Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Ethio Construction

Description
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month, 2 weeks ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month ago

1 week ago
Ethio Construction
1 week ago
Ethio Construction
1 week, 3 days ago

💎*ወ/ሮ ህሊና ካላት የመሬት ይዞታ ላይ 400 ካ.ሜ የሆነ ቦታ በመስከረም 2 ቀን 1999 ዓ.ም በተደረገ የመንደር ሽያጭ ዉል ለአቶ ታረቀኝ በብር 500 ሺ ትሸጥላቸዋለች፡፡ ይህን ተከትሎ አቶ ታረቀኝ በገዙት ይዞታ ላይ (G+1) መኖሪያ ቤት ገንብተው በቤቱ ውስጥ መኖር ከጀመሩ 7 ዓመት ተቆጥሯል፡፡ ነገር ግን የይዞታውን ስመ ሀብት ወደ እራሳቸው ባለማዛወራቸው ወ/ሮ ህሊናን የይዞታውን ስመ ሀብት አዛዉሪልኝ ካርታና ፕላን ላሰራበት ብለው ቢጠይቋትም ሻጭ ወ/ሮ ህሊና ፈቃደኛ ሳትሆን ትቀራለች፡፡

ይባስ ብላ ለአቶ ታረቀኝ የሸጠችውን ይዞታ በስሟ ካርታና ፕላን አሰርታ ከይዞታዋ ጋር ትቀላቅለዋለች፡፡ ይሄን ጊዜ አቶ ታረቀኝ ይዞታውን የገዛሁበትን ብር 500 ሺ እና መኖሪያ ቤቱን ለማሰራት ያወጣሁትን ወጪ ብር 700 ሺ #በድምሩ ብር አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ ብር ወ/ሮ ህሊና እንድትከፍለኝ በማለት ክሳቸውን ለፍ/ቤት አቅርበዋል፡፡

#ጥያቄ** አቶ ታረቀኝ ይዞታውን የገዙበት ብር 500 ሺ እና ለመኖሪያ ቤቱ ግንባታ ያወጡትን ወጪ ብር 700 ሺ ፤ እንድትከፍል ፍ/ቤቱ ወ/ሮ ህሊናን ያስገድድ ይሆን*

መልሱን Next Post ላይ ይጠብቁ እናመሰግናለን፡፡

https://t.me/ethioengineers1

2 weeks ago

የመኖሪያ ቤት እጥረትን የሚያስወግዱ የፕሪካስት ሕንፃዎች

*ሀገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ ፈጣን የሆነ የህዝብ ቁጥር ዕድገት በሚታይባቸው ሀገራት ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ወይም አፓርትመንት እጥረት እየተከሰተ ነው፡፡

የሰው ልጅ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች አንዱ የሆነውን መኖሪያ ቤት ለኑሮ አመቺ በሆነ ቦታ እና ተገቢ በሆነ ወጪ ማግኘት ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡

ይህንን እጥረት እና ፍላጎት ለማሟላት ከሚያስችሉ የግንባታ ዘዴዎች ውስጥ ቀደም ብለው በተለያዩ ሳይቶች የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት የወለል ምንጣፎች፣ ግርግዳዎች እና ቋሚ ማዕዘኖች "ፕሪካስት ኮንክሪቶች" ትኩረት ከሚሹ የግንባታ ዘዴዎች መካል በቀዳሚነት የሚቀመጡ ናቸው፡፡

በፕሪካስት ቴክኖሎጂ በፋብሪካ ውስጥ እየተመረቱ በሰለጠነ መንገድ የሚገጣጠሙ የሕንፃ ቁሳቁሶች፣ የመኖሪያ ቤትን ዕጥረትን በፍጥነት ለመቅረፍ ከሚያስገኙት ተጨማሪ ጠቀሜታዎች እና የአመራረት ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡****የጥራት ደረጃን መጨመር እና መጪን መቀነስ

ለሕንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ ተገጣጣሚ ኮንክሪቶች የሚዘጋጁት ለቁጥጥር አመቺ በሆኑ ገላጣ ቦታዎችና መጠኑ ባልተዛባ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ውኃ በመሳሰሉ የግንባታ ቁሳቁሶች በመሆኑ አላስፈላጊ ብክነት ወይም ዕጥረትን በማስወገድ ወጪን ይቀንሳሉ፡፡

ኮንክሪቶቹ የሚዘጋጁት ከሰው ፍላጎት እና ተጽዕኖ በጸዳ፣ በፕሮግራም በሚታዘዝ (አውቶማቲክ) የማምረት ዘዴ በመሆኑ የተፈለገውን ምርት በተፈለገው ፍጥነት በማምረት የጊዜ ብክነትን ያስወግዳሉ፡፡

በተለመደው የሕንፃ ግንባታ ዘዴ በግንባታ ሳይት ላይ የተለያየ ቅርፅ ያላቸው ዲዛይኖችን ለመስራት የሚያስፈልጉ ውስብስብ የእንጨት እና የብረት ድጋፎችን በማስወገድ ለሚፈለገው ቅርፅ ሞልድ (ቅርፅ) ማውጫ በማዘጋጀት የተፈለገውን ዲዛይን በፍጥነት ለማምረት የባለሙያን ወጪን ይቀንሳል፡፡****አስተማማኝ የስራ ዕድል ይፈጥራል

አንድ የፕሪካስት ማምረቻ ድርጅት ወደ ማምረት ሂደት የሚገባው አንድ አስገንቢ ድርጅት ለሚሠራው ሕንፃ የሚያስፈልገውን የተገጣጠመ ኮንክሪት መጠን እና ዲዛይን መነሻ በማድረግ ቀደም ያለ የውል ስምምነት በመፈረም ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ አምራች ድርጅቱ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ የማያቋርጥ አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርለት ያደርጋል፡፡****የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳል

በፕሪካስት የሚገነቡ ሕንፃዎች ትርፍ የሆነ ሙቀትን በማመቅ በዝግታ ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ እንዲወገድ በማድረግ፣ በሕንፃ ላይ የሚፈጠረውን አላስፈላጊ ክብደት ወይም ጭነት በማስወገድ፣ በተለመደው መንገድ ሳይት ላይ ከሚገነቡ ሕንፃዎች ከ50 በመቶ የበለጠ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን ይቀንሳሉ፡፡

ይህን ብቃት እንዲላበሱ ከሚያደርጋቸው ውስጥ ለምሳሌ፣ የተለያዩ ፎቅ ባላቸው ሕንፃዎች ለወለል የሚዘጋጁ ውስጣቸው ክፍት በሆነ ብሎኬት እና ኮንክሪት የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ የኮንክሪት ምንጣፎች ከተለመደው ግንባታ ከ50 እስከ 60 በመቶ ክብደታቸው የቀነሰ ከመሆኑም በላይ ጥራታቸው በተጠበቀ እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት እና የመሳሰሉት የግንባታ ቁሶች የሚዘጋጁ ናቸው፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ፣ እንደየአስፈላነቱ ግንባታው በሚካሄድበት ቦታ ያለውን የከባቢ አየር ድምጽ መስተጋባት፣ የመሬት ርደት ወዘተን መነሻ አድርገው ስለሚመረቱ አላስፈላጊ የሆነ የኮንክሪት እና የኃይል ወጪን በመቀነስ  የበለጠ ዕድሜ እና ጥንካሬን እንዲኖራቸው የሚያደርግ ብቃት የተላበሱ ያደርጋቸዋል፡፡****ለዕድሳት፣ ለግንባታ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን ጊዜ እና ወጪን ይቀ ንሳል

