The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 2 Monate, 1 Woche her
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 11 Monate her
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 Wochen, 6 Tage her
አስ-ሰላሙ ዐለይኩም
አዱረቱ አል መክኑና የተርቢያና የቁርአን ማዕከል ለ2017 አዳሪ ትምህርት ምዝገባ ጀምረናል::
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
??ቁርአን 15 ጁዝ ከተፍሲር ጋር እንዲሁም ከ10 በላይ የሀዲስና ኡሉም አሸርኢያ ኪታቦች
??ለወንዶችና ለሴቶች በተለያዩ ቅርጫፎች
??የተርቢያ ስልጠናዎች
??ጉዞና ሸልማቶችን
ሁሉንም በአንድ አመት በአዱረቱ አል መክኑና
እንዲሁም የተደራጀ የኦላይን ትምህርት እንሰጣለን::
ለመመዝገብ
በአካል አንፎና ቤተል በሚገኙ ቅርጫፎች ዘውትር በስራ ሰአት::
በስልክ ቁጥር
???0945777755/?0945777744
ፈጥነው በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ
በቁርአን ልዕልናውን ከፍ ያደርገ ትውልድ መፍጠር የዘውትር ህልማችን ነው
የሼካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ሙስሊም አይነ ስውራኖች ላይ እያደረሰባቸዉን ያለዉን የተለያየ ተፅዕኖዎች እንዲያቆም ተጠየቀ::
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
የአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም የቁርአን ማህበር ለአዲስ አበባ መጅሊስ የሚከተለዉን ደብዳቤ አቅርቧል:-
በሃገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ ሙስሊም አይነ ስውራን መደበኛ ትምህርታቸውን ለመማር በሚያደርጉት ጥረት በሃገሪቱ የተለያዩ የሚሽን ትምህርት ቤቶች ዉስጥ መግባታቸው የግድ የሆነበት እውነታ ለብዙ ጊዜያት የቆየ እንደነበር እሙን ነው። በዚህም በነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከመደበኛ ትምህርቱ ጎን ለጎን ሙስሊም አይነ ስውራን ተማሪዎች እንዲወሰዱ የሚገደዱበት ኢስላማዊ ያልሆኑ መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ትምህርቶች ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጉዳቶችን እና የተለያዩ እስከ መከፈር የሚያደርሱ ተጽዕኖዎችን ሲፈጥሩባቸው ቆይተዋል።
በቅርቡ መንግስት ባገኘው የውጭ እርዳታ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ተገንብቶ ባለፈው ቅዳሜ 02/13/2016 ዓ.ል ለስራ ከፍት የሆነው የሼካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት በሃገሪቱ የሚገኙ አይነ ስውራንን የመማር ተስፋ ከፍ ያደረገ ተቋም ነው። ይህ ትምህርት ቤት ከ9 እስከ 12ኛ ከፍል ድረስ ያሉ አይነ ስውራንን በአዳሪ ለማስተማር እቅድ ይዞ ስራ የጀመረ ሲሆን ይህንን መልካም እድል ለመጠቀም በማሰብ ሙስሊም አይነ ስውራንም አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት በትምህርት ቤቱ ተገኝተዋል።
እነዚህ ወጣት ሙስሊም አይነ ስውራንም አንድ ሙስሊም ግደታ የሆነበትን አምስት አውቀት ሶላት የመስገድ ኢስላማዊ ግደታ በመኝታ ከፍላቸው ዉስጥ ለመፈጸም በሚሞከሩበት ጊዜ በአዳሪ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ምንም አይነት እምልኳዊ ተግባር መፈጸም እንደማይቻል በመጥቀስ እየተከለከሉ መሆናቸውን እና መስገጃቸውንም የተቀሙ መሆኑን ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ለማህበራችን ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ይህም ከዚህ በፊት አልፈው የመጡበት ፈተና በዚህ አዳሪ ትምህርት ቤትም መቀጠሉ በወጣቶቹ ላይ የተመዘገቡበትን የመደበኛ ትምህርት እስከ ማቋረጥ ሊያደርስ የሚችል ተጽዕኖ እየፈጠረባቸው የሚገኝ ሲሆን በማህበራችን አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም የተሰጣቸውን የብሬል ቁርዓን ስልጠና እና የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶችን በተግባር ለመኖር የነበራቸውን ተስፋም እየተፈታተነው የሚገኝ ትልቅ ጉዳይ ሆኗል።
በመሆኑም የአ/አ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት እነዚህ ሙስሊም ወጣት አይነ ስውራኖች በትምህርት ቤቱ እየተደረገባቸው ላለው ያልተገባ ተጽዕኖ እንዲሁም በቀጣይ የህይወት ጉዟቸው ሊያጋጥሙ ለሚችሉ መሰል ተግዳሮቶች አስፈላጊውንና ተመጣጣኝ ከትትል፣ ቁጥጥር እና መፍትሄ እየሰጠ እንዲቀጥል በአላህ ስም እንጠይቃለን።
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 2 Monate, 1 Woche her
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 11 Monate her
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 2 Wochen, 6 Tage her