Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Khalid Zemen

Description
በዚህ Channel ሚተላለፉትን ከቁርዐን፣ ከሀዲስና ከዑለማዎች በማስረጃ የተደገፉ መልእክቶችን Follow በማድረግ ይከታተሉ

📩 ስለ ዲናችን መማማር ላይ በቂ ትኩረት እናድርግ። “በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ።” ብለዋል ረሱል (ﷺ)
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

7 months, 3 weeks ago

ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ሁኑ

🧩 አላህ በሰጠን ጸጋዎች አመሥጋኝ መኾን ይጠበቅብናል፡፡ የተሰጡን ጸጋዎች ለተፈጠሩበት ዓላማም ልንጠቀምባቸው ይገባል፡፡

አላህ ከባሪያዎቹ ምሥጋናን ይወዳል፡፡ የሰጣቸውን ፀጋ በአግባቡ ተጠቅመውበት፡ እሱንም ያመሰግኑት ዘንድ ይወዳል፡፡

🟢📖 ۞ "ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡" ۞ (ሱረቱ ኢብራሂም14፡7)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 አላህ ለባሮቹ ከለገሳቸው ጸጋዎች ውስጥ ማየት፣ መስማት እና መናገር መቻል ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡

👂 በጆሮአችን ሐቅን ልንሰማ፣ ምክርንና ተግሳጽን ልናዳምጥ እንጂ ሙዚቃን ለመስማት፡ ሐሜትንና ነገር ማዋሰድን ለመስማት አልተፈቀደልንም፡፡

🗣 በአንደበታችን ሐቅን ልናወራ፡ ለእውነት ምሥክርነት ልንጠቀምበት እንጂ፡ ሐሰትን፣ ሐሜትን ለማውራትና የሀሰት ምስክርነትን ለመመሥከር አይደለም፡፡

👀 አይናችን የተፈቀዱልን ነገሮች ለማየት እንጂ ያልተፈቀደ ነገር ልንመለከትበት አይደለም፡፡ እነዚህ ጸጋዎች አላህ ዘንድ ያስጠይቁናልና፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

🟢 ۞ "ለአንተም በርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ (ባለቤታቸው) ከእነሱ ተጠያቂ ነውና፡፡" ۞ (📖 ሱረቱል ኢስራእ 17፡36)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

🟢 ۞ "አላህም ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም አደረገላችሁ፡፡" ۞ (📖 ሱረቱ-ነሕል 16፡78)

🟢 ۞ "እርሱም ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡" ۞ (📖 ሱረቱል ሙእሚኑን 23፡78)

🟢 ۞ "ከዚያም (ቅርጹን) አስተካከለው፡፡ በእርሱ ውስጥም ከመንፈሱ ነፋበት፤ (ነፍስ ዘራበት)፡፡ ለእናንተም ጆሮዎችን፣ ዓይኖችንና ልቦችንም አደረገላችሁ፡፡ በጣም ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ፡፡" ۞ (📖 ሱረቱ-ሰጅዳህ 32፡9)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 መስማት፣ ማየትና መናገር የተሳናቸው የአካል ጉዳተኞች ካሉ ደግሞ፡ በተቀረው ሰውነታቸውና ጤናቸው አላህን እያመሰገኑ፡ በደረሰባቸው ነገር ደግሞ ሶብር እንዲያደርጉ ታዘዋል፡፡ ታጋሾች ከኾኑ አላህ ዘንድ ወሰን አልባ የኾነ ሽልማት አላቸው፡፡ የአላህ ቃል እንደሚለው፡-

🟢 ۞ "ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው» (ይላል) በላቸው፡፡" ۞ (📖 ሱረቱ-ዙመር 39፡10)

📗 በሐዲሡል-ቁድሲይ ላይም እንደቀረበው ጌታ አላህ ሲናገር፡-

"ባሪዬን በሁለቱ እሱ ዘንድ ተወዳጅ በኾኑት (በአይኖቹ) ፈትኜው ከታገሰ፡ ከጀነት ውጭ ሌላን አልወድለትም" ይላል፡፡ (ቡኻሪይ 5329)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 ማስታወስ ያለብን ነገር አላህ የፈጠረን ሊፈትነን ነውና ፈተናም በሁለት አይነት መንገድ የሚሰጥ መኾኑን አምነን መቀበል አለብን፡፡ እሱም፡- በጥሩና በመጥፎ መፈተን ይባላል

በሕይወታችን ውስጥ የሚከሰቱ ማንኛውም መልካምም ሆነ መጥፎ ሂደቶች በጠቅላላ ‹‹ኢብቲላኡን ሚነሏህ›› ከአላህ ዘንድ የኾኑ ፈተናዎች ናቸው

አላህ ከፊል ባሮቹን መልካም ነገራትን በመለገስ ይፈትናቸዋል። በዚህ በተሰጣቸው መልካም ጸጋ ጌታቸውን በተግባርም (አላህን በሚያስደስት ነገሮች ላይ ማዋል) በምላስም አመስጋኝ ኾነው የአመስጋኞችን ምንዳ ሊያገኙበት ነው

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 እያንዳንዱ ሰው በተሰጠው ጸጋ ልክ ነው የሚጠየቀው፡፡ ባልተሰጠው ነገር አይጠየቅም፡፡ አላህ ጸጋውን አሟልቶ የሰጠው ሰው፡ አላህን በብዛት ሊያመሰግን ይገባል፡፡ እንደውም ካመሰገንክ ገና ሊጨምርልህ ቃል ገብቶልሀል

በአካሉ ላይ የተወሰነ ፈተና የደረሰበት ደግሞ ትግስት ሊያደርግ ይገባል፡፡ ይህን ካደረጉ ሁለቱም የአመስጋኝና የታጋሽን ምንዳ ከጌታቸው ይቀበላሉ፡፡

ባለ-ጸጋው ከካደ፣ የተፈተነው ደግሞ ትግስት ካጣ፡ ሁለቱም የጌታቸውን ቁጣ ያተርፋሉ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📲 ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች እንዲደርሳቸው ያድርጉ፣ ነብያችን (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፡- "የኸይር አስተማሪ ለሱ ሁሉ ነገር ምህረት ያደርግለታል፣ በባህር ውስጥ ያሉ አሳዎች ሳይቀሩ።"📗(አሶሒሐህ፡ 3024)

ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen

Telegram

Khalid Zemen

በዚህ Channel ሚተላለፉትን ከቁርዐን፣ ከሀዲስና ከዑለማዎች በማስረጃ የተደገፉ መልእክቶችን Follow በማድረግ ይከታተሉ ***📩*** ስለ ዲናችን መማማር ላይ በቂ ትኩረት እናድርግ። “በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ።” ብለዋል ረሱል (ﷺ)

ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ሁኑ
7 months, 3 weeks ago
Khalid Zemen
7 months, 3 weeks ago

🟢 መውሊድ

🧩 አክባሪዎቹም፣ ማናከብረውም፣ ምነው ከአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የታዘዝነው ነገር ላይ በመቃወምም በመተግበርም እንዲህ ብንበረታእውነት እኛስ በታዘዝነው ላይ ነን

ለአክባሪዎቹ ደሞ እውነተኛው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወዳጅ ማነውትእዛዝ የሚያከብረው ወይስ

መውሊድ አለማክበር ከሆነ “የረሱል ወዳጅ አይደላቹም ወይም ሌላ ቅጥያ ስም ሚያሰጠው”፣ ሶሐቦቹም ቀጥለው የመጡት ታቢዖች ከነሱ የቀጠሉት አትባዑት-ታቢዒን በዚህ መዝገባችሁ ውስጥ እንዳትረሷቸው።

⭕️ እስኪ ጉዳዩን በግላችን ከጭፍን ስሜታዊነት በፀዳ መልኩ እንድንመልከተው ይህችን አጠር ያለች ፅሁፍ እናንብብ

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 የተከበሩትን ነብይ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ልደት ማክበር ኸይር ነው ሸር? ኸይር ነው ካልን፣ ይህንን ኸይር የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እና ሰሐቦቻቸው አያውቁትም ነበር?

ከአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እና ከሰሐቦቻቸው ይሰወራል ተብሎ ፍፁም የማይታሰብ ነው።

እኛ ኢስላምንም ኢማንንም በሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መንገድ እንጂ በሌላ አላወቅነውም፡፡ እሳቸው የማያውቁትን ኸይር እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ይሄ ፍፁም የማይሆን ነገር ነው!!

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 መልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የማያውቁት ኸይር በፍፁም የለም። ኸይርን ሁሉ ያወቅነው በመልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መንገድ አማካኝነት ነው፡፡

ይህን አባባል ከሚደግፉ የመልእክተኛው ሐዲሦች ውስጥ (ወደ አላህ የሚያቃርባችሁ ሆኖ ሳላዛችሁ የቀረኝ ነገር የለም) የሚለው ይጠቀሳል፡፡

እናም መውሊድ ኸይር ከሆነ ወደ አላህ የሚያቃርበንም ከሆነ የግድ መልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያመላከቱን ነው ማለት ነው፡፡ ነው ወይስ አይደለም?

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 የመውሊድ ደጋፊዎች “ጥሩ ቢድዐ ነው” ከማለት ባለፈ ማስረጃ አይጠቅሱም፡፡ የመውሊዱ ደጋፊዎችም ተቃዋሚዎችም በመልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመንም በክቡራን ሰሐቦች ዘመንም በታላላቅ መሪዎች ዘመንም እንዳልተከበረ ይስማማሉ፡፡

ነገር ግን የሚያከብሩት ሰዎች መውሊድ ውስጥ ምን ችግር አለበት? ነብዩን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለማስታወስ ነው፣ በሳቸው ላይ ሰለዋት ለማውረድ ወዘተ ይላሉ፡፡ እኛ ግን “ኸይር ቢሆን ኖሮ ይቀድሙን ነበር” እንላለን፡፡

የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመን ማለት እሳቸውና
ሰሐቦቻቸው የኖሩበት ጊዜ ነው፡፡ ቀጥለው የመጡት ታቢዖች ናቸው፡፡ ከነሱ የቀጠሉት ደግሞ አትባዑት-ታቢዒን ናቸው። በእውቀትም (ሸሪዐዊ እውቀት) በተግባርም እኛ ልንቀድማቸው የምንችለው ኸይር ሊኖር አይችልም።

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🧩 ይሄ መውሊድ ኸይር ቢሆን ኖሮ መልካም ቀደምቶቻችን በዋናነትም የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከኛ የበለጠ ያውቁት ነበር፡፡ ከኛ ቀድመውም ይሰሩት ነበር፡፡

እነሱ ለምን አልሰሩትም? እኛ ከነሱ የበለጠ ወደ አላህ የቀረብን ነን

🤲 አላህ እውነትን አውነትነቱን አይተው ከሚከተሉት ሀሰትን ሀሰትነቱን አይተው ከሚርቁት ያድርገን፡፡ ኣሚን፡፡

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📩 ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች እንዲደርሳቸው ያድርጉ

ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen

Telegram

Khalid Zemen

በዚህ Channel ሚተላለፉትን ከቁርዐን፣ ከሀዲስና ከዑለማዎች በማስረጃ የተደገፉ መልእክቶችን Follow በማድረግ ይከታተሉ ***📩*** ስለ ዲናችን መማማር ላይ በቂ ትኩረት እናድርግ። “በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ።” ብለዋል ረሱል (ﷺ)

***🟢*** መውሊድ
7 months, 3 weeks ago
Khalid Zemen
8 months ago

☑️ አልሐምዱ-ሊላህ በል

ቢስሚላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ወስ-ሶላቱ ወስ-ሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ

☑️ አሁን በአለማችን ምናየው ጦርነት፣ መፈናቀል፣ ረሀብ፣ ጎርፍ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ …. መከራና እንግልት በሞላበት አለም አላህ አንተን ሰላም አደረገህ

☑️ ስንቱ ነው አንድ አፉን ሚመገበው፣ ጎኑን ሚያሳርፍበት ማደሪያ የሌለው፣ ለአንተ አላህ ቤትህን በምግብና በመጠጥ ሞልቶልህ ማደሪያም ሰጦሀል። የሰው ፊት የሚገርፈው ሚለምን ስንቱ መሰለህ? አላህ አንተን ከሰዎች አብቃቃህ

☑️ ስንቱ በከባድ ጤና ቀውስ ይሰቃያል፣ አላህ አንተን ሰላም አደረገህ፣ ከህመም ብዛት በስቃይ አይኑን ሳይከድን የተኛ ስንቱ መሰለህ? አላህ ላንተ ሰላማዊ እንቅልፍን ሰጠህ

📗 የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም) እንዲህ ብለዋል፡-

“ከናንተ ዉስጥ በነፍሱ እና በአካሉ ላይ ሰላም ሆኖ እርሱ ጋር የእለተ ጉርሻዉ ኑሮት ያነጋ ሰዉ በእርግጥም ለሱ ዱንያ ሙሉ በሙሉ እንደተሰበሰበችለት ነዉ።” (ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 2346)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

☑️ ሌላው ሌላ አካል እያመለከ፣ አላህ አንተን መርጦ እስልምናን ሰቶሀል። አልሐምዱሊላህ ዐላ ኒዕመቲል ኢስላም!

☑️ ስንቱ በተከበረበት ተዋርዶ፣ ረበል ዓለሚን ያንተን ወንጀልህንና ነውርህን ደብቆልሀል

☑️ በሌሎች ላይ ቦንብ እየዘነበ፣ በአንተ ላይ ግን ዝናብ እንዲዘንብ ነው የተደነገገው። ልብ በል የአንተ ዝናብ ውሀ፣ የእነሱ ደሞ እሳት እንዲሆን የተደረገበት ሚስጥር በጣም ሩቅ ነው። ግን ባይገባህም አልሐምዱሊላህ በል

☑️ ለነገ ይሆነኛል ብለህ ገንዘብ እንደምትቆጥበው ሁሉ፣ ማመስገን ብትፈልግ እድሉን እና አቅሙን የማታገኝበት ቀን ቅርብ ነው፣ እናም ለዚያ ቀን ከአሁኑ ምስጋናህን አከማች

🔘 ያጣሀውን አትመልከት፣ ያለህን ተመልከትና አልሐምዱሊላህ በልና አላህም እንዲህ ካላቸው ሰዎች ሁን....

🟢 ۞ “ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡" ۞ (ሱረቱ ሰበዕ:13)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📗የአማኞች እናት አኢሻ፣ የአላህ መልእክተኛ ሆይ፣ አላህ ያለፈውንም የሚመጣውንም ወንጀል ምሮልዎታል።

ለምንድን ነው ይህን ያህል የሚደክሙት? በማለት ጠየቀቻቸው። እርሳቸውም፡- አመስጋኝ ባሪያ ልሆን አይገባኝምን? በማለት መለሱ። (ቡኻሪና ሙስሊም)

📗 ሱሀይብ ኢብኑ-ሲናን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-

"የሙእሚን ነገር ይደንቃል፡፡ ነገሩ ሁሉ መልካም ነው፡፡ ይህ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አልተሰጠም፡፡ መልካም ነገር ሲያገኘው ጌታውን ያመሰግናል ለሱም መልካም ይሆንለታል፡፡ መጥፎ ነገር ሲነካው ደግሞ ይታገሳል ለሱም መልካም ይሆንለታል፡፡" (ሙስሊም

