Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 9 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 2 months ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 3 months, 3 weeks ago
"በጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በመቸገራቸን ትልቅ ፈተና ውስጥ ነን" የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት
ከሌሎች ወሮች በተለየ መልኩ በየዓመቱ ጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚቸገር የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በአገልግሎቱ የደም ለጋሾች መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ዶክተር መላሽ ገላው በ2016 አ.ም እንደ ሀገር 349 ሺ ዩኒት ደም መሰብሰቡን፤ ይህም የእቅዱን 82% መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በተያዘው ዓመት 6 ወራት እንደሀገር 217 ሺ ዩኒት ደም በላይ መሰብሰቡን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 55 ሺ 300 ዩኒት ደም ከአዲስ አበባ ከተማ የተሰበሰበ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የጥር ወር ፈተና
ዶክተር መላሽ፥ ''በተለይ ከሌሎች ወሮች በተለየ መልኩ በየዓመቱ ጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በተለያዩ ምክንያቶች ስለምንቸገር ትልቅ ፈተና ውስጥ ነን '' ሲሉ ወቅቱ ደም ለመሰብሰብ አስቸጋሪ መሆኑን ያነሳሉ።
ለማሳያም፤ "ተማሪዎች ፈተና የሚፈተኑበትና ዕረፍት የሚሆኑበት ጊዜ መሆኑን፤ ስለሆነ ባለፍቱ 2 ሳምንታት ውስጥ ከትምህርት ቤቶች ምንም አይንት ደም አላገኘንም" ያሉት ዶ/ር መላሽ የበዓላት መደራረብም ተጽዕኖ እንዳለው ጠቅሰዋል።ከበዓላት ጋር ተያይዞሞ በተለያዩ ምክንያቶች ደም መሰብሰቢያ ቦታዎች ፈቃድ ባለማግኘታቸው በጥር ወር ከታሰበው 60% በታች የሆነውን ብቻ ማሳካት መቻላቸውን ነው የገለጹት።
ያለውን ክፍተት ለመሙላትም ከበጎፈቃደኞች ጋር አብረው እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው "ሚዲያዎችን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ደም ለመሰብሰብ እየሞከርን ነው "ብለዋል።አክለውም "ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና እሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን የኮሪደር ልማቱን በሚመጥን መልኩ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ የደም መሰብሰቢያ ቦታዎችን ለማግኘት እየሰራን ነው" ሲሉ ነግረውናል።በክልሎች የደም የመሰብሰብ ምጣኔን ለመጨመር ባለሙያዎችን ወደ ክልሎች በመላክ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያረጉ እየተደረገ ነው ያሉን ዶ/ር መላሽ፥ "የየክልሎች ጤና ቢሮዎች ደም ማሰባሰብ ላይ ትኩረት ሰጠው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል '' ሲሉ ገልፀዋል።
የሚመጡት ወራቶች ከዚህ የበለጠ የደም መሰብሰባችን ምጣኔ ሊቀንስ እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀመጡ ሲሆን ለዚህም ማህበረሰቡ ደም በመለገስ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን በሽያጭ የተሽከርካሪ ስም ዝውውር ለማድረግ ሊሟሉ እሚገባቸው ጉዳዮች ብሎ የሚከተሉትን ነጥቦች አስቀምጧል።
