The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 month ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
?? https://donorbox.org/zemedemedia እና
?? https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 months ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
?For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 10 months ago
በልጅነቴ ሪሞቱን እየነካካሁ ቲቪው ወደ Radio Mode ሲቀየርብኝ ከቤት ለመጥፋት አስቤ ነበር 😂****
*💖ፍቅር ያሸንፋል*❤️🔥 *💝ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በከምርጦችማህደር የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ*💝 ክፍል 9⃣ **እንዴት በቶሎ ሰከርኩ ወይስ እራሴን እንዳላውቅ መጠጤ ውስጥ መዳኒት አረጉብኝ? ምንም አላውቅም ብቻ ከንቅልፌ ባልነቃ ይሻለኝ ነበር እንደዛ እያለቀስኩና ደፍሮኛል ብዬ ያሰብኩትን ሰውዬ ምን እንደማደርገው እየዛትኩ የስልኬ ጥሪ አቃጨለ በዛ ስሜት ውስጥ ሆኜ ማውራት አይደለም ደዋዩን ማየት አልፈለኩም ዘጋ ከዛ ድጋሚ ተደወለ አሁንም ዘጋ በመጨረሻ አነሳሁት ይሄኔ የኔሰካራም አስቸኳይ ጉዳይ ስለነበረኝ ነው ሳትነቂ ትቼሽ የሄድኩት አለኝ ይሄ በትክክልም የዮናስ ድምፅ ነው ግን ጆሮዬን ማመን አቃተኝና ማን ልበል አልኩ ወይ ጣጣ ሰካራም ጓደኛ መያዝኮ ችግሩ ይሄ ነው ዮናስ ነኝ ስመጣ የተፈጠረውን እነግርሻለሁ አለኝ የማወራው ስለጠፋብኝ ምንም ሳልለው ተሰናብቶኝ ስልኩን ዘጋው፡፡ በህይወቴ እንደዚ ጓጉቼ የማውቅበት ቀን ትዝ አይለኝም ዮናስን አግኝቼው ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ጓጓው አንድ ልቤ ደግሞ ከኔ ጋር ነው ያደርሽው ቢለኝ ሀፍረቱን መቋቋም የምችል አልመስልሽ አለኝ ብቻ ግን ሰአቱ መገስገሱን ቀጥሎ ፀሃይዋ ለመጥለቅ ትሰናዳ ጀመር እኔም ስራ የማታ ተረኛ ስለነበርኩ የመስተንግዶ ዩኒፎርሜን ለበስኩ ምሽት 12፡00 ሰአት ላይ ዮናስ ደወለ ስራ መሆኔን ስነግረው መጣ ግን ለማውራት እድል አጣሁ እሱም ይህን ተረድቶ ጠዋት እንደሚመጣ ቃል ገብቶልኝ ወደ ቤቱ ሄደ:: ልክ ሲነጋ ከእንቅልፌ ስነቃ ቶሎ ብዬ ስልኬን አየሁ መልክት ገብቶልኝ ነበር ዮኒ ነው እዛው አካባቢ የሚገኝ ካፌ ቀጠረኝ ተጣጥቤ ወደዛው አመራሁ ልክ ስደርስ ተነስቶ ሰላም አለኝና እንድቀመጥ ወምበር ስቦ ጋበዘኝ ለሴት ልጅ ክብር እንዳለው ያሳያል እኔ ግን ጉዳዬ የትላንት አዳሬን ማወቅ ነበር እናም ትኩስ ነገር አዘን ማውራት ቀጠልን፡፡ እእእእእእ አልኩ ጥያቄዬን ከምን መጀመር እንዳለብኝ ለማሰብ እየሞከርኩ የኔ ቆንጆ የምሬን
ልንገርሽ በጣም ታምሪያለሽ አለኝ ይሄኔ እንዲ ሊከዳኝ እንደንግስት ሲክበኝ የኖረው ካሌብ ትዝ አለኝና አይደል አልኩት እውነቴን ነው ትላንት ያ ሰውዬ ቀጥሮሽም ቢሆን ፈልገሽም ብትሄጂም የእንቅልፍ ኪኒን ብርጭቆሽ ውስጥ መጨመሩ አናዶኛል ሲቀጥል ገና ልጅ ነሽ እድሜሽን ከሚመጥን ሰው ጋር አትዝናኚም?አለኝ፡፡ ንግግሩ ይበልጥ ሳበኝ ኪኒን? ብዬ ቃሉን ደገምኩትና አስከትዬ ከዛስ ቆይ አንተ እንዴት... ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ እኔ ገና በግዜ ስደውልልሽ ያለሽበትን ነግረሽኝ ነበር በርግጥ ና አላልሽኝም ግን መጣሁ ስመጣና ከሰውጋ ሳይሽ ልክ ባልሆንም ከፋኝ ከዛ ሰውዬውን እህቴ ናት ስለው አንቺም ምንም ብሰክሪም እንኳን አላሳፈርሽኝም ወንድሜ ነው ብለሽ ሙጭጭ አልሽብኝ እናም ይዤሽ ያደርሽበት ሆቴል ወሰድኩሽ አለና ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው ደሞ ያሳቅሽኝ አብረከኝ ሁን እፈራለው እያልሽ ስታለቅሺ አንጀቴን ነበር የበላሽኝ አለ ይሄኔ እኔም ምን እንዳረኩ እንኳ ባለማስታወሴ በሀፍረት አቀርቅሬ ፈገግ አልኩ ሳላስበው ደግሞ ምንም ሳያረገኝ ከዛ ሰውዬ ስላስጣለኝ በጣም ተደስቼና ወንድም ያገኘው ያህል ተሰምቶኝ ተነስቼ ጥምጥም አልኩበት ይሄኔ ከየት መጣ ሳልለው ካሌብዬ ከሰላም ጋር ካጠገቤ መቶ ቆመ ድንግጥ ብዬ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ይሄኔ ካሌብ አሀ ለካ አንቺም ወንድ አጊንተሽ ነው ትተሺኝ የሄድሽው አለኝ.......... በርግጥ ካሌብዬን አሁንም ቢሆን አልጠላሁትም ያም ማለት ግን በሱ ተስፋ አልቆረጥኩም ማለት አይደለም እናም ካጠገቤ መቶ ሲቆም ብደነግጥም በንግግሩ ግን በጣም ተናደኩ የከዳኝ ሳያንሰው ከዮናስ ጋር ጠረጠረኝ መጠርጠሩም ሳያንሰው ይሄን ያክል ቀን የት እንደሆንኩ እንኳ የማያውቅና ያላሳሰበው ሰው ዛሬ ደርሶ እሱው ተበዳይ ሆነ ሁኔታዬ ሲቀያየርበት ዮናስ ያስሚን ችግር አለ እነሱ ማናቸው አለኝ ይሄኔ ሰላም ቀበል አድርጋ እሱ ፍቅረኛዋ ነው እኔ ደግሞ ጓደኛዋ ስትል ንዴቴን መቆጣጠር ይሳነኝ ጀመር ግን ከመናገር ይልቅ ጥያቸው መሄድን መረጥኩ ዮናስ አላስቻለውም ጠብቂኝ ቢያንስ ልሸኝሽ አለኝ ፀጥ ብዬው እርምጃዬን ቀጠልኩ ፡፡
ዮናስም ከጎን ከጎኔ እየሄደ ባለትዳር ነበርሽ እንዴ አለኝ ዝም አልኩት እሺ ተይው አትንገሪኝ ቅድም ስታቅፊኝኮ ሀንግ ልትሰሪኝ ነው የሚመስለው የማቀፍ ልምድ እንደሌለሽ ያስታውቃል ሆ አንቀሽ ልገዪኝ ... አለና ከት ብሎ ሳቀ እውነትም ዮናስ ይለያል ከካሌብ ጋር ያሳለፍኩትን እያሰብኩ ስረበሽ እሱ ግን አስረሳኝ ጭራሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉን እረስቼ መሳቅ ጀመርኩ ከዛ ወደስራዬ ገባሁ ማታ ልምጣ ሲለኝ እና ላትመጣ ነው አልኩት እውነትም ቢቀር ይደብረኛል እሱም አንድ ቀን እንደካሌብ ቢከዳኝም እስከዛው ግን አብሬው በንፁ ጓደኝነት እቀጥላለው፡፡ እየሰራው የማስበው ጠዋት ካሌብዬ እንዴት ሰላምን አግኝቷት ነው አሷ ደሞ ማን ካፌ እንዳለው አውቃ ነው ይዛው የመጣችው እንዴት ወደኛ መጡ የሚለውን ነው ሲቀጥል ሰላም እንደዛ እንደተጎዳሁ እያወቀች ከካሌብ ጎን እንዴት ትቆማለች ጭራሽ ዮናስ እንዲርቀኝ ብቻ ሰላም ሁሉም ጠባሳዎቼ ላይ አሻራዋ ይታየኝ ጀመር እቺ ልጅ ከኛ ስር ለምን አልጠፋ አለች?? ብቻ ጭንቅላቴ እንዚን ጥያቄዎች እየፈጠረ ያስጨንቀኛል ግን ምንም መልስ ስላልነበረኝ በቃ አጋጣሚዎች ናቸው ብዬ አልፈዋለው. እንደምንም መሸ ይሄኔ ተጣጥቤ ልብሴን ቀይሬ ልወጣ ስል በር ላይ ካሌብን አገኘሁት አናግሪኝ አለኝ ግን ላናግረው አልቻልኩም ምክንያቱም በሱ ምክንያት እየሆንኩ ያለሁት በጣም ይጎዳል ዝምብዬው ስሄድ ለዚ ነበር ብዙ ፈተና አልፈሽ እኔን መርጠሽ የመጣሽው ለዚ ነበር አባትሽን አልሰማ ብለሽ እኔን የመረጥሽው? አለኝ ይሄኔ እርምጃዬን ገታ አድርጌ ማሰብ ጀመርኩ ከዛም ዞር ብዬ ምን ቀረህ ወይስ ሪታ ጥላክ ሄደች አልኩት እንደምታስቢው አይደለም ሲል ሊያሳምነኝ ሞከረ እኔም ከስካሁኑ ልፋቴ አይበልጥም ይቅርታ ላርግለት ብዬ ይቅርታ አረኩለት፡፡ ከካሌብ ጋር እንደገና አብረን መኖር ጀመርን በርግጥ በሙሉ ልቤ አላመንኩትም ግን ግዜ ሁሉን ያሳየኛል በሚል ፍቅር መስጠቴን ቀጠልኩ ሪታ ከቤታችን ወታለች ግን የት እንዳለች መጠየቅ አልፈለኩም ዮናስንም ሳገኘው ስለካሌብ ሁሉንም አጫወትኩት ግን ዮኒ ለምን ቀድመሽ አልነገርሽኝም አላለኝም ወንድም ሊሆነኝ ቃል ገባልኝ ካሌብዬ ደግሞ ዮናስ ከሚባል ልጅ ራቂ ሲል አስጠንቅቆኛል እኔም ካሌብዬን ቅር ከሚለው እያልኩ ዮናስን ማግኘት ተውኩ፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ተነስቼ ቁርስ እየሰራው ቤት አፀዳለው ይሄኔ የፍቅሬ እንቅፋት ሪታ በር አንኳኳች ስከፍት እሷ ናት በሩን ብጠረቅምባት ደስ ባለኝ ግን እንደምንም እራሴን ተቆጣጥሬ ምን ፈለግሽ አልኳት ካሌብን አለችኝ ካሌብዬ ተኝቷል አልኳት ፊቷ ልክ አይደለም እናም ችግር አለ አልኳት ይሄን ስል እንባዋ ዱብ ዱብ እያለ እርጉዝ ነኝ አለች ይህን ስትል ከካሌብ ነው እንደምትለኝ እርግጠኛ ሆንኩ ብዥ አለብኝ ...
ክፍል አስር ከ*2⃣*0⃣like👍በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍ማድረግ አይርሱ።
Admin x
Cross
emtfelgu anagrugn @anu_lil_peep
Like?❤️
አድርጉ ቶሎ እንዲለቀቅ ቤተሰብ??
ታሪኩ ይቀጥል?
comment
ሰላም ቤተሰቦቼ በያላችሁበት ሰላም ለናንተ ይሁን❤️?
?አዲስ ታሪክ ይጀመር አንባቢ አለ?
እስቲ አለን በሉ?
#ትሂድ አትከልክሏት//…
የዛሬን አይበለው አያድርገውና
ስታቆላጵሰኝ አኔን አሽሞንሙና
በሚያምር አንቀልባ ባለሰለሰችው
እንሷሱላ ሙቃ እጇን ባቀላችው
በጣፈጣ ገላ ሽቶ በቀባችው
እሹሹ ስትለኝ በድሎት አድጌ
ሄደች አትበሉኝ ዛሬ በማ‘ረጌ
♡♡♡
ይህ ነው ማንነቴ የዛሬ ፋንታየ
ያርባ ቀን እድሌ ልዩ ስጦታየ
ትሂድ አትከልክሏት…
ሰውነቴ አድፎ ጸጉሬ አስፈርቷት
ቡትቶ ደርቤ ህልሜ ጠፍቶ ታይቷት
ትሂድ አትከልክሏት…ከቶ አልፈርድባትም
ሰላሟን ትፈልግ ፍቅር ይገኛል የትም
♡♡
ማስታወሻ የላት ከኔ ላይ የቀረ
የህይወት አቅጣጫ እንድህ ተቀየረ
ትሂድ… መርቁልኝ ራሷን ፍለጋ
እኔም ወደ ጸሎት ይህ ቀን እስኪነጋ
♡
ትሂድ አትከልክሏት ጥልቅ ነው ሚስጥሬ
በመሄዷ አላዝንም ደስ ይበላት ፍቅሬ
እሷ ለኔ ስትል… እኔ ለኔ ኑሬ
አስከፍቻታለሁ ሳትሞት ቀብሬ
*? °?.•°@kemrtochumahaderr*?.•°**#Ѕнαяє#ʝσιи
???
መሄድ መለየትሽ ምንም እንኳን ቢያመኝ?
ሰዉ መሆንሽ እንጂ እኔን የጠቀመኝ?
ፈጣሪ ሲፈጥስሽ ገና ድሮ ድሮ
ጠባቂዬ መልአክ አርጎሽ ቢሆን ኑሮ?
እንዲህ እንዳሁኑ እንዲህ እንደዘበት
ጥለሽኝ ስትሄጂ ገንዘብ ወዳለበት?
ያለ ዘብ ትተሽዉ ክፍቱን የነፍሴን በር
በሌሊት #መጋኛ ባስመታሽኘኝ ነበር?
@kemrtochumahaderr
??????
ሼር አደራ ?
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 month ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
?? https://donorbox.org/zemedemedia እና
?? https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 months ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
?For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 10 months ago