Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Saint George Sport Club - Offical Page/የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል

Description
Professional Sport Club


Website -http://saintgeorgefc.com/blog/

Facebook - https://www.facebook.com/Saint-George-SA-177342563049631

YouTube -https://www.youtube.com/channel/UC1M4f0IYEbdcwjMz-QQrepg


💛❤አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ 💛❤
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

2 weeks, 2 days ago
***👉***ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት …

👉ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

👉የኢትዮጵያ ፕሪሚየር _ሊግ _23ኛ ሳምንት ጨዋታ
#Ethiopia_ premier_ League

⚽️ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዋሳ ከተማ ⚽️

📆 እሁድ ሚያዝያ 27/2016 ዓ.ም
🕗12:00
🏟 በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም
👉 ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ!!
https://t.me/stgeorge123
#ሼርShare_በማድረግ_መረጃውን_ለደጋፊዎች_ያጋሩ!

2 weeks, 6 days ago
***👉*** ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪምየር …

👉 ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር 22ኛ ጨዋታ

👉የጨዋታው ውጤት

⚽️ቅዱስ ጊዮርጊስ (20) 2 - 0 አዲስ አበባ ከተማ (20)⚽️ግዛቸው ጀማል 41'48'
💛❤️ድል -ለተስፋ ቡድናችን 💛❤️

3 weeks, 2 days ago
4 weeks ago

ይርበተበታሉ እንደያዛት ምጥ››
ይጨበጨባል፡፡፡ፉጨት ይሰማል እንደገና ሌላም ግጥም
የምን ማራዶና የምን ፔሌ ፔሌ
እኛም ሀገር አለ ገብረመድህን ሀይሌ......
ግጥሙ ለአሁኖቹ ብቻ ሳይሆን ታሪክ ለሰሩት ለነመንግስቱም እየተዳረሰ ነው፡፡ ምሽቱን ሲጨፈር አደረ፡፡ አልጋ ያላገኘ ድንኳን ጥሎ አደረ፡፡ለብቻው የተኛ አልነበረም አንድ አልጋ ላይ ተጠጋግተው ሶስትና አራት ሰው መተኛት ነበረበት፡፡ ፍቅር ካለ ..ምቾት ዛሬ አይስራም፡፡ፍቅር ካለ ታሲክም ባስ ይሆናል ይሉ የለ? እንደዚያ ነው፡፡ በነጋታው ሌላ ቀን ነው....ሁለቱ ቡድኖች መጋቢት 27 ቀን በኬንያ 0ለ0 ስለተለያዩ ጊዮርጊስ በጥንቃቄ ካልተጫወተ አደገኛ ነገር ይፈጠራል የሚል ስጋት ማሳደሩ አልቀረም፡፡የጊዮርጊስ እድል በማሸነፍ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው፡፡ብሪዌሪ ጎል አስቆጥሮ አቻ ከሆኑ ጊዮርጊስ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ተጫዋቹ በዝና ብቻ የሚውቁትን የጅማ ከተማ ህዝብ ማሳፈር የለበትም፡፡