በዚህም በሽያጭ የተሽከርካሪ ስም ዝውውር ለማድረግ፦
በተሽከርካሪው ላይ የተላለፈ ማንኛውም ዓይነት እዳ እና እገዳ እንዲሁም ቀረጥ ያለበት ከሆነ የስምምነት ደብዳቤ መኖሩን ማረጋገጥ፣
ኮድ 01 እና ኮድ 03 ከሆነ ከገቢዎች የግብር ክሊራንስ መቅረቡን
የዘመኑን ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ/ቦሎ፤ ያደረገ መሆኑን፤
የጸደቀ የውልና ማስረጃ ሰነድና የስም ዝውውር 2% የከፈለበት ማስረጃ መኖሩን፣
የንግድ ተሽከርካሪ ከሆነ አንዱ የግምት ውጤት ለሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ይላካል፤ ሁለተኛውን የግምት ውጤት ሁለቱ ተዋዋዮች ውል መፈፀም የሚችሉ ለመሆኑ በሸኚ ደብዳቤ ለሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተላከበት ሰነድ፤
የቤት ተሸከርካሪ ከሆነ የግምት ውጤቱን በቀጥታ ሰሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የተላከበት ሰነድ፤
7 . የገዢ ሁለት ፎቶ ግራፍ
በተጨማሪም ቢሮው በዚሁ መረጃው ላይ በሰጠው ማሳሰቢያ፦
የሚገዙት ተሽከርካሪ የሻንሲና ምተር ቁጥር ትክክለኛነት የማረጋገጥ፣
የተሚገዙት ተሽከርካሪ ሊብሬና ተሽከርካሪ ስለያዙ እና ዉክልና ስለተሰጦት ብቻ ሀጋዊ ተሽከርካሪ ማለት ስላልሆነ የሚገዙት ተሽከርካሪ በተመዘገበበት ቅ/ጽ/ቤት ትክክለኛነቱ መረጋገጥ አለበት ሲል ገልጿል።
ለልጆቻችን ምን እንመግብ ?
በሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ዩኒሴፍ ዘገባ 38.6% ከ5 አመት በታች ያሉ ልጆች የቀነጨሩ ሲሆኑ 21% የሚሆኑ 5 አመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠበቅባቸዉ ክብደት በታች ያሉ ሲሆን ከ15-49 ያሉ ሴቶች በምግብ እጥረት የተጎዱ ናቸው።
ስለተመጣጠነ ምግብ ማውራት ብዙ ሰው ቅንጦት ይመስለዋል፤ ነገር ግን ቅንጦት ሳይሆን እጅግ በጣም ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።
ምክኒያቱም የምግብ ጉዳይ ከጽንስ ጅምሮ እስከ 2 አመት ለልጆች የምናበላዉ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸዉ ድረስ ተጽኖ ስለሚያመጣ ትኩረት ልናደርግ ይገባል።
ለልጆች መመገብ ካለብን ውስጥ፦
1፡ ጥሩ ቅባት (smart fat)፡
ህጻናት ትክክለኛ ቅባት/ fat /ያስፈልጋቸዋል። ይህ ማለት ዝቅተኛ ቅባት ሳይሆን ምርጥ ቅባት ያለዉ ምግብ ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው።
-:ለህጻናት ጥሩ ቅባት ምንጭ ከሆኑ ምግቦች መካከል የባህር ምግብ(salmon)፣ ተልባ(flax oil)፣ አቮካዶ ፣ የአትክልት ዘይት ፣ ለውዝ (አላርጂክ ሊያስከትል ስለሚችል ከ2 አመት በኋላ)
- ለህጻናት ጥሩ ያልሆኑ ቅባቶች፡ ዘይት የበዛባቸውና የተጠበሱ ምግቦች፣ ብስኩት (crackers)
2: ጤናማ ስኳር (Best Carbs)
ህጻናት በተፈጥሮአቸዉ ስኳርና ጣፋጭ ነገሮችን ይወዳሉ፣ ሰዉነታቸዉም ይፈልጋል። ስኳር የሰዉነታቸዉ ዋናዉ ነዳጅ እና ሀይል ሰጪ ነዉ።
ጤናማ ስኳር የያዙ ምግቦች፦
አፕል ፣ ሙዝና ፍራፍሬ ፣ የጡት ወተት ፣ የወተት ተዋዖዎች (በተለይ ባዶ እርጎ) ፣ ትኩስ ፍራፍሬ፣ ፓስታ፣ ድንች ፣ አኩሪ አተር። ስኳር ድንች ፣ አትክልት እና አዝእርቶች።
3፡ ፕሮቲን
ፕሮቲን ገንቢ ምግብ በመባል ይታወቃል። ፕሮቲን ለእድገት፣ ለሰዉነትን ግንባታ ትልቁ ድርሻ ይወስዳል።
በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች፦
የባህር ምግብ ፣ የወተት ተዋዕዖ (እርጎ፣ቺዝ እና ወተት) ፣ ጥራጥሬ (አኩሪ አተር፣ ምስር፣ ቦሎቄ)፣ ስጋና የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል የለዉዝ ቅቤ ፣ያልተፈተጉ እህሎች (ስንዴ፣ ሩዝ፣ አጃ፣ በቆሎ እና ማሽላ)
4፡ በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር
ፋይበር/ቃጫ/ የምንለዉ የማይፈጨው የአትክልት እና የፍራፍሬ አካል ነው። በተፈጥሮ አንሸራታችነት ባህሪ ስላለዉ ከሰውነታችን አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎችን ለማሶገድ ይረዳል። ለህጻናት በፋይበር የበለጸገ ምግብ ሰገራቸዉ እንዲለሰልስና አላስፈላጊ ቆሻሻ ቶሎ እንዲወገድ ከመርዳቱም ባሻገር ድርቀትን ይከላከላል።
በፋይበር የበለጸጉ ምግቦች፦
አትክልት( ድንች ከነልጣጩ)፤ ያልተፈተጉ እህል፤ ቡኒ ሩዝ፤ ቦለቄ የመሳሰሉት፤ ካልተፈተገ እህል የተዘጋጀ ፓስታ፣ መኮረኒ፣ አጃ፣ ጥራጥሬ።
5፡ ቪታሚን
ከሶስቱ ዋና የምግብ ክፍሎች ( ቅባት፣ ፕሮቲን፣ ሃይል ሰጪ ምግቦች) በተጨማሪ ቪታሚን ለህጻናት እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል። እንደ ዋና ምግቦች( Macro nutrients) እኚህ ቪታሚንና ሚኒራለስ (micro nutrients) በቀጥታ ለሰዉነታችን ሃይል አይሰጡንም። ነገር ግን ለህጻናት የበሉት ምግብ በአግባቡ እንዲጠቅማቸውና የሰውነት ክፍላቸው በአግባቡ እንዲሰራ ያደርጋል።
ሰውነታችን እነዚህን ንጥረነገሮች ካላገኘ በአግባቡ መስራት አይችልም። ሰውነታችን 13 ቪታሚኖች ያስፈልጉታል። ቪታሚን A, C, D, E, K, እና 8 የ B ቤተሰቦች ማለትም thiamine, niacin riboflavin, pantothenic acid, biotin, folacin, B6 and B12.
6: ሚኒራልስ
እንደ ቪታሚንስ ሚኒራልስ (micro nutrients) የሚካተት ሲሆን ለህጻናት እድገት አስፈላጊ ንጥረነገር ነው። ሚኒራል የምንላቸው ካልሽየም፣ ፎስፈረስ፣ ማግኒዝየም እነዚህ ሶስቱ ጠንካራ አጥንትን ለመገንባት ይጠቅማሉ።
አይረን እና ኩፐር (copper) ደምን ይገነባሉ። ዚንክ( zinc) በሽታ የመከላከል አቅምን ይገነባል፣ሶዲየምና ፖታሺየም( sodium and potassium) ኤሌክትሮ ላይት የምንለዉ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የውሃ መጠን ይቆጣጠራል።
7፡ የአይረን መጠንን መጨመር
እያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል( organs) በአግባቡ እንዲሰራ ብረት በጣም አስፈላጊ ንጥረነገር ነው። ዋናው ስራውም ሂሞግሎቢንን (hemoglobin) መገንባት እና በቀይ የደም ሴል ውስጥ ያለውን ኦክስጅን የሚሸከም ነው።
አንድ ህጻን ልጅ ከ9_10 ወራት ውስጥ ሂሞግሎቢኑ መለካት አለበት፣ ይህም የሚሆንበት ምክኒያት ህጻኑ የደም ማነስ እጥረት ይኑርበት አይኑርበት ለማጣራት ነው።
በአይረን የበለጸጉ ምግቦች፦
የጡት ወተት፣ በብረት የበለጸጉ የህጻናት ወተቶች፣ የቲማቲም ጁስ፣ምስር፣ አኩሪ አተር፣አሳ፣ የዶሮ ስጋ፤ ቦለቄ እና የመሳሰሉት።
[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]
መምህራንን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸውን እውቀት እንዲያሳድጉ የቀረበው ስልጠና
የሰውሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማበልጸግ የሚታወቀው OpenAI ከኮመን ሴንስ ሚዲያ ጋር በመሆን መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ጄኔሬቲቭ AI እና ChatGPT ላይ መሰረታዊ እና ሥነ-ምግባራዊ እንድምታዎችን የሚማሩበት ሞጁል አዘጋጅቷል።
ይህ ስልጠናም መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የትምህርት ዕቅዶችን እና ለተማሪዎች ተጨማሪ አጋዥ ትምህርቶችን እንዲሰጡ የሚያስችላቸዋል ሲል ነው የገለጸው።