በፕሪካስት ኮንክሪት የሚገነቡ ሕንፃዎች ከሚያስፈልጋቸው ቁሳቁሶች ውስጥ በብረት እና በኮንክሪት የሚዘጋጁ ተገጣጣሚ ወለሎች፣ በአራት መዐዘን እና በተፈለገው ቅርጽ የሚዘጋጁ ጠፍጣፋ የኮንክሪት ወለሎች ተገጣጣሚ ግድግዳዎች፣ የቋሚ እና የአግድም መዐዘን የኮንክሪት ፍሬሞች ይገኙባቸዋል፡፡ እነዚህ ተገጣጣሚ የግንባታ ቁሳቁሶች የሚዘጋጁት በተወሰነ ሳይት ላይ ሆኖ፣ በቀላሉ ሊገጣጠሙ በሚችሉ እና ለማጓጓዝ አመቺ በሆነ መጠን እና ዲዛይን ነው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ሳይት ላይ ጥሬ ቁሶችን በማቅረብ እና በተለመደው መንገድ ለመገንባት የሚያስፈልጉ የቁሳቁስ ማጓጓዣ፣ በኮንክሪት ሙሌት የሚወጣ የጉልበት እና የመሳሪያ አቅርቦት ወጪን ይቀንሳሉ፡፡ ክፍት የሆኑት የኮንክሪት ምንጣፎች እስከ 20 ሜትር የሚረዝም ቁመና የተላበሱ በመሆናቸው በተለመደው መንገድ ከ6 እስከ 10 ሜትር ብቻ በሚረዝም ፓሌት (የብረት ማዕዘን) እየተገጣጠመ የሚሞላ የኮንክሪት መዐዘን ለማዘጋጀት የሚያስፈልግ የጉልበትና የግንባታን ወጪን በመቀነስ ግንባታው በፍጥነት እንዲከናወን በማድረግ ያላቸውን ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡*

https://t.me/ethioengineers1

2 weeks ago

የ MS ፕሮጀክት ሶፍትዌር ጥቅሞች

የማይክሮሶፍት ፕሮጄክት ሶፍትዌሮች በእቅድ፣ በፕሮግራም አወጣጥ፣ በንብረት አስተዳደር እና በሂደት ላይ ለማገዝ በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።*⚫**በግንባታ ውስጥ የ MS ፕሮጀክትን ለመጠቀም አንዳንድ ቁልፍ ዓላማዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  1. የፕሮጀክት እቅድ ማውጣት፡ MS ፕሮጀክት የግንባታ ፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ዝርዝር የፕሮጀክት እቅዶችን ከተግባራት፣ ከችግሮች እና ከጥገኛዎች ጋር እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል።

ይህም የእንቅስቃሴዎችን ቅደም ተከተል በመለየት እና ሀብቶችን በአግባቡ ለመመደብ ይረዳል.

  1. መርሐግብር ማውጣት፡- የግንባታ ፕሮጀክቶች በተወሰነ ቅደም ተከተል መጠናቀቅ ያለባቸውን በርካታ ሥራዎችን ያካትታሉ።

MS ፕሮጄክት ዝርዝር መርሃ ግብር ለመፍጠር ፣ ለተግባራት ቀናትን ለመመደብ እና ሁሉም ነገር በጊዜው መጠናቀቁን ለማረጋገጥ ይረዳል።

  1. የሀብት አስተዳደር፡- የግንባታ ፕሮጀክቶች የተለያዩ ግብዓቶችን ማለትም ቁሳቁስ፣መሳሪያ እና ጉልበት ይፈልጋሉ።  ኤምኤስ ፕሮጄክት የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች ሃብቶችን ለተግባራት እንዲመድቡ፣ መኖራቸውን እንዲከታተሉ እና ከመጠን በላይ ወይም ከጥቅም ውጪ እንዳይሆኑ ያስችላቸዋል።

  2. የሂደት ክትትል፡ MS Project የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች የፕሮጀክቱን ሂደት በቅጽበት እንዲከታተሉ ያስችላቸዋል።

ይህ የተጠናቀቁ ተግባራትን መከታተል, መዘግየቶችን መለየት እና የጊዜ ሰሌዳውን እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከልን ያካትታል.

  1. ትብብር፡ MS ፕሮጀክት የፕሮጀክት ቡድኖች ሰነዶችን በመጋራት፣ ተግባራትን በማዘመን እና በእውነተኛ ጊዜ በመገናኘት በፕሮጀክት እቅድ እና መርሃ ግብር ላይ እንዲተባበሩ ያስችላቸዋል።

በአጠቃላይ የኤምኤስ ፕሮጄክት ሶፍትዌር የፕሮጀክት አስተዳደር ሂደቶችን በማሳለጥ፣ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና የግንባታ ፕሮጀክቶችን በወቅቱ እና በበጀት ውስጥ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።*

https://t.me/ethioengineers1

2 weeks, 2 days ago
2 months, 2 weeks ago

💥Hydraulics and water supply Lecture

🚧*ለዛሬ ደሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች ኣዘጋጅተናል

🌟⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት እንዳይገቡ ያግዳል ።

🌟⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3) አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል

🌟⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት (coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።

🌟⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ።

ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።

🌟⓹ ማጥራት (filtration)፦በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት  አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።

🌟⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ (በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች) ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።

ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።

በሃገራችን በዋነኛነት ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን።

ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።

ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ።

🏷ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን*

https://t.me/ethioengineers1

2 months, 2 weeks ago

💥ውል ለብዙ ስራዎች መቀላጠፍ መሰረት የሆነና የተለያዩ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ችግሩን የመፍቻ ዘዴ ነው። የአገራችን ህዝብ ስለውል ያለው ግንዛቤ የዳበረ ነው ለማለት የሚከብድ ቢሆን የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ባለሙያዎችን በማማከር ውል አዘጋጅተው ወደ ስራ የሚገቡበት ሁኔታ አለ። የሰው ልጅ በቃሉ ይታሰራል ነውና ውል ለሚያስፈልገው ጉዳይ ሁሉ ህጉን በተከተለ መልኩ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱ የተሻለ ነው።💫የዉል ይዘቱም የተለያየ ሲሆን የኮንስትራክሽን ሰራ ውል ስናዘጋጅ መከተል ያለብንን መንገድ ይህ የተዘጋጀው ፅሁፍ አብራርቶ ያስቀምጣል

https://t.me/ethioengineers1

2 months, 3 weeks ago

🌟የ ኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከ መሬት ወይም ከወለል ያላቸው ከፍታ

(Electrical Accessories Height from the floor):-

☑️ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ማለትም ማብሪያና ማጥፊያ፣ ሶኬት፣ ቆጣሪ፣ ዲስትሪቢዩሽን ቦርድ ወ.ዘ.ተ. ከወለል  ያላቸውን ከፍታ ነው የምናየው።
☑️ብዙዎቻችሁ ስለነዚህ አክሰሰሪዎች ትክክለኛ ቦታ ለማወቅ ብዙ መፅሐፍ አንብባችሁ ይሆናል፤ ምናልባት ትክክለኛ መረጃ አላገኝ ብላችሁ ግራ ተጋብታችሁ ይሆናል፤ ወይም ደግሞ አንፃራዊ  ትክክለኛ ቦታውን አውቃችሁ የምትሰሩም ትኖራላችሁ። ጭራሹንም ደግሞ ስለ አቀማመጡ ግድ የማይሰጣችሁ አስባችሁትም የማታውቁ መስራቱ ላይ ብቻ ትኩረት የምታደርጉ ትኖራላችሁ። ሁላችሁም ተከታተሉን መልሱን ታገኛላችሁ።
☑️አሜሪካን ሀገር የሚገኘው "ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ደንብ" ወይም "National Electrical Code" የተባለው የግል ድርጅት ስለሁሉም ጥቃቅን የሚባሉት እንኳን ሳይቀሩ በስፋት ህጎችንና መመሪያዎችን አስቀማጧል። አሁንም የአለማችን ሀገሮች እየተጠቀሙበት የገኛሉ። ነገር ግን የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ስላላቸው ከፍታ ምንም ያለው ነገር የለም።
☑️"አለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ደንብ" "International Electrical Code" ቢሆንም ግለፅ የሆነ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ስላላቸው ከፍታ ያስቀመጠው ነገር የለም።
☑️"የኢትዮጵያ ህንፃ ደንብ መመሪያ" ወይም "Ethiopian Building Code standard" የሚለው መፅሃፍም ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ህጎች በዚህ መፅሐፍ የሚዳኙ ቢሆንም አብዛኞቻችሁ እንዳያችሁትና ከስሙም እንደምንረዳው ለግንባታ/ለሲቪል ስራው ብቻ የተዘጋጀ ነው የሚመስለው ፤ ለማንበብ ስትሞክሩም እንቅልፍ ጠሪ ነው ። ራሱን የቻለ የኤሌክትሪክ ህግ የለም በዛ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ  ስራውም ተጠቅልሎ ለሲቪል ምህንድስናው ተሰቷል። እንኳን ስለኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች  ከወለል ስላላቸው ከፍታ ሌሎች ህጎችም መፅሐፉ ላይ የተጠቀሱት በግልፅ አልተቀመጡም።
☑️ ስለዚህ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች  ከወለል ያላቸው ከፍታ እነዚህ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ  ካልተጠቀሰ ለምን ከፍታቸውን ማወቅ አስፈለገ? ለምን እንደፈለግን አንዘረጋቸውም/አናስራቸውም?
🔸*መለሱም አዎ በግልፅ የተቀመጠው ህግ ያላቸው ሀገሮች ሊኖሩ ቢችሉም። እንደምሳሌ በተጠቀሱት ላይ ግልጽፅ የሆነ ህግ የለም። ነገር ግን ለእይታ እንዳይደብር በማሰብ፣ ለመጠቀም ለሁሉም አምች እንዲሆን፣ አደጋን ለመቀነስ በማሰብ እንዲሁም  አቅመደካምችን፣ ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተለመደ የከፍታ መጠን አለ።

🔹ስለዚህ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች  ከወለል ያላቸው ከፍታ የስምምነት ወይም የምርጫ ጉዳይ ነው። ነገር ግን በጣምም ከፍም ሆነ ዝቅ ማለት የለባቸውም የተለየ ፍላጎት ከሌለ በስተቀር። በተቻለ መጠን ፊት ለፊት የሚታይና ለአጠቃቀም ምቹ ማድረግ ነው። በብዛት የምንጠቀምበት የተለመደ ከፍታ አለ እሱን ከማየታችን በፊት የበለጠ ትኩረት ስለሚገባን ነጥቦች እንይ:-

🔘አንዴ በጀመርነው ከፍታ መጨረስ። ይህ የአብዛኛው ሙያተኛ ችግር ነው። ነገር ግን መሆን ያለበት ቦታ ላይ  በተለያየ ምክንያት ማድረግ ካልቻልን ትንሺ ከፍ ወይም ዝቅ ልናደርግ እንችላለን። 
🔘በተቻለ መጠን አክሰሰሪዎች ተመሳሳይ ቀለም፣ መጠንና ቅርፅ  እንዲኖራቸው ማድረግ
🔘ስንገጥም ውሃ ላክችን መጠበቅ መንጋደድ የለበትም። ትንሽም ቢሆን።
🔘point ለመጨመር ወይም ለመቀነስ ተብሎ ለይታ ደስየማይልና ከተለመደው አስራር ውጭ በፍፁም አለመስራት።
🔘ለአቅመ ደካሞች(ለሽማግሌዎችና ለአዛውንቶች)ና ለአካል ጉዳተኞች ሲባል ሶኬቶችን በጣም ዝቅ ማለት የለባቸውም፤ ማብሪያ ማጥፊያዎች ደግሞ በጣም ከፍ ማለት የለባቸውም።
🔘በተቻለ መጠን በጣም ህፃን ልጆች ካልሆኑ በስተቀር ሁሉም የቤተሰብ አባል እራሳቸውን ችለው አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ።
🔘አዲስ ዝርጋታ ካለሆነ በስተቀር የሚቀየር ወይም የሚጠገን ከሆነ ከፍታውን ከሌሎች ጋር እኩል ማድረግ ነው ያለብን።
🔘የሻወር ቤት ወይም የመፀዳጃ ሶኬትና ማብሪያ ማጥፊያ በተቻለ መጠን ከፍ ማለት አለባቸው። ይህ ብቻ ሳይሆን ከውሃ መራቅ አለባቸው።
🔘በተቻለ መጠን ከማንኛውም ኮርነር፣ በር፣ መስኮት ወ.ዘ.ተ. 35cm መራቅ አለባቸው።

🔸እነዚህን ግንዛቤዎች ከያዝን በብዛት  የተለመደውንና ከላይ የጠቀስናቸውን መሰረት ያደረገ የከፍታ መጠን በቀጣይ እናያለን።

🔹በበዛት የተለመደውና አብዛኛቻችን የምንስማማበት የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ያላቸው ከፍታ:-
የአክሰሰሪ ከወለል ያላቸው አይነቶች ከፍታ በ cm

  1. ማብሪያ/ማጥፊያ ...130-140
    2.ሶኬት ... 45-50
    3.ዲስትሪቢዩሽን ቦርድ...170-175
    4.ኪችን ሶኬት...90-100
    5.አኑንሴተር...170-175
    6.ቤል ስዊች...130-140
  2. ቆጣሪ...175-180
    8.ሻወር/መፀዳጃ ቤት ሶኬት..180-200
  3. ሻወር/መፀዳጃ ቤት ማብሪያ ማጥፊያ...150

🚧ማሳሰቢያ:- ከዚህ በፊትም እንዳልነው ዋናው ነገር ለአጠቃቀም ቀላልና ምቹ ማድረግ ነው።

ስለዚህ  ቦታው ላይ ያሉትን ነገሮች ታሳቢ በማድረግ እንደሁኔታው ከፍም ዝቅም ማለት ይችላል።

Via Amen Electric*

https://t.me/ethioengineers1

4 months, 3 weeks ago

💥የቁፋሮ ሥራ (Excavation works) ላይ መረጋገጥ ያለባቸው የቁጥጥር ነጥቦት

🌟*የቁፋሮ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቁፋሮዎች፣ አጎራባች ቦታዎች እና የመሬት መንሸራተት መከላከያ ዘዴዎች በባለሙያ ጥናት ሊደረግባቸው ይገባል።

ይመረመራሉ በመሆኑም በቁፋሮ ሥራ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያው የሚከተሉትን ነጥቦች ትኩረት አድርጎ ማረጋገጥ አለበት።

1. የአጎራባች ወሰንን ከመፍረስ መታደግ፦ በግንባታ ሥራ የመጀመሪያው ተግባር ቁፋሮ ሲሆን ማንኛውም ቦታ አጎራባች የሆነ የሕንጻ ቦታ ወይም መንገድ የሚኖረው ሲሆን ቁፋሮው ወደአጎራባች ወሰን ተጠግቶ የሚከናወን ከሆነ በቁፋሮው መጠጋት አልያም በንቅናቄ (Vibration) የተነሳ የአጎራባች መሬት በመውደቅ ወይም በመንከባለል ለሁለቱም ቦታዎች አደጋ እንዳይፈጥር የሚያስችል ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉን ማረጋገጥ አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ የጎረቤት ወሰን/አጥር/ ቢፈርስ ወይም ሕንጻ ቢወድቅ በመሐንዲሱ የክትትል ድክመት የተነሳ ካሳ እንዲከፍሉ ሊገደዱ ይችላሉ።

  1. በሕግ የሚፈቀደውን የውጪ መስመር አለማለፉን ማረጋገጥ፦ ሕንጻው የሚሰራበት የካርታ ቦታ በአካባቢ ልማት (Local development plan) መሰረት ከፍተኛ የኢሌክትሪክ ኃይል (High Electric tension) የሚያልፍበት አልያም የመንገድ ማስፋፊያ ስፋት (Road Widening Area) የሚገባበት ሊሆን ስለሚችል በግንባታ ወቅት የተዘጋጀ አዲስ የፕላን ስምመትን በማመሳከር እንደዲዛይኑ በተፈቀደ ክልል ውስጥ ማረፉን እና በባለቤት ግፊት የተነሳ ያልተፈቀደ ቦታ ላይ አለማረፉን ማረጋገጥ አለበት።

  2. በቁፋሮ ክልል ደህንነትን ማረጋገጥ፦ ከቁፋሮው በኋላ ከመሬት ውስጥ ያለው ሥራ (Sub Structure Works) ተጠናቆ የተቆፈረው ክፍል እስኪሞላ ድረስ የሰከረ፣ ወይም የአእምሮ እክል ያለበት፣ ወይም ሕጻናት፣ ወይም ሽማግሌዎች ወደጉድጓድ ገብተው አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከተፈቀደላቸው የግንባታ ሰራተኞች ውጪ ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የታጠረ (Fenced) እና የውስጥ መሸጋገሪያ (Bridge Ladders) የተሰራላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

  3. የመሬት ውስጥ ዝርጋታዎች (Underground installations)፦ በሰፋፊ ግቢዎች ውስጥ ለግቢው አግልግሎት የሚሰጡ አስቀድሞ የተዘረጉ የውኃ፣ የኢንተርኔት፣ የመረጃ እና የመብራት ዝርጋታዎች የሚኖሩ ከሆነ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በጥንቃቄ እንዲነሱ አልያም ግንባታው ጉዳት ሳያደርስባቸው እንዲከናወን ማድረግ ይኖርበታል።

  4. የቁፋሮውን ልኬት ማረጋገጥ፦ በተለይ በአርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል እና ሳኒታሪ ንድፎች ላይ የተመለከተው ተጓዳኝ የቁፋሮ ሥራ የሚጠይቁትን ልኬቶች ማሟላቱን (ወርዱን፣ ስፋቱን፣ ርዝመቱን፣ ዲያሜትሩን፣ ጥልቀቱን) ጠብቆ ቁፋሮ መንዲከናወን የመቆጠጠርና መከናወኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።

  5. ውኃ እንዳይቋጥር ማስደረግ፦ በዝናባማ እና የመሬት ውኃ በሚፈልቅባቸው አካባቢዎች ቁፋሮ እንደተከናወነ ዝናብ ቢዘንብ ቢያንስ የጎርፍ ውሃ እንዳይገባ የመከላከያ ሥራዎች፣ እንዲሁም የመሬት ውስጥ ምንጭ ውሃን የመከላከያ (like: Permeable hardcore layer, geotextile material, channelization...) መንገዶች ተግባራዊ የሚደረጉበት መሆኑን ማረጋገጥና መከታተል አለበት።

  6. የቁፋሮ ግብአቶችና ማሽኖችን ደህንነት ማረጋገጥ፦ በቁፋሮ ሥራ መወጣጫ የሚሆኑ የብረት፣ የእንጨት እና የፕላስቲክ ግብአቶችን ብልሽት የሌለባቸው መሆኑ እና ለቁፋሮ ሥራ የቀረቡ የእጅ መሳሪያዎች እና ማሽኖች የደህንነት ችግር የሌለባቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።

  7. በቂ አየርና ብርሃን የሚገኝበት መሆኑን፦ በጣም ልዩ ሁኔታ የሚባልና በብዙዎቹ ግንባታዎች ላይ የማይገጥም ቢሆንም በውኃ ውስጥ፣ በመሬት ውስጥ ለሚከናወኑ ቁፋሮዎች የሚሳተፉ ሰራተኞች በቂ የሆነ የኦክስጅን አየር ማግኘት ስላለባቸው መሐንዲሱ የአየር ሁኔታውን የሚቆጠጠሩ ማሽኖች፣ አልባሳት እና ብርሃን መቅረባቸውን ማረጋገጥ ማድረግ አለበት።*

https://t.me/ethioengineers1

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month, 2 weeks ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month ago