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

☑️ አንድ ሙስሊም መልካም ነገር ቢገጥመው፣ ከጌታው ዘንድ የመጣ ችሮታ (ራሕመት) መሆኑን በማወቅ አመስጋኝ ይሆናል እንጂ፣ ከልክ አልፎ አይኮራም አይኩራራም

☑️ በዛው ተቃራኒ፣ የማያስደስተው የሆነ መጥፎ ነገር ቢደርስበት፡ ይህም ከጌታው ዘንድ የተወሰነበት መሆኑን በማወቅ እራሱን ለትእግስት ያዘጋጃል እንጂ፣ በምሬት ለሃዘንና ተስፋ መቁረጥ አይዳረግም

🔘 ሰው የገዛ ነፍሱን ድክመት በሸይጧን ጉትጎታ ያሳብባል? አላህም እኮ ነጻ ፈቃድ የሰጠን፣ አመስጋኝ ሆነን የእምነትን መንገድ እንድንከተል፣ ወይንም ከሀዲ ሆነን የጥመትን መንገድ በመከተል በፈቃዳችን እንድንወስን ነው፡፡ የአላህ ቃል ሲናገር እንዲህ ይላል፡-

🟢 ۞ "እኛ ሰዉን፥ (በሕግ ግዳጅ) የምንሞክረዉ ስንሆን፥ ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፤ ሰሚ ተመልካችም አደረግነዉ። እኛ፥ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሐዲ ሲሆን መንገዱን መራነዉ፤ (ገለጽንለት)።" ۞ (📖 ሱረቱል ኢንሳን 76፡2-3)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

☑️ አላህ ከባሪያዎቹ ምሥጋናን ይወዳል፡፡ የሰጣቸውን ፀጋ በአግባቡ ተጠቅመውበት፡ እሱንም ያመሰግኑት ዘንድ ይወዳል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

🟢📖 ۞ "ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡" ۞ (ሱረቱ ኢብራሂም14፡7)

🟢📖 ۞ "ብትክዱ አላህ ከእናንተ የተብቃቃ ነው፡፡ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም፡፡ ብታመሰግኑም፤ እርሱን ይወድላችኋል፡፡" ۞ (ሱረቱ-ዙመር 39፡7)

🟢 ۞ "እላንተ ሰዎች ሆይ! በናንተ ላይ (ያለውን) ጸጋ አስታውሱ፤ ከአላህ ሌላ ፈጣሪ አለን? ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አልለን? ከርሱ በስተቀር አምላክ (ሰጪም) የለም፤ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ።" ۞ (📖 ሱረቱ ፋጢር 3)

🟢 ۞ "ምስጋናም በሰማያትና በምድር ውስጥ ለእርሱ ብቻ የተገባው ነው። በሠርክ እና በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ አመስግኑት። ۞ (📖 30፥18)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📲 ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች እንዲደርሳቸው ያድርጉ፣ ነብያችን (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፡- "የኸይር አስተማሪ ለሱ ሁሉ ነገር ምህረት ያደርግለታል፣ በባህር ውስጥ ያሉ አሳዎች ሳይቀሩ።"📗(አሶሒሐህ፡ 3024)

ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen

Telegram

Khalid Zemen

በዚህ Channel ሚተላለፉትን ከቁርዐን፣ ከሀዲስና ከዑለማዎች በማስረጃ የተደገፉ መልእክቶችን Follow በማድረግ ይከታተሉ ***📩*** ስለ ዲናችን መማማር ላይ በቂ ትኩረት እናድርግ። “በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ።” ብለዋል ረሱል (ﷺ)

***☑️*** አልሐምዱ-ሊላህ በል
8 months ago
Khalid Zemen
9 months, 2 weeks ago
***🌧️*** ዝናብ የሚዘንብበት ጊዜ ከአላህ ዘንድ …

🌧️ ዝናብ የሚዘንብበት ጊዜ ከአላህ ዘንድ የሆነ ችሮታ እና እዝነት ጊዜ ሲሆን፣ ምናደርገው ዱዓ ተመላሽ የሚሆንበት ጊዜ ነው።

9 months, 3 weeks ago

የዓሹራ ቀን

ቢስሚላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ወስ-ሶላቱ ወስ-ሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ

🔆 ዛሬ ሙሐረም 1️⃣0️⃣ ታላቁ የአሹራ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ነው

ስለሆነም ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም በነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ትዛዝ እየጾምነው እንገኛለን

🗓️ ለዛሬ ስለዚህ ታላቅ ቀን የተወሰኑ ነገሮችን እናኛለን፡-

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🔆 ይህ ቀን ከሌላው የላቀ የሆነበት ምክንያት አላህ ነብዩ ሙሳን እና ተከታዮቻቸውን መርዳቱና ፊርዓውንን እና ሰራዊቶቹን በማስመጥ ድል እንዲጎናፀፉ ማድረጉ ነው።

🟢 ۞ “ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡ መታውና ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡…

እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን፡፡ ሙሳንም ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳንን፡፡ ከዚያም ሌሎቹን “አሰጠምን”፡፡…

በዚህ ውስጥ “”ታላቅ ታምር”” አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡” ۞ (📖 26: 63-67)

💬 ይህንን ያደረገው ቅድሚያ በሙሳ ባህሩን በበትር እንዲመታ አስደርጎ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ በማድረግ ሙሳንም ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም ካዳነ በኃላ ያስተባበሉትን ሌሎቹን አሰጠመ።

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🔆 አምላካችን አላህ ሙሳን ወደ ፊርዖንና ወደ መማክርቶቹ በታምራት ልኮታል፣ እነዚህም ታምራት ዘጠኝ ናቸው፡-

🟢 ۞ “ከዚያም ከበኋላቸው ሙሳን ወደ ፊርዖንና ወደ መማክርቶቹ “በታምራታችን” ላክነው፤ በእርሷም ካዱ፤ የአጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት።” ۞ (📖 7: 103)

🟢 ۞ “ለሙሳም “ግልጽ” የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” በእርግጥ ሰጠነው።” ۞ (📖 17: 101)

🔆 አላህ ስምንቱን ታምራት ሲያስተባብሉ በባህር ውስጥ አሰጠማቸው

🟢 ۞ “እነርሱ “በታምራታችን” ስለአስተባበሉም ከእርሷ ዘንጊዎች ስለኾኑም፤ ከእነርሱ ተበቀልን፤ በባሕርም ውስጥ አሰጠምናቸው።” (📖 7: 136)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🔆 አልተሳካለትም እንጂ ሙስሊም ሁኖ መሞትን በመጨረሻው ሰዓት (የተውበት በር ከተዘጋ በኋላ) ፊርዐውን ሞክሮት ነበር፡-

🟢 ۞ "የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡…

መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡-አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከሙስሊሞቹ ነኝ» አለ፡፡

ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክ ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን (አመንኩ ትላለህ) ዛሬማ ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ (ከባሕሩ) እናወጣሃለን (ተባለ)፡፡" ۞ (📖 ሱረቱ ዩኑስ 90-92)

🟢 ۞ "ጸጸትንም መቀበል ለነዚያ ኃጢያቶችን ለሚሠሩ፣ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እኔ አሁን ተጸጸትኩ ለሚልና ለነዚያም እነርሱ ከኃዲዎች ሆነው ለሚሞቱ አይደለችም። እነዚያ ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አዘጋጅተናል።" ۞ (📖 ሱረቱ-ኒሳእ 18)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

🔆 የአላህ ህግ በደለኛን ለጥቂት ጊዜ ቢያቆየውም እንዲመለስ እና እንዲያስብ ለማድረግ ነው። ድንበሩን ሲያልፍ እና የነገሮች መክፈቻ ሁሉ በእጁ እንዳለ ሲያስብ የአሸናፊው ጌታ እጅ ይጨመድደዋል።

አላህ ሐሰትን ጥቂት ጊዜ ሊተወው ይችላል። ሊዘል፣ ሊወራጭ፣ ሊጠናከር፣ ሊገድል። ይህ ሁሉ ግን የአላህ ቻይነት የሚታይበት ጥቂት ጊዜ ድረስ የሚዘልቅ ፍቃድ ነው። የሚቸኩሉ ሰዎች ሊቸኩሉ ይችላሉ።

ኢማናቸው ደካማ የሆኑ ሰዎች እንግዳ ሊሆንባቸው ይችላል። ሐሰት እነዚህን አመታት ሁሉ ሲያይል አላህ ለምን ተወው?! የአላህ ባሮች አሳማሚ የበደለኞችን ቅጣት እየቀመሱ እንዲኖሩ አላህ ለምን ፈቀደ?! እያሉ ይጠያየቃሉ። የአላህን ጥበብ ግን አያውቁም።

🟢 ۞ "አላህንም፤ በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው ዓይኖች በርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው።" ۞ (📖 ሱረቱ ኢብራሂም 14፡42)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📲 ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች አስታውሱ። ۞ "አስታውስ ማስታወሱ አማኞችን ይጠቅማልና።" ۞ (📖 አዛሪያት፡ 55)

ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen

Telegram

Khalid Zemen

በዚህ Channel ሚተላለፉትን ከቁርዐን፣ ከሀዲስና ከዑለማዎች በማስረጃ የተደገፉ መልእክቶችን Follow በማድረግ ይከታተሉ ***📩*** ስለ ዲናችን መማማር ላይ በቂ ትኩረት እናድርግ። “በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ።” ብለዋል ረሱል (ﷺ)

የዓሹራ ቀን
9 months, 3 weeks ago
Khalid Zemen
9 months, 3 weeks ago

የጁሙዓና የጾመኛ ዱዓእ

ቢስሚላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ወስ-ሶላቱ ወስ-ሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ

☑️ ጁሙዓ ላይ አንዲት ዱዓ የማይመለስባት/ተቀባይነት የሚያገኝባት ሰዓት አለች ብለው ታማኙና እውነተኛው ነቢይ ነግረውናል፣ እንዲሁም ጾመኛ ሰው ሚያደርገው ዱዓእ ተመላሽ አይሆንም ብለውናል።

☑️ አላህ የባሮቹን ዱዓእ 24/7 ሰሚ የሆነ አምላክ ቢሆንም፣ በእነዚህ ወቅቶች የሚደረግ ዱዓእ የበለጠ ተቀባይነት ያገኛል።

🗓️ ለዛሬ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝባት የጁሙዓ ልዩ ሰዓት መቼ እንደሆነና ስለ ጾመኛ ዱዓእ አጠር አድርገን እናኛለን፡-

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

☑️ እሱ አላህ አል-ሙጂብ (የባሮቹን ልመና) ተቀባይ ነው፣ አላህ ለባሮቹ ቅርብ እንጂ ሩቅ ያልኾነ፣ ዱዓን ሰሚና ተቀባይ እንጂ መላሽ ያልኾነ አምላክ መኾኑን እንዲህ ይነግረናል፡-

🟢 ۞ "ባሮቼም ስለእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡" ۞ (📖 ሱረቱል በቀራህ 2፡186)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

☑️ ጾመኛ ሰው የሚያደርገው ዱዓእ ተመላሽ አይሆንም፡-

📗አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን፣ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-

"ሶስት ሰዎች ዱዓቸው ተመላሽ አትሆንም፡-

ፍትሀዊ መሪ፣
ጾመኛ እስኪያፈጥር፣
የተበዳይ ዱዓእ”።

(ኢብኑ ማጀህ 1752፣ ቲርሚዚይ 3598፣
ሶሒሕ ኢብኑ ማጀህ 2/86)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

ጁሙዓ ላይ ዱዓእ የማይመለስባት/ተቀባይነት የሚያገኝባት ሰዓት

📗ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው፣ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የጁምዓን ቀን አወሱና፡-

በውስጧ አንዲት ሰአት አለች፡፡ አንድ ሙስሊም የአላህ ባሪያ፡ ሶላትን እየተጠባበቀ ዱዓእ በማድረግ አላህን አንዳች ነገር ለመጠየቅ አይወፈቅም፡ አላህ ያንኑ ነገር የሰጠው ቢኾን እንጂ

📗 (ቡኻሪይ 935፣ ሙስሊም 1807፣
ኢብኑ ማጀህ 1139፣ ቲርሚዚይ 493፣ ነሳኢይ 1431)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

የጁሙዓ ይህ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝባት ሰዓት ጊዜ መቼ እንደሆነ ብዙ እይታዎች አሉ። በጣም ትክክለኛዎቹ 2️⃣ እይታዎች ናቸው፡-

💬 ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፡-

ከእነዚህ አመለካከቶች ውስጥ በጣም ትክክለኛዎቹ በተረጋገጡ ሀዲሶች ውስጥ የተገለጹት ሁለቱ ሲሆኑ አንደኛው ከሌላው የበለጠ ነው

1️⃣ የመጀመሪያው ኢማሙ ሚንበር ላይ ከተቀመጠበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሶላት መጨረሻ ድረስ ነው።ለዚህ አስተያየት ማስረጃው፡- (ሙስሊም በሶሂህ 853)

የኢማሙን ኹጥባውን ሰምቶ፣ ኢማሙ ዱዓ ሲያደርግ አሚን በማለት እና በሰላቱ ወቅት ሲሰግድ እና ሰላቱን ከመጨረሱ በፊት ዱአ ማድረግ አለበት፣ ከዐስር በኋላ በመጨረሻው ሰዓት ዱዓ ቢያደርግ ያ ደግሞ የተሻለ ነው። ወላሁ አዕለም

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

2️⃣ ሁለተኛው እይታ ከ ‹አስር› በኋላ ነው፣ ይህ ከሁለቱ እይታዎች የበለጠ ትክክለኛ ነው። ይህ የአብዱላህ ኢብኑ ሰላማ፣ ኢማም አህመድ እና ሌሎችም አመለካከት ነው ለዚህ አመለካከት ማስረጃው፡-

📗 (አል-ሀፊዝ ኢስናድ በአል-ፈትህ 2/489 ሰሂህ ተብሏል)
📗 (አቡ ዳውድ 1048 እና አል-ነሳይ 1389) በአል-አልባኒ ሰሂህ ተብሏል)
📗 (ሱነን ኢብኑ ማጃህ (1139) በአል-አልባኒ ሰሂህ ተብሏል)

ከዐስር በኋላ ያለው ሰዓት አብዛኞች ሰሓባዎችና ታቢዒዮች "ዱዓ የማይመለስባት የጁሙዓ ልዩ ሰዓት/ ያለችበት ወቅት እሱ ነው ብለዋል፣ እኛም በያለንበት ቦታ ሁሉ ልባችንን ወደ አላህ አዙረን አላህን መማጸን አለብን። ወላሁ አዕለም

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📲 ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች አስታውሱ። ۞ "አስታውስ ማስታወሱ አማኞችን ይጠቅማልና።" ۞ (📖 አዛሪያት፡ 55)

ቴሌግራም 👉 t.me/khalidzemen

Telegram

Khalid Zemen

በዚህ Channel ሚተላለፉትን ከቁርዐን፣ ከሀዲስና ከዑለማዎች በማስረጃ የተደገፉ መልእክቶችን Follow በማድረግ ይከታተሉ ***📩*** ስለ ዲናችን መማማር ላይ በቂ ትኩረት እናድርግ። “በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ።” ብለዋል ረሱል (ﷺ)

የጁሙዓና የጾመኛ ዱዓእ
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago