Ethio Construction

Description
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 3 days, 16 hours ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 3 weeks, 3 days ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 8 months, 3 weeks ago

2 months ago
***✅******🔹*****Bad Construction***🏗*****

🔹Bad Construction🏗****

✅️Reasons for slab leaks:*
Slab leaks can be caused by poor quality or damaged pipes as well as improper installation. Leaks and bursts can happen when there are bends, kinks, or poor fittings.
✅️*Soil Shifts:*
Many factors can cause soil to shift, such as earthquakes and under construction the case of soil movement, pipes and connections bend and rub together, damaging them.
✅️*Poor Water Quality:
Your pipes can be damaged by poor water quality, such as hard water.

https://t.me/ethioengineers1

2 months ago
***✅***Set back***❗️******❗️***

Set back❗️❗️

2 months ago

የግንባታ ተቆጣጣሪ መሒንዲሶች (𝐒𝐮𝐩𝐞𝐫𝐯𝐢𝐬𝐨𝐫) ዋና ዋና ሥራዎች

🏷የግንባታ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (𝔖𝔲𝔭𝔢𝔯𝔳𝔦𝔰𝔬𝔯) የአንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአስተማማኝ፣ በብቃት እና ሀገሪቷ በምትጠቀምባቸው የግንባታ መሪ ሰነዶች (𝔰𝔱𝔞𝔫𝔡𝔞𝔯𝔡𝔰) መሰረት መከናወኑን የመቆጣጠርና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።

ተቆጣጣሪዎች ለግንባታ ባለቤት እና ተቁቅራጭ ዋና ዋና የግንባታ ውስንነቶችን ወይም 𝔠𝔬𝔫𝔰𝔱𝔯𝔞𝔦𝔫𝔱𝔰 ተብለው የሚታወቁትን (ወጪ ገንዘብ፣ ጥራት እና ጊዜ) በአግባቡ ለመጠቀም እና ከማንኛውም ግጭት ወይም ቅሬታ ነጻ ለማድረግ የሚሰየሙ አካላት ናቸው።

⭐️ጠቅላል ሲል የሚከተሉት የሥራ ድርሻዎች አሉባቸው።

[1] የጥራት ቁጥጥር - 𝑸𝒖𝒂𝒍𝒊𝒕𝒚 𝒄𝒐𝒏𝒕𝒓𝒐𝒍፦ የግንባታ ስራዎች የተቀመጡትን ደረጃዎች (𝚜𝚝𝚊𝚗𝚍𝚊𝚛𝚍𝚜) እንዲያሟሉ እና የፕሮጀክቱን የጥራት መስፈርቶች እንዲያከብሩ የስራውን ጥራት መከታተል

[2] የጊዜ አስተዳደር - 𝑻𝒊𝒎𝒆 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፦ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ (መርሐግብር) መሰረት እንዲጠናቀቅ የግንባታ ሂደቱን በየጊዜው መመዘንና መከታተል፣ መዘግየቶችን መለየት እና በፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ

[3] የሀብት አስተዳደር - 𝑹𝒆𝒔𝒐𝒖𝒓𝒄𝒆 𝑴𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፡ ለተገቢ ተግባራት ተገቢውን ግብአት መመደብ፣ ትክክለኛ ሰውን ለትክክለኛው ስራ በትክክለኛው ጊዜ መመደብ፣ የቁሳቁስ እና የመሳሪያ ሃብቶችን በብቃት ማስተዳደር፣ ለተያያዥ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት

[4] ደህንነትን እና ጤናን ማረጋገጥ - 𝑰𝒏𝒔𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒔𝒂𝒇𝒆𝒕𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒉𝒆𝒂𝒍𝒕𝒉፦ በግንባታው ቦታ ላይ የደህንነት እርምጃዎችን በመተግበር የደህንነት ፕሮቶኮሎችን በመከተል የመከላከያ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና አደጋዎችን እና ጉዳቶችን ለመከላከል እርምጃዎች እንዲተገበሩ ማድረግ

[5] የክፍያ ልኬቶችን ማስተዳደር - 𝑪𝒉𝒆𝒄𝒌𝒊𝒏𝒈 & 𝑨𝒑𝒑𝒓𝒐𝒗𝒊𝒏𝒈 𝑾𝒐𝒓𝒌𝒔 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅፦ ተቆጣጣሪዎች በኮንትራክተሩ ለክፍያ ጥያቄ የተዘጋጁትን መጠኖች የማረጋገጥ እና ትክክለኛ መጠን ከሆኑ ማሳለፍ ወይም አስተያየት በመስጠት ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ማስደረግ