የከተማው ወጣትና ነዋሪ ተጨዋቾቹ ባረፉበት ሆቴል ተኮለኩሉ ‹‹ዳኛቸው የቱ ነው?...ሙሉጌታ የቱ ነው?...ገበረመድንስ?.....እያለ በስምና በዝና የሚያውቃቸውን አላስገባም አላስወጣም አለ፡፡...... በነጋታው የድል ስታዲየም በሚል ስያሜ በሚጠራው ስታዲየም በነቂስ ወጥቶ ስታዲየሙን አጨናነቀው፡፡በስታዲየሙ ቢጫና ቀይ ባንድራ በዙሪያው ይውለበለባል፡፡ቡድኑም ያንን ግርማ ሞገስ የሚያጎናጽፈው ቢጫና ቀይ ማሊያ ለብሶ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን ወደ ሜዳው ዘልቆ የገባው የጊዮርጊስ ቡድን አረንጓዴ ማሊያ ለብሶ ብቅ አለ ፡፡ክለቡ ፈልጎ አልነበረም ይሄ ያደረገው፡፡የእንግዳው ቡድን ቢጫ ማሊያ ለብሶ ‹‹አርማዬ ይሄ ነው›› ብሎ በመገኘቱ ነው፡፡ወቅቱ ደግሞ የካፍ ህግ ለእንግዳው ቡድን ቅድሚያ የሚሰጥበት በመሆኑ ጊዮርጊስ ማሊያ ለመቀየር ተገደደ፡፡ነገር ግን ጊዮርጊስ ሁለተኛ ማሊያ አልነበረውም፡፡ምን ይሻላል?፡፡
የእርሻ ሰብል ቡድን ከጅማ ምርጥ ጋር ለመጫወት ወደ ከተማው ብቅ ብለው ነበር፡፡ በ8 ሰዐት ተጫወቱ ፡፡እርሻ የሚታወቁበትን አረንጓዴ ማሊያ ለጊዮርጊስ ሰጡና ያንን ለብሰው ወደ ሜዳ ብቅ አሉ፡፡ ደጋፊው ግራ ተጋባ ፡፡ጊዮርጊስን በዚህ አይነት ማሊያ አይተውት አያውቁም፡፡፡.የጅማ ድል ስታዲየም ከአቅሙ በላይ ይዟል፡፡ሀዝቡ ቆሞ ነው የሚያየው፡፡ ወደ ሜዳ የገባው የጊዮርጊስ ቡድን አሰላለፍ
ተሰፋዬ ዘለቀ
ሰይፉ(ኮማንደር)
ሰለሞን ሀይሌ
ዳኛቸው ደምሴ
ታረቀኝ ቢሻው
ሰለሞን ዮሀንስ
ህሩይ እቁበእዝጊ
አዲስ ብስራት
ሰለሞን መኮንን
ሙሉጌታ ከበደ
ገበረመድን ሀይሌ
እንደተጀመረ በህዝቡ ጩኸት እየታገዙ ጊዮርጊሶች በፍጥነት ያጠቃሉ፡፡ግብ ግን የለም፡፡በዝና ብቻ የሚያውቃቸው የጅማ ደጋፊ አሸናፊነታቸውን ማየት አለባቸው፡፡12ተኛ ደቂቃ ሆነ ፡፡ሰለሞን ሀይሌ እገፋ ሄዶ ለገብረመድን ሰጠው፡፡ ገብረመድን ለህሩይ አቀበለ፡፡ ህሩይ አታለለና ለገብረመድን፡፡ገብረመድህን እንደገና ለህሩይ....... ህሩይ እይታለለ ሄደ፡፡ አሾልኮ ለሙሉጌታ ሰጠው፡፡ ሙሉጌታ በጥግ በኩል ገባ፡፡ በረኛው ባጠበበት በአስደናቂ ሁኔታ አሰቆጠረ፡፡ ደጋፊው በጭፈራ ስታዲየሙን ቀውጢ አደረገው፡፡ብረት እንደጋለ መቀጥቀጥ እንደሚባለው ሁካታው እንደቀጠለ ማጠዳፍ ተጀመረ፡፡ ከአስር ደቂቃ በኋላ ገበረመድን እያታለለ ሲገባ በመጠለፉ ሪጎሬ ተገኘ፡፡ዳኛቸው ደነሰ፤ ጨፈራና በረኛውን ሸውዶ አስቆጠረ፡፡
ማታ ነው ድሌ የሚለው ዘፈን ቀረ፡፡ማታ እስኪሆን የሚያስጠብቅ ነገር አልነበረም ፡፡በጧት ድሉ ተገኝቷል፡፡ እረፍት ሊወጡ አንድ ደቂቃ ሲቀር ብሪወሪ አገባ፡፡ከእረፍት መለስ ተጨማሪ ግብ ለስማቆጠር መሯሯጥ ተጀመረ፡፡ ሆኖም ግን የቡድኑ ቴምፖ እተቀዛቀዘ መጣ፡፡ ብሪዎሪ ማንሰራራት ጀመረ፡፡ጊዮርጊስ በእጁ የያዘውን እድል ላለማጣት መከላከል ጀመረ ፡፡አሰልጣኙ ታደሰ ወልዳረጋይ ከሜዳቸው ወጥተው እንዲያጠቁ ትእዛዝ ሰጠ፡፡በእርግጥም ማጥቃት ጀመሩ፡፡ ግን ግብ የለም፡፡ጊዮርጊስ እንደመጀመሪያው ባለመሆኑ ደጋፊው ስጋት ውስጥ ወደቀ፡፡ ብሪዎሪ እያጠቃ መጣ ፡፡ነገሩ አስፈሪ ነው፡፡ብሪዎሪ አንድ ግብ አስቆጥሮ አቻ ከሆነ ነገሩ አከተመ ፡፡ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋል፡፡ ይሄ ደግሞ መሆን የለበትም ፡፡የጅማ ህዝብ ለክለቡ የነበረውን ታላቅ አድናቆት መኮሰስ የለበትም፡፡
የባከነ ሰዓት ላይ በግብ ክልላቸው ቅጣት ምት ተገኘ፡፡አደገኛ ነው ፡፡ቅድም ያገባው የብሪወሪ ተጫዋች ለመምታት ተዘጋጀ፡፡ ሁኔታው የሚያስፈራ ነው፡፡በዚህ ሰኣት ከተቆጠረ አከተመ፡፡ ቅጣት ምቱ ከመመታቱ በፊት የጊዮርጊስ ደጋፊ ሜዳ ገብቶ አጥር ቢሰራ ደስ ባለው ነበር፡፡ነገር ግን መቺው ወደ ውጭ ሰደዳት ፡፡የብሪወሪ የማለፍ እድል እንደዚህች ኳስ ተነነና የማለቂያ ፊሽካ ተነፋ፡፡እንደገና ጭፈራ ፡፡ጅማ ደመቀች፡፡ሲነጋ ግን ዝናብ ነበር፡፡
. በነጋታው በጭፈራ ጉዞ ተጀመረ፡፡ ተጫዋቾቹን መሀል አድርገው አውቶብሶቹ በጡሩንባ እያስገመገሙ ጅማን ቻው ብለው ነጎዱ፡፡ማርሽ ተቀያየረ፡፡ከተማው ጫፍ ኬላው ጋር ደረሱ፡፡፡የእንጨት መቀርቀሪያ ተወድሮ አውቶብሶቹ እንዲቆሙ ምልክት ሰጠ፡፡ጡሩምባው ማርሽ ባንድ በሚመስል ሁኔታ የሚያምቧርቁት አውቶብሶቹ ‹‹ዝነኛው የጊዮርጊስ ባለድሎች ነው የያዝነው ገለል በሉ ››እያሉ እንዲያሳልፏቸ ምልከት ሰጡ፡፡ ነገር ግን ኬላውን ወጥረው የያዙት ፈታሾች ‹‹አውቶብሱን አቁሙ እንናተም ውረዱ›› አሉ፡፡ፍተሻ ተደረገ፡፡ ብዙ ቡና ጭነው ነበር፡፡
ተጫዋቾቹ በቋጠሮ የያዙትን ማራገፍ ነበረባቸው፡፡ነጋዴዎች አይደሉም፡፡ኮንትሮባንድም ሰርተው አያውቁም ፡፡ወደዚህ ከተማ እየተመላለሱ ቡና አይነግዱም፡፡ በእንግድነት ስለመጡ የጅማን ምርት ተቋድሰው ለመሄድ ነበር፡፡ደግሞም አስተዳዳሪው ስላስደሰታችሁን የምትፈልጉትን ያህል ይዛችሁ ሂዱ ብለው ፈቅደውላቸው ስለነበር ነው የያዙት፡፡ነገር ግን ፈታሾቹ ምህረት አልነበራቸውም ፡፡አንዲት ፍሬ እንዲያልፍ እድል አልሰጧቸውም፡፡አንድ የተበሳጨ ደጋፊ ፈታሾቹን ‹‹እነዚህ የብሪወሪ ደጋፊ ናቸው እንዴ ?››ብሎ እስከመናገር አድርሶት ነበር ፡፡ፈታሾቹ ስራቸው ነው ፡፡ነገር ግን ‹‹ትንሽ ለቤተሰብ የምንወስደው ልቀቁልን›› ቢሉም አልተሳካም፡፡ ልመናውን ባለመቀበላቸው ቅር አሰኛቸው፡፡ ብዙ ኪሎ ለተወሰደባው ተጫዋቾች ደጋፊው ኪሳራ እንዳይገጥማቸው እዛው ካሳ እስከመክፈል ደርሷል፡፡ኬላውን በድል ባይሻገሩም አስፈላጊውን ነጥብ ከብሪወሪ ወስደው ወደ ቀጣዩ ዙር መሻገር ችለዋል፡
ምንጊዜም ጊዮርጊስ ✌️