በዚህም ከኬጂ እስከ -12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ መምህራን የኩባንያውን AI chatbot በመጠቀም እንዴት በክፍል ውስጥ መጠቀም እንደሚችሉ የሚያግዙ የኦንላይን የትምህርቶች ተዘጋጅተውላቸዋል።
AI በቅድመ መደበኛ እንዲሁም በመደበኛ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተግባራዊ የሚድረጉ ሂደት ገና በጅምር ላይ ያለ ቢመስልም OpenAI ጨምሮ ሌሎች ኩባንያዎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው።
ምንም እንኳን መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መጠቀማቸው እየጨመረ ቢሆንም በአብዛኛዎቹ አስተማሪዎች ዘንድ ቴክኖሎጂውን በመማሪያ ክፍል ውስጥ እንዲተገበር መታሰቡን አልወደዱትም።
ኮመን ሴንስ ሚዲያ በቅርብ ጊዜ በታዳጊ ወጣቶች ላን በሰራው አንድ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው 70 በመቶዎቹ የቤት ሥራቸውን ለማገዝ ወይም አሰልቺ የሚሏቸውን ሂደቶች ላለመከተል Generative AI ይጠቀማሉ። ነገር ግን ከዚህ ውስጥ አንድ ሶስተኛው ብቻ ናቸው ይህን ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ መሆናቸውን ለወላጆቻቸው ያሳወቁት።
?For ladies and gentlemen ?
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች?
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች ?
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery ?
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ ???
https://t.me/+NuL9kONj3Mw1YzM0
https://t.me/+NuL9kONj3Mw1YzM0
https://t.me/+NuL9kONj3Mw1YzM0
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በትራንስፖርት ዘርፍ ለማሰማራት የሚያስችል ስምምነት ከተማ አስተዳደሩ ከስዊፍት ቴክኖሎጂ እና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።
የስዊፍት ቴክኖሎጂ ተወካይ አቶ ብሩክ አሸብር በሚቀጥሉት ሶስት አመታት የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን በኤሌትሪክ መኪኖች ለመተካት መታቀዱን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለትም 21 የኤሌትሪክ መኪኖች መመረቃቸውን የገለጹት አቶ ብሩክ፥ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እነዚህን ዘመናዊ የኤሌትሪክ የትራንስፖርት መኪኖች በፍጥነት ስራ ለማስጀመር የብድር ምችችት እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።
ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖቹ ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት የሀይል አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት በተለያዩ ቦታዎች ቻርች ማድረጊያ ጣቢያዎች እንደሚዘጋጁም ተገልጿል።
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 9 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 2 months ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 3 months, 3 weeks ago