[6] ተከታታይ ሥራዎች በጊዜው እንዲከናወኑ ማዘዝ/መፍቀድ - 𝑶𝒓𝒅𝒆𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒐𝒓 𝒑𝒓𝒐𝒄𝒆𝒆𝒅𝒊𝒏𝒈 𝒕𝒂𝒔𝒌፦ በተቋራጩ አስቀድሞ የተፈጸሙ ሥራዎችን በአግባቡ የተከናወኑ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ተከታይ (ቀጣይ) ተግባራት እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠት።

[7] ባለድርሻ አካላትና መገናኘት እና የሥራ ቅንጅትን መፍጠር - 𝑪𝒐𝒎𝒎𝒖𝒏𝒊𝒄𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒐𝒐𝒓𝒅𝒊𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፡-  ለፕሮጀክቱ ስኬታማ አፈፃፀም ያግዙ ዘንድ በተለያዩ የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል ለሚደረግ ንግግር ግልጽ እና ውጤታማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደ መገናኛ/ድልድይ ማገልገል

[8] የተፈጸሙ ስራዎችን ማረጋገጥ - 𝑪𝒐𝒏𝒇𝒊𝒓𝒎𝒊𝒏𝒈 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒌𝒔፡- የተከናወኑ የሥራ ክፍሎችን ለእያንዳንዱ ሥራ ማረጋገጫ በሆኑ ተያያዥ የፍተሻ ዝርዝሮች (𝚝𝚊𝚜𝚔-𝚛𝚎𝚜𝚙𝚎𝚌𝚝𝚒𝚟𝚎 𝚌𝚑𝚎𝚌𝚔𝚕𝚒𝚜𝚝𝚜) መገምገም እና የተግባር ማረጋገጫ መስጠት /𝚌𝚘𝚗𝚏𝚒𝚛𝚖𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም ውድቅ ማድረግ /𝚛𝚎𝚓𝚎𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም የጥገና ማዘዣ መስጠት /𝚖𝚊𝚒𝚗𝚝𝚎𝚗𝚊𝚗𝚌𝚎 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም እንዲፈርሱና እና እንደገና እንዲሰሩ ማዘዝ /𝚍𝚎𝚖𝚘𝚕𝚒𝚜𝚑𝚒𝚗𝚐 𝚊𝚗𝚍 𝚛𝚎𝚠𝚘𝚛𝚔 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም አሳማኝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ማድረግ /𝚖𝚘𝚍𝚒𝚏𝚒𝚌𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ የመሳሰሉትን ውሳኔዎችን /𝚍𝚎𝚌𝚒𝚜𝚒𝚘𝚗𝚜/ ለኮንትራክተሩ መስጠት

[9] ችግር መፍታት - 𝑷𝒓𝒐𝒃𝒍𝒆𝒎 𝑺𝒐𝒍𝒗𝒊𝒏𝒈፦ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ተግባራዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ያልተጠበቁ ተግዳሮቶችን መከላከል

[10] መረጃን ሰንዶ ማስቀመጥ -   𝑫𝒐𝒄𝒖𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፦  የእለት ሪፖርቶችን፣ የሂደት ማሻሻያዎችን፣ እና የፕሮጀክት ምእራፎችን ለመከታተል፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ እቅዶች ላይ የተደረጉ ማናቸውንም ለውጦችን ጨምሮ የግንባታ ስራዎችን ትክክለኛ ክስተት ወይም አጋጣሚዎች ወይም ሂደቶች በአግባቡ መዝግቦ መያዝ

[11] የአካባቢን ሁኔታ ታሳቢ ማድረግ  - 𝑬𝒏𝒗𝒊𝒓𝒐𝒏𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒍 𝑪𝒐𝒏𝒔𝒊𝒅𝒆𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒔፦  በግንባታ ተግባራት ላይ የሚኖረውን የአካባቢ ተፅእኖ ለመቀነስ እርምጃዎችን መተግበር፣ የአካባቢ ደንቦችን እና ምርጥ ልምዶችን ማክበር እና ማስከበር::

2 months, 1 week ago

ቤዝ አይሶሌሽን/Base isolation
የመሠረት ማግለል:-

*ሕንፃዎችን ከመሬት መንቀጥቀጥ ለመከላከል በግንባታ ላይ የሚውል ዘዴ ነው።

ህንጻውን በተለዋዋጭ ማሰሪያዎች ወይም ማግለያዎች ላይ እንደ ጎማ ወይም ተንሸራታች ቁሶች በመዋቅሩ እና በመሠረቱ መካከል ማስቀመጥን ያካትታል።

እነዚህ ገለልተኞች ህንጻው የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ኃይልን በመሳብ እና በማሰራ ከመሬት ተነጥሎ እንዲንቀሳቀስ ያስችለዋል።

ይህ ዘዴ የህንፃውን የመሬት መንቀጥቀጥ የመቋቋም ችሎታን ያሻሽላል ፣ የነዋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና መዋቅራዊ ጉዳቶችን ለመቀነስ ፣ የመሠረት ማግለል በሴይስሚክ ክስተቶች ጊዜ ሕንፃዎችን በመጠበቅ ረገድ የተሳካ ነበር፣ ይህም ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ በሆኑ የከተማ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ ጠቃሚ ስትራቴጂ እንዲሆን አድርጎታል።*⭐️*ለጠቅላላ ዕውቀትየመሬት መንቀጥቀጥ ደረጃ ዝቅተኛው በሬክተር ስኬል 0 ሲሆን ከፍተኛው 10 ነው::ስለዚህ ትናንት ማታ ከምሽቱ 5:12 የተከሰተው 4.6 ነው። አለማቀፍ ጂኦሎጂካል ሰርቬዮቹ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረጃን በሬክተር ስኬል እንዲሁም ሊያስከትል የሚችለውን የጉዳት መጠን እንደሚከተለው አስቀምጠውታል።

1ኛ. መጠን ከ 1.0 እስከ 3.0: ይህን ያህል አይሰማም  ግን ተመዝግቧል.

2ኛ. መጠን ከ 3.0 እስከ 3.9: ብዙ ጊዜ የሚሰማው ነው  ነገር ግን ብዙም ጉዳት የለውም

3ኛ.  ከ 4.0 እስከ 4.9 መጠን: ጉልህ የሆነ የቤት ውስጥ እቃዎች መንቀጥቀጥ;  አነስተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል.

4ኛ ከ 5.0 እስከ 5.9 መጠን: በህንፃዎች እና ሌሎች  ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል.

5ኛ. መጠን ከ 6.0 እስከ 6.9: ጠንካራ መንቀጥቀጥ እና ለከባድ ጉዳት ያስከትላል:

6ኛ. 7.0 እና ከዚያ በላይ መጠን: ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት እና ሰፊ ውድመት ሊያስከትል ይችላል።*https://t.me/ethioengineers1

5 months, 1 week ago

የቤት ዋጋ እንዴት ሊቀንስ ይችላል?

"*ቤት አትግዙ " የሚል የሶሻል ሚዲያ ቻሌንጅ የማከብረው ወዳጄ ልኮልኝ ተመለከትኩ።
አላማው በደምሳሳው ቤት ውድ ስለሆነ እስኪቀንስ ድረስ አትግዙ የሚል ነው...ይሄ ብዙም ውጤታማ ሊሆን የማይችል ቻሌንጅ እንደሆነ ቢታወቅም ሀሳቡ ግን የሚበረታታ  አይደለም ምክንያቱም ስሁት ነው።

የሪል እስቴት ዘርፍን በቅጡ ካለመገንዘብ የመጣ ቤት ተወዷል ብሎ ለውድነቱም አልሚዎችን ብቻ ተወቃሽና ተከሳሽ ለማድረግ የታሰበ የችግሩን መሰረት ያልተረዳ ነው።  እስኪ የዘርፉን አሰራርና ችግሩን እንድንረዳ ስለ ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዋና ተዋናዮችና አስተዋጽኦዋቸው ጥቂት እንበል። 

ሀ) ባለድርሻ አካላትና ድርሻዎቻቸው

የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አምስት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት አሉት። የሀገራችንን ሁኔታ ታሳቢ አድርገን ስናቀርበው ከዚህ በታች የተገለጸውን ሊመስል ይችላል:-

፩) አልሚ (Developer) :- ስራ ፈጣሪ ነው፣ መሬትን ወደ ውጤታማ የሆነ ተፈላጊ የመኖሪያ ስፍራ በመቀየር ትርፍን የሚያገኝ መላ ፈጣሪ ነው፣ የገንዘብ አምጪ፣ የኪሳራሃላፊነት ወሳጅ፣ ቀጣሪ ሲሆን ዓላማው የገንዘብ ትርፍ ማግኘት፣ የቤት ችግር መቅረፍ ቢዝነሱ ያደረገ፣ ዘላቂ ንብረት ማፍራት፣ ጥሩ ስም መገንባት ...

፪) መንግስት(public organization):- መንግስት ዜጎች ቤት እንዲያገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን ያወጣል፣ ለቤት ልማት የሚሆን መሬት ያቀርባል፣ የግንባታ ሂደቱን ይከታተላል፣ የግብይት ሂደቱን ይቆጣጠራል....

በሪል እስቴት ልማት ውስጥ የመንግስት ዋና ፍላጎት  የልማቱ ሂደት በስኬት ተከናውኖ   ዜጎች ቤት እንዲያገኙ ማድረግ፣  የህዝብ ሃብት የሆነው መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ....

፫) ካፒታል ማርኬት:- ይህ ለግንባታም ሆነ ለቤት ገዢዎች ብድር የሚሆን የገንዘብ አቅርቦትን የሚያቀርቡ ባንኮችንና ሌሎች ወደፊት የሚመጡ የገንዘብ አቅርቦት የሚሰሩ ተቋማት ሲሆኑ ተሳትፏቸውም ለልማቱና ለቤት ገዢዎች ገንዘብ ማቅረብና ከልማት ሂደቱ ማትረፍ ነው። ፍላጎታቸው ኢንቨስትመንቱ አዋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ነው።

፬) የቤት ገዢዎች (ተከራዮች) (ደንበኞች):- ዋና ፍላጎታቸው ለመኖር በቂ የሆነ ፣ በጊዜው ተጠናቅቆ መረከብ፣ በቂ ስፋት ያላቸው መገልገያ ክፍሎች ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ማግኘት ሲሆን። የቤት አልሚው ይህንን የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት በገበያ ጥናት አጥንቶ መገንባት ይጠበቅበታል።

፭) የተለያዩ ባለሙያዎች (Development Team ) :- የሪል እስቴት ዘርፍ ብዙ ሙያዎችን የሚጠቀም ዘርፍ ነው። ለምሳሌ አርክቴክቶች፣ መሃንዲሶች፣ ገንቢዎች፣ የግብይት ሂደት ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች፣ የፋይናንስ፣ የባንኪንግ ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ባለሙያዎች፣ IT ባለሙያዎች፣ የህግ ባለሙያዎች ወዘተ.... ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ። ባለሙያዎቹ በግልም በህብረትም በየሙያቸው ያለውን ከፍተኛና ፈጠራ የተካተተበት የደንበኞችን  ፍላጎት መሰረት ያደረገ ውጤት እንዲመጣ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው።

ለ) ቤት ዋጋ እንዲቀንስ የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ

የሪል እስቴት ልማትና ግብይት የተሳካ እንዲሆን ከላይ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት የሚጠብቃቸውን ያለማጓደል ሊያበረክቱ ይገባል።

ለምሳሌ :-
፩) መንግስት ለአልሚዎች መሬት በቅናሽና በብዛት ካቀረበ፣  የዲዛይን ማጽደቅና ክትትል ስራውን ካሳለጠ፣ ግብይቱ የሚመራበት መመሪያና ግብይቱን የሚመራ  አካል ሰይሞ በስርዓት እንዲመራ ካደረገ፣ በርካታ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች የግንባታ  ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ  ካደረገ።

፪) የገንዘብ አቅራቢ ተቋማት ለአልሚዎችና ለቤት ገዢዎች በቂ የሆነ የገንዘብ አቅርቦት ካደረጉ
፫) ቤት ገዢዎች ጠንክረው ሰርተው ቁጠባን ባህላቸው ቢያደርጉና እቅም ከፈጠሩ

፬) ባለሙያዎች ገበያውንና የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት ያገናዘቡ ቤቶች የሚገነቡበትን ዲዛይን፣ ወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂ ፣ የአከፋፈል ስርዓት በጥናት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ካዘጋጁ

፭) አልሚዎች ዘርፉን በእውቀት በባለሙያዎች እንዲመራ ካደረጉ

ሐ) መውጫ በምሳሌ

ነገር ግን ከአምስቱ  አንዱ ሲያጎድል ዘርፉ ውጤታማ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል በሌሎቹ አካላት ላይም ተጽዕኖን ያሳድራል ።

ለምሳሌ :- ባለሙያዎች ገበያውን ያላገናዘበ ውድ ቤቶች ንድፍ ቢሰሩና የሰሩትም ቢገነባ  ቤት ገዢዎች ሊገዙት አይችሉም፣ ካልተሸጠ ባንኮች ያበደሩት ብር በወቅቱ አይመለሰም፣ የቤት ችግርን ስለማይቀረፍ መንግስት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ከልማቱ ማግኘት የነበረበትን ገቢ ያሳጣል፣ አልሚውም ይከስራል...

ስናጠቃልለው የቤት ዋጋ ሊቀንስ የሚችለው በአልሚዎች ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱት አካላት የተናበበ የጋራ ተሳትፎ ሲኖር ብቻ ነው።

በ ደሳለኝ ከበደ
(አቶ ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ፣ ስራ ተቋራጭ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ ሲሆኑ በግንባታው ዘርፍ ላይ ሰፊ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያ ናቸው)*

https://t.me/ethioengineers1

5 months, 1 week ago

#ተዓምረ_Dog ???????

? በሁለት ቀናት ውስጥ 9.4 ሚሊዮን ህዝብ ተቀላቅሏል::

? Varified ነው

? #Tap ማድረግና #Task የለውም (ጊዜ አይወስድም)

? ስትጀምሩ ቴሌግራም ላይ የቆያችሁበት ዓመት አስልቶ #Coin ይሰጣችኋል

? "Who are you dawg?" የሚል ጽሁፍ ከመጣላችሁ አካውንታችሁ @Username የለውም ማለቱ ነው - አስገቡበት::

? ብዙ ተከታይ ያላችሁ የራሳችሁን link በማጋራት ራሳችሁንም ሌሎችንም ጥቅሙ::

? ያልጀመራችሁ - ጊዜ አትውሰዱ:: በአቃራጭ የመጣ የማይደገም እድል ነው::
???

https://t.me/dogshouse_bot/join?startapp=cfb5cSz1TdO8TWlQQe0jTw

5 months, 2 weeks ago

የአዲስ አበባ ከተማ ሪል ስቴት ገበያ በዋጋ ደረጃ ለመስከኑ የኦቪድ ግሩፕ አስተዋፅዎ ቀላል አይደለም ። ኦቪድ ግሩፕ በሪል ስቴት ልማት ክንፉ ፣ የገነባቸው ቤቶችን በብዛት ለገበያ ማቅረቡ የሪል ስቴት ገበያው እንዲሰክን አድርጓል - ወይም ሰብሯል ።

*ቀደም ባሉት ወራት በዋጋ ሽቅብ ይጎን የነበረው የሪል ስቴት ገበያ የዋጋ ቅናሽ እየታየበት ነው - ዋጋውን ጣሪያ የሰቀሉ ጭራሽኑ ጠያቂ አጥተዋል ።

ግዙፉ የሪል ስቴት ዘርፍ ዘገር ነቅናቂ ሆኖ የቀረበው ኦቪድ - በታሪክ ተመዝግቧል ...... ብራቮ ዮናስ ታደሰ !

በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት የካሬ ሜትር ዋጋ ወቅታዊ ነፀብራቅ ምን መልክ ይዟል ተብሎ ቢታይ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ባስጠናው ጥናት የአንድ ካሬ ሜትር የሪል ስቴት መገንቢያ ዋጋ ከ 30,000 ብር እስከ 40,000 ብር - አለፍ ብሎም እስከ 50,000 ብር ነው ።

ነገር ግን ይህንን ዋጋ ብዙዎቹ የሪልስቴት አልሚዎች በፍፁም አይቀበሉትም ። ይልቁኑ እንደየ ሪልስቴት ግንባታው ደረጃ የሚለያይ ቢሆንም በአልሚዎች ጥናት የሪል ስቴት የግንባታ ዋጋ በካሬ ሜትር ከ 63,000 ብር እስከ 70,000 ብር ይደርሳል።

የሪል ስቴት መገንቢያ ቦታ በሁለት መንገድ ይገኛል ። አንድም ከአስተዳደሩ ሁለትም ከግለሰቦች በግዥ ። ከግለሰቦች በግዥ የሚገኘው ውድ እንደመሆኑ በግንባታው ላይ የመሬት ዋጋ ፣ የሠራተኛ እና የመሳሰሉ ወጪዎች ሲጨመሩበት ዋጋውን ማናሩ አይቀርም ።

ኦቪድ ግሩፕ ገበያውን ከመቀላቀሉ በፊት አብዛኛዎቹ አልሚዎች ለገበያ ያቀረቡትን ሪል ስቴት በካሬ ከ 80,000 ብር እስከ 120,000 ብር ይጠሩ ነበር - በውጭ ምንዛሪ ደግሞ በካሬ ሜትር ከ 3,000 እስከ 4,000 ዶላር ድረስ ይጠራሉ - ከዚህም በላይ ዋጋ የሚጠራላቸው ቅንጡ ሪልስቴቶች እዚህም እዚያም እንዳሉ አሉ!

በአሁኑ ገበያ ግን በካሬ ሜትር 70,000 ብር እና ዙሪያውን ፣ በውጭ ምንዛሪም 2,000 እና ዙሪያውን እየተጠራ ይገኛል ። ከዚህ ባለፈም ከ10 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ማማለያ እየተሰጠ ነው ።

በዚህ መሀል ማን ሰንጥቆ መጣ !? ለሦስት አስርት ከግንባታ ተገልሎ የቆየው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በለውጡ ዳግም አንሰራራ - ረሻድ ከማል የሚባል ዶዘር መጣለት - ፌቤኮ ተገማች ባልሆነ መንገድ በዋና ዋና ግንባር ቦታዎች ሁነኛ ህንፃዎችን ገንብቶ ባልተጠበቀ ዋጋ ቤቶችን ገንብቶ ለገበያ ሲያቀርብ - ገበያው ከኢኮኖሚ ማንሰራሪያ ባሻገር ለብዙሃኑ ሃብት ሆነ ...

ግን ግን የግልና መንግስት አጋርነት ( PPP ) ከመንግስት በ 70/30 ቀመር መሬት የወሰዱ ሪል ስቴት አልሚዎች በስንት ብር ቢሸጡት ያዋጣቸው ይሆን !?

በ70 ሽህ ? መንግስት ከተገነባው ሪል ስቴት ድርሻውን ሲወስድ አልሚዎቹ የመገንቢያ ዋጋውን እንዴት አብቃቅተው አትራፊ ይሆኑ ይሆን - ልናይ ኋላ!

በልዩ ሁኔታ የሚታይ ቢሆንም የፐርፐዝ ብላክ ዋጋ ሳያስደምም የሚቀር አይደለም - የፐርፐዝ ብላክ ነገር እስካሁን መጨረሻው ባይለይም አምስት ቢሊየን ብር ቦታ ገዝቶ ፤ በ 60 ቢሊዮን ብር 113 ወለል ህንፃ ከነ አጀቡ ገንብቶ - ከአክሲዮን ድርሻ ጋር ፣ መቶ ካሬ ሜትር ቤት በ 1.5 ሚሊዮን ብር ፤ ቆየት ብሎም በ3.5 ሚሊዮን ብር ሂሳብ ( በካሬ ሜትር 15,000 ብር እና 35,000 ብር መሆኑ ነው ) መዋዋሉ ከትርፋማነት ቀመር ውጭ ነው ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሪል ስቴት ዘርፍ ለመኖሪያ ፈላጊው ጥሩ አማራጭ ገበያ እንዲሆን ካስፈለገ የመሬት አቅርቦት ፣ የፋይናንስ አማራጭ ፣ የሸማች መብት ጥበቃ ወሳኝነት አላቸው - በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ቢሊየነሮች የገቡበት ዘርፍ መሆኑ ልብ ይሏል - የዚያኑ ያህልም የተካኑ ባለካልኩሌተሮችም ዘርፉን ተቀላቅለዋልና መፍዘዝ ጥሩ አይደለም !*

https://t.me/ethioengineers1

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 3 days, 16 hours ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 3 weeks, 3 days ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 8 months, 3 weeks ago