Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

አቡ ዑመይር

Description
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ (ሱረቱል ነህል 125)


ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Yabekeir

ስህተት ባያችሁም ጊዜ አርሙኝ።
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 month, 3 weeks ago

እትብቱ የተቀበረው በሶሪያ ምድር ነው። በሀያዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወጣት። ከፈይሩዝ ጋር በፍቅር እፍ ክንፍ ብሎ የኒካህ ቀጠሮ በሽማግሌዎች ተይዟል። ቀናቸውን እየቆጠሩ የቀለሱት ጎጆ ድንገት በአሜሪካ ጥምር ጦር ዶግ አመድ ሆኖ እናት አባቶቻቸው ሲሞቱ የአላህ ውሳኔ ሆኖ እነርሱ በህይወት ተረፉ።

ፍቅራቸውን እንኳ በወጉ ሳያጣጥሙ ሀገር ቀየው ነደደ። ማደርያ አጡ። ከአንድ ጥግ ሸራ ወጥረው ከሶስት ወንድሞቿ ጋር ህይወታቸውን መግፋት ጀመሩ። ለፍቶ ደክሞ አመድ ለብሶ እሷንም ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ወንድሞቿንም ይቀልብ ያዘ። በርካታ ለሊቶችን የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ሆዳቸውን በርሀብ አንጀታቸውን በፍቅር አስረው አድረዋል። አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ ተባብለው ተቦሳቁለዋል። የእርሷማ አይነገር አጥንቷ እስኪታይ ከስታለች። ስለርሱም አይወራ ሆድና ጀርባቸው በርሀብ ተጣብቋል።

ከዕለታት አንድ ቀን ሚስት ወንድሞቿን ይዛ ከቤት ጠፋች። ፈለገ አፈላለጋት ሊያገኛት ግን አልተቻለውም። ቆዝሞ መዋል አልቅሶ ማደር የዘወትር ተግባሩ ሆነ። ከአንድ አመት በኋላ ድንገት አንድ ዜና ደረሰው። በፍቅር የነደደላት በመውደዱ ሽፋሽፍት ልቡ ላይ ያኖራት ሚስቱ ሌላ ወንድ አግብታ እንደኮበለለች ሰማ። መቋቋም ተሳነው። አንደበቱ ተሳሰረ። የዓይኑ ቋጠሮ ተፈቶ ዕንባው ኩልል ብሎ በጉንጮቹ መሐል ፈሰሰ። ይይዝ ይጨብጠውን አጣ።

ክስተቱን ከጓደኛው አንደበት እንስማ:-
ከብዙ ድካም በኋላ ባገኘሁት ስልክ ደውዬ ሰላምታን አቀረብኩላት። ስሙን ከመጥራቴ ስለ እኔ በፍጹም እንዳያስብ ንገረው አለችኝ። በእርግጥም እርሱ... ሳግ እየተናነቃት "ምድር ላይ በጣም የማፈቅረው ውድ ሰው ነው" እንደምንም ትንፋሿን ውጣ ንግግሯን ቀጠለች "አባቴ ከዓመታት በፊት ነበር በድሮን የተገደለው። ሶስት ታናናሽ ወንድሞቼን አደራ ሰጥቶ ይህን አለም ተሰናበተ። ወንድሞቼን የሚያስተምረው ፍላጎታቸውን የሚያሟላው እርሱ ነበር። ሲከብደው ሸክሙን ለማቅለል ወሰንኩ... አለችና ተንሰቅስቃ አነባች። "ጀነት ስንገባ አላህን እጠይቀዋለሁ የታለ ብዬ እፈልገዋለሁ ስላዘንኩለት ብቻ እንደራቅኩት እነግረዋለሁ። እሱም ይቅር ይለኛል" አለችና ለማንም እንዳልናገር አስጠንቅቃ ስልኩ ተዘጋ። ተቃራኒውን የማድረግ ፍላጎቱ ቢኖረኝም ምስጢሯን አክብሬ ቃሏን ለመጠበቅ ወሰንኩኝ።

ፍቅሩን በማጣቱ በእጅጉ ታመመ። ከምግብ ውሀ ራቀ። ስቃዩን መቋቋም ተስኖት ከሚኖርበት ቀዬ ተሰዶ ቱርክ እንደደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ህንፃው በላዩ ላይ ፈረሰ። የመጨረሻ እስትንፋሱ ላይ ሆኖ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አንጋጠጠ "በዱንያ ዓለም ዳግም እንደማንገናኝ ይሰማኛል ግን አላህ በጀነቱ ከአንቺ እንዲያጋባኝ እለምነዋለሁ" እያለ ሩሑ ከጀሰዱ ተላቀቀ። ይህንን ክስተት የሚያትት ደብዳቤ ከወዳጆቹ ደረሰኝ ይላል የታሪካችን ተራኪ።

ፌይሩዝም ከወራት በኋላ በሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከዚህ አለም በሞት ተለየች። ስለምታዝንለት ብቻ እንደተወችው ትነግረዋለች። እሱም ይቅር ይላታል ኢንሻ አላህ።

ስንት ተፋቃሪ ጥንዶች በሰው አልባ አውሮፕላኖች ተለያይተዋል?
በሚሳኤሎች ተበታትነዋል?! በሀዘን የታጨቀ የታሪኩን መጨረሻ የማያውቅ ስንትና ስንት አለ?!
በሚሳኤል ከመገደላቸው በፊት "እወድሀለሁ" የሚለውን ቃል ከሚስቶቻቸው ለመስማት የጓጉ ስንት ባሎች ነበሩ?!

የቦምብ ፍላፃ ሲነጥላቸው ተቃቅፈው የነበሩም በርካቶች ናቸው። ታሪክ ራሱን ጋዛ ላይ እየደጋገመ ይገኛል። አላህ ይርዳቸው።

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ

Mahi Mahisho

https://t.me/Abu_Umair2

1 month, 3 weeks ago

**ረመዿን 18 / 1444 ሂ

የመጨረሻዎቹ 10 ቀናት

🎙 አማን ኢብራሂም

ቦሌ ቡልቡላ አንሷር መስጂድ**

https://t.me/Abu_Umair2

1 month, 3 weeks ago

ረመዷን 17፦ ጁዝእ፡ 17

ቃሪእ፡ ማሂር አል-ሙዐይቂሊ

https://t.me/Abu_Umair2

1 month, 4 weeks ago

ረመዷን 10፦ ጁዝእ 11

ቃሪእ፡ አሕመድ አል-ዐጀሚ

https://t.me/Abu_Umair2

1 month, 4 weeks ago

ጾምና ሙቀት

🔅ሙቀት በበረታበት ጊዜ እየተቸገሩ መጾም ምንዳን ከፍ ያደርጋል። ደጋግ የአላህ ባሮች ዱኒያ ላይ መቆየትን እንዲመኙና እንዲወዱ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከልም አንዱ ጾም በሚከብድበት ጊዜና ቦታ ላይ ችግሩን ተቋቁሞ መጾም ነው።
🔅አቡ አድ'ደርዳእ رضي اللہ عنہ "በሙቀት ጊዜ (በረሃ ውስጥ) ጥምን ተቋቁሜ መጾም፤ የሌሊት ሰላት ላይ የሚደረግ ሱጁድና እውቀትን አዋቂዎች ዘንድ ተንበርክኮ መማር ባይኖር ኖሮ ዱኒያ ላይ መቆየትን አልፈልግም ነበር" ሲሉ፤
ታላቁ ሰሓቢይ ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ رضي اللہ عنہ
ደግሞ ምን ትመኛለህ ተብለው ሲጠየቁ "በጋ ላይ መጾም፤ በአላህ መንገድ እየታገልኩ ጠላትን በሰይፍ መምታትና እንግዳን በክብር ማስተናገድ " ብለዋል።
🔅ስለዚህ የዘንድሮ ጾም የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሙቀት በበረታበት ወቅት ላይ መሆኑ ይበልጥ ሊያስደስተን ይገባል።
🔅ከመሆኑም ጋር የሙቀትን ድካም የሚያቀንሱ ነገሮችን ማድረግ ይፈቀዳል። ለምሳሌ፥ በማንኛውም ሰዓት ገላን በቀዝቃዛ ውኃ መታጠብ፣ ፊት እና ጸጉር ላይ ውኃ ማፍሰስ፣ አፍን በውኃ መጉመጥመጥና መልሶ መትፋት፣ ከጸሐይ መሸሽ፣ አናትና ደረት ላይ የረጠበ ፎጣ ማስቀመጥ ወዘተ።

💥 የዱኒያው ቀላል ሙቀት የጀሀነሙን ከባድ ግለት አስታውሷቸው ከርሱ የሚድኑበትን መልካም ስራ ለመስራት ደፋ ቀና ከሚሉ ባሮች አላህ ያድርገን!

🔅ማታ ማታ ተራዊሕ ላይም ሙቀት አልችልም ብሎ ሰላት ትቶ ከመሄድ ይልቅ ታግሶና የጀሀነምን ግለት እያስታወሱ አላህን ከጀሀነም ጠብቀኝ ብሎ መማጸን በላጭና ብልሕነት ነው።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ረመዷን 10/1445 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ

https://t.me/Abu_Umair2

2 months ago

ረመዷን ዘጠኝ፦ ጁዝእ 10

ቃሪእ፡ ዐዲል ረያን

https://t.me/Abu_Umair2

2 months ago

🛑👉በረመዷን በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ቁርአን መቅራት እናብዛ። ነብዩ ከጅብሪል ቁርአን የሚማማሩት በረመዷን በሌሊቱ ክፍለጊዜ ነበር።

قال الحافظ ابن رجب رحمه الله :

‏`في حديث ابن عباس أن المُدَارسة بين النبي  ﷺ وبين جبريل كانت ليلًا.

👈 ‏وهذا يدل على استحباب الإكثار من التلاوة في ‌ رمضان⁠ ⁠⁩  ليلًا ؛ ‏فإن الليل تنقطع فيه الشواغل، ويتواطأ فيه القلب واللسان على التدَّبر.`

📚لطائف المعارف (٢٣٤)

2 months ago

أياما معدودات
|•|አምና ረመዷን 17ኛው ለይል ላይ በ ሰላም መስጂድ ከተደረገች ሙሓደራ የተወሰደ!―
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

2 months ago

ረመዷን 4

አሥራ አንድ ወራት ያበላሸነዉን አንድ ወርሀ ረመዷን ያስተካክልናል።ረመዷን የለውጥ ወር ነው፣ የተዘበራረቀ ሕይወታችንን መስመር ያስይዝልናል። ከአላህ የተሰጠን ችሮታ ነውና ዕድሉን በአግባቡ እንጠቀምበት።

2 months, 1 week ago
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago