The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 2 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months ago
ሁሉም ነገር ያልፋል።ሲያልፍ ግን ግዜ በክንውን ነው...እንጂ ክንውን በግዜ አይደለም። ሁሉም ነገር ሲፈፀም ግዜን ተከትሎ ነው የሚፈፀመው! አላህ ፈፅሙ ያለንን ስንፈፅም አፈፃፀማችን ግዜ አለው። ለዚያ ነው ግዴታ፣ሱና፣ዋጂብ እንዲሁም ፈረድ የሚባሉት በግዜ ላይ ጥገኛ የሆኑት።ከተገበርናቸው በግዜ ተጠቀምን ይባላል። በተቃራኒው አራም፣ ሙነከር፣ ቢድዓ እንዲሁም ኩፍር የሚባሉት ሰዎች ሲተገብሯቸው ባላቸው ግዜ ላይ ነው። ከተተገበሩ ግዜ ባከተነ ይባላል። አንድ ሰው ግዜውን ከሚያባክኑ ሰዎች ውስጥ ነው, አልያም ግዜያቸውን ከሚጠቀሙ ሰዎች ውስጥ ነው።ልብ በሉ መሀል ሰፋሪ የሚባል ነገር በዚች አለም ላይ እንደሌለ! ለዚያም ነው አላህ ስለሰራነው ስራ የቂያማ ቀን ሲጠይቀን ሁሉም ጥያቄዎቹ ከግዜ ጋር የተያያዙ ናቸው።ለዚህም ረቂቅ ምክንያቱ ግዜ ማለት ህይወት ስለነበረ ነው!
ትክክለኛ ሙስሊም ሁሌም ግዜውን ይጠቀምበታል..ምክንያቱም ለዚያ የአላህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሆኑት ዘንድ ማለት ነው።
------------------- መልካም ግዜ ------------------
ISLAMINDSET
የሙዕሚን መሳሪያ
ዘመናችን ከየትኛውም ግዜ እና ሰዓት በላይ ቀላል ምቹ ቢሆንም ከየትኛውም ዘመን በላይ ግን የሰው ልጆች ደም እንደ ወንዝ ዥረት በየቦታው እየፈሰሰ ይገኛል። በተለይም በአላህ አንድነት ጥርት አድርገው ባርነታቸውን ባረጋገጡት ሙዕሚኖች ደግሞ በጣም ባስ እያለ መጥቷል።ነገር ግን በአንፃራዊ ሰላም ላይ ያሉ ሙዕሚኖች ድቅድቅ ባለ የድሎት ዝንጋቴ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ የህይወት ገጠመኞች ሲታይ ይስተዋላል። ለዚያም ይመስላል አላህ በተለያዩ የዱንያ ህይወት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈተና ውስጥ የሚያስገባን! የሰላምን ትንፋሽ ተነፍገው በጥበት ላሉ ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን የነሱን ህመም ህመማችን ነው ብለን ከየትኛውም የአጀንዳ እንቅስቃሴ ነፃ ሁነን ልባችን ተቃጥሎ ዱዓ የማናረግላቸው..ምክንያቱም አላህ የሱን መሳሪያ በግልፅ ነፍጎናል። የሙዕሚን ዋነኛው መሳሪያ እና አስተማማኙ ዱዓ ብቻ ነው። ልባችን ተቃጥሎ ከውስጣችን ዱዓ ስናደርግ የኛም ህይወት ይቀላል።
አላህ ከልባቸው ዱዓ ከሚያደርጉት ባሮች ያድርገን!
#gaza
#dua
#islamindset
አላህ እኛ ሙስሊሞችን ደረጃ የሚሰጠን በስብስብ ብዛታችን ሳይሆን በዉስጣችን ባለው የተቅዋ ጥንካሬያችን ብቻ ነው።በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ይሄንን ዘንግተነዋል።ለዚህም መረጃው እንደ ገለባ በዝተን በመካከላችን ፍሬ መታጣቱ በቂ ነው። አላህ ብቸኛን ሰው ከህዝብ መንጋ ስብስብ እንደሚበልጥ በራሱ ንግግር በሚገባን መልኩ አሰቀምጦልናል።ማስተንተኛ አዕምሮ ካለን! ስለዚህ የራሳችንን ትልቁን የቤት ስራችንን ሳንጨርስ ሌላ ስራዎች አንጀምር።ምክንያቱም እንሰበራለን። ሁላችንም በመጀመሪያ ተቅዋችንን እንመርምር! የሙስሊም ትልቁ አጀንዳ ስብስብን ማጠናከር ሳይሆን ተቅዋን በልብ መጠንከር የሚችልበትን መንገዶችን መስራት እና መዘርጋት ነው። ይህ የዛሬው መልዕክታችን ነው አላህ ከመጥፎ ነገር ሁሉ ይጠብቃችሁ...!
#አሚን..
t.me/@mind_islam
#share
#like
#ቤተሰብ_ይሁኑ
በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ።
ያንተ ማንነት ለነገሮች ቦታ በምትሰጠው ነገር ይወሰናል።ለጊዜውም ቢሆን...!
ለነገሮች ቦታ መስጠት ማለት ደግሞ ውድ የሆነውን ሰዓትህን በምሰጠው ነገር ማሳለፍ ማለት ነው። ምንድን ነው የምታሳልፈው ሰዓትህን ራስህን ጠይቅ...!?
" ጥንካሬ ሲተረጎም!"
ብዙዎቻችን በብዙ መልክ ጥንካሬን የምንለካበት ሚዛን ይኖረናል። አንዳንዶች ተሳስተን, ሌሎቻችን ደግሞ ልክ ልንሆን እንችላለን። በብዙ እይታዎች አንፃር!.. አንዳንዶች ጥንካሬን ባልተረጋገጠ ታሪክ ስንለካ፤ ሌሎች ደግሞ ባለንበት ዘመን በሚከወነው እውነታ ይመዝኑታል።ጥንካሬን ከሀብት እና ከማጣትም ጋር የሚመዝኑም አይጠፉም። ከዚህም ባስ ሲል... ጥንካሬን ከጀግንነት ጋር በማያያዝ... ክብረትን እና ዝናን ማገኘት የመጨረሻው ቁንጮ ነው ብለው የሚያስቡ ሙስሊሞችም ከምንግዜውም በላይ ተበራክተዋል። ይሄ ሁሉ አስተሳሰብ ከእምነታችን መላላት መሆኑን ሙስሊሞች ልብ ልንል ይገባል።በተለይ ወጣቶች! የሰው ልጅ በእምነት የሚኖር ፍጡር ነው።ሌሎች ፍጡሮች ለአላህ ተገዢነትን ብቻ እንጂ የኔ እምነት ይሄ ነው ብለው አይናገሩም አይወያዩም ብሎም በዕምነታቸው ምክንያት አይጋደሉም፣ መስዋት አይከፍሉም። የሰው ልጅ ግን ለዚህ ታድሏል።ጥንካሬ የሚመዘነው በእምነት ብቻ ነው። እኛ ሙስሊሞች በኢማናችን ልክ ነው ጥንካሬያችን! ለአላህ ባለን ቅርበት እና ርቀት ብቻ ነው የምንለካው። የዘር እና የቀለም፤የጎሳና የጎጥ፣የተራነት እና የባለስልጣንነት በኢስላም ላይ ቦታ እንደሌለው ምሳሌ አድርገን ልንወስድ የሚገባን, የነብይነት ህይወታቸው የ23 አመት ጉዞ ብቸኛ መመዘኛችን መሆኑን እንወቅ፣እንገንዘብ። ከጥቃቅን እስከ ትላልቅ የእለት ከእለት ዉሏችን በቁርአን አንቀፆች እና በሀዲሶች ይለካ! ዉስጣችንንም እንመርምር ፣የማይነጥፍ እና የማይዛነፍ ሚዛን ለጥንካሬያችን እናስቀምጥ። እንደ ተምሳሌታችን ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) ጥንካሬን በወህይ እውቀት እንገንባ! እምነታችን፣ኑሮአችን፣ትምህርታችን፣መረዳዳታችን፣ሰራችን፣ትግላችን ሁሌም በዲነል ኢስላም ይመዘን።ያኔ ጠንካሮች እንሆናለን። የተረሳውንም ጥንካሬን ለትውልድ እናስተምራለን እናሳያለን!..
t.me/@mind_islam
youtube.com/@islam_mindset
tiktok.com/@islam_mindset
fb.com/@islam_mindset
#ፎሎው_ያድርጉ
#ቻናሉን_እናሳድገው
#ቤተሰብ_እንሁን
#እንጠቀማለን_ኢንሻአላህ
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 2 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months ago