Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Mujib Amino Z islam

Description
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month, 2 weeks ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month ago

3 days, 3 hours ago
Mujib Amino Z islam
3 days, 3 hours ago
Mujib Amino Z islam
3 days, 3 hours ago

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ዶር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋና ልዑካቸዉ ጅግጅጋ ገቡ።
••••••••••••••••••••••••••••••
Mujib Amino

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ዶር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የሚመራ የኡለማዎች ልዑካን ጅግጅጋ ከተማ የገቡ ሲሆን ልዑኩ በሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር የሚመራ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና የመንግሥት ከፍተኛ አመራር አባለት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የጠቅላይ ም/ቤቱ ልዩ አማካሪ ኡስታዝ አቡበክር አህመድም በጅግጅጋ ከተገኙ የልዑክ ቡድኑ አባላት መካከል አንዱ ናቸዉ።

1 week, 6 days ago
Mujib Amino Z islam
1 week, 6 days ago

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን Federal Housing Corporation የቤት ልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ረገድ የታዩ ልምዶች ይበልጥ መጎልበት እንዳለባቸው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የበጀት ዓመቱን የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሲገመግሙ የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።

በዚህም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የኮርፖሬሽኑን ዋና መሥሪያ ቤት፣ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል፤ ኮርፖሬሽኑ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቁበት የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ አንጋፋ የመንግሥት ተቋም ቢሆንም ለውጡ እስከመጣበት 2010 ድረስ ዕድሜውን በማይመጥን ችግር ውስጥ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከለውጡ ማግስት በተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም ለ42 ዓመታት ከቆየበት ችግር በማውጣት ትርፋማና ተወዳዳሪ ተቋም ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በሪፎርሙ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር፣ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የኮርፖሬሽኑን የማስፈፀም አቅም ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የቤቶችን የይዞታ ካርታ በማዘጋጀት፣ ለቤቶች መለያ ምልክት በመለጠፍ፣ ጂ.ፒ.ኤስ እና ወደ ጎግል ካርታ በማስገባት የኮርፖሬሽኑን የቤት አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻል መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡

ተቋሙ የንግድ ቤቶችን ኪራይ በማሻሻል የገቢ አማራጮችን እያሰፋ መሆኑን ገልጸው፤ በ2010 ዓ.ም.የተቋሙ ገቢ ከነበረበት 308 ሚሊየን ብር በ2015 ወደ 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ለ28 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የቤቶች ግንባታ ከማስጀመርም ባለፈ፤ የጥራት፣ ጊዜና የግንባታ ዋጋ ማሻሻል ተችሏል ነው ያሉት፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ነመራ ገበየሁ፤ የኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ አመራር ከዋና መሥሪያ ቤት እስከ ቅርንጫፍ ወጥነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የቤት አስተዳደር ሥርዓት ለማሻሻል የተጀመረው የቤቶች የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቶችን በአግባቡ በመከታተል በተያዘላቸው ጊዜ፣ ጥራት እና ዋጋ እንዲጠናቀቁ እየተደረገ ያለው ተግባር ለሌሎች አርዓያ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡

ከቤቶች ልማት ጎን ለጎን በቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገነባው የብሎኬት እና የኮንክሪት ማምረቻ ፋብሪካ የዘርፉን ችግር ከመፍታት ባለፈ ለኢንዱስትሪው ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ፤ የኮርፖሬሽኑ የቤቶች ግንባታ እንደ ሀገር ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በግንባታ ሂደት የሚሳተፉ ባለቤቶች፣ አማካሪዎችና ተቋራጮች ጥምረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል በበኩላቸው፤ የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን የመስክ ምልከታ የበለጠ ለመሥራት የሚያበረታታ ነው ብለዋል።

የተሰጠውን አስተያየት በመቀበል ተቋሙ አሁን ካለበት በተሻለ መልኩ ለመሥራት እንደሚያነሳሳም አቶ ረሻድ ተናግረዋል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በተመረጡና ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች የሚያደርገው የመስክ ምልከታ እስከ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 የሚቀጥል ይሆናል፡፡

1 week, 6 days ago

ክቡር ዶ/ክ ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፉ በዓለም አቀፉ የሙስሊሞች ሊግ የጠቅላላ ጉባዔ አባል በመሆን ሳዉዲ-ሪያድ ተጉዘዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••
Mujib Amino

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የዑለማ ጉባዔ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር ዶ/ር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፉ ነገ ሚያዚያ 15/2016 በዓለም አቀፉ ሙስሊም ሊግ ጉባዔ ላይ የጉባኤው መስራችና የጠቅላላ ጉባዔዉ አባል በመሆን ወደሳዉዲ/ሪያድ አቀኑ።

ነገ በሚጀምረዉና ለሁለት ቀናት በሚቆየዉ ጉባዔ ላይ ከፕሬዝደንቱ በተጨማሪ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማህበራዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ዳሮክትሬት ዶር አብደላ ኸድር የተጓዙ ሲሆን በአለም የሙስሊሞች ሊግ ዉስጥ የመስራች አባልነት እንዲካተቱ የተደረጉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በመወከል በተለያዩ የአለም ሀገራት በተከናወኑ ኮንፈረንሶች ላይ ባቀረባቸዉ ኢስላማዊ የጥናት ዉጤቶች መሰረት በማድረግ መሆኑ ታዉቋል።

በረመዳን መጀመሪያ በመካ ኮንፈረንስ ላይ ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተዉጣጡ በቁጥር ከአራት መቶ በላይ ሙህራን፣ሙፍቲዎች፣ ዑለማዎች፣ የየሀገራቱ የእስልምና ጉዳዬች ተወካዮች ...በተገኙበት ባቀረቡት ኢስላማዊ ጥናት መሰረት ፤ የጥናት ገምጋሚዉና የኮንፈረንሱ አዘጋጆች የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ዶር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ያቀረቡትን ጥናት በአንደኛ ደረጃ ማስቀመጣቸዉ ይታወቃል። ይህንም ግብዓት በመዉሰድ የዓለም አቀፉ ሙስሊም ሊግ መስራች አባል እንዲሆኑ ተመርጥዋል። ሊጉም ለክቡር ፕሬዝደንቱ በደብዳቤ በመግለጽ ፈቃደኝነታቸዉን አጽድቋል።

የዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ በኩል ዋና ጸሀፊዉ ዶክተር ሙሐመድ ቢን አብዱልከሪም አልኢሳ ኢትዮጵያ/አዲስ አበባ በመጡ ጊዜ ለሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ያላቸዉን አክብሮት መግለጻቸዉ ይታወሳል።

መልካም ጉዞ፤ አሏህ(ሱ.ወ) በሰላም ይመልሳችሁ። አሚን

2 weeks, 5 days ago
Mujib Amino Z islam
2 weeks, 5 days ago
Mujib Amino Z islam
2 weeks, 5 days ago

🇪🇹🇺🇸
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ በዛሬው ዕለት ከአሜሪካው አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ክቡር ሸይክ ሐጂ ኢብራሂም በኢትዮጵያ ከአምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር በአምባሳደሩ ጽሕፈት ቤት በተገናኙበት ወቅት፣ ኤምባሲው እና ጠቅላይ ምክር ቤቱ በጋራ ሊሠሯቸው በሚችሏቸው ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ጊዜ አምባሳደር ማሲንጋ፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በሰላም፣ በልማት፣ በሰብኣዊ ረድዔት፣ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ዙርያ በጋራ ለመሥራት ፍላጎት ያለው መሆኑንና በቀጣይ አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም በበኩላቸው የአሜሪካ ኤምባሲ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በተለያዩ መስኮች የሚሰጠው እገዛ አዲስ እንዳልኾነ ጠቅሰው፣ አሁንም አምባሳደሩ ላሳዩት የትብብር ፍላጎት የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ለሚያደርገው የትብብር ሥራ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስ የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተናግረዋል።

አምባሳደር ማሲንጋ እና ክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ኤምባሲውና ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሊሠሯቸው በሚችሉት ሥራዎች ዙርያ ሰፋ ያሉ ሐሳቦች ተለዋውጠዋል በቅርቡም የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ አፈፃፀም ለመግባት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት በዚህ መልኩ ከአሜሪካው አምባሳደር ጋር ተገናኝተው ሲወያዩ ይህ ለሁለተኛ ጊዜያቸው ነው።

3 weeks, 6 days ago

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ Inter Religious Council of Ethiopia በምዕመናን ከመስጂድ ደጃፍ ላይ የተፈጸመዉን ዘግናኝ ግድያ : እንዲያወግዝና የሽብር ቡድኑንን እኩይ አላማ ለሕዝባችን እንዲገልፅ በአክብሮት እንጠይቃለን::

Mujib Amino

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 1 week ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month, 2 weeks ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month ago