከመላእክቱ ጋር በአንዲት ዕሪና የሰገዱለት በማናቸው ዕለት ነው? በማናቸው ዕለት እግዚአብሔር ከፈጠራቸው መላእክቱ ጋር ተካክሎ እግሩን ታጠበ? በማናቸው ዕለት በሰው መጠለያ በታች ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ ተጠለለ? በማናቸው ዕለት ከፈጠራቸው መላእክት ጋር ተካክሎ እግዚአብሔር በላ? በማናቸው ዕለት ከአዳም ልጆች ወገን ሰው ወደ ፈጣሪው በለመነ ጊዜ መላእክቱ ከፈጣሪያቸው ከእግዚአብሔር ጋር ተካክለው እንዲኽ አድርግ መቼ አሉ? አንተ ሥላሴን የማታምን ፍጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር በመተካከል እንዲሰገድላቸው ለምን ታመጣቸዋለኽ? ፈጡራን መላእክትን ፈጣሪ ከኾኑ ከሥላሴ ጋር ተካክለው በአብርሃም ቤት እንደተጠለሉ፤ እግራቸውን እንደታጠቡ፤ ዐብረው እንደበሉ አድርገኽ ለምን ታስተካክላለኽ? አንተ ከእኛ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አንድነት የኾንኽ ክርስቲያን አንዱ እግዚአብሔር ነው፤ ኹለቱ መላእክት ናቸው አትበል) በማለት አስፍቶ ይጽፋል፨

❖በቤተ አብርሃም የገቡ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ዘወትር በቤተ ልቡናችን ውስጥ ግቡልን፨❖
[ለበለጠ ምስጢር "መልክአ ሥላሴ ንባቡና ትርጓሜው" መጽሐፌን ያንብቡ]፨
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በድጋሚ ፓስት ያረኩት]

5 months, 3 weeks ago

?❖የሐምሌ ሥላሴ በዓል ድንቅ ምስጢር❖?
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
?❖ አብርሃም ከደግነቱ ብዛት እንግዳን ከመውደዱ የተነሣ ድንኳኑን በተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን ሲቀበል የሚኖር በሥራው ኹሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ጻድቅ ነበር (ዘፍ 18:1-10)፡፡ ጽድቁም ሊታወቅ ስድስት ሰዓት ላይ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ፤ በመምሬ ዛፍ ሥር እግዚአብሔር በአንድነት በሦስትነት ተገለጸለት ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፤ ሥላሴ በአምሳለ ዕደው ቆመው አይቶ፤ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ።

?❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሰለዚኽ ነገር በድጓው ላይ፦
"ዮም አብርሃም ሰገደ ለፈጣሪሁ
ሶበ ነጸረ ዋሕደ በሥላሴሁ"
(ዋሕደ ባሕርይ የኾነ እግዚአብሔርን በአካላዊ ሦስትነቱ ባየው ጊዜ አብርሃም ዛሬ ለፈጣሪው ሰገደ) ይላል፨

?❖ የተገለጡለት ሰዓቱ ቀትር (ስድስት) ሰዓት በዕንጨት ሥር በሰው አምሳል መኾኑ ቀደምት ሊቃውንት ሲያራቅቁት በአብ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በራሱም ፈቃድ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ዘመኑ ሲፈጸም የአብርሃምን ባሕርይ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ በስድስት ሰዓት በዕንጨት መስቀል ላይ ለቤዛ ዓለም የሚሰቀል መኾኑን ያጠይቃል ይላሉ፨

?❖ ይኽነን ይዞ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በሕማማት ሰላምታው፦
"ለአብርሃም አብ ቀዳሚ ዘአስተርአይኮ ክርስቶስ
ቀትረ ታሕተ ዕፀ ድርስ
ተሰቀልከ ከመ እቡስ ስብሐት ለከ"
(ምስጋና የተገባኽ ጌታ ድርስ በሚባል የዛፍ ዐይነት ሥር በስድስት ሰዓት ለአባታችን አብርሃም ቀድሞ የተገለጥኽለት ክርስቶስ ሆይ እንደ በደለኛ ተሰቀልኽ) ይላል፨

?❖ ከዚኽ በኋላ "አቤቱ በፊትኽስ ሞገስ አግኝቼ እንደኾነ ባሪያኽን አትለፈኝ ብዬ እለምናለኍ፤ ጥቂት ውሃ ይምጣላችኍ፤ እግራችኹን ታጠቡ፤ ከዚኽችም ዛፍ በታች ዕረፉ…" በማለት ተናግሯል፡፡
"በፊትኽ ሞገስን አግኝቼ" ብሎ አንድነታቸውን፤
"ውሃ ይምጣላችኍ፣ ዕረፉ፣ ትኼዳላችሁ" ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

?❖ ይኸው ሊቅ ያሬድ ይኽነን ይዞ በድጓ ላይ፦
"ይቤሎሙ ዮም አብርሃም ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አመጽእ ማየ ወአሐጽብ እገሪክሙ ወእርከብ ሞገሰ በቅድሜክሙ" (አብርሃም ዛሬ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስን ባለሟልነትን በፊታችሁ አገኝ ዘንድ ውሃን አምጥቼ እግራችኹን አጥባለሁ አላቸው) ይላል

?❖ ይኽቺ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን እግዚአብሔር የተገለጠባት ዛፍ፤ አንድነት ሦስትነት በጐላ በተረዳ ነገር የታወቀባት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በድንግልና የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን፤ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ እንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ
"አንቲ ውእቱ ዕፀ ድርስ ዘለአብርሃም በርስአኒሁ
ዘብኪ አጽለለ እግዚአብሔር በሥላሴሁ"
(ለአብርሃው በእርጅናው ወቅት፤ እግዚአብሔርን በሦስትነት ያስጠለለብሽ የወይራ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት ሲገልጥ፦

?❖ ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፉ፡-
"እንቲ ውእቱ ዕፀት ዘነበርኪ ጥቃ ኀይመት፣
ዘብኪ አጽለሉ ሠለስቱ አጋዕዝት"
(ባንቺ ሦስቱ ጌቶች (ሥላሴ) የተጠለሉብሽ በድንኳን አጠገብ የቆምሽ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት በአንድነቱ ምንታዌ (ኹለትነት)፣ በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) ለሌለበት አምላክ የሦስትነቱ የአንድነቱ ምስጢር መገለጫ የሥላሴ ማደሪያ መኾኗን መስክሯል፡፡

?❖ ከዚኽም ምስጢር የተነሣ አብርሃምም ሳራን “ሦስት መስፈሪያ የተሠለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፤ ለውሺውም እንጎቻም አድርጊ” በማለት የተገለጸለትን የሦስትነት የአንድነት ምስጢርን አጒልቶ ተናግሯል፡፡

?❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይኽነን ይዞ በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
"ግናይ ለክሙ ሥሉስ ቅዱስ ነገሥተ ሰብዐቱ አብያት
እለ በላዕክሙ ውሣጤ ኀይመት
አሐደ ኅብስተ ትሥልስት"
(ከሦስት መስፈሪያ ዶቄት የተጋገረ አንድነት ያለው ኅብስትን በድንኳን ውስጥ የተመገባችሁ የሰባት ቤቶች (ሰማያት) ነገሥት ሆይ ለእናንተ መገዛት (ምስጋና) ይገባል) ይላል፨

?❖ አብርሃምም በደስታ ኾኖ መዐር፣ ወተት፣ ያዘጋጀውን ጥጃ አመጣላቸው፤ እነርሱም ደስ ይበለው ብለው በግብር አምላካዊ ተመግበዋል፤ መላእክት ሎጥ ቤት፤ ቅዱስ ሩፋኤል ጦቢት ቤት ተመገበ የተባለው አንድ ነው፤ እሳት ቅቤ በላ እንደማለት ብቻ ነው፨

?❖ ይኸውም ወተትና መዐር መመገባቸው ኦሪትን ወንጌልን መሥራታቸውን ሲያጠይቁ ነው፤ መዐር የኦሪት፤ ቅቤ የወንጌል ምሳሌ ነው፨ ማር ለጊዜው ሲይዝ የሚለቅ አይመስልም፤ ግን ይለቃል ኦሪትም ስትሠራ የምታልፍ አትመስልም ነበር ግን በኽዋላ ዐልፋለች፨ ወተት የወንጌል ምሳሌ ነው፤ ይኽ ወተት ለጊዜው የሚለቅቅ ይመስላል በኽዋላ ሲያጥቡት አይለቅም ወንጌልም ለጊዜው ስትሠራ የምታልፍ ትመስል ነበር፤ በኽዋላ ግን ጸንታ የምትኖር ኾናለችና በማለት መተርጉማን ያራቅቁታል፡

? ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ወልድ አብርሃምን "የዛሬ ዓመት እንደዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለኍ፤ ሚስትኽ ሳራም ልጅን ታገኛለች" በማለት ዘመኑ ሲፈጸም እግዚአብሔር ወልድ ከቤተ አብርሃም ከተገኘች ከእመቤታችን የመወለዱንና፤ በሳራ የተመሰለች ወንጌል ምእመናንን እንደምታስገኝ በምስጢር ገልጾለታል፤ ቅዱስ ጳውሎስም አካላዊ ቃል በሰጠው ተስፋ መሠረት ከነገደ አብርሃም የመወለዱን ነገር ለዕብራውያን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ "በሕይወታቸው ኹሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ኹሉ ነጻ እንዲያወጣ፤ በሥጋና በደም እንዲኹም ተካፈለ፣ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም" በማለት ገልጾታል (ዕብ ፪፥፲፭-፲፮)፡፡

?❖ ይኽቺ ሥላሴ የገቡባት ኀይመተ አብርሃም (የአብርሃም ድንኳን) የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፤ ይኸውም ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ኹሉ፤ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም፤ አብ ለአጽንኦ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመዋሐድ ዐድረዋል (ሉቃ ፩፥፴፭)፤ በመኾኑም አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ብቻ ናት፡፡

?❖ ሊቁም በነገረ ማርያም ይኽነን ምስጢር ሲገልጽ "ወይእቲ ኀይመት ትትሜሰል በድንግል ወዕደው አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እሙንቱ፤ አብ አጽንኣ፣ ወወልድ ተሰብአ እምኔሃ፣ ወመንፈስ ቅዱስ ቀደሳ ከመ ትጹር አምላከ በከርሣ" (ያቺ ድንኳንም በድንግል ትመሰላለች፤ ሰዎቹም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ አብ አጸናት፣ ወልድም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፣ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ቃል አምላክን ትሸከም ዘንድ ለያት) በማለት ተርጉሞታል፨

?❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በሰላምታ መጽሐፉ ላይ መጽሐፉ፦ "ኀይመተ አብርሃም አብ ሰላም ለኪ፤
ዘኮንኪ ከመ ተድባብ ሰላም ለኪ"
(እንደ ጥላ የኾንሽ የአባት አብርሃም ድንኳን ሰላምታ ይገባሻል) በማለት አመስግኗታል፡፡

?❖ ይኽ አብርሃም የተቀበለውን የተስፋ ቃል ሊቃውንት ሲተረጒሙት "ኦ አኃውየ በይነ መኑ እንከ ዘይቤ እግዚአብሔር ለአብርሃም አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ አኮኑ እግዝእትነ ማርያም ይእቲ ዘወፅአት እምነ ሥርው ለአዳም ..." (ወንድሞቼ ሆይ እግዚአብሔር አብርሃምን እንደዛሬው ኹሉ ወደአንተ ተመልሼ እመጣለኍ ያለው ስለማን ይመስላችኋል? ከአዳም ሥር ወጥታ፤ ከኖኅ አብራክ ተገኝታ፤ ወደ አብርሃም አብራክ ልትከፈል፤ ሥላሴ በአብርሃም ቤት በእንግድነት ተገኝተው፤ ከአብርሃም ዘር ከእመቤታችን

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months ago