4 weeks ago

👉 ከማያልቀው ድንቅ ታሪክ - ዘወትር እሁድ ጠዋት
====/////====//////======
ሚያዝያ 12/1978 - ጅማ - የድል ብስራት
====/////====////=====
ከሰአት እላፊ ጋር እየታገለ በሌሊት ከየሰፈሩ ወደ ስታዲየም የነጎደው የጊዮርጊስ ደጋፊ አዲስ አበባ ስታደየም ተሰባስቧል፡፡ በዚህ ሁኔታ ላያቸው ሰው ያስገርማል ፡፡ በሌላ ቀን ቢሆን የቡድኑን ጨዋታ ለመከታተል ትኬት ስለማይገኝ በሌሊት ሰልፍ ይዘው ነው ሊያሰኝ ይችላል፡፡ዛሬ እዚህ ስታዲየም ወረፋ ለመጠበቅ አይደለም የተገናኙት ፡፡አላፊው አግዳሚው ሲመለከት በሌሊት ደጋፊው ስታዲየሙ አቅራቢያ ተሰብስቦ ሲጨፍር ምንድነው ነገሩ ያስብላል፡እንደወትሮው ስታዲየሙን ከበው ወረፋ አልጠበቁም፡፡
አስፓልቱ ላይ ተሰብስበው ባንድራውን እያውለበለቡ የድል ዜማ እያሰሙ ይጨፍራሉ፡፡ ነገሩ አሁንም በሌሊት ወደዚያ አካባቢ ለሚያልፉት መንገደኞች ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ጥቂት ቆይቶ አውቶብሶች በሰልፍ በመሆን በቀስታ እያሽከረከሩ እነርሱ ጋር ደረሱ፡፡ አውቶብሶቹ ተደረደሩ፡፡ ቁጥራቸው ከ30 ከፍ ይላሉ፡፡ የአንበሳ አውቶብስ ናቸው፡፡ መንገደኛው አሁንም ይመከለታል፤ አውቶብሶቹ የከተማ ቢሆኑ ወደ አንድ ሰፈር ሊጓዙ ነው ብሎ ይገምታል፡፡ የክፍለ ሀገር አውቶብስ ናቸው፡፡ ደጋፊው የተደረደሩትን አውቶብሶች እየዞረ ይጨፍራል፡፡ ጭፈራው አንድም የሌሊቱን ብርድ ለማላቀቅ ጭምር ነበር፡፡
እለቱ ሚያዝያ 11 ቀን 1978 ነበር፡፡ የአውቶብሶቹ ቀለምና ደጋፊው የያዘው ባንድራ ቀለም ተመሳሳይ ነበር፡፡ቢጫና ቀይ የአንበሳ አውቶብስ ቀለም ከጊዮርጊስ ማሊያ ጋር በመቀራረቡ አውቶብሶቹ የስፖርት ክለቡ ሰርቪስ ይመስሉ ነበር፡፡ የአንበሳ እግር ኳስ ክለብ ና ጊዮርጊስ ባይቀያየሩ ኖሩ አብረው አንድ ዲቪዚዮን መጫወት ይችሉ ነበር፡፡ አንበሳ በ1976 ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ሲወርድ ጊዮርጊስ ወደ ላይኛው ዲቪዚዮን ወጣና መንገድ ላይ ተላለፉ፡፡ የሚገርመው አንበሳ ለመውረድ የመጨረሻውን ጨዋታ ያደረገበትና ጊዮርጊስ ለማለፍ ወሳኙን ግጥሚያ ያደረገበት እለት ልዩነቱ የአምስት ቀን ብቻ ነው፡፡ አንበሳ ቡድኑ ወደ ታችኛው ዲቪዚን ቢወርድም ዛሬ ድርጅቱ አውቶብስ አንበሳ ለሆነ ክለብ አግልግሎት ለመስጠት በሌሊት አዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቷል፡፡ጭፈራው ካበቃ በኋላ እያንዳንዱ ለጉዞ የተመዘገበ የጊዮርጊስ ደጋፊ ስሙ እየተጠራ ወደ አውቶብስ ወስጥ ገባ፡፡ገብቶ ቁጭ አላለም፡፡ ጭፍራው ሆታው ቀለጠ፡፡ይሄ ሁሉ ነገር ለምድነው?
የጊዮርጊስ ቡድን ከ7 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በኢንተርናሽናል ውድድር ለመሳተፍ ወደ ጅማ ሊጓዝ ነው፡፡ወትሮ ጊዮርጊስ ኢንተናሽናል ውድድር በአ/አ ስታዲየም ነው የሚያደርገው ፡፡አንድም ቀን ሌላ ቦታ ተጫውቶ አያውቅም፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ከናይጀርያ ጋር በ1977 ባደረገው ጨወታ በተፈጠረው ረብሻ ስታዲየሙ በመታገዱ ከአዲስ አበባ መውጣት ግድ ነበረበት፡፡ መጀመሪያ የተመረጠው አስመራ ነበር፡፡ የፖለቲካ ሰዎች ወደዚያ ለቅስቀሳ ቡድኑ እንዲሄድላቸው አመቻችተው ነበር፡፡ ሆኖም ባልተወቀ ሁኔታ ቦታው ተቀየረ፡፡ ምናልባትም በርካታ ደጋፊ ቡድኑን እንዲከተል ቀረብ ያለ ቦታ እንደተመረ ይገመታል፡፡ ጅማ አዲስ ስታዲየም ከተሰራ ቅርብ አመት ስለሆነው እዚያ ለመጫወት ተመረጠ፡፡ትልቁ ችግር ትራንስፖርት ለማግኘት ነበር፡፡ በወቅቱ ለክፍለ ሀገር ጉዞ የትራንስፖርት እጥረት ስለነበር ይሄን ሁሉ ደጋፊ የሚያጓጉዝ አውቶብስ ለማግኘት ችግር ነበር፡፡
ወደ ክፍለ ሀገር የሚሰማሩ አውቶብሶች ቁጥር ውስን ነው፡፡ ወደ ምስራቅ ወይም ወደ ሰሜን አንድ ከተማ ግፋ ቢል ሁለት አንበሳ አውቶብስ እንዲሄድ ይመደባል፡፡ በአንድ ግዜ 10 አውቶቡስ ወደ አንድ ከተማ መላክ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ከብዙ ውጣ ወረድ በኋላ 20 ማስፈቀድ ተቻለ፡፡ እንደገናም ሌላ ተጨመረ፡፡ ችግሩ በቅድሚያ ስለታወቀ ደጋፊው ሎንችናዎችን በጋራዥ እያስመረመሩ ለጉዞ የተዘጋጁ ነበሩ፡፡ አውቶብስ ተፈቀደ፡፡መሄድ የሚችለው በተመደበው አውቶብስ ቢሆንም በርካታዎች ተመዝግበው ነበር፡፡ አቅም ያለው መኪና እየተኮናተረ የተቀረው በግሉ መኪና ወደ ጅማ ተመመ፡፡ ወደ ከተማው ለመግባት አምስት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው እንዲቆሙ ተነገራቸው፡ ፡እነርሱ ወደ ከተማው ከመግባታቸው በፊት ህዝቡ ወደ እነርሱ መጥቶ የክብር አቀባበል ተደርጎ ተያይዘው ወደ ከተማው እንዲገቡ ነው፡፡ሀሳቡ ጥሩ ነው፡፡ በሞተር ሳይክል፤ ብስክሌት፤በፈረስና በተለያየ ትራንስፖርት በማጀብ እየተጨፈረ ወደ ከተማው ሲገቡ የሀገሬው ሰው ከዚህ በፊት ለእግር ኳስ ታይቶ በማታወቅ ሁኔታ በመንገድ ሰው ወጥቶ እያጨበጨበ የክላክስና የጥሩምባ ድምጽ እያደበላለቀ ቀውጢ አደረጉት፡፡
በከተማው ልዩ ነገር ተፈጠረ ሁኔታውን ላየ ትልቅ ብሄራዊ በዓል ይመስል ነበር፡፡ሆታና ጭፍራው ጊዮርጊስ አሸንፎ ዋንጫ ይዞ የገባ እንጂ ገና ለመጫወት ወደ ከተማው ሊገባ ነው ብሎ ያመነ አልነበረም፡፡ እያገሳ፤እያሰገመገመ ና እያንጫጫ የገባው ደጋፊ ከተማዋን በአንድ እግር አቆማት፡፡ የብሪወሪ ተጨዋችና አባላት ያንን ሁሉ ደጋፊ ሲያዩ ተደናገጡ፡፡የአንበሳ አውቶብሶችን አይተው ክለቡ ብዙ አውቶብስ እንዳለውና ሀብታም ክለብ እንደሆነ ተናገሩ ፡፡የአውቶብሱቹ ቀለምና የጊዮርጊስ ማሊያ ስለተመሳሳለ የክለቡ አውቶብስ ነበር የመሰላቸው፡፡ ቅዳሜ ምሽቱን ሁሉ አልጋ ያገኘና ያላገኘ በአንድ ስፍራ ተሰባስቦ መጨፈሩን ተያያዘው፡፡ ከአዲስ አበባ የመጣው ብዙ ቢሆንም ከጎሬ፤ በደሌ መቱ የመጡትም ደጋፊዎች ቁጥር ስፍር አልነበራቸውም፡፡
የከተማው ቡና ቤቶች ሙዚቃቸውን ዘግተው ደጋፊው እየጨፈረ አደመቁት፡፡ በየቡና ቤቱ ቦታ የለም ቆሞ ይጨፍራል ቢራ ይጎነጫል፡፡ በከተማው የቢራ እጥረት እንዳይፈጠር ፋብሪካው ቀድሞ በማዘጋጀቱ ለእንግዶቹ ችግር አልነበረም፡፡ ጋባዥና ተጋባዥ አይተዋወቁም፡፡ ማን ማንን እንደሚጋብዝ ስልት ባይኖረውም ብቻውን የሚበላና የሚጠተጣ አልነበረም፡፡ ሁሉም ነገር የጋራ ነው ፡፡ ጠጪ ይኑር እንጅ ለግብዣው ችግር አልነበረም፡፡ አንዱ ጓደኛውን ሲጋብዝ ለእሱ ደግሞ ሌላ ሰው ሲጋብዘው ከተማው ተለየ ድባብ ነበረው፡፡ተጋባዥ ጋባዥን አያውቅም፡፡ ማወቅም የለበትም፡ ሁሉንም እዚህ አምጥቶ ያስተሳሰራቸው ጊዮርጊስ ነው፡፡አሳላፊ ተጋባዥ ሆኖ ያመሸበት በከተማው ልዩ ነገር ተፈጠረበት እለት ነው፡፡
ሚያዝያ 11!!!!
ስለነገው ጨዋታ ማንም የሚያስብ የለም፡፡የጊዮርጊስ ደጋፊ በሰሜን ደቡብ፤ ምስራቅ፤ ምእራብ ያለው ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ግዜ የተገናኘበት እለት ነው፡፡የካታንጋው፤የትሪቡኑ ምስመር ተራው በጋራ አንድ ሌሊት የሚያሰላፉበት እለት ሆነ፡፡ወትሮ በአዲስ አበባ ከድል በኋላ ይጨፈርና ሁሉም ወደ ሰፈሩ ይተማል፡፡ዛሬ ግን ማንም ወደ ሰፈሩ የሚሄድ የለም፡፡ ሁሉም በየቡና ቤቱ ስለጊዮርጊስ ክለብ ይጨፍራል፡፡ የነገውን ነገር ለሚያምናቸወ ገብረመድህን፤ ዳኛቸው ታረቀኝ፤ህሩይ....ለእነርሱ ትቷል፤፡፡......... አዝማሪ በየቡና ቤቱ ይገጥማል፡፡ አንዱን ይጥላል ሌላውን ያነሳል ...እንካ ተቀበል ይላል፡፡አንዱ ለአዝማሪ ግጥም ይሰጣል ‹ ገብርዬ ሲመታ ሙልዬ ሲሮጥ

4 weeks ago

2ኛአጋማሽ 90'+7

⚽️ ወላይታ ዲቻ 1 - 0 ቅዱስ ጊዮርጊስ ⚽️

💛❤️ ድል ለታላቁ ክለባችን 💚💛❤️

2 months, 3 weeks ago
Saint George Sport Club - Offical …
2 months, 3 weeks ago
Saint George Sport Club - Offical …
2 months, 3 weeks ago
Saint George Sport Club - Offical …
5 months ago
የተራዘመው የደርቢ ጨዋታ የሚደረግበት ቀን፣ ሰዓት …

የተራዘመው የደርቢ ጨዋታ የሚደረግበት ቀን፣ ሰዓት እና ስታዲየም መረጃ !

ቅዳሜ ህዳር 29/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወቃል።

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተደረገ ውይይት የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የ7ተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዳሜ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአዳማ ከተማ - አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

ⓒ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago