Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Ethiopian Premier league Share company

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 месяц назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 месяц назад

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 недели, 1 день назад

6 days, 19 hours ago
6 days, 19 hours ago
Ethiopian Premier league Share company
1 week, 4 days ago

የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሚያዝያ 16 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ስምንት መደበኛ እና አንድ የ19ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ስድስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 12 ጎሎች በ11 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 45 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ ሶስት ቀይ ካርድ ተመዝግቧል።

በሳምንቱ በተጫዋቾችና አሰልጣኝ ቡድን አባላት ላይ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፏል። ወንድማገኝ ማዕረግ(ወልቂጤ ከተማ)፣ ፍቅሩ አለማየሁ(አዳማ ከተማ)፣ መናፍ ዐወል(ፋሲል ከነማ)፣ ቢኒያም ገነቱ(ወላይታ ድቻ) እና ዳንኤል ደምሴ(ወልቂጤ ከተማ) በሳምንቱ ጨዋታ አምስተኛ የጨዋታ ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን(ሲዳማ ቡና) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ  መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ፥ አጥናፉ ታደሰ(ሻሸመኔ ከተማ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሲሆን የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ የውድድር ደንብ  መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺ/ እንዲከፍሉ ፥ ፋሪስ አለው(ወልቂጤ ከተማ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ  ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

ሞሰስ ኦዶ /ቅዱስ ጊዮርጊስ-ተጫዋች/ የውሃ ፕላስቲክ ወደ ተጋጣሚ ቡድን ተጫዋቾች መቀመጫ ስለመወርወሩና አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን ተጫዋቹ የውሃ ፕላስቲክ በመወርወሩ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 25 000 /ሃያ አምስት ሺህ /እንዲሁም አፀያፊ ስድብ  በመሳደቡ 3/ሶስት ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3 000 /ሶስት ሺህ / እንዲከፍል ፥ ግዛቸው ጌታቸው/ወላይታ ድቻ-ምክትል አሰልጣኝ/ የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች አጸያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርበባቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ  መሠረት 6 /ስድስት/ ጨዋታ እንዲታገዱና ብር 5 000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍሉ እንዲሁም ጊት ጋትኩት(ሲዳማ ቡና) 10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከተ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 /ሁለት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

2 months, 2 weeks ago
2 months, 2 weeks ago
Ethiopian Premier league Share company
2 months, 2 weeks ago
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዲጂታል መፅሔት …

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዲጂታል መፅሔት - ቅፅ 3 ቁጥር 50

ቅፅ 3 ቁጥር 50 ሳምንታዊ ዲጂታል መፅሔት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ስታቲክሳዊ መረጃዎች ይዞ መጥቷል። በመፅሔቱ ውስጥ የጨዋታ ሪፖርት እና ተጨማሪ መረጃዎች ተካተዋል። ከታች ባሉት ሊንኮች በሁለት ቋንቋ(በአማርኛ እና እንግሊዘኛ) ያገኙታል። በቴሌግራም ገፃችን በፒዲኤፍም ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ

https://online.fliphtml5.com/gmtiv/fbtr/index.html

https://online.fliphtml5.com/gmtiv/tngi/index.html

4 months, 3 weeks ago
Ethiopian Premier league Share company
4 months, 3 weeks ago

የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ታህሳስ 08 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች ሰባት በመሸናነፍ ቀሪ አንዱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 23 ጎሎች በ21 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 43 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ ሶስት ቀይ ካርድ(በሁለተኛ ቢጫ) ተመዝግቧል ።

በሳምንቱ አራት ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። ሱሌማን ሀሚድ(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሲሞን ፒተር(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ወንድሜነህ ደረጄ(ኢትዮጵያ ቡና) በሳምንቱ ጨዋታዎች ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀማቸው ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ሲሆን ተጫዋቾቹ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱ እንዱሁም ሚሊዮን ሰለሞን(ሃዋሳ ከተማ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከተ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ተወስኗል ።

በአራት ክለቦች ላይም በተጫዋቾች ካርድ ምክንያት የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ ተላልፏል። ከሀምበሪቾ አቤል ከበደ፣ ቶሎሳ ንጉሤ፣ ምንታምር መለሰ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ እና ፀጋሰው ዴማሙ የተባሉ አምስት ተጫዋቾች፥ ከኢትዮጵያ መድን ኦሊሴማ ቺኔዱ፣ ንጋቱ ገ/ስላሴ፣ ሙሴ ከበላ፣ ያሬድ ካሳዬ፣ ተመስገን ዮሃንስ እና ያሬድ ዳርዛ የተባሉ ስድስት ተጫዋቾች፥ ከሀዲያ ሆሳዕና ብሩክ ማርቆስ፣ ኩሊባሊ ካድር፣ ተመስገን ብርሃኑ፣ ቃለአብ ውብሸት እና ሰመረ ሀፍተይ የተባሉ አምስት ተጫዋቾች ፥ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኪቲካ ጅማ፣ ብሩክ እንዳለ፣ ሱሌማን ሀሚድ እና ሲሞን ፒተር የተባሉ አራት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ክለቦቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡

4 months, 3 weeks ago
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም

⚽️ስምንተኛ ሳምንት ደረጃ ሰንጠረዥ

7 months, 3 weeks ago
Ethiopian Premier league Share company
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 месяц назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 месяц назад

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 недели, 1 